“… የአመራሩ ድክመት ድርጅቱን ጎድቷል፤ … የበላይ አመራሩ ሥራውን ሲገመግም ብዙ ጉድለት ተገኝቶበታል” በማለት ለፋና ቃለምልልስ የሰጠው አዲሱ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር የወንበዴዎች ቡድን መሪ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ነው። በበፊቱ አመራር ውስጥ ምክትል ሊቀመንበር የነበረው ደብረጽዮን፤ 35 ቀናት በፈጀውና ዋናው ችግር አመራሩ መሆኑን በገመገመው ስብሰባ መሠረት መባረር ሲገባው ይልቁንም ሊቀመንበር ሆኗል።
Capella University ከተባለው የዲግሪ ወፍጮ ቤት “የዶክትሬት ዲግሪ” ተቀብሏል የሚባልለት ደብረጽዮን እንደ ቀድሞ አመራር “የበላይ አመራሩ ጉድለት ተገኝቶበታል” ካለው ድርጅት ራሱን ማግለል ሲገባው ራሱን በዓለምአቀፍ የአሻባሪነት የመረጃ ቋት ውስጥ የተመዘገበው ህወሓት ሊቀመንበር አድርጎ ራሱን ሾሟል።
በከሁለት ቀናት በፊት “በጨለንቆ በተፈፅመው የጅምላ ግድያ በስተጀርባ ማን ነው ያለው?” በሚል የኦሮሚያ አስተዳደር ያቀረበውን ጥያቄ ደብረጽዮን በህወሓት ላይ የተነጣጠረ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ በሚል እርምጃ እንደሚወስድ ተናግሯል፡፡ “አመራሩ ዝምታን መርጧል፤ ወይም ራሱ ችግር ውስጥ እየገባ ነው ያለው፤ ነገሮች እየተባባሰ ነው … እርምጃ መውሰድ ይገባል” ብሏል።
ይህ የደብረጽዮን ንግግር “በጨለንቆ በተፈፅመው የጅምላ ግድያ በስተጀርባ ማን ነው ያለው?” ለሚለው የኦሮሚያ መግለጫ ኃይለማርያም ከተናገረው በተለይ የተሰጠ ምላሽ ተደርጎ ተወስዷል።
No comments:
Post a Comment