Translate

Wednesday, April 23, 2014

የወያኔዎች አስቂኝ መመሪያዎችና ዐዋጆች

ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)

በመጀመሪያ የክርስትና እምነት ተከታይ አንባቢዎች እንኳን ለ2006ዓ.ም የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡
ሕወሓት ወደ ሥልጣን መጥቶ በዓይነቱ የተለዬ የጥቁር አፓርታይድ ሥርዓትን በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ካቆመ ወዲህ እጅግ ብዙና ለመቁጠርም የሚያዳግቱ መመሪያዎችንና ዐዋጆችን ቀርፆአል፡፡ አንዳንዶቹን በዘፈቀደና በነሲብ እየቸከቸከ በፈለገው ሰዓትና ወቅት ራሱ ተግባራዊ በማድረግ፣ አንዳንዶቹንም ለማስመሰል ያህል በእንቅልፋምና ደናቁርት የ“ፓርላማ” አባላቱ አማካይነት በዐይን ጥቅሻ በሚታዘዝ የሆዳም ማይማን ጭብጨባ “አጸድቆ” ሥራ ላይ በማዋል ሀገርንና ሕዝብን ማተራመስ ከያዘ ሁለት ዐሠርት ዓመታትን ጨርሶ የሦስተኛውን ዐሠርት አንድ ሦስተኛ ያህል ጊዜ ለማገባደድ ጥቂት ወራት ብቻ ይቀሩታል፡፡
ከቅርቦች ልጀምር፡፡ ቅድም ቡና ስጠጣ እንዲህ የሚል ወሬ ሰማሁ፡፡ እውነት ይሁን ሀሰት ገና አላረጋገጥሁም – ይሁን እንጂ የወያኔን ባሕርይ ለሚያውቅ ይህን ወሬ ሀሰት ነው ማለት የሚያስችል አዲስ ነገር አይገኝም፡፡ ከዚህ የበላለጡ አስቂኝና አስገራሚ መመሪያና ዐዋጆችን እየታዘብን 23 የመከራና ፍዳ ዓመታትን ስላቀናን ይህኛውን የተለዬ አያደርገውም፡፡ የሰማሁት ምን መሰላችሁ – ልማታዊ የወያኔ ሙዚቀኞችና ዳንኪረኞች በኮፒራይት መቸገራቸውን ስላመለከቱና ለዚህም ችግር መባባስ ትልቁን ሚና እየተጫወቱ የሚገኙት የስልኮች ሚሞሪዎችና ብሉቱዝ በመሆናቸው እነዚህን አገልግሎቶች የሚሰጡ ማናቸውም የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወደ ሀገር እንዳይገቡ መንግሥት ማገጃ አውጥቷል የሚል ነው፡፡ በዚህም ሳቢያ የእጅ ስልኮችና የመሳሰሉት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ማዕቀብ ሊጣልባቸው እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡
ለነገሩ ከኢትዮጵያ የወያኔ ሚዲያዎች በውዴታየ ስለራቅሁ ይህ መመሪያ በገሃድ ወጥቶ ይሁን አይሁን እስካሁን አላወቅሁም፡፡ በበዓሉ ምክንያት ከጎረቤት ውጪ ራቅ ወደሚል ሌላ ውጪ አልወጣሁም፡፡ ግን አይሆንም አይባልም፡፡ ወያኔ ከፈለገ “ከዛሬ ጀምሮ ከትግሬ በስተቀር ነጭ ጤፍ እንጀራ የሚበላና ጮማ የሚቆርጥ ሌላ የማኅበረሰብ ክፍል እንዳይኖር ዐውጃለሁ፤ ቢኖር ግን ህገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ እንደቃጣ ተቆጥሮ በአሸባሪነት የክስ ቻርጅ እስከሞት ሊደርስ በሚችል ከፍተኛ ቅጣት ዋጋውን ያገኛል፡፡” ብሎ ሊያውጅ ይችላል፡፡ ማንን ወንድ ብሎ ነው ወያኔ የፈለገውን ከማድረግ የሚቆጠበው? ወያኔ በምን ይዳኛል? በምንም፡፡ ለነገሩ ቀን የሰጠው ጅብ አንበሣንና ነብርን ሲቆረጣጥም ቢታይ ዘመኑ የትንግርት ነውና አያስገርምም፡፡ በኢትዮጵያም ሆነ በተቀረው ዓለም እየሆነ ያለውም ይሄውና ይሄው ብቻ ነው፡፡ ግን ግን በሀገራችን ለወደፊቱ ጅብ የማያሸንፍበትን ቀዳዳ መዝጋት የሚያስችለንን ታላቅ የሦስተኛው ሚሌንየም ሥልት መንደፍ እንደሚገባን ከወያኔው አዋራጅ የተፈጥሮ ልክስክስ ጠባይ የተማርን ይመስለኛል፤ የመንጌን አማርኛ ልጠቀምና ብታምኑም ባታምኑም የአፄውና የደርጉ ሥርዓቶች መንገዱን ባበጃጁለት ወያኔ ክፉኛ ተዋርደናል፡፡ አሸንፎ የማያውቅ ትንሽ ሰው እንዳያሸንፋችሁና መሣቂያና መሣለቂያ እንዳያደርጋችሁ በርትታችሁ ጸልዩ፡፡ ትንሽ ስል ማሸነፍን እንደህልም ይቆጥር የነበረ የባንዳዎችና የሥነ ልቦና ደዌ የተጣባቸው በበቀልና ጥላቻም የተሞሉ ዜጎች ውላጅ የሆኑ መለስን፣ ስብሃትንና ሣሞራን የመሰሉ የታሪክ አራሙቻዎች ማለቴ ነው፡፡ እንደነዚህ ያሉ ቀላሎች በታሪካዊ መደላድሎች መመቻቸት ምክንያት አንዳች ዕድል ካገኙ እንዴቱን ያህል ወጥ እንደሚረግጡና ነገሮችን በምን ያህል ደረጃ እንደሚያበለሻሹ በሚገባ ተረድተናል፡፡ ለማንኛውም ሚሞሪ ያላቸው ስልኮችና መሰል ጋጄቶች ሊከለከሉ ነው አሉ፡፡ አልጋህ ውስጥ ተደብቀህም በሙዚቃ መቆዘም ሊቀር ነው፡፡ ኧረ ባል በሚስቱና ሚስትም በባሏ ቀረጥ እንዳይከፍሉ ያሰጋል፡፡ “እያንዳንድሽ ማን በሚገዛው ሀገር ውስጥ ተኝተሸ ዓለምሽን ትቀጫለሽ?” ብሎ ምቀኛው ወያኔ ለአንድ ግንኙነት ብር 50 ግብር ቢጥልና በየጉያችን ኤሌክትሮኒክ ሥውር ባልቦላ(ማይክሮቺብስ) እንደኖር ፕላንት ቢተክል ባለትዳሮች ምን ይውጠናል? ያቺው ብቸኛ መዝናኛችን ላይ ወያኔ በመብረቃዊ የማጥቃት እርምጃው ቢዘምትባት ወዴትና ለማንስ አቤት እንላለን? የሰይጣን ጆሮ ይደፈን፡፡ የምንተነፍሰውን አየርና የፀሐዩንማ በኑሮ ውድነቱ ላይ ጨምሮ ባልተወለደ አንጀት እያስገፈገፈን ነው፡፡
ከውጭ ሀገራት በበርሜል ዕቃ ማስገባት ተከልክሏል፡፡ በካርቶንና በከረጪት እንጂ በርሜል አይገባም፡፡ ምክንያቱን መጠየቅ አያስፈልግም፡፡ ሊሆን የሚችለው ብቸኛ ምክንያት አንዱ ወያኔ ትግሬ – አንዱ ዘመነኛ በጥጋብ የተወጠረ ትግሬ ወያኔ – የበርሜል ፋብሪካው ገበያው ቀንሷል ማለት ነው፡፡ ለዚህ መፍትሔው ደግሞ ቀላል ነው፡፡ ማታ ሼራተን ወይ ሂልተን ላይ ለሚጋብዛቸው ወያኔ ተጋዳላዮች ለአንዱ ሹክ ማለት ነው – “ከነገ ጀምሮ ከዐረብም ይሁን ከሌላ ሀገር የበርሜል ዘር በቦሌም ይሁን በባሌ ወደኢትዮጵያ ሕዝቦች መኖሪያ ክልሎች እንዳይገባ ጥብቅ መመሪያ አውጣልኝ፡፡” በቃ፡፡ ይቺ ትዕዛዝ ብቻ በቂ ናት፡፡ ከማግስቱ ጀምሮ በርሜል ይቅርና አንዲትም የላስቲክና የብረት ኩባያ ወደሀገር እንዳትገባ ማድረግ ነው፤ ለወያኔዎች ይህን ማድረግ ቀላል ነው፡፡ ሣተናዎቹ ወያኔዎች የፈለጉት ይሆናል፤ ያልፈለጉት አይሆንም – ዘጠና ሚሊዮን ሕዝብ አንቀጥቅጠው መግዛት የቻሉ የአጋንንት ወኪሎች በመሆናቸው ለጊዜው የሚያቅታቸው ነገር የለም፡፡ ይህንን ደግሞ ዕንወቅ፡- እነዚህ ሽል መንጣሪ ዘረኛ የሣጥናኤል ልጆች ከራሳቸው የሚወጣ አንዳችም ኃይል የላቸውም፤ ኃይላቸው የኛ ክፋት፣ የኛ ብዙ ክፋት ነው፡፡ (ለምሳሌ አሁን አንቺ ለኔ መልካም ታስቢያለሽ? ካሰብሽልኝ እሰዬው – ካልሆነ ግን አሁኑኑ ጀምሪውና ሞክሪው፡፡) አዎ፣ በርግጥም ክፉዎች ነን፡፡ በክፋታችንና በአመፀኝነታችንም ሰበብ እያገኘን ያለነውን እያገኘን ነን – በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻም ሣይሆን በመላው ዓለም ዙሪያ፡፡ እንጂ እነዚህ የት እንዳሉ እንኳን የማይታወቁ ‹ረቂቅ› ጠላቶቻችን ይህን ሁሉ ሚሊዮን ሕዝብ እንዲህ ኮድኩደው ባላሰቃዩት ነበር፡፡ ወደኅሊናችን ብንመለስ፣ ብንደማመጥ፣ ቁስላችንን ብንመለከት፣ የተፋፋቅነውንና የተጋጋጥነውን በጋራ ለማከም – ለመተካከም- ብንቆርጥ….. እውነቴን ነው የምለው ችግራችንን ለማስወገድ ጥቂት ወራት ብቻ በበቁን፡፡ ግን ብዙዎቻችን በአሉታዊነት የተጠመቅን፣ የክፋታችን ክርፋት ቀድሞን አካባቢን በመጥፎ ጠረን የሚበክል፣ በአስመሳይነትና በሥልጣን ጥም የታወርን፣ በንቀትና በትዕቢት ተወጥረን በጥላቻ ገመድ አንዳችን አንዳችንን የምንጠልፍ፣ በመታች ደብተራና በአባይ ጠንቋይ ድቤ መቺ አበጋር በሰው ላይ እያስመተትንና እያስተበተብን የተቀየምናቸውን ወይም የተመቀኘናቸውን ሰዎች የምናሳብድና የምናደኸይ፣ ለአገዛዝ እንዲያመቸን ብዙኃኑን ዜጎች በማይምነት ጥቁር መጋረጃ ሰነካክለንና በማይረባ የትምህርት ሥርዓት ወጣት ትውልድን አደንቁረን የምናስቀር፣ በሚዲያና በወረቀት ላይ ያልሠራነውን እንደሠራን እያስመሰልን የውሸት ልቃቂት የምንተረትርና የሀሰት እስታትስቲክስ በየዋሃን ዜጎች ጆሮ ዙሪያ የምናዳውር፣ ከጥረት ይልቅ በሰይጣናዊ መንገድና በሙስና በአቋራጭ እንዲያልፍልን የምንሞክር ግብዞችና አንዳችን ለሌላኛችን የማንተኛ ሸፍጠኞች … በመሆናችን የምናስበውን ከመፈጸማችን በፊት ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር አምላከ ኢትዮጵያ ስንኩል ዕቅዳችንንና በራስ ወዳድነት ላይ የተመሠረተ አጥፊ ሤራችንን አስቀድሞ የእምቧይ ካብ ያደርገዋል – ይህን ነገር ‹ሀሰት ነው› ብለህ የምትሞግተኝ ካለህ ወደ ኢትዮጵያ ምጣና ተጨባጩን ማኅበረሰብኣዊ ተራክቦ ተመልከት፤ ከዚያም “አሃ፣ እውነትም ወያኔም ሲያንሰን ነው ለካንስ” ብለህ ልትፈርድ ትችላለህ – ይህንን እነሱም ያውቁታል፤ እኛም እናውቃለን፤ ፈጣሪም ያውቀዋል፤ ሰይጣንም ሣይቀር በሚገባ ያውቀዋል – የክፋት ሠራዊት አባላት ግና ጊዜያቸውን በደንብ እንደሚጠቀሙበት የታወቀ ነውና ካለሰዓቱ ንቅንቅ አይሉም፤ ጅብ የጎረሰውን እያላመጠ ይሞታታል እንጂ እየሞተም ቢሆን መብላቱንና ግዳይ መጣሉን በተስፋ መቁረጥ ምክንያት አይተውም፡፡ የሚመር አውነት ነው፡፡
በሳይጋገር ተቦካና በላም አለኝ በሰማይ ገና ለገና ሥልጣን ተገኝቶ፣ ገና ለገና ወያኔ ወድቆ፣ ገና ለገና በሀገር ላይ “ዴሞክራሲ” ‹ሰፍኖ›፣ ገና ለገና ከአንበሣ አፍ ሥጋ ወድቆ ለጅብ ተርፎ … ተቃዋሚዎቻችን የሚያሳዩትን የርስ በርስ መጠላለፍና የሚያካሂዱትን ዶንኪሾታዊ ፍልሚያ እንኳን አታይም? ከዚህ አንጻር ውጥንቅጡንና አስጠሊታውን የታሪካችንን ገጽታ ስናይ በመቶዎችና በሺዎች በሚገመቱ የፖለቲካና ማኅበረሰባዊ ኩይሣዎች እየተቧደንን በሁለንተናዊ የሥነ ልቦናና አካላዊ ጦርነት ለዘመናት መፈሳፈሳችን የወያኔን ተልእኮ ስኬታማነት ለማረጋገጥ ከማገዛችን ውጪ የትም ልንደርስ አልቻልንም፤ ያማረ ንግግር፣ ያማረ የፖለቲካ ፕሮግራምና የተዋበ ፍልስፍናም እንዲሁ የዕውቀታችንን ምጥቀትና የመጻፍ ችሎታችንን ከማሳየት ባለፈ የረዳን ነገር የለም – እንጂ ለምሁር ለምሁርማ ስንት ሺህ ዶክተርና ፕሮፌሰር ሞልቶን አልነበረምን? የጥንት አስተሳሰብ በዘመናዊ ቆዳ ተሸፍኖ በጠበጠን እንጂ ንግግር ዐዋቂና ነገር ሰላቂማ ሞልቶናል፡፡ እናሳ፡- ከእኛ ከኢትዮጵያውያን በላይ ጉዶችና ተዓምረኞች ይገኛልን? “እባብ ልቡን አይቶ እግሩን ነሣው” እንደምንል የብዙዎቻችን ፍላጎት ከአነጋገራችንና ከዐይነ ውኃችን ጭምር ይታወቃል፤ በክፉ አሳባችንም ምክንያት ውጥናችን ሳይጀመር ይከሽፋል፡፡ እናም እንደመፍትሔ ሁላችንም እውነተኞች እንሁን፤ ማስመሰልን እንጠየፍ፤ ለወገናችን የዓዞን ሣይሆን ለልጇ ስትል እንደተወጋችው ጎሽ ከአንጀት እናልቅስ፤ ከዘረኝነትና ጎጠኝነት አረንቋ ባፋጣኝ እንውጣ፤ ያለንበትን ዘመን እንረዳ፡፡ ወገናችንን እንውደድ – እናፍቅርም፤ ሀገራችንንና ሕዝባችን የምንለውን ወገናችንን ለሥልጣን መወጣጫነት ሣይሆን በሀቅ ወደን እስከሕይወት መስዋዕትነት ትልቅ ዋጋ በመክፈል ከገቡበት አዘቅት እናውጣቸው፡፡ ያኔ ነው ፈጣሪ የሚባርከንና ዕቅዳችንን ቀድሶ በተገቢው መንገድ እውን የሚያደርግልን፡፡ አለበለዚያ ወያኔ አሁን እንደሌለ ሁሉ በሌለበት ሁኔታ አገዛዙን በእጅ አዙር ቀጥሎ የመለስና የመሪ ድርጅቱ የወያኔ አፅም ጉድጓድ ውስጥ ሆነው በሹምባሾቻቸው አማካይነት እስከወዲያኛው እያንቀጠቀጡ ይገዙናል – ልብ አድርጉ የሚገዛን ግን የወያኔ ጥንካሬ ሣይሆን የኛ ልፍስፍስነትና የኛ መጥፎ ሃሳብ ካርማዊ ዕድፍ የሚያጠላብን የመርገምት ውጤት ነው፡፡ አሁንና እስካሁን አንድ ያላደረገን የተለያየው ፍላጎታችን እንጂ የሚደርስብን ግፍና በደል ተለያይቶ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ እስከዚህን ደረጃ ያለያየን ለምንም ዓይነት ሕዝባዊ ስቃይ ሊንበረከክ ያልቻለው ግላዊ የሥልጣንና የሀብት ፍላጎታችን እንጂ በርግጥም በእውነት ተለያይተን እንዳልሆነ ኅሊናችን ያውቀዋል፡፡ (በሰላም ቀን የሀገራችን ልዩ መመኪያ ሊሆናት ይችል የነበረውና በሥልጣንና ሀብት አራራው ምክንያት ግን የወያኔ ሥውር ወኪል (mole/double agent) ሆኖ ሀገሩን በክፉ ቀን ከድቶ ከጠላቶቿ ጋር ያበረው ልደቱ አያሌው እንዲያ በመንታ እያነባ ለኢትዮጵያና ሕዝቧ “ሕይወቱን” እስከመሰዋት በሚደርስ “ጽናት” ዝዋይና ሸዋሮቢት የተንከራተተው ለማንና ለምን እንደሆነ በተለይ አሁን ላይ ቁልጭ ብሎ ይታየናልና ከዚህ ዓይነቱ ቁጭ በሉ አስተሳሰብና ዕኩይ ድርጊት በቶሎ እንውጣ፡፡ እውነቴን ነው – በተለይ ከእንግዲህ ማንም ማንንም ሊያታልል አይችልም፡፡ ሁሉም ነቅቷል ፤ ቀኒቷን ግን በጉጉት ይጠብቃል – የነፃነቷን የማትቀር ቀን፡፡) በበኩሌ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ለዚህ ዓይነቱ ፖለቲካዊ ድራማ የማትመች እንደምትሆን ተስፋ አለኝ፡፡ አማራ – ትግሬ፣ ኦሮሞ – ሶማሌ …. መባባሉ የታይታና ዘመን ያለፈበት የትግል ስትራቴጂ እንጂ ውስጠ ምሥጢሩ ሌላ መሆኑን እናውቃለን፡፡ ሌላው ልብ ማለት የሚገባ ነገር ደግሞ አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ዘጠና ሚሊዮን ወንበር የለውም፤ አንድ ነው፡፡ ያንንም በዘር ሣይሆን በ‹ሜሪት›ና በሕዝብ እውነተኛ ምርጫ ማስያዝ ይጠበቅብናል – ጊዜው ሲደርስ፡፡… እውነትን ተናግሮ እመሸበት ማደር እንዲህ ይመስለኛል፡፡ ወዳልተነሳሁበት ርዕስ ጥልቅ እያልኩ ማስቸገሬን ይቅርታ አድርጉልኝ፤ ወድጄን እንዳይመስላችሁ፡፡
በዚህ ዘመን ወያኔዎችን “ይህ እኮ ህገ መንግሥታዊ መፍቴ ነው!” ብትል “እሱን ቀቅለህ ከቤተሰቦችህ ጋር ሆነህ ብላው!” ሊሉ ይችላሉ ብቻ ሣይሆን ዘወትር የሚደግሙልህ ውዳሤ ማርያማቸውና መዝሙረ ዳዊታቸው ነው፡፡ ህገ መንግሥቱ – ምን አለፋህ ወንድሜ – የዐዋጁን በጆሮ እንዳትለኝ እንጂ ለአሰለጥ ትግሬዎችና ለፌዴራል የትግሬ ሠራዊት በፍጹም አይሠራም – ሀገርን በቅኝ ግዛት ለወረረ የአንበጣ መንጋ ምክንያታዊነትና ሰብኣዊነት የሚገመዝዘው ቀልድ በመሆኑ ከጠበንጃ ውጪ የሚታየው የችግሮች ማስወገጃ ሌላ ብልሃት ብሎ ነገር የለም፤ ጤናማና ለኅሊናው ተገዢ የሆነ ትግሬ እንደኛው መሰቃየቱን በታሳቢነት ያዝልኝ ታዲያ – ጥቂትም ቢሆኑ አሉ፤ የምን ጥቂት – ብዙ ናቸው ኧረ! እርግጥ ነው ነገሩ ዕንቆቅልሽና ግራ የሚያጋባ ሊመስል ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚባለውን የሥልጣን ቦታዎችን፣ የንግድ ተቋማትን፣ የአነስተኛና ጥቃቅን ንግዶችን፣ የሕንፃዎችንና የፋብሪካዎችን ባለቤቶች፣ የመንግሥት ቤቶችን በነፃ ተከራዮችን፣ ኮንዶሚኒየም ቤቶችን፣ የወታደርና የፖሊስ ተቋማትን፣ የደኅንነት መዋቅሩን፣ የባንኩንና የአክሲዮን ሸያጩን፣ ውድ ውድ የሚከፈልባቸው ትምህርት ቤቶችንና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን፣ መዝናኛ ሥፍራዎችን፣ … በጠቅላላው በሀብቱ ማማ ላይ ፊጥ ያለውንና በትንሹም በትልቁም ሲቆጣ የቀድሞ ወንድምና እህቶቹ የአሁን አሽከሮቹና አጫዋች አኗኗሪዎቹ ላይ፣ የሀብቱም አድናቂዎች የሆኑ ሌሎች ምሥኪን “ወገኖቹ” ላይ በዕብሪት “እቧይ” ሲል የምትሰማውን ትግሬ ስታይ ኢትዮጵያ በአንዳች ትግሬያዊ ምትሃትና ሰሜናዊ ዋግ የተመታች ሊመስልህ ቢችል ዘመኑና አበቅቴው ነውና ቻል ማድረግ ሊኖርብህ ነው፡፡ ኧረ እንዲያውም በተጋቦት ትግሬ የሆነ ሌላ ዜጋም ሲያስመስል “እቧይ!” ሲልና የስልክ መጥሪያውን ካለውዴታው ለማስመሰልና ለመወደድ ሲል ብቻ የትግርኛ አድርጎም ልትታዘብ ትችላለህ፤ አቤት ይህ ጊዜ ሲገርም – ራስን ሲያሳጣና ባዶ ሲያስቀር፡፡ ዘመቻው እኮ ሁለገብ ነው – ኢኮኖሚያዊም፣ ወታደራዊም፣ ሥነ ልቦናዊና ባህላዊም፣ ሃይማታዊም፣ ምናምናዊም ሁሉ ነው፡፡ ታዲያን እንዲህ ያለ ነገር በታሪክ አልፎ አልፎ ሊያጋጥም እንደሚችል “ሚዉቴሽናል ክስተት” በመቁጠር መታገስ ይኖርብናል – ቂሎችን ተከትሎ ቂል መሆንና ለቂም በቀል መነሳሳት አይገባም ብቻ ሣይሆን ቂም በቀል የሚወልደው ሌላ ቂም በቀልንና የዐመፃ ተግባርን በመሆኑ ከዚህ ዓይነት ሃሳብ መታቀብ አማራጭ የሌለው ግዴታ ነው – ከእግዚአብሔር መንገድ የወጡ ሰዎች ከዚሁ የፈጣሪ መንገድ ሊያስወጡን አይገባም – ምንም እንኳን የነሱ ፍላጎት ይሄው ቢሆንም እኛ ግን እነሱ በመጡበት መንገድ በጅልነት ልንማገድበት አይገባንም – ጎጂ ነው፤ ለጊዜው ካልሆነ በዘለቄታዊነት አያዋጣምም፡፡ የአነስታይንን ምክር መቀበል አለብን – “አንድ ችግር በተፈጠረበት የአስተሳሰብ ደረጃ ተጉዞ ችግሩን ማስወገድ አይቻልም፡፡” ክርስቶስም ቀድሞ አለ “ጠላትህን ውደድ፤ አንድ እርምጃ ከእርሱ ጋር እንድትራመድ ቢጠይቅህ ሁለት ድገምለት፤ እጀ ጠባብህን ቢጠይቅህ መጎናጸፊያህንም ድገምለት፤ ግራ ጉንጭህን ቢጠፋህ ቀኝህንም ድገምለት …” ይህ ምክሬ የተለያዩ የትግል አማራጮችን ለሚከተሉ ወገኖች እንደማይጠቅማቸው አውቃለሁና ከነርሱ አንስቻለሁ፡፡ ምርጫን ደግሞ አከብራለሁ – እንደምርጫ፡፡ ይህ አስተያየቴ ተቀባይነት እንዲኖረው የምሻው በተለይ በሃይማኖቱ ማኅበረሰብና በሰላማዊው ሕዝብ መካከል ነው፡፡
አንድ ነገር እንገንዘብ፤ ይህ ጊዜ ዘንጦ ያልፋል፤ ዘንጦ ያላለፈ የክፋት ዘመን በታሪክ እንዳልነበረ ሁሉ ዛሬም አይኖርምና፡፡ በተረፈ ግን እንደውነቱ ከሆነ ይሄ ዘመን ትግሬዎችን አልጠቀመም የሚሉት የጅሎች ፈሊጥ ከፍ ሲል ከገለጽኩት አስቀያሚ ሀገራዊ ገጽታ አኳያ አይገባኝም፡፡ በዚህ ዘመን የማይጠቀም ትግሬ ካለ አእምሮው ጤናማ የሆነና ዛሬ በነገው ቀን ላይ የሚጥለውን ታሪካዊ ዳፋ ከወዲሁ በማጤን አስተሳሰቡን ከአብዛኛው ጭቁን ወገን ጋር ያጣመረ ደግ ትግሬ ብቻ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ትግሬ እንኳንስ በሌባውና በአጭበርባሪው ወያኔ-ትግሬ በእኛ በኢ-ትግሬያውያኑም ጭምር ሞኝ የሆነ ያህል ይቆጠራል፡፡ ለምን ቢባል ጤናማ አእምሮ በጠፋበትና ይሉኝታቢስነት በነገሠበት የዘረኞች አገዛዝ ውስጥ እንኳንስ ትግሬ የሆነ ሰው ይቅርና የትግሬዎች አንጋችና እግር አጣቢ የሆነ ዜጋ ራሱ ትርፍራፊ መቅቡጥ አያጣምና ነው – ስንቱ የመንደር ካድሬ እንዴት እየተዝመነመነ እንደሚኖር አውቃለሁ፡፡ ኅሊና የሌለው ሰው በአንድ አዳር ከብሮ ሊያድር የሚችልባቸው በሮች በርካታ ናቸው – ወያኔ ደግሞ ለፖለቲካው ሥጋት አትፍጠርበት – ትዛዙንም በጭፍን ተቀብለህ ተግብርለት እንጂ ለጊዜውና እስክትሰባለት ድረስ አያርድህም፡፡ Literally speaking, to my understanding, non-Tigrians are slaves of Tigrians in all denotative and connotative meanings of slavery. Though we cannot differentiate a Tigrian from non-Tigrian especially with respect to color, unlike the case in the apartheidal South Africa or the segregational US, during which the blacks and whites were easily pinpointed, unless maybe by the so called “number 11”, which, again, some non-Tigrians might have it on their temples in their face as well, the difference in life style and possession of wealth between Tigrians and non-Tigrians is absolutely unfathomable. A Tigrian, unless they fear their conscience, can, for example, kill an Amhara in a broad day light and live out of bars. Don’t get surprised, dear sister or brother! There are more severe punishments inflicted upon the Amharas by the TPLF junta, with the blessing of “some” foreign forces, of course. The ‘world’ has been silent, even at times has also been cooperative, and hence, complicit, while Ethiopia and Ethiopians have been suffering for so long, and be sure, everyone will be paid accordingly. Now in Ethiopia, except Tigrians, no one has the right to demand any right that humanity and/or Ethiopian-ness used to give, relatively in abundance, just some decades ago. I think this is the result of animalism from the side of the Tigrians who are ruling, rather, misruling the nation; to my conviction, I do believe that they are missing certain component(s) in their evolution and I can surely say that Ethiopia is currently ruled by a crew of people who have not yet finished their human development in terms of evolution. Could they be homosapiens or australopitecus? I don’t know. But, in reality, the situation is regrettable and pitiful, not necessarily from the vantage point of Stockholm syndrome.
አሁን እንጃ እንጂ አንድም ሹፌር ከጂቡቲ አንዲትም ቡትሌ የምግብ ዘይት ይዞ እንዳይመጣ ተከልክሎ ነበር፡፡ እንደሰማሁት የዛሬን አያድርገውና ከወያኔ ጋር ድብን ያለ ፍቅር ውስጥ የነበረው የጌትአስ ኢንተርናሽናል ካምፓኒ ባለቤት – እልም ያለ ማይም ባለሀብት – ነበር አሉ ያስከለከለው፡፡ ልብ አድርጉ! አንድ የከባድ መኪና ሹፌር በመቀመጫ ወንበሩ ግርጌ ወይ ራስጌ ወትፎ የሚያመጣት አንዲት የ20 ሊትር ጀሪካን ዘይት፣ የዘይት አስመጪውን ሁለገብ ባለሀብት ገበያ ሲሻማበት ይታያችሁ፡፡ ያሳዝናል፡፡ ለዚህ ነው እኛ ኢትዮጵያውያን ምቀኝነትን ከሰውነታችን መንጥሮ የሚያወጣ ፍሪ አንቲቫይረስ ማስጫን እንደሚያስፈልገን ዘወትር ለጓደኞቼ የምናገረው – ማካፌ ወይ አቫስትና ካስፐርስኪ ከተገኙ፡፡ ሀብታሞች ገብጋቦች ናቸው፡፡ ሀብታሞች – በተለይ ኢትዮጵያውያን – የሰው ደም መጣጮች ናቸው – በቀሰምና በስሪንጋ አይደለም – ግን ከዚህ በማይተናነስ የገብጋባነትና ስስታምነት ጭካኔ፡፡ ሀብታሞች ሃይማኖት የሌላቸው – አለን ቢሉም ለይስሙላ ካልሆነ ከልብ የሚያመልኩት አምላክ የሌላቸውና ገንዘብን በርሱም ውስጥ ሰይጣንን የሚያመልኩ- የአጋንንት ማደሪያ ናቸው፤ የጨከንኩባቸው አይመስለኝም፡፡ በምናገረው ጥርጥር የለኝም – ክርስቶስስ ለዚህ ሳይሆን ይቀራል ያቺን የግመልና የመርፌ ቀዳዳ ምሳሌ የተናገረባቸው? በነገራችን ላይ የዚያ ማይም ነጋዴ የአሁኑ ዕጣ በስደት መኖር ነው አሉ – ሰይጣኖች ፍቅራቸውም ጠባቸውም አንድ ነው፤ ሁሉም ነገራቸው ወረትና በህገ ወረትም የሚገዛ ነው፡፡ ሲፋቀሩና ሲጣሉ ጊዜ አይወስድባቸውም – በተለይ በዘር ሐረግ የማይገናኙ ከሆነ፡፡ እንደዚህ ዓይነቱን ቀፎ ሀብታም በልዩ የርቀት መቆጣጠሪያ ነው የሚከታተሉት፡፡ ስለሆነም በሀብት እየበለጣቸው ሲመጣ ተተናኮሉት ማለት ነው – በፖለቲካውስ የሚያገኙት አይመስለኝም፡፡ የርሱ ፖለቲካ እንደከብት በልቶና ጠግቦ ከማደር አያልፍምና፡፡ ይቅርታና ብዙው የወያኔ ጥገኛ ሀብታም በምግብና መጠጥ ከርሱን ከመቀብተትና ከማግሳት እንዲሁም በአጠንካሪ መድሓኒቶች የታገዘ እንትኑን ባገኘው እንትን ሁሉ ከማሾለክ ባለፈ ለሀገር የሚቆረቆረውና የሚጨነቀው ባለሀብት ዜጋ ከቁጥር የሚገባ አይመስለኝም፡፡ የዛሬ ሀብታም እንማንትስ ወርቃለማሁን ጨምሮ በብልግናው ጎዳና መትመምና ባህልንና ወግን ማጨቅየት ከወያም ጋር ካባ እየደረቡ በፍቅር መጫወት እንጂ ለሀገር ማሰቡን ትተውታል፤ ለዚህ ወጣቶቹ ተሸለው ተገኝተዋል፡፡ እነአንዱኣለምንና ርዕዮትን ያስቧል፡፡ ሌላውስ ተከድኖ ይብሰል – ሆዳቸውና እንትናቸው ብቻ አይጉደልባቸው እንጂ የሚሸጥን ሀገራዊ ነገር ሁሉ ይቸበችባሉ፡፡
ሁላችሁም እንደምታወቁት ስዬ አብርሃ፣ በኢትዮጵያ የቀድሞ የዲያብሎስ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር መለስ ዜናዊ ሊያውም በጫት ምርቃና አነሳሽነት በደቂቃዎች ውስጥ በተነደፈ የፀረ-ሙስና መሥሪያ ቤት ማቋቋሚያ ዐዋጅ ምክንያት ፍርድ ቤት እንኳን ቢለቀው ለበርካታ ዓመታት እንዲታሰር ተደርጓል፡፡ እንዲህ ናት ኢትዮጵያ! እንዲህ ናቸው ወያኔ ትግሬዎች! የጭንቅላት ችግር ከዚህ በላይ ሊኖር አይችልም፤ ጤናማ የሰውነት ዕድገት ዕጦት ችግር ከዚህ በላይ የለም፡፡ ወያኔ ጋ ፍርድ ቤት የለ፤ ፖሊስ የለ፤ መከላከያ የለ፤ የገንዘብ ሚኒስቴር የለ፤ የውጭ ገበያ የለ፤ የሀገር ውስጥ ገበያ የለ … ሁሏንም ለግላቸውና በግላቸው ተቆጣጥረው መምነሽነሽ ነው፡፡ ይሉኝታ? ከየት ያውቁና! ሀፍረት? የት ያውቁትና! ትዝብት? የት “ገብቷቸው!”፡፡ ግን እንዳይመስላችሁ፡፡ ሁሉንም ያውቁታል፡፡ የመጨረሻ ዕጣ ፋንታቸውን ሳይቀር በሚገባ ያውቁታል፡፡ ክፋትንና መጥፎነትን የመጨረሻ አማራጫቸው ያደረጉት ሌላ አማራጭ በማጣታቸው ይመስላል – ከመነሻው አበላሽተውታልና፡፡ አንዴ ጨክነው ገብተውበታልናም ከአሁን ወዲያ ሌላ በጎ አማራጭ ያላቸው አይመስለኝም፡፡ ለማንኛውም ማሸነፍንና መሸነፍን የማያውቅ አጉል ሰው አያሸንፍህ፡፡ ቀን አይጣልህ ወንድማለም፡፡ ቀን የጣለውን ቀን እስኪያነሳው ያለውን ውጣ ውረድ ለመረዳት ኢትዮጵያዊ ሆኖ መፈጠር ከበቂ በላይ ነው፡፡ ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን እኛ ኢትዮጵያውንም በወያኔ-ትግሬ ክፉኛ ተፈተንን፤ አንዳንዶቻችን በፈተናው ወደቅን፤ ጥቂቶቻችን ቢያንስ እስካሁኒቷ ደቂቃ ያሸነፍን መስለን አለን፡፡ ጊዜ በእግዚአብሔር ዘንድ ብዙ ነገር ማለት ነውና የጊዜን የማይዘባበቱበት ፍርድ እንጠብቅ፡፡ ቀኑ ቀርቧል!
የወያኔን ዐዋጆችና መመሪያዎች በሚመለከት ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ በእውነቱ እጅጉን ጉደኞች ናቸው፡፡ ሀገር ለመሸጥና ገንዘብ ለማግኘት፣ መኪና ለማስገባት፣ የተወደደ ዕቃ ለማስገባትና ለመሸጥ፣ የሚጠሏቸውን ወገኖች ከገበያ ለማውጣት፣ መሬት ለባዕዳን ለመቸብቸብ፣ ቤትና መሬት ከዜጎች ለመቀማት፣ አንድን ግለሰብ ሳይቀር ለማክበር ወይም ለማደኽየትና ከፈለጉም ዘብጥያ ለማውረድ፣ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ተቀናቃኝን ቀንዱን ለመምታት፣ ኑሮን ሰማይ በመስቀል የሕዝብን ቅስም ለመስበርና በዚያውም ሕዝብን የማጀቱ ጣጣ ውስጥ በመወተፍ ሌላ ቁም ነገር እንዳያስብ በማድረግ የበቀል ጥማታቸውን ለማርካት… ወያኔዎች የማንም እገዛና የዓለም አቀፍ ህግ ከለላ ሳያስፈልጋቸው ያሻቸውን ዐዋጅና መመሪያ አውጥተው – እነሱንና ተላላኪ ጭፍራዎቻቸውን ግን ሲያልፍም የማይነካ መሆኑ መታወቅ አለበት – በደቂቃዎች ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ፡፡ በህግ ስም የፈለጉትን እያደረጉ ሀገርንና ሕዝብን እንደገደሉ ቢያንስ እስካሁን ካለተቀናቃኝ ቀጥለዋል፡፡ ነገስ? ነገ ሌላ ቀን ይሆናል፡፡ ሒሳብ ማወራረዳቸውን መጠራጠር አይገባም፡፡
በሰሞኑ የፋሲካ ገበያ አንዳንድ የአሃዝ ስህተቶችን ከኢሳት ታዝቤያለሁ፡፡ ይህ ስህተት የመረጃ አቀባይ ስህተት ይመስለኛል፡፡ የዕቃዎችና የዓመት በዓሉ ገበያ የዋጋ ዝርዝር አንዳንዱ ትክክል ሆኖ አንዳንዱ ስህተት ነበር፡፡ ስህተት ያልኩት ዋጋው ከእውነቱ የቀነሰ በመሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ የበግ፣የፍሪዳ፣የዶሮ፣ የቅቤ፣ የቀይ ሽንኩርትና የመሳሰሉት ዋጋዎች በኢሳት የተነገረው ከእውነቱ በጣም ቀንሶ ነው፡፡
ሰሞኑን ሁለት ተራራ እሚያህሉ የደለቡ በሬዎች በ90 ሺህ ብር እንደተሸጡ እዚያው የነበረ ሰው አጫውቶኛል፡፡ ዛሬ የበሬ ዋጋ እንዲህ ጥንቡን ጥሎ ለአንድ በጣም የደለበ በሬ ብር 45 ሺህ ተከፈለ እንጂ የዛሬ ዓመት በነበረው የፋሲካ በዓል አንድ በሬ 60 ሺህ ብር መሸጡን ከሁነኛ ሰው በጊዜው ሰምቻለሁ፡፡ 30 ሺህና 20 ሺህማ በብዙ ቦታዎች ተሸጧል፡፡ የምላችሁ እውነቴን ነው፡፡ እያንዳንዳቸው 45 ሺህ ብር የተሸጡት ከብቶች ታዲያ ከውፍረታቸው የተነሣ ወደሚጫኑበት መኪና ለመድረስ የተዘረጋውን የአራት ኪሎ ሜትር ርቀት በእግራቸው ለመጓዝ አንድ ሙሉ ቀን ፈጅተዋል – እያለከለኩና ሊፈርጡ ደርሰው፡፡ 90 ሺህ ብር ሲያነሳቸው ነው አይደል?
የልጄ ልጅ አቡጡ ጢል አድርጎ የሚያነሳው ኮሳሳ በግ ከ1500 ብር ብዙም አይቀንስም – በጣም የደለበውማ ከአራትና ከአምስት ሺህ ድምቡሎ እንዲቀንስልህ ከፈለግህ ከፋሲካና ከዳግማይ ትንሣኤ ማለፍ አለብህ፡፡ ገበያው እሳት ሆኗል፡፡ ያ በኢሳት የሰማሁት ዘፋኝ “ማገዶ ለቃሚ ምን አደከመሽ፤ ኑሮው እሳት ሆኖ ገብቶ ከቤትሽ” ማለቱ በሥነ ጽሑፍ ቋንቋ እንዴት ያለ ምስል ከሳች መሰላችሁ! በነገራችን ላይ ‹ኢሳት ቲቪ› የማልለው በኢሳት ውስጥ ቲቪ ስላለ ነው፡፡ ኢሳት ሲተረተር ‹የኢትዮጵያ ሣተላይት ቴሌቪዥን› አይደል? በእግረ መንገድ “ድህረ ገፅ” የሚሉ ወገኖቼ “ድረ ገፅ” እንዲሉና ትክክለኛው ይህኛው እንደሆነ ብጠቁም ያስነውረኝ ይሆን? “ድህረ” ሲባል “በኋላ” እንደማለት ነው፤ “ድረ” ማለት ግን “ድር” ከሚለው የሸረሪት ድር ውስጥ የተመዘዘ ሆኖ “ዌብ” የሚለውን የ(እንግሊዝኛ?) ቃል በአማርኛ ለመተካት የተሞከረ ይመስለኛል፡፡ ከተሳሳትኩ ይቅርታ፡፡ እናም ‹ፕሊዝ› “ድረ-ገጽ” ወይም “ድረ-ገፅ” እንበል፤ እናስብልም፡፡
ለማጠቃለል ያህል የ500 ብር ደሞዝተኛና የአምስት ልጆች አባት የሆነው አቶ አዝብጤ ሸዋንግዛው በዚህ የሰሞኑ ፋሲካ የቀረበለት ገበያ በመጠኑ ሲዳሰስ ይህን ይመስል ነበር፡- (ጥራቱን ግን ለአንድዬ ብቻ ሰጥተን ነው ታዲያ – ለምሳሌ ቅቤው አንዱ ጉራንጉር ውስጥ ብልጦቹ ኅሊናአልባ ነጋዴዎች ባላገሮችን ሰብስበው ከምናምን ያለቡት ሊሆን ይችላል – የጥራት ጉዳይ በተለይ በምግብ ነክ አቅርቦቶች ላይ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል፤ በዘይትና ማር እንዲሁም በሌላ ሌላው ሥሪቱ የማይታወቅ የምግብ ግዢ አለማለቃችን የፈጣሪ ረድኤት ታክሎበት ነው እንጂ እንደነጋዴዎቻችን ቢሆን ኖሮ የፈለጉትን በቀጥታ ከአውሮፓና አሜሪካ ከሚያስመጡት ከራሳቸው ከሀብታሞቹና ከባለሥልጣኖቻችን በስተቀር አንድም ሰው በሕይወት ባልተገኘ – አሁን የምንመራው ሕይወታችን በ“ሕይወት አለን” የሚያስብል ከሆነ፡፡) ለማንኛውም ቅቤ ከ170 – 200፣ ዶሮ ከ100 – 280(እኔ 120 ብር የገዛሁት ዶሮ ድስቱ በላው መሰለኝ – እውነቴን ነው የምላችሁ ከዕንቁላሎቹ በስተቀር ጠላታችሁ እልም ይበል ሥጋው ድራሹ ጠፋ! ፈረሰኛ ነው እግረኛ የሚሉት የአባውራ ብልት(የዶሮው አጥንት ማለቴ ነው) ቆዳ ይሁን አንገት መሆኑ ተለይቶ ሳይታወቅ ሟሙቶ አገኘነውና በ“ቆይ ብቻ!” የዘመን መውቀሻ ዛቻ ተሳስቀን አለፍን፡፡ ምን ይደረጋል?)፣ የፈረንጅ ቀይ ሽንኩርት ከ12-17፣ በግ ከ1200 – 5000(+)፣ ምን አለፋችሁ ሁሉም ገበያ ድሃ አይነካሽ ነበር፡፡ የዓመት በዓሉ ብቻ ሣይሆን የአዘቦቱ ገበያም ያው ነው፡፡ ነጋዴው ከማን ጋር እልህ እንደተጋባ ማወቅ አልቻልኩም፡፡ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዴት ይኖራል? ይህንንም በውል አላውቅም፡፡ ብቻ ይመሻል፤ ይነጋልም፡፡ የሚገርመው ደግሞ መምሸት መንጋቱ ለነሱም ለኛም እኩል መሆኑ ነው፤ ወይ እኛ አናልቅ ወይ እነሱ አይጠረቁ፡፡ ከወያኔ ትግሬዎችና ከአንጋቾቻቸው በስተቀር ሌላው ሰው ሁላ ችግሩን በሆዱ ይዞና ተፈራርቶ መኖርን መርጧል፣ እየኖረ እየመሰለው ግን ሳይኖር ይኖራል፡፡ ሞቶ የሚኖር እንደኢትዮጵያ ሕዝብ የለም እላለሁ፡፡ እንወራረድ! ነገስ? ነገማ ያው ሌላ ቀን ነው፡፡ መልካም ዳግማይ ትንሣኤ፡፡

No comments:

Post a Comment