Translate

Tuesday, June 30, 2015

ሰበር ዜና፦ ቴዲ አፍሮና ጎሳዬ ለሀሙሱ ESFNA ኮንሰርት ይደርሳሉ!

32ኛው በሰሜን አሜሪካ በድምቀት እየተከበረ የሚገኘው የኢትዮጲያዊያን የሰፖርትና የባህል ፌስቲቫል ላይ ከተዘጋጁት ዝግጅቶች መሀከል በጉጉት የሚጠበቁት የሃሙስ እና የዓርብ የሙዚቃ ዝግጅቶች በወጣላቸው ፕሮግራም መሰረት እንደሚደረጉ ተረጋገጠ።
ቴዲ አፍሮና ጎሳዬ ተስፋዬ ቪዛቸውን ለማግኘት የአሜሪካ ኤምባሲ የሲስተም መበላሸት ያዘገየው ቢሆንም አሁን ከደቂቃዎች በፊት ኤንባሲው ችግሩን እንዳስተካከለ የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል።
U.S. Embassy Addis Ababa
በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ባለፉት ሳምንታት የተፈጠረው የሲስተም ችግር መፈታቱን በደስታ እየገለጠ፡ ቪዛችሁ የተፈቀደላችሁ አመልካቾች ፓስፖርቶቻችሁን መረከብ እንደምትችሉ እናስታውቃለን፡፡ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በ011-558-2424 ይደውሉ፡፡
The consular section of the American Embassy in Addis Ababa, Ethiopia is pleased to announce that the technical problem of Consular Sections throughout the world is resolved. Applicants who were issued visas can now collect their passports accordingly. Should you have further question, please contact፡ 011-558-2424
በቪዛው ጉዳይ ኮንሰርቱ አይደረግም የሚለው የሰሞኑ ፍርሀት የተወገደ ሲሆን የአርቡ ኮንስርት የአሰቴር አወቀ፣የቡዛየሁ ደምሴ፣የጃኪ ጎሲ ኮንሰርትም በተያዘው ፕሮግራም እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል።

No comments:

Post a Comment