Translate

Friday, November 2, 2012

በትንሹ ሰባሁለት ኢትዩጵያዊያን ስደተኞ ሞቱ ተባለ


ኢሳት ዜና:-በትንሹ  72  ኢትዩጵያዊያን  ስደተኞች  ከሶማሊያ  ቦሳሶ  ወደብ  ወደ የመን  ለመግባት ሲሞክሩ  ባህር ውስጥ  ሰጥመዋል  ሲሉ  የየመን  ባለስልጣኖች አስታወቁ ።

የተወሰኑ  የ ኢትዮጵያውያኑን  አስከሬን  በፎቶ  አስደግፎ  የተሰራጨው  ይሕ ዘገባ  እንዳመለከተው  በሁለት ጀልባ ተጭነው  በገልፍ-ኦፍ  ኤደን ባህር ወደየመን  በማምራት  ላይ እያሉ  ነው  በተነሳ  ሀይለኛ  ንፋስና  ማዕበል አስጥሞአቸው  የከፊሉ  አስከሬን  በየመን  ሰላጤ  አካባቢ  የተገኘው  ።

ከ ኢትዮጵያ  በየጊዜው  የሀገሪቱን  የፖለቲካና  የ ኢኮኖሚ  ቀውስ  በመሸሽ ወደ  የመን  በባህር  የሚመጡ  በሺዎች  የሚቆጠሩ  ኢትዮጵያውያን  ለተመሳሳይ አደጋ  እንደተዳረጉና  እንደሚዳረጉ   ይኸው  ዘገባ  አመልክቶዋል።

የየመን  የሀገር  ውስጥ  ሚኒስትር  አብዱል-ቃድር  ከታን  ዋቢ  ያደረገው ዘገባው የመን  በየጊዜው  የሚፈልሱትን  ኢትዮጵያዊ  ስደተኞች  ለመግታት  በቅርቡ  ጥብቅ  እርምጃ  እንደምትወስድ  አስታውቀዋል  ብሎዋል ።

የተባበሩት  መንግስታት  ምንጮች  እንደሚየመለክተው  በ የአመቱ  75 000 ኢትዮጵያውያን  ስደተኞች  ገልፍ-ኦፍ  ኤደንን  ይሻገራሉ  ወይም  ለመሻገር ይሞክራሉ ።

በአዲስ አበባ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ዛሬም ተቃውአቸውን አሰሙ


ኢሳት ዜና:-ላለፉት 11 ወራት ድምጻችን ይሰማ በማለት የመብት ጥያቄዎችን ያነሱ ኢትዮጵያውያን ዛሬም ተቃውሞአቸውን አሰምተው ውለዋል።

ኢትዮጵያውያኑ ሙስሊሞች ተቃውሞአቸውን የገለጡት ነጭ ጨርቅ በማውለብለብና በዝምታ ሲሆን፣ የነጩ ጨርቅ ትርጉሙ በእስር ላይ የሚገኙት መሪዎቻቸው አሸባሪዎች ሳይሆኑ የሰላም ምልክቶች መሆናቸውን ለመግልጽ  መሆኑ ታውቋል። ተቃውሞዓቸውን በዝምታ ያደረጉትም መሪዎቻቸው ህገመንግስታዊ መብታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ የታሰሩ ይህሊና እስረኞች መሆናቸውን ለመግልጽ ነው ሲሉ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ለኢሳት ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች የተሳተፉበት የዛሬው ተቃውሞ በሰላም ተጠናቋል። መንግስት ባለፈው ሳምንት 29 የሙስሊም መሪዎችን በአሸባሪዎች እና አክራሪነትን በማስፋፋት ወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል። አብዛኛው ሙስሊሞች ግን በመንግስት በኩል የቀረበውን ክስ አይቀበሉትም።

በሌላ በኩል በወልድያ ከተማ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሙስሊሞች ከጁመአ ስግደት በሁዋላ ተይዘው መታሰራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሀይማኖት መሪዎቻችንን በነጻነት እንምረጥ፣ መንግስት አህባሽ የተባለውን እስልምና ለማስፋፋት የሚያደርገውን የተቀነባበረ ዘመቻ ያቁም እንዲሁም መሪዎቻችን ይፈቱ  የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳታቸው ይታወሳል።

የኦፌዴንና የኦፕኮ ፓርቲ አመራሮች ጥፋተኞች ተባሉ


ኢሳት ዜና:-የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራቲክ ንቅናቄ ( ኦፌዴን)ና የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ ፓርቲ አመራሮች ጥፋተኞች ተባሉ

በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስ ዲሞክራቲክ ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባና የኦሮሞ ህዝበ ኮንግረስ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ኦልባና ሊሌሳ ከሌሎች 9 የኦሮሞ ተወላጆች ጋር በመሆን በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ ተብለዋል።

ፍርድ ቤቱ ለአቶ በቀለና አቶ ኦልባና የቅጣት ማቅለያ ሀሳብ እንዲያቀርቡ ጥያቄ ቢያቀርብላቸውም ሁለቱም እንዲሁም አንድ ስማቸው ያልተወቀ ተከሳሽ ጥፋተኞች ባለመሆናችን የፍርድ ማቅለያ ሀሳብ የለንም በማለት መናገራቸውን የኦፌዴን ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ነገአ ገልጸዋል ።

ኦፌዴን ቀድሞ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ይመራ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ደግሞ አቶ በቀለ ነገአ በበላይነት ንቅናቄውን እየመሩ ነው። ኢህኮ ደግሞ በዶ/ር መራራ ጉዲና እንደሚመራ ይታወቃል።

November “Ethiopian Election Massacre” Commemoration Month


We remember and respect those fellow Ethiopians who gave their lives for their right to vote and for their vote to be counted.


Ethiopian Election Massacre Commemoration Month
On May 15, 2005, over 26 million Ethiopians voted peacefully to elect their leaders.

የሃሪኬን ዐውሎ ነፋሳት መነሻቸው ከኢትዮጵያ መሆኑን የናሳ ሳይንቲስት አረጋግጠዋል


በፍቅር ለይኩን

የአሜሪካን በተለያዩ ጊዜያት የመቱ አውሎ ንፋሳትና ወጀቦች መነሻቸው ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራራማ ቦታዎች መሆናቸውን የናሳ ሳይንቲስቶች ጥናቶች በተለያዩ ጊዜያት ሲያመለክቱ ነበር፡፡ ኦውን ኬሊ የተባሉ የናሳ ተመራማሪ በ2006 ዓ.ም ጥናታቸው፡- A lot of hurricanes start out over the Ethiopian Mountains. Air steadily flowing over those mountains and they cause waves in the air. በማለት የሄሪኬን አውሎዎችና ወጀቦች መነሻ ኢትዮጵያ መሆኗን በጥናታቸው አመልክተዋል፡፡

HARRICANE SANDY GOES FULLሌላኛው የናሳ ሳይንቲስትና ተመራማሪ የሆኑት ስኮት ብራውን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የሄሪኬን መነሻዎች ከባሕሮችና ከውቅያኖሶች ዳርቻዎች ነው ከሚለው በተጨማሪ ለሄሪኬን መከሰት ከምዕራብና ምስራቅ አፍሪካ የሚነሱ ንፋሳትና አውሎዎችም የብዙዎች ሳይንቲስቶችና አጥኚዎች ትኩረትን እየሳቡ መምጣታቸውን በጥናታቸው በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

የWall Street Journal የናሳ ሳይንቲስቶችን ጥናት ዋቢ በማድረግ እንዳስነበበው ደግሞ አሜሪካንን የመታው ‹‹ሄሪኬን አርል›› የተባለው አውሎና ወጀብ መነሻው ከኢትዮጵያ እንደነበር በወቅቱ አስነብቦ ነበር፡፡

Thursday, November 1, 2012

ላለፉት አስር ቀናት ሲካሄድ የሰነበተው የአገር ቤቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጠናቀቀ


ኢሳት ዜና:-ቅዱስ ሲኖዶሱ በርካታ ጉዳዮችን አንስቶ በጥልቀት በመዳሰስ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን ያሳለፈ ሲሆን፤ በአገር ቤትና እንዲሁም በውጭ አገር በሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ መካከል በመጪው ኅዳር ወር በዳላስ ቴክሳስ ለሚካሄደው የዕርቀ ሰላም ውይይት አስመልክቶ የቅዱስ ሲኖዶሱ ልኡክ መደራደሪያ ናቸው የተባሉ አምስት ነጥቦች ለይቶ ማስቀመጡን ደጀ ሰላም ድረ ገጽ ዘግቧል።

እነኚህም አምስቱ ነጥቦች “የሰላምና አንድነት ጉባኤው” ላቀረባቸው ሰባት ጥያቄዎች በተሰጡ መልሶች ላይ በመመሥረት የተዘጋጁ መኾናቸውን ምንጮቹን ጠቅሶ የዘገበው ደጀ ሰላም፤ ከሰባቱ “የሰላምና አንድነት ጉባኤው” ጥያቄዎች መካከል “ብሔራዊ ዕርቅ”ን አስመልክቶ የቀረበው “ከዕርቀ ሰላሙ አጀንዳ ጋራ ግንኙነት የለውም” በሚል ተቀባይነት እንዳላገኘ አስታውቋል።

በስደት የሚገኙትን የቤተክርስቲያኗ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን በተመለከተም “በመረጡት ስፍራ በጸሎት ተወስነው ሲኖሩ መንበረ ፓትርያርኩ ደግሞ ደመወዝ፣ መኖሪያ ቤት፣ ተሽከርካሪና ሌሎችንም አስፈላጊ ነገሮች በማሟላት የደኅንነት ጥበቃም ያደርግላቸዋል፡፡” የሚል ውሳኔ ተላልፎአል።

በደብረብርሀን ዩኒቨርስቲ በተቀሰቀሰ ግጭት ተማሪዎች መጎዳታቸው ተሰማ


ኢሳት ዜና:-ትናንት ጥቅምቅ 21 ቀን 2005 ዓም በደብረብርሀን ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲው ያወጣውን አዲስ የውጤት አሰጣጥ ደንብ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አድረገዋል።

ተማሪዎች ጥያቄያቸውን በሚያቀርቡበት ወቅት፣ የወረዳው ፖሊስ አባላት ወደ ዩኒቨርስቲው ገብተው አስለቃሽ ጭስ በመበተን ተማሪዎችን ደብድበዋል።

ተማሪዎቹ እንዳሉት መብታቸውን ተጠቅመው  ጥያቄያቸውን ቢያቀርቡም የዩኒቨርሲቲው ባለስልጣናት ግን ጥያቄያቸውን በቅንነት ከመመለስ ይልቅ ዛቻና ማስፈራሪያ መጠቀማቸውን ተማሪዎች ገልጠዋል።

በዚህም ምክንያት ውዝግብ መነሳቱን የገለጹት ተማሪዎቹ፤ ፖሊሶቹ  በስፋራው በመድረስ ወደ ሀይል እርምጃ መግባታቸው በተማሪዎቹ ዘንድ ይበልጥ ቁጣ በመቀስቀስ የተፈጠረውን ውዝግብ ወደ ወደ ተቃውሞ ቀይሮታል።
ፖሊስ ዱላና አስለቃሽ ጭስ ጭምር በመጠቀም በወሰደው የሀይል እርምጃ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተማሪዎች መጎዳታቸውንና አንዳንዶችም ተጎድተው ወደ ህክምና ቦታ መወሰዳቸውን ተማሪዎቹ ተናግረዋል።