አክሎግ ቢራራ (ዶር)
ክፍል ሁለት
Click here for PDF
“ውኅ እየጠማው ያባዪን ልጅ
እሚያዘጋጅለት ቢጠፋ
እሚያበጃጅ ለልማት የሚያመቻች ዓባይን
አኮላሽቶለት ፈንጂውን”
ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው፤ ዐባይ–ፈንጅ የቀበረ ውሃ
ኢትዮጵያ ታላቅና ሃብታም ለመሆን የምትችል አገር ናት። የተፈጥሮ ሃብቷ፤ አቀማመጧና የሕዝብ ስርጭቷ ለታላቅነቷ የማይገኙ ምሰሶዎች (Social Pillars) ናቸው። ሆኖም፤ ይህ የአገርና የማህበረሰብ ታላቅነት መሰረት ጎሳዊና አምባገነናዊ የሆነ ስርዓት ባመጣው ጦስና ቀውስ እየባከነ ነው። ህወሓት ከተመሰረተበት ጀምሮ የተካውን መንግሥትና ሌሎችን በማዋረድ፤ በማጋለጥ፤ በማጥላላት፤ በማሰር፤ በመግደልና ከሃገር በማባረር ሃያ ሶስት ዓመት ገዝቷል። የጥቂቶችን ኪስ በሚያሳፍር ደረጃ ሞልቶ፤ ቢያንስ ሃያ አምሥት ቢሊዮን ዶላር ከሃገር ተዘርፎ ወደ ውጭ ሃብታም አገር ባንኮች እንዲዘዋወር አድርጓል። ይኼን ሲያደርግ ደጋግሞ የሚነግረን ተግባሩ ሁሉ ለጭቁን ሕዝቦች፤ ለድሃዎች ጥቅም የሚል ፕሮፓጋንዳ እየተጠቀመ ነው። ኢትዮጵያ የብዙ ምሁራን፤ ጠበብቶች፤ ሰራተኞች፤ አገር ወዳዶች ወዘተ አገር ብትሆንም ዛሬ የተማረና አገሩን ለማልማት የሚችል የተማረና የሰለጠነ የሰው ኃይል ድሃ ሆናለች። በሃያ አንደኛው መቶ ክፍል ዘመን ተቀባይነት የሌለው በኢትዮጵያ ተከስቷል።