ሳሞራ ወይስ ሕወሃት “ሕገመንግሥቱን” የጣሱት? ወይስ ሁለቱም?
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ስብሰባ ባደረገበት ወቅት ሳሞራ የኑስ ህወሃትን ለብሰው፣ ህወሃትን አጥልቀው (ጫማቸውና ሌላው አይታይም እንጂ) ህወሃትን ሆነው ታይተዋል፡፡
“ተጋብዘው ነው” ለማለት ለምትፈልጉ እንትኖች መልሱ ህወሃት ላይ ተጋብዘው ከተገኙ ወደፊት እንደ ሰማያዊ፣ መድረክ፣ ወዘተ ያሉ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ የፓርቲዎቹ አርማ ያለበት ባርኔጣ አድርገው ይገኛሉ ማለት ነው – የተነፈሰ ሃሳብ ነው፡፡
ሳሞራ ህወሃትን ሲያይ ዋለ
ተቃዋሚ ፓርቲ የት ነሽ እያለ
ተቃዋሚ ፓርቲ የት ነሽ እያለ
ከነጠላው ፉከራ መልስ – “ሕገመንግሥቱ” ያለጥርጥር ተጥሷል፤ ይህ ከሆነ ደግሞ “ሕገመንግሥቱንና ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ …” በሚል ክስ መመሥረት አለበት ማለት ነው፡፡ ይህ ሲሆን ተከሳሽ “አሸባሪ” ሊባል ነው፡፡ ከዚያ ተከሳሽ ወደ …
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ኢትዮጵያዊ ወንድሞቹን “ጠላት” በማለት የገደለበትን 40ኛ ዓመት ሲያከብር አስቴር በዳኔ “እናንተስ በምርጫ ትወርዱ ይሆን?” በማለት ላነሳችው ጥያቄ ሳሞራ ምንድን ነበር ያሉት? “እኔ ምድብተኛ ወታደር ነኝ”፡፡ ያኔ ግን ባርኔጣ አላደረጉም ነበር፤ ማድረግ አላስፈለጋቸውም፡፡ (የሳሞራ ፎቶና የሕገመንግሥቱ ሃሳብ የተገኘው ከAbenezer B. Yisihak ፌስቡክ ነው)
ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ
No comments:
Post a Comment