Translate

Thursday, July 30, 2015

ኦባማ፡ “በንግግር (ወሬ) A፣ በተግባር D” ኦባንግ ሜቶ

“በነጻነት መንገዳችን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑብን”

obang voa4

ለፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ውጤት ቢሰጥ በእስካሁኑ የአፍሪካ ፖሊሲያቸው በንግግር (በወሬ) ደረጃ A በተግባር ግን D እንደሚሰጧቸው ኦባንግ ሜቶ አስታወቁ፡፡ አፍሪካውያንም ሆኑ ኢትዮጵያውያን ለነጻነት በሚያደርጉት ትግል ምዕራባውያን ዕንቅፋት ከመሆን እንዲቆጠቡ አስረዱ፡፡

ኦባማ በአዲስ አበባ

ይገረም አለሙ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በአዲስ አበባ ጉብኝታቸው ከጠቅላይ ምኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ጋር በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት በሰላማዊ ምርጫ የተመረጠ ብለዋል በሚል ከተለያየ አቅጣጫ ተቃውሞና ነቀፌታ እየተሰነዘረባቸው ነው፡፡ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ባደረጉት ንግግር ምርጫው በሰላማዊ ሁኔታ ተካሂዷል ይህ ማለት ግን ዴሞክራሲያዊ ነው ማለት አንዳልሆነ ከአቶ ኃይለማሪያም ጋር መነጋገራቸውን ስም ጠቅሰው ተናግረዋል፡ ምርጫ ግዜ እየጠበቁ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ነጻና ፍትሀዊ መሆን አንዳለበትም አስረግጠው ገልጸዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረቱ ንግግራቸው እስካሁን ተቃውሞ አልተሰማበትም፡፡Obama in Addis Ababa, Ethiopia
የዚህች ጽሁፍ አላማ ኦባማ ስለተናገሩት ማውሳት አይደለም፤በተለይ ሀገር ቤት ያሉ ተቀዋሚዎች ሰላማዊ ምርጫ የሚለውን አገላለጽ ሲቃወሙ አንድም ትናንትን የረሱ ሁለትም በሚቃወሙት ድርጊት ውስጥ የእነርሱ ድርሻ መኖሩን ያልተገነዘቡ ሆኖ ስለተሰማኝ ይህን ለማመለከት ነው፡፡ ትናንትን መርሳትና ራስን ነጻ አድርጎ ሌላውን መውቀስና መኮነን ስር የሰደደ ችግራችን ነው፡፡ ከዚህ መላቀቅ ካልቻልን ደግሞ ለውጥ ናፋቂ ሆነን መኖራችን አይቀሬ ነው፡፡

Thursday, July 23, 2015

ህወሓት በፈጠራቸው ድርጅቶች ውስጥ ተኩኖ ህወሓትን ማዳከም አርበኝነት ነው!

አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ለኢህአዴግ እና አጋር ድርጅቶቹ አባላት የሚከተለው መልዕክት ማስተላለፍ ይሻል።
Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracyህወሓት ጥቂት አባላትና ደጋፊዎች ይዞ ታላቂቷን ኢትዮጵያ ለማንበርከክ እና ሀብቷን ለመመዝበር እናንተን መጠቀሚያ ያደረጋችሁ መሆኑን የምታውቁት ነው። እናንተ አባል የሆናችሁባቸው ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴድ የተባሉ ድርጅቶች የራሳቸው ድርጅታዊ ነፃነት የሌላቸው የህወሓት አገልጋዮች መሆናቸው እነሱ ራሳቸው የሚነግሯችሁ ከመሆኑም በላይ እናንተም በዕለት ተዕለት ተግባራችሁ የምትታዘቡት ሀቅ ነው። እነዚህ ድርጅቶች ህወሓትን ለማስደሰት ሲሉ የራሳቸውን ሕዝብ የሚያስሩ፣ የሚገድሉ፣ የሚዘርፉ፣ ከቀየው የሚያፈናቅሉ፣ መኖሪያ ቤቱን የሚያስፈርሱ መሆናቸው እናንተም እየተሳተፋችሁበት ያለ ሥራ ነውና የምታውቁት ነው። “አጋር ድርጅቶች” የሚል ስያሜ የተሰጣችው አብዴፓ፣ ቤጉህዴፓ፣ ጋህአዴን፣ ሀብሊ እና ኢሶዴፓ “አጋር” ሳይሆን የህወሓት ጀሌዎች መሆናቸው እናንተም እኛም የምናውቀው ነው። እናንተ አባል የሆናችሁባቸው ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴድ፣ አብዴፓ፣ ቤጉህዴፓ፣ ጋህአዴን፣ ሀብሊና ኢሶዴፓ የተባሉ አድርባይ ድርጅቶች ባይኖሩ ኖሮ ህወሓት ለ24 ዓመታት ኢትዮጵያዊያን እየገደለና እያሰረ፤ እየዘረፈ በውሸት ምርጫና በውሸት ዲሞክራሲ ስም ፍጹም የሆነ ዘረኛ፣ ከፋፋይ፣ አምባገነናዊ ሥርዓት በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያሰፍን ባልቻለም ነበር። ህወሓት በኢትዮጵያዊያን አናት ላይ እንዲፈነጭ እናንተ አባል የሆናችሁባቸው ድርጅቶች አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነው።

Tuesday, July 21, 2015

የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጉዞ… (ክንፉ አሰፋ)



ክንፉ አሰፋ
“…ከዚህ በኋላ ህዝብ ሰብስቦ ማውራት ላቆም ነው። ጊዜው ተቀይሯል። ትግል ለደካማ መንፈስ አይሆንም። ትግል መውደቅን ይጠይቃል። ሲወድቁ ግን ለመነሳት መሞከርን ይጠይቃል። ስንወድቅ ልታዩን ትችላላችሁ ስንነሳ ግን ታዩናላችሁ … ” ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ይህንን የተናገሩት የአስመራ ጉዟቸው ከመሰማቱ ጥቂት ቀናት በፊት ነበር። ንግግሩ ለብዙዎች ግርታ መፍጠሩ አልቀረም። ከቀናት በኋላ የኤርትራን ምድር ሲረግጡ “ስንነሳ ግን ታዩናላችሁ…” ማለታቸው ግልጽ ሆነ።Professor Berhanu Nega in Eritrea
ከምርጫ 97 በፊት ዶ/ር ብርሃኑ በፖለቲካ ስብእናቸው የሚታወቁት ለሰላማዊ ትግል ባላቸው የከረረ አቋም ነበር። በእስር ቤት ሆነው በጻፉት “የነጻነት ጎሕ ሲቀድ፤ …” መጽሐፋቸው ሰላማዊ ትግል ያለውን የሞራል፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ የበላይነት ምሳሌ እያስቀመጡ ዘርዝረዋል።
ለዚህም ነበር ከሰላማዊ ትግል ወጥተው “ሁለገብ ትግል” ለማካሄድ ማቀዳቸውን ሲገልጹ ለብዙዎች ድንገተኛ እና አስደንጋጭ የሆነው። የጦርነትን አስከፊ ገጽታ ሲነግሩን የነበሩ እኝህ ምሁር በአንድ ግዜ ወደ ተቃራኒው የትግል ስልት ሲዞሩ ያቀርቡት የነበረው ምክንያት በወቅቱ ብዙዎችን ሊያሳምን አልቻለም። ምክንያቱም አመጽ ወይንም ጦርነት ከባድ ነገር ነው። ገንዘብ እና ግዜን ይበላል። ከሁሉም በላይ የህይወት መስዋእነትን ይጠይቃል። የሰላማዊ ትግሉ ስልቶች ገና በደንብ አልተፈተሹም የሚሉም ጥቂቶች አልነበሩም።

Sunday, July 19, 2015

ሊቀመንበራችን ትግል ሜዳ ውስጥ ነው!- መግለጫ

ሊቀመንበራችን ትግል ሜዳ ውስጥ ነው!- መግለጫ

ሐምሌ 12 2007 ዓ.ም.
ህወሓት በኢትዮጵያዊያን እና በኢትዮጵያ ላይ ያሰፈነው ዘረኛና ፋሽስታዊ አገዛዝ እንዲያበቃ፤ በምትኩም ፍትህ፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሰፈኑበት የፓለቲካና የኢኮኖሚ ሥርዓት እንዲመሠረት እና የሀገራችን አንድነት በጠንካራ መሠረት ላይ ለማኖር አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ተገዶ የገባበት የመረረ የአመጽ ትግል መጀመሩን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያዊያን የነፃነት አርበኞች በጀግነትና በጽናት እየታገሉ ነው።
ይህ ትግል በባርነትና በነፃነት መካከል የሚደረግ ወሳኝ ትግል ነው። የዚህ ትግል ውጤት የእኛ የዚህ ዘመን ትውልድ ሕይወት ብቻ ሳይሆን የአገራችንን የወደፊት ታሪክ፤ የልጅ ልጆቻችንን ሕይወት ይወስናል። በዚህም ምክንያት ይህንን ትግል በድል መወጣት ግዴታችን ነው። በዚህ ወሳኝ ወቅት ለነፃነት ግድ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከጎናችን ሊቆም ይገባል።

Thursday, July 16, 2015

ፍርድ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ወሰነ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ወሰነ፡፡ የፌደራል አቃቤ ህግ ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር በአካል ተገናኝታችኋል›› የሚል ክስ የመሰረተባቸው ተከሳሾቹ ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር ተገናኝታችኋል ከተባለ አቶ አንዳርጋቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ታስረው የሚገኙ በመሆናቸው መከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ይታዘዝልን›› የሚል ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡Ato Andargachew Tsige, Ginbot 7
የፌደራል አቃቤ ህግ በበኩሉ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ እና በእነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ መዝገብ ላይ ክስ ቀርቦባቸው በእድሜ ልክና በሞት እንዲቀጡ ተወስኖባቸው የህዝባዊ መብታቸው የተሻረ በመሆኑ በምስክርነት ሊቀርቡ አይችሉም ብሎ ተቃውሟል፡፡ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ህዝባዊ መብት በመሻሩ ለፍርድ ስራ ልዩ አዋቂ ወይንም ነባሪ ሆነው መስራት አይችሉም ያለው የፌደራል አቃቤ ህግ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በተጨማሪ ምስክርነት ቀርበው መመስከር አይገባቸውም ሲል የተከሳሾቹ ጥያቄ ውድቅ እንዲሆን ለፍርድ ቤቱ አመልክቶ ነበር፡፡

Wednesday, July 15, 2015

አሻራ መጽሄት – ቁጥር 2 (ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም፣ ጸጋዬ ገብረመድህን አርአያ፣ ዩሱፍ ያሲን፣ ደረጀ ደስታ…)

– ጸጋዬ ገመዴህን አርአያ – “ጠፍአት አገርነ” ትናንት ማታ ጨረቃዋንም አዋልደናል!

– ዩሱፍ ያሲን – የአረቡ ዓለም መቆራቆስ ቀይ ባህርን ይሸጋገር ይሆን?

– ደረጀ ደስታ – ቆም በል! ህዝብ ከሚያልቅ ህዝብ ቢያልቅ ይሻላል!

– ቆይታ ከፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ጋር እና ሌሎችም…

Ashara Magazine Number 2

Tuesday, July 14, 2015

“የክስ መቋረጥ” ወይስ የኦባማ ጉብኝት?

ክስ ከተቋረጠ ሊቀጥል ይችላል ማለት ነው?!

z9


“ክሴን አቋርጫለሁ” ከማለት ባለፈ ምክንያቱን ከመናገር ተቆጥቧል
ከአንድ ዓመት በፊት ሚያዝያ 26 እና 27 ቀን 2006 ዓ.ም. በድንገት ተይዘው ከታሰሩ በኋላ፣ በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ ተመሥርቶባቸውና የሰነድና የሰው ማስረጃ ቀርቦባቸው፣ ለብይን የተቀጠሩበትን ቀን እየተጠባበቁ ከነበሩት አሥር ተከሳሾች መካከል አምስቱ በድንገት ሐምሌ 1 እና 2 ቀን 2007 ዓ.ም. መፈታታቸው እያነገጋገረ ነው፡፡

Friday, July 10, 2015

ስለ እውነት፣ ስለፍትሕ እናት ኢትዮጵያ አሁንም ትጮኻለች!!

በዲ/ን ተረፈ ወርቁ
Few bloggers and journalists freed in Ethiopia
የኢሕአዴግ መንግሥት አሸባሪዎች ናቸው፣ በዜጎች ክቡር ደም የቆመውን ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ የተደራጁ ናቸው፣ በውጭ አገር ካሉ ሰላማችን፣ ዕድገታችን በቅናት ብግን እያደረጋቸው ካሉና አገራችንን ለማተራመስ ቆርጠው ከተነሡ ከፈረደበት ሻቢያ፣ ሽብርተኛ ድርጅቶችና ጽንፈኛ ኃይሎች ጋር አብረው ይሠራሉ፣ የአገርንና የሕዝብን ደኅንነትና ፀጥታ አደጋ ላይ ጥለዋል፣ በኢትዮጵያ ሰላምና በሕዝቦቿ ልዑላዊነትም ላይ በመደራደር ይቅር የማይባል ክህደት ፈጽመዋል ያላቸውን የዞን ፱ ጦማርያንና ሌሎች ጋዜጠኞችን ከአንድ ዓመት በላይ ፍርድ ቤት ሲያመላልሳቸው ቆይቷል፡፡

Thursday, July 9, 2015

አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ላይ የሰነዘረውን ድንገተኛ ማጥቃት ተከትሎ ኃይለማርያም ደሳለኝ “ህዝብን አስፈቅደን ከሻብያ ጋር እንዋጋለን” አሉ

አርበኞች ግንቦት 7 በተለያዩ ግንባሮች በወያኔ ላይ የከፈተውን ማጥቃት ተከትሎ ከወያኔ ጎራ የተምታቱ ዜናዎች እየተደመጡ ነው።Ethiopian PM Hailemariam Desalegn on Al Jazeera
ቀደም ሲል የተሰነዘረባቸውን ጥቃት “ምንም ነገር የለም” ብለው ለማድበስበስ የሞከሩት የወያኔ ሹማምንትና ካድሬዎች ዜናው በኢሳት ቴሌቪዥን፣ ሬድዮ፣ በተለያዩ ድረ-ገጾች እና በዋንኛነት ደግሞ በማህበራዊ መገናኛ ገጾች በስፋት በመዘገቡ “ምንም ነገር የለም” ከሚለው ወደ ተምታታ ዜና ማሰራጨት ተሸጋግረዋል።
የወያኔዎቹ ቃል-አቀባይ ጌታቸው ረዳ በሚሚ ስብሃቱ ኤፍ ኤም ራድዮ ላይ ቀርቦ “በአካባቢው በመሬት የተነሳ መጠነኛ ግጭት ነበር” በማለት ሁኔታውን ከገለጸ በኋላ ወድያውም “በሻብያ ላይ የማያዳግም ቅጣት” ሊሰነዝሩ እንደሚችሉ ተናግሯል።

የ ‹‹ይቅር ባይ›› መንግስት ‹‹ይቅር የማይባል›› ድርጊት!!

አሌክስ አብርሃም
‹‹በመንግስት›› ካባ የተጀቦኑት ግለሰቦች ፈፅሞ ‹‹ይቅር ባይ ›› አይደሉም!! …ይቅር የማይባል ስህተት የህዝብ ልጆች ላይ የሚሰሩ ጭፍን ጥላቻ እና የበታችነት ስሜት የተጠናወታቸው አንባገነኖች እንጅ …አሁንም ‹‹ መንግስት ›› በጭፍን ጥላቻ ያሰራቸውን በርካታ ኢትዮጲያዊያን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ … የማንንም አገር መሪ መምጣት ሳይጠብቅ ሊፈታ ይገባል ! እኛ ኢትዮጲያዊያን አባቶቻችን በከፈሉልን ንፁህ መስዋእትነት ከነድህነታችን ተከባብረንና ተፋቅረን የምንኖር የተከበርን ህዝቦች እንጅ …መንግስት ለብድርና እርዳታ ጥማቱ አበዳሪ በመጣ ቁጥር እንደዘንባባ እየዘነጠፈ ሃያላን መሪዎች እግር ስር የሚያነጥፈን ርካሽ ህዝቦች አይደለንም !!Ethiopian arrested zone 9 bloggers
እዝኛለሁ … ከእስሩ የበለጠ የተፈቱበት መንገድ አሳዝኖኛል …መንግስት ለዜጎች ያለውን እጅግ የወረደ ንቀትና ‹‹ማን አለብኝነት›› የሚያሳይ ድርጊት ነው … ኢትዮጲያዊያን ባልቴቶች በምርኩዝ ፍርድ ቤት ድረስ ሂደው እያለቀሱ ሲለምኑት በወታደር እያስገፈተረ ያስባረረ መንግስት …ህዝቦች በአደባባይ ወንድማ እህቶቻችንን ፍታልን እያልን ስንለምን ከነደጋፊወቹ ያሻውን ፀያፍ ስም እየለጠፈ ሲሳለቅና ሲያሽጓጥጥ የኖረ መንግስት… አሁን የባርነት ስነልቦናው በፈጠረው መሽቆጥቆጥ ‹‹ወደቤታችሁ ሂዱ›› ብሎ ከየቤታቸው አፍኖ የወሰዳቸውን ዜጎች መፍታቱ … ብሔራዊ ውርደት ነው !! እንዲህ አይነት ‹‹ስፈልግ አስራችኋለሁ ስፈልግ እፈታችኋለሁ ›› መልእክት ያዘለ ‹ነፃነት› ከጠባብ እስር ቤት ወደሰፊ እስር ቤት ሰዎችን ማዘዋወር እንጅ ፍትህ ያመጣው ነፃነት አይሆንም …አይደለምም!

Tuesday, July 7, 2015

ወቅታዊውን የሕዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች የፍርድ ሂደት አስመልክቶ ከ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› የተሰጠ መግለጫ

ሰኔ 29/2007፤ አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ
በሙስሊሙ ህብረተሰብ ወኪሎች ላይ የተላለፈውን የግፍ ፖለቲካዊ ፍርድ አንቀበልም!
በአንድነት በመቆም ለረጅም የትግል ጉዞ በአዲስ መንፈስ እንነሳ!
Ethiopian Muslims protest, Addis Ababaላለፉት ሶስት ዓመታት በበርካታ አስቂኝ እና አሳዛኝ ድራማዎች ታጅቦ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ ዳዒዎች፣ ጋዜጠኞች እና አርቲስቶች የፍርድ ስነ-ስርዓት እንደተጠበቀው የኢትዮጵያ የፍትህ ስርዓት የደረሰበትን ዝቅጠት በሚያሳይ መልኩ እነሆ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ ኮሚቴዎቻችንም በግልፅ ከችሎት ፊት ‹‹አሁን ባለው የፍትህ ስርዓት ሚዛናዊ የሆነ ፍትህ እናገኛለን ብለን ሳይሆን ለታሪካዊ እማኝነቱ ብለን ቀርበናል›› ሲሉ የተቹት የችሎት ክርክር መንግስት ራሱ ከሳሽ ራሱ ዳኛ የሆነበት እና ፍትህ የተዘነበለበት አሳዛኝ ክስተት ሆኖ አልፏል፡፡ ሂደቱ የተጠርጣሪዎች ከፍርድ በፊት እንደ ነፃ የመታየት መብት በመንግስት መገናኛ ብዙሃን የተጣሰበት፣ መንግስት የሃሰት ምስክሮችን በፕሮጀክተር ታግዞ በግልጽ ያሰለጠነበት፣ አቃቤ ህግ የዳኞች አለቃ መሆኑ የታየበት እና ዳኞች ማረሚያ ቤቱን እንኳን ማዘዝ እንደማይችሉ የታዘብንበት ትልቅ የፍትህ ክስረት ነበር፡፡

ወያኔ አርበኞች ግንቦት 7 የከፈተበትን ጦርነት ከህዝብ ለመደበቅ እየሞከረ ነው

ባለፉት ሦስት ቀናት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ትግራይ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የወያኔን ሃይል ገጥመው የወያኔ መኮንኖችን ጨምሮ በርካታ የወያኔ ሰራዊት አባላትን እንደገደሉ በቃል-አቀባያቸው አማካኝነት ለኢሳት ቴሌቪዥን ገልጸዋል። ለጥቀውም እስከ ትላንት ድረስ ውጊያው ቀጥሎ እንደሚገኝ በድጋሜ ዜናውን አብስረዋል።arbegnoch-ginbot7-fighters
በወያኔ ዘረኛና ግፈኛ አገዛዝ የተንገፈገፈው የኢትዮጵያ ህዝብም ጆሮውን አቅንቶ ሁኔታውን በመከታተል ላይ ነው። ቀድሞውንም የወያኔ ሥርዓት ያለ ሃይል ትግል አይንበረከክም፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካም ሆነ የሥርዓት ለውጥ ሊመጣ የሚችለው በተቃውሞው ጎራ የተሰለፉት ተባብረው በወያኔ ላይ ክንዳቸውን ሲያሳርፉ ብቻ ነው ብለው የሚያምኑት ኢትዮጵያውያን አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ላይ የከፈተውን ማጥቃት በከፍተኛ ደስታ ነው የተቀበሉት።
አንዳንዶች አርበኛውን በገንዘብ ለመደገፍ እና ለማጠናከር ከወዲሁ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ በወያኔ ጎራ በኩል ይህን ጉዳይ በተመለከተ ምንም የተሰማ ነገር የለም። ጥያቄው… ለወትሮው ትንሽ ትልቁን “የግንቦት 7” አባል ነው ብሎ በመፈረጅ ንጹሃንን እስርቤት የሚወረውረው ወያኔ በይፋ ስለተከፈተበት ጦርነት ለምን ዝምታን መረጠ? ነው።

Thursday, July 2, 2015

Ethiopia: Respect court rulings and release opposition members

Woyneshet Molla (left), Ermias Tsegaye, Daniel Tesfaye(right) and Betelehem Akalework( not in the picture) have been rearrested repeatedly on the same charges. 

TPLF/EPRDF Makes a Mockery of Judges’ Decision to Release Semayawi Youth by Over-riding Court Verdict

SMNE Press Release | Washington, DC

Not only are Ethiopian elections a farce—reconfirmed by recent regime claims of a 100% victory in the May 24, 2015 national elections—but so is the independence of the judicial system. This mockery of justice was shown when police re-arrested four young members of the Semayawi opposition party [Blue Party} after they were released from court. This happened not once, but three times, despite the fact they had already been freed each time by the court. They remain in jail as of today.Obang Metho, Executive Director SMNE
Weynishet Molla, Ermias Tsegaye, Daniel Tesfaye and Bethlehem Akalewerk had been arrested, jailed and beaten on April 22, 2015 after being charged with creating violence and disturbing the rally the EPRDF had called in response to the ISIS killing of 30 Ethiopians in Libya. Following their fourth arrest and jailing for the same incident, a security agent revealed that “someone at the top” of the ruling party opposed their release.

Wednesday, July 1, 2015

ፀሃፍ፦ አሰባሳቢ ማንነት፣ ባንድ ሃገር ልጅነት የኢትዮጵያ እጣ ፋንታ

ፀሃፊ፦ ዩሱፍ ያሲን

ምስክርነት፦ በጥላሁን አፈሣ
Yousuf Yassen's book

አለም አቀፍ ድጋፍ የተቸረው “ልማታዊ” አንባገነናዊነት በኢትዮጵያ


Time_oppress_FLAT.JPG


“የአፍሪቃ ድሃ ባይጠግብም እንኳ ቀምሶ ካደረ ይበቃዋል” አይነት ንቀት የተሞላው የምዕራቡ አለም ምልከታ ከመቼውም ጊዜ በከፋ መልኩ አፍጦና አግጦ እየታየ ነው፡፡ በርሃባችንና በእርስ በእርስ መናቆራችን ለዘመናት ሲነግዱበትም ሲማረሩበትም ቆይተዋል፡፡ ዛሬ ዛሬ የመጫወቻው ካርድ ተቀይሮ ለአፍሪቃ አንባገነኖች አንድ ቃል ተለጥፎላቸው ካሳላፍነው ታሪክ ምናልባትም በከፋ መልኩ ጉዟችንን ቀጥለናል፤ የኋሊት ይሁን ወደፊት እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን የምዕራቡ አለም “ልማታዊ” በሚል ካባ የተከናነበውን የለየለት አንባገነናዊነት ሙሉ ድጋፋቸውን እየሰጡ ለመሆኑ የኦባማን የኢትዮጵያ ጉዞ ጨምሮ በርካታ ምልክቶችን እያየን ነው፡፡ ከምርጫው በፊትም ሆነ ከተጠናቀቀ በኋላ የአውሮፓ ኅብረትና የአሜሪካን መንግስት ያሳዩትም ድጋፍ የእዚሁ መገለጫ ነው፡፡