Translate

Tuesday, January 24, 2017

ቀዝቃዛዉ ጥምቀትና የበረከት ስምዖን “ግብረኃይል” በጎንደር

ቀዝቃዛዉ ጥምቀትና የበረከት ስምዖን “ግብረኃይል” በጎንደር


ጥምቀትን ያለ ጎንደር ማሰብ የሚቻል አይደለም። ጥምቀት ከኃይማኖታዊ በዓልነቱ ባሻገር ባህላዊ ገጽታ የሚንጸባረቅበት ጉምቱ የአደባባይ በዓል ነበር። የጎንደር ጥምቀት እንኳን ለቱሪስቶች ለቀየዉ ነዋሪዎችም ታይቶ የሚጠገብ አልነበረም። በየዓመቱ በአማካይ 1500 የሚደርሱ ቱሪስቶች ከተለያዮ የአለማችን ክፍሎች ተሰባስበዉ ጎንደር ላይ ይከትሙ ነበር። ታይቶ የማይጠገበዉን የጥምቀት ትዕይንት ከከተራ እስከ ሚካኤል ንግስ ድረስ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚጎበኙት የዉጭ አገር ቱሪስቶች ብቻ ሳይሆን የአገር ዉስጥ ጎብኝዎችም በስፋት ይታደሙ ነበር። “ነበር እንዲህ ቅርብ ኑሯል ለካ” እንድትል ንግስት ጣይቱ ብጡል፤ የ2009 የጥምቀት በዓል አከባበር በጎንደር፡-ያን አስደማሚ ኃይማኖታዊና ባህላዊ ትዕይንት “ነበር” አድርጎት አልፏል።

Monday, January 16, 2017

የአቦይ ስብሃት ነጋ የሙስና ወጎች (ክንፉ አሰፋ)

ክንፉ አሰፋ
በአሜሪካ ሃገር፤ አንድ ባለስልጣን በሙስና ሲባልግ እስር ቤት ይገባል።  በፊሊፒንስ ሃገር አንድ ባልስልጣን የሙስና ወንጀል ቢፈጽም አሜሪካ ይገባል።  የኛ ሃገር ባለግዜ ግን ሙስና ሲሰራ አሜሪካ እየተመላለሰ ይነግዳል። ለግዜው ልዩነቱ የዚህን ያህል ነው። ገለልተኛ የፍትህ አካል  ባለበት ሃገር፤  ሙስና አፍ አውጥቶ አይናገርም፣  እግር አውጥቶም አይራመድም።Sibhat Nega Medhaniye, 81, is one of the founders of the Tigray People's Liberation Front (TPLF).
አዲሱ ቀልድ፤  “ሙስና አለ፣ ማስረጃ የለም!”
በያዝነው “ጥልቅ ተሃድሶ” ዘመን ሙስና ለሁለት ተከፍሎ እንዲታይ ተደርጓል። ማስረጃ ያለው ዘረፋ እና ማስረጃ የሌለው ዘረፋ። ልክ እንደ ግብር አከፋፈል። ግብር ከፋይ “ሀ” እና ግብር ከፋይ “ለ”። ምድቡ በዘረፋው መጠን እና በባለስልጣኑ ጉልበት ይወሰናል።  የዘረፋው መጠን ከአስር ሺህ በር በታች ከሆነ እና ዘራፊው የድል አጥቢያ ታጋይ ከሆነ ማስረጃ ያለው፣  ሙስና ምድብ “ሀ” ይሆናል። መጠኑ ከአስር ሚሊዮን በላይ ከሆነ ደግሞ ሙስና ምድብ “ለ” ተብሏል።  ይህ አይነኬው ምድብ  “ማስራጃ የሌለው ዘረፋ” መሆኑ ነው።  አቅመ-ቢሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በብሄራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው የነገሩን ከዚህ እውነታ የተለየ አልነበረም። የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ የፖሊት ቢሮ እና ምክትል ሚኒስትሮች ከአይነኬዎቹ ጎራ ይመደባሉ። የ4 ሺ ብር ደሞዝተኛ፤  ጀነራል የ10 ሚሊየን ብር ቪላ አሰርቶ ሲያከራይ በግላጭ እየታየ፣ “ማስረጃ የለም” ብሎ ማለፍ የሚያሳምን አይሆንም።  የእያንዳንዱ ዘረፋ ማስረጃ፤ እዚያው አፍንጫቸው ላይ ነው ያለው። ግና የሚወሰነው በባለስልጣኑ ጉልበት መጠን ነው።  ምድብ “ለ”ዎችን ለመድፈር መሞከር ራሱ በሙስና ያስቀፈድዳል።  ጸረ-ሙስና የሚባለውም ድርጀት የተፈጠረው ለእነሱ እና በእነሱው በመሆኑ የሚበየነውም የተገመደለ ፍርድ ነው።

ሂውማን ራይትስ ውች 2017 ሪፖርት፡ ኢትዮጵያ

Armed security officials watch as protesters stage a protest against government
የታጠቁ የመንግስት ወታደሮች በመስከረም ወር 2009 ዓ. ም በቢሾፍቱ ኢትዮጵያ በተከበረው የኢሬቻ በአል ላይ ተቃውሞ የሚያሰሙ ሰዎችን ሲመለከቱ።
እ.ኤ.አ. ከህዳር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ በስፋት ትልቁ በሆነው በመላው ኦሮሚያ ክልል እና ከሃምሌ 2016ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በአማራ ክልል ያልተጠበቀ እና እጅግ ከፍተኛ የህዝብ ተቃዉሞዎች ተደርገው ነበር። የኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች ባብዛኛው ሰላማዊ የነበሩትን ሰልፈኞች ለመበተን በወሰዱት የሀይል እርምጃ ከ500 በላይ ሰዎችን ተገድለዋል።

Friday, January 13, 2017

የህወሓት ተላላኪ ሆኖ በርካታ በደሎችን በህዝብ ላይ ሲፈፅም የነበረው ደረጄ መከታው የተባለው ግለሰብ በአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች እርምጃ የተወሰደበት መሆኑ ታወቀ

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)

ሰሞኑን በአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች የተገደለው ደረጄ መከታው የተባለው ግለሰብ ከዚህ በፊት የቀድሞው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር አባል የነበረና በድርጅቱም ግዳጅ በመላክ ወደ ኢትዮጵያ ሲሄድ አብሮት ሲሄድ የነበረውን የትግል ጓዱንና ድርጅቱን በመካድ የጠላት ተባባሪ በመሆን በታጠቀው የድርጅቱ መሳሪያ ጓዱን በመግደል ለወያኔ ስርዓት እጁን በመስጠት ተቀላቅሏል፡፡ ከአገዛዙ ተቀላቅሎ በመኖር ላይ እያለም ከአንድ የስርዓቱ አገልጋይ ጓደኛው ጋር በመሆን የትጥቅ ትግሉን ይደግፋሉ እንዲሁም በገዢው ቡድን ላይ ህዝብን ያሳምፃሉ ብለው የሚፈርጇቸውን ሰዎች እንዲሰልሉ በአገዛዙ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበረ ቢሆንም ከእለታ አንድ ቀን ሰው በመግደል ታስረው የቆዩ ሲሆን ባልታወቀ ምክንያትም ብዙም ሳይቆዩ ከእስራት ተፈተዋል፡፡ ይኸው ደረጄ መከታው የተባለው ግለሰብ ከእስራት ከተለቀቀ በኋላም ከወያኔ ደህንነት ጋር በመሆን በአሳቻ ሰዓትና በማታ ንፁሃን ዜጎችን በማደን ሲያሳስርና ሲያስደበድብ በተጨማሪም ሲያስገድል መቆየቱን የአካባቢው ህዝብ የአይን ምስክሮች ናቸው፡፡