Translate

Thursday, June 1, 2017

የአርበኞች ግንቦት 7 የህዝብ ግኑኝነት የነበረው ታጋይ ዘመነ ካሴ ከኤርትራ ለህክምና ወደ አውሮፓ መግባቱ ታውቋል

Ethiopian Patriot Zemene Kassse
አርበኛ ዘመነ ካሴ ለህክምና ወደ አውሮፓ እንዲጓዝ ትልቁን ድጋፍ ያደረገለት ድርጅቱ አርበኞች ግንቦት 7 መሆኑን ከስፍራው ያገኘነው ማስረጃ ያመላክታል።

ከጥቂት ግዚያት በፊት ባጋጠመው ህመም፣ ከትግሉ ላልተወሰነ ግዜ ርቆ የተቀመጠው ዘመነ፣ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል። ትግል መስዋዕትነት መክፈል መሆኑን ለማወቅ የተሳናቸው ግለሰቦች፣ ዘመነ አንድ ግዜ በኤርትራ እስር ቤት ይገኛል በሌላ ግዜ አርበኛች ግንቦት 7 አስገድሎታል እያሉ የተለያዩ የሀሰት አሉባልታዎችን ሲያሰራጩ መቆየታቸው የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው።
እነዚህ የኪቦርድ ታጋዮች፣ ህይወቱን ለመስጠት በርሃ የገባ ታጋይን ካላሳያችሁን እያሉ ያዙን ልቀቁን ሲሉ መስማት እንጭጭነታቸውን ወይም አለማወቃቸውን በአደባባይ ከማስመስከር ውጭ የትም እንደማይደርሱ መገንዘብ እንኳ የተሳናቸው ናቸው። የዘመነ ፋይል እዚህ ላይ ሲዘጋ ነገ ደግሞ በረሃ ያሉትን ሌሎች ጓዶቻችንን ምክንያት እየፈጠሩ አዲስ የመጨቃጨቂያ አጀንዳ እንደሚከፍቱ ምንም ጥርጥር የለም። በዘመነ ላይ በተወራው ብዙ ማለት ይችላል። ስለዚህ አሉባልታዎችን ትተን የሁላችንም ጠላት የሆነውን ወያኔ አምርረን መታገል አለብን። አሁንም ቢሆን ዘመነ ለህክምና የወጣው በአርበኞች ግንቦት 7 ፍቃድና ድጋፍ እንጅ በኪቦርድ ጩኸት እንዳልሆነ ሊያውቁት ይገባል። ዘመነ ተገድሏል፣ ታስሯል እያሉ ሲያደነቁሩን የነበሩ አሉባልተኞች አውሮፖ መግባቱን ሲሰሙ ምን አርዕስት ይከፍቱ ይሆን?
ከዲሲ ግብረ ሃይል ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ

No comments:

Post a Comment