Translate

Friday, June 30, 2017

አርቲስቶቹ ሚዲያ ላይ ነበራቸው በተባለ ተሳትፎ የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው


(በጌታቸው ሺፈራው)
ሰገሌ ብሊሱማ ቄሮ ኦሮሚያ (የኦሮሚያ ወጣቶች ድምፅ) በሚባል ሚዲያ ዜና እና ቃለ መጠይቅ ሰርተዋል እንዲሁም ዜና አንብበዋል የተባሉ 4 አርቲስቶች እና ሌሎች 3 ግለሰቦች የሽብር ክስ ቀረበባቸው፡፡ በእነ ኦሊያድ በቀለ የክስ መዝገብ ስር ክሱ የቀረበባቸው አርቲስቶች ኦሊያድ በቀለ (1ኛ ተከሳሽ)፣ ሞይቡል ምስጋኑ (2ኛ ተከሳሽ)፣ ኢፋ ገመቹ (4ኛ ተከሳሽ) እና ኤልያስ ክፍሉ (7ኛ ተከሳሽ) ሲሆኑ ቀነኒ ታምሩ (3ኛ ተከሳሽ)፣ ባይሉ ነጮ (5ኛ ተከሳሽ) እና ሴና ሰለሞን (6ኛ ተከሳሽ) ከአርቲስቶቹ ጋር ዜና እና ቃለ መጠይቅ ሰርታችኋል፣ እንዲሁም ዜና አንብባችኋል ተብለው የሽብር ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡

ጎንደር ቅዳሜ ገበያ ፈንጂ ፈነዳ

Image result for Gonder Ethiopia sateday shop
(ዘ-ሐበሻ) መሬታችንን እና መሪዎቻችንን አስበልተን አንቀመጥም ያሉት የጎንደር አማራ ታጋዮች የሕወሓትን መንግስት በየአቅጣጫው እየተፈታተኑት በሚገኙበት በዚህ ወቅት ዛሬ በጎንደር ከተማ ቅዳሜ ገበያ አካባቢ ከተማዋን ያናወጠ ፈንጂ መፈንዳቱ ተሰማ::
የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከስፍራው እንደገለጹት ቦምቡን ያፈነዳው አካል ማን እንደሆነ ባይታወቅም በጎንደር የአማራ ተጋድሎ እያደረሰበት ያለውን ሽንፈት በሽብርተኝነት ስም ለመደፋፈን ስርዓቱ ሆን ብሎ ያፈነዳው ሊሆን ይችላል በሚል ሕዝቡ እየተነጋገረበት መሆኑ ታውቋል:

የህወሓት የማኅበራዊ ሚዲያ ካድሬዎች አዲስ ተልዕኮ ተሰጣቸው

(ቢቢኤን) የህወሓት/ኢህአዴግ የማኅበራዊ ሚዲያ ካድሬዎች አዲስ ተልዕኮ እንደተሰጣቸው ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ተልዕኮው፣ ከትላንት በስቲያ ይፋ የተደረገውን የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ግንኙነት የተመለከተውን ሰነድ የሚመለከት ሲሆን፣ ሰደኑ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ከሚገባው በላይ እንዲራገብ፣ ግራ እንዲያጋባ እና ብዥታ እንዲፈጥር መስራት እንዳለባቸው ተነግሯቸዋል፡፡ በተጫማሪም ሰነዱ፣ የኦሮሞ ህዝብ ለዓመታት ሲያቀርብ የነበረውን ጥያቄ እንደመለሰ በማድረግ፣ ትግል ላይ የሚገኘውን ህዝብ ለማደናገር ጥረት እንዲያደርጉ ታዝዘዋል፡፡

ሌ/ጄነራል ጻድቃን፣ ህወሃት፣ ኤርትራ እና ቀይ ባህር (በነጻነት ቡልቶ – ክፍል ሁለት)

በነጻነት ቡልቶ
ክፍል ሁለት
ጀ/ል ጻድቃን ፣ የቀይ ባህር እና ኤርትራTsadkan Gebretensay and Eritrea
ጄነራል ጻድቃን “ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ሀይል መሆን አለባት” የሚል አስገራሚ ሃሳብ አንስተዋል። “ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ሀይል መሆን አለባት” የሚለው ማደናገሪያ  ሃሳብ ሕወሃቶች ያዳከሙትን የኢትዮጵያን ብሄረተኝነት ስሜት ለማነሳሳት ይጠቅመናል በሚል ስሌት በእነ ጄ/ል ጻድቃን በኩል ነገሮችን ለማጥናት እየሞከሩ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል ። እንደሚታወሰው ቀደም ሲልም በአረብ ጸደይ (ኣረብ ስፕሪግ) ወቅት የአረቡን አለም ያናወጠው የለውጥ ማዕበል ወደ ኢትዮጵያ ይዛመታል የሚል ስጋት ውስጥ ገብቶ የነበረው ሟቹ መለስ ዜናዊ አባይን የመገደብ ፕሮጀክት በማስተዋወቅ የህዝብን ትኩረት ለማስቀየስ- ውሱን በሆነ መልኩም ቢሆን- አስተዋጽዖ አድርጎላቸው ነበር ። አሁን ደግሞ ስርዓቱ ከገባበት አጠቃላይ ቀውስ ለመውጣት ባለተራው “የቀይ ባህር ሀይል” ሆኖ የመውጣት ጥያቄን ማራገቡ ያዋጣል የሚል መደምደሚያ ላይ  ደርሰውም ሊሆን ይችላል። በዚህ “ገዢ ሃሳብ” የ”ህዝብ የአስተሳስብ አንድነት” ይመጣል ከሚል እሳቤ የተሰላ ይመስላል።  በተጻራሪው ከዚህ አመለካከትና ኣቋም የተለዩ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በግብጽ ወይንም ባጠቃላይ በአረብ  “ቅጥረኛነትና ተላላኪነት” ይፈረጃሉ  ማለት ነው፡፡ የደርግ ስርዓት ሻዕቢያን፣ ወያኔንና ሌሎች ተቃዋሚዎችን በዘመኑ ከፈረጀው ጋር ተመሳሳይነት ባለው መልኩ ማለት ነው። ደርግና ሕወሃት በዚህ ተቃዋሚዎችን ከመክሰስና ከመፈረጅ አኳያ ተመሳሳይነት እንዳሏቸው ማጤን ያስፈልጋል።

የአጋዚ ክ/ጦር በሰሜን ጎንደር መሳሪያ ለማስፈታት ያደረገው ሙከራ ግጭት አስከተለ

ኢሳት (ሰኔ 22 ፥ 2009)

የአጋዚ ክፍለጦር አባላት በሰሜን ጎንደር ወገራ ወረዳ መሳሪያ ለማስፈታት ያደረጉት ሙከራ ወታደራዊ ግጭት አስከተለ።
የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት ሃሙስ ሰኔ 22/2009 በተካሄደ ግጭት 7 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ ሶስት መቁሰላቸው ተመልክቷል።

የኦሮሞ ህዝብ እኩልነት እንጂ ልዩ ጥቅም ፈላጊ አይደለም (ገለታው ዘለቀ)

ገለታው ዘለቀ
Bishoftu, Irreecha massacre
የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የኢትዮጵያ ብሄሮችም ሆኑ ዜጎች በጋራ ከመሰረቱት ሃገር ልዩ ጥቅም ፈላጊዎች አይደሉም። ኢትዮጵያውያን በመሬት ዙሪያ በኢኮኖሚ ዙሪያ ለየቡድናቸው ልዩ ጥቅም (special interest)  ይዘው በአንድ የፓለቲካ ጠገግ ዘንድ ለማረፍ አይስማሙም። አልተስማሙም። ኢትዮጵያውያን ለእንደዚህ ዓይነት ራስ ወዳድ ስምምነት ሃይማኖታዊም ባህላዊም መሰረት የላቸውም። ለእንግዳ እንኳን ቅድሚያ የሚሰጥ ባህል ነው ያላቸው።

Wednesday, June 28, 2017

“በአፋን ኦሮሞ” አማካኝቶ ማስተር ፕላኑን በጓሮ በር! (ከኤርሚያስ ለገሰ)

ከኤርሚያስ ለገሰ
Ermias Legesse, author and ESAT TV and Radio contributor
ኤርሚያስ ለገሰ
ህውሃት ለሁለት የተሰነጠቀ ሰሞን ጐልተው ከታዩ ባህሪያት አንዱ የኦህዴድ ካድሬዎች “የኦሮሞ ብሔርተኝነት” ካርድ የመዘዙበት ነበር። እነ ኩማ ደመቅሳ እና ግርማ ብሩን ጨምሮ በመዘዙት ካርድ “የትግራይ የበላይነት ሊውጠን ነው” በማለት ወደ ስልጣን ጫፍ (ጠቅላይ ሚኒስትርነት ጨምሮ) ለመቆጣጠር የተጉበት ነበር።
እናም በእነ ግርማ ብሩ የተመራው ቡድን የኦሮሞ ብሔርተኝነት ይቀሰቅሳል ብሎ ያሰበውን እቅዶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ይፋ አደረገ። ከእነዚህ ተግባራት አንዱ በአዲሳአባ የሚሰሩ ሥራዎች ተለይተው የቀረቡበት ነበር። ከስራዎቹም ውስጥ አንዱ ” በአዲሳአባ አምስት ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 28 ወረዳዎች በአፋን ኦሮሞ የሚያስተምሩ 28 አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች መክፈት” የሚል ነበር።( በነገራችን ላይ በወቅቱ አዲሳአባ በአምስት ዞኖችእና 28 ወረዳዎች የተከፈለችበት ነበር።)

ሌ/ጄነራል ጻድቃን ፣ ህወሃት ፣ ኤርትራ እና ቀይ ባህር (በነጻነት ቡልቶ – ክፍል አንድ)

በነጻነት ቡልቶ
ክፍል አንድ
ጄነራል ጻድቃን፣ “የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፓሊሲ” እና  “የፓለቲካ ችግሮች”
General Tsadkan Gebretensay
በግሪክ አቴናና በስፓርታ መካከል የተካሄደውን የጦርነት ታሪክና ከጦርነቱ ጋር የተያያዙ ስትራቴጃካዊ ጽንሰ ሃሳቦች በማፍለቅ ከሚደነቀው ጥንታዊው የታሪክ ጸሃፊ  የቱስዳይስ  The Peloponnesian war  ጀምሮ  እስከ  የጀርመኑ ካርል ቮን ክልሽዊትዝ  On War ፣  የባህር ሃይል  ስትራቲጂ አባት አልፌሬድ ማሃን The influence of Sea Power Upon History፡ ከዘመን ተሻጋሪ  የስትራቴጂ አስተምሮዎች ፈላስፋ ቻይናዊው ከሰን ዡ The Art of War  አንስቶ እሰከ ሉትዋርክ፣ ኮሊንስ የመሳሰሉ የዘመናችን የስትራቴጂና የደህንነት ጥናቶች ታላላቅ ተመራማሪዎችና  ምሁራን  የጻፏቸውንና ያፈለቁዋቸውን የስትራቴጂ ጽንሰ ሃስቦችና ቀመሮች  በጥልቀት ማጥናትና ማወቅ አስፈላጊና ጠቃሚ ናቸው፡፡

“ተዋከበና!”

“ተዋከበና!”


ለቴዲ አፍሮ ዉበት ያምራል እንዴ? ቁንጅናስ ያምራል?
አንዳንድ ጊዜ ሰዎች “I didn’t do nothing” ወይም “I didn’t say nothing” ሲሉ መስማት አዲስ አይደለም። እጅግ በጣም አልፎ አልፎ ቢሆንም፣ እንግሊዝኛ ያፍ መፍቻ ቋንቋቸው የሆኑ ሰዎችም ሲሉት ይሰማሉ። በቋንቋው ህግ መሰረት ይህ አ/ነገር ጎደሎ ነው። “double negative” የሚፈጥረው  የ“positive” ትርጉም/ፍቺ ግድፈት ይመስለኛል። ሁለት ነጌቲቭ (“didn’t” እና “nothing”) ቃላት/ሃረጎች፣ አንዳንዴ ፖዚቲቭ ትርጉም የሚያስከትሉ መሆኑ ነው። “I didn’t do nothing” ወይም “I didn’t say nothing” በሚሉት ዓ.ነገሮች ውስጥ ለማለት የተፈለገው “ምንም አላደረግሁም”/“ምንም አልተናገርኩም” ሲሆን፣ ትርጉሙ ግን የተገላቢጦሹ ሊሆን እንኳን ባይችልም፣ በጣም ያደናግራል። እናም ጎደሎ ነው። እንዲህ አይነቱን ጎደሎ “ቋንቋ” (“ቋንቋ” እንደ አንድ የስነ-ጽሁፍ አላባ) አንዳንድ ጊዜ በስነ-ግጥም እና በዘፈን ግጥሞች ውስጥ ሰዎች ሊጠቀሙበት ቢችሉም እንኳን ጎደሎ ነው።

Saturday, June 24, 2017

አንዳርጋቸው ጽጌ የጽናታችን ና የቁርጠኝነታችን ዓርማ ነው!!!


የንቅናቄያችን መስራችና ዋና ጸሀፊ የነበረው ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ በዘረኛው የህወአት አገዛዝ ከየመን አየር ማረፊያ ታግቶ እስር ቤት ከተወረወረ እነሆ ጁን 23 2017 ዓም 3 አመት ሞላው።
ህወአት አንዳርጋቸውን ባገተበት ወቅት የንቅናቄያችን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ይሽመደመዳል የሚል ተስፋና እምነት ነበረው። ይህንን እምነቱን ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ በሚፈጸምበት ሰቆቃ ውስጥ ሆኖ እንዲያረጋግጥለትና ነጻነት ናፋቂ የሆነው ህዝባችን ተስፋ እንዲቆርጥ ብዙ ጥሮአል ፤ ደክሟል።

Friday, June 23, 2017

ይድረስ ለትግል አባቴ አንዳርጋቸው ጽጌ

የአርበኛ  ታጋዩ ትውስታ
ተ—ጠ—ቀ—ቅ!!
Andargachew Tsige is Ethiopian
ለፍትህ፣ለእኩልነት፣ለዴሞክራሲያዊ መብት መከበር፣ለሰባዊ መብት ልዕልና መጠበቅ፣ለኢትዮጵያ አንድነት ሲሉ—ውድ ህይወታቸውን አሳልፈው ለሰጡ ሰማዕታት ጓዶቻችን የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት እናድርግላቸው!! —-ይበቃል!!
ታች!!

ትልቁ የኢትዮጵያ ‘ፌደራል’ በጀት ድክመቱ፣ ገጽታዎቹና ውስብስብ ችግሮቹ

በከፍያለው ገብረመድኅን The Ethiopia Observatory (TEO)
Ethiopia's ambitious, bold budget
ለኢትዮጵያ አስተዳደራዊ ሥራ ማስፈጸሚያ በከፍተኛነቱ የመጀመሪያው የሆነውና በ2010 ዓ.ም (2017/18) ተግባራዊ የሚሆነው ብሔራዊ በጀት ብር 320.8 ቢሊዮን ($14 ቢሊዮን) የተመደበለት መሆኑን የፋይናንስና ኤኮኖሚ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ የፓርቲያቸው ብቻ ለሆነው ፓርላማ ለወጉ ረቂቁን እንዲያጸድቅ ሰኔ 1/2009 ማቅረባቸው በሕዝብ መገናኛ ተገልጿል።

Thursday, June 15, 2017

የሥብሰባ ጥሪ

የሥብሰባ ጥሪ
የኢትዮጵያ ሐገራዊ ንቅናቄ ፕሮግራሙንና ዓላማውን በጥልቀት ለማስተዋወቅና ከኢትዮጵያውያን ጋር ለመወያየት በኖርዌይ ኦሥሎ ከተማ ህዝባዊ ውይይት አዘጋጅቷል። በመሆኑም በነዚህ ከተሞች እና በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በስብሰባው ላይ እንዲሰተፉ ሀገራዊ ጥሪ አቅርበዋል።
ቀን ፣ ጁን 17- 2017
ሰዓት ፣ 15 00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ ፣ በቅርቡ ይገለጻል
አዘጋጅ ፣የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጭ ድርጅት በኖርዌይ

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!


ህወሃት በሜካናይዝድና (ብረት ለበስ በከባድ መስራያ የታገዘ) ጦርነት ተጋርጦብኛል ይላል


ሰበር መረጃ (ሰኔ 7/2009)
በልኡል አለሜ
በሰሜን ግንባር ሁለት የጦር ቀጠናዎች ቀይ መስመሩን ማለፋቸዉ እየተነገረ ነዉ። ሦስት የህወሃት ክ/ጦሮች በመረባረብ ላይ ናቸዉ።

Monday, June 12, 2017

ጊዜው የሕዝባዊ አሻጥር ነው !!!

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ “ሴፍ ሀውስ” እያሉ የሚያቆላምጧቸው ከ50 በላይ ድብቅ የማሰቃያ ቦታዎች አሉ። ከፊሎቹ የምድር ውስጥ ዋሻዎች አሏቸው። ብዙዎቹ መሀል ከተማ ውስጥ ሲገኙ ጥቂቶቹ በከተማው ዳርቻዎች ይገኛሉ። በማዕከላዊና በሌሎች እስር ቤቶች ውስጥም የማሰቃያ ቦታዎች ያሉ ቢሆንም ወገኖቻችን ከፍተኛ ፍዳ እንዲደርስባቸው የሚደረገው በእነዚህ ከእይታ በተሰወሩ የማሰቃያ ቦታዎች ነው። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዋዜማ በናዚ ፋሽስቶች ይፈፀሙ ከነበሩ ሰቆቃዎችን የባሱ አስነዋሪና ኢሰብዓዊ ግፎች በእነዚህ የማሰቃያ ቦታዎች ውስጥ ይፈፀማሉ።

Tuesday, June 6, 2017

የቴዲ አፍሮ ቁጭት (ከኤርሚያስ ለገሠ – ቁጥር ሁለት)

ከኤርሚያስ ለገሠ (ቁጥር ሁለት)
Teddy Afro, by Ermias Legesse
ባለፈው ሳምንት  የቴዲ አፍሮ … ተሞክሮ!” በሚል ርዕስ ዘለግ ያለ መጣጥፍ አቅርቤ ነበር። በመጣጥፉ ላይ የኢትዮጵያ ኪነ-ጥበብ ሙያተኞች ከቴድሮስ ካሳሁን እና ከእሱ በፊትና በኋላ ከነበሩ (ካሉ) መስዋዕት እየከፈሉ ካሉ አርቲስቶች መቅሰም የሚገባቸውን ትምህርት ለማሳየት ሞክሯል። የኪነ-ጥበብ ሙያተኞች ስራዎቻቸውን ለህዝብ ሲያቀርቡ ራሳቸውን የሚያዩበት መስታዋት ምን ዓይነት ሊሆን እንደሚገባ ተመላክቷል። “የቴዲ አፍሮ ተሞክሮ” በሚለው ማስታወሻው እንደተገለጠው የኢትዮጵያ ህዝብ ባጠቃላይ የኪነ -ጥበብ ሙያተኞች በልዩ ሁኔታ ከድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ሁለት ትላላቅ ተሞክሮዋችን ሊወስዱ ይገባል። የመጀመሪያው  አገራችን በአሁን ሰዓት ያለችበትን ሁኔታ በአግባቡ መገንዘብ ይሆናል። አርቲስቱ እንደገለጸው “ኢትዮጵያዊነት እና ብሄራዊ ስሜት አደጋና ፈተና ላይ ወድቋል ” የሚለው ቀዳሚ ቁም ነገር ይሆናል።

Monday, June 5, 2017

ሰበር ዜና – በሰሜን ጎንደር ዋግ ሃምራ ወያኔ ጥቃት ደረሰበት

በልኡል አለሜ (ግንቦት 28/2009)
TPLF security members killed in Gondar
የህወሃት ወታደራዊ ደህንነቶች ባቀረቡት መረጃ መሰረት በምእራብ አቅጣጫ በሰሜን ጎንደር ዋግ ሃምራ፣ እንዲሁም ደባርቅ፣ ዳባትና፣ እንፍራዝ አካባቢዎች ላይ ወታደራዊ አሰሳና ጥቅት ለማድረግ ታስቦ የነበረ ቢሆንም ኦፐሬሽኑ ትናንት ሙሉ ለሙሉ ተሰርዟል!

Thursday, June 1, 2017

ከቴዎድሮስ እስከ ቴድሮስ (በኤፍሬም ማዴቦ)

በኤፍሬም ማዴቦ (እዚህ ጽሁፍ ዉስጥ ያለዉ ሃሳብ ሁሉ ዬኔ ዬኔና የኔ ብቻ ነዉ)
Téwodros II was the Emperor of Ethiopia from 1855
ዕለቱ ሰኞ ነዉ . . . .  ሰኞ ሚያዚያ 6 ቀን 1860 ዓም። እቺ ቀን “ መቅደላ አፋፉ ላይ ጩኸት በረከተ የሴቱን አናዉቅም፥ ወንድ አንድ ሰዉ ሞተ” ተብሎ የተገጠመላት ቀን ናት። እቺ ቀን ኢትዮጵያ ዘለዓለማዊ ጀግናዋን ያገኘችበትም ያጣችበትም ቀን ናት። እቺ ቀን ቴዎድሮስ የሞተብንም የሞተልንም ቀን ናት . . . .  አዎ ሰኞ ሚያዚያ 6 ቀን 1860 ኢትዮጵያ መስዋዕትነትንና ባዶነትን፥ ተስፋና ተስፋ መቁረጥን፥ ቁጭትንና ሀሴትን አንድ ላይ ያስተናገደችበት ቀን ነዉ። እሲቲ አማክሩኝ እቺን ቀን ምን ልበላት? የቀን ቅዱስ ብዬ እንዳላወድሳት የአንድነታችን ጀማሪ የሆነ ሰዉ ሙሉ ራዕዩን ሳናይለት አለግዜዉ የተለየን በዚች ቀን ነዉ።

የአርበኞች ግንቦት 7 የህዝብ ግኑኝነት የነበረው ታጋይ ዘመነ ካሴ ከኤርትራ ለህክምና ወደ አውሮፓ መግባቱ ታውቋል

Ethiopian Patriot Zemene Kassse
አርበኛ ዘመነ ካሴ ለህክምና ወደ አውሮፓ እንዲጓዝ ትልቁን ድጋፍ ያደረገለት ድርጅቱ አርበኞች ግንቦት 7 መሆኑን ከስፍራው ያገኘነው ማስረጃ ያመላክታል።