Translate

Monday, March 31, 2014

አምባገነናዊውን ስርዓት አቅፈውና ደግፈው የያዙት ምዕራባዊ አገራት

(እዮብ ከበደ ኖርዌይ)

IMPERIALISM


በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ጭቆና፣ ስቃይ እና መከራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና ተጠናክሮ እንዲቀጥል ካደረጉት ምክንያቶች መካክል አንዱ፣ የወያኔ መንግስት ከምዕራባዊያን የሚያገኘው ያልተቋረጠ ድጋፍ እና ሙገሳ ትልቅ ቦታ ይይዛል። ከነዚህ መንግስታት የሚያገኘው ድጋፍ እና ሙገሳ ምክንያት የማን አለብኝነት ስሜት ስርዓቱ እንዲሰማውና የኢዴሞክራሲያዊ ስርዓት በህዝቡ ላይ እንዲንያሰራፉ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ስርዓቱም ከነችግሩ ለረዥም ጊዜ በስልጣን እንዲቆይ ካደረጉት ምክንያቶች መካከል የምዕራባዊያን ድጋፍ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።

ኢህአዴግ የአፍሪካ ቀንድ ስጋት?

አሜሪካ መለስ ከቆፈሩት ጉድጓድ ለመውጣት ወስናለች

eprdf and the usa

ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ብቸኛ ተዋናይና ፊት አውራሪ አድርጎ ራሱን የሾመው ኢህአዴግ ለቀጠናው ስጋት እንደሚሆን ተጠቆመ። አልሸባብንና አልቃይዳን ከምንጩ እናጠፋለን በሚል ስትራቴጂ መለስ ከቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ሰምጣ የነበረችው አሜሪካ ከጉድጓዱ ለመውጣት ወስናለች። ኢትዮጵያዊያን የሚያምኑትና የሚቀበሉትን መሪ በድፍረት አደባባይ የማውጣት ሃላፊነቱ “አገር ወዳድ” በሚሉ ዜጎችና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጫንቃ ላይ ነው።

Sunday, March 30, 2014

ኢህአዴግ የእምነት ተቋማትን በጥብቅ የሚቆጣጠርበት ህግ ሊያጸድቅ ነው

ህጉ ጣጣ እንዳያመጣ የሰጉ ኢህአዴግን እየመከሩ ነው

religions


ኢትዮጵያን ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ እየገዛ ያለው ኢህአዴግ የሃይማኖት ተቋማትንና ምዕመናኑን በጥብቅ የሚቆጣጠርበትን ህግ ለማጽደቅ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ። የህጉ ረቂቅ የደረሳቸው ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ኢህአዴግን አበክረው እየመከሩና በሚያመጣው አጠቃላይ መዘዝ ዙሪያ እያስጠነቀቁ ነው።

የቀድሞው የጋምቤላ ፕሬዚዳንት ደቡብ ሱዳን ከሆቴል ውስጥ ታፈኑ

“ወያኔ እጅ ገብተዋል”

south sudan juba

የጋምቤላ ክልልን ሲመሩ ቆይተው ባለመስማማት የኮበለሉት የቀድሞው የክልሉ ፕሬዚዳንት ደቡብ ሱዳን ከሆቴል ውስጥ ታፍነው መወሰዳቸው ተጠቆመ። ዜናው በገለልተኛ ወገን ባይገለጽም ኖርዌይ በስደት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይኖሩ የነበሩት አቶ ኦኬሎ አኳይ በኢህአዴግ በጥብቅ የሚፈለጉ ሰው ነበሩ።

Saturday, March 29, 2014

መሪን ልዩ የሚይደርገው በጨለማ ዘመን ከሩቅ ተስፋ አይቶ ማሳየት መቻሉ ነው!!!

መሪን ልዩ የሚይደርገው በጨለማ ዘመን ከሩቅ ተስፋ አይቶ ማሳየት መቻሉ ነው!!!

P1000785
ተስፋዬ ዘነበ(ኖርዌይ በርገን)
ሕዝባዊ ተቋም ለመመስረት ሕዘባዊ መሆን ያስፈልጋል፡፡ የተቋሙን ሕዘባዊነት ለማረጋግጥ ሕዝባዊ አወቃቀር ሊኖረው ግድ ነው፡፡ የሕዝብን  መሰረታዊ ጥያቄ ሊፈታ የሚችል ትልቅና ሁሉን አቀፍ አጀንዳ ወይም መርሃ-ግበር ሊኖሩት ይገባል፡፡
ተቋማት በተለይም የፖለቲካ ሕዝብን ማእከል አድርገው ካሉት ወይም በስልጣን ላይ ካለው የተሻለ እቅድና መርሃ-ግብር ነድፈው ሕዝብን ለለውጥ ማንቃት ሲችሉ እንዲሁም በሃገርና በሕዝብ ላይ የሚደርሱ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እንዲሁም አስተዳደራዊ ችግሮች በመንቀስ የተሻለ አማራጭ ማቅረብ የሚችሉና የትኛውንም የህብረተሰብ ክፍል መድረስ የሚችሉ መሆን ይጥበቅባቸዋል፡፡
በሃገራችን ውስጥ ባለው የይስሙላ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት በዘመነ ሕወሃት የተቋቋሙት ለቁጥር  የሚታከቱ የብሔርም ሆነ የሕብረብሔር የፖለቲካ ድርጅቶች የረባ የስማቸውን ያህል ትጋት ሳይታይባቸው ሲያሻቸው በቡድን አለያም በተናጠል መግባባት አቅቷቸው የእመቧይ ካብ እየሆኑ ሕዝብን ሲያቆስሉ ሁለት አስርተ አመታት ተቆጥረዋል፡፡

ኢሕአዴግ ለምን ማኅበረ ቅዱሳንን ማፍረስ ፈለገ?

Enqu Magazine Megabit Cover
  • ሥርዐቱ በተለይም መንግሥታዊ ሥልጣናቸውን ለሃይማኖታዊ ተልእኮ የሚጠቀሙ ሓላፊዎችና አማሳኝ የደኅንነት ግለሰቦች አሁን በተያዘው መንገድ ቀጥለው ማኅበረ ቅዱሳንን አላግባብ ወደ መገዳደር ብሎም ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አማሳኝ ግለሰብ ሓላፊዎች ጋራ ተባብረው ወደ ማፍረስ የሚሸጋገሩ ከኾነ ያለምንም ጥርጥር የተቃውሞው ጎራ ይጠናከራል፡፡ ይህም አገሪቱን በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ የአውራ ፓርቲ ሥርዐት ለአርባና ኃምሳ ዓመታት እመራለው ለሚለው ገዥው ፓርቲ ግብዓተ መሬት አፋጣኝ ምክንያት ሊኾን እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ይስማማሉ፡፡

የወያኔን ከፋፋይ አገዛዝ እናምክን (ግንቦት 7)

Ginbot 7 weekly editorial የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰብ ሊከበርላቸውና ሊያሳድጋቸው የሚገቡ የተለያዩ የባህልና የታሪክ ቅርሶች ያሏቸውን ያህል በብዙ መንገድ የሚያይዝ የጋራ ታሪክ ቅርስና ዝምድና አላቸው። ልዩነቶቹ ራሳቸው ተጠቃቃሚ ለሆነ የእርስበርስ ግንኙነታቸው ጠቃሚ እንጂ ከአንድ ሀገር ማህበረሰብነታቸውና ከጋራ ህልማቸው ጋር የሚጋጩ የጠብና የግጭት መንስኤዎች አይደሉም። ከጠብና ግጭት ማንኛውም ብሄር ብሄረሰብ ተጠቃሚ አይደለም። ከጠብና ግጭት ጥቅም ይገኛል ብለው የሚያስቡ “ግርግር ለሌባ ይመቻል” የሚለውን የወሮ በላ ፍልስፍና የሚከተሉ የቀን ጅቦች እንጂ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች አይደሉም። በወያኔ የግዛት ዘመን የደረሱትን ግጭቶች መፈናቅሎችና የተፈጠሩትን የእርስበርስ ጥርጣሬዎችን ልብ ብሎ ለተመለከተ ሁሉም በአገዛዙ እና በሎሌ የበታች ሹማምንቱ የተፈጠሩ እንጂ አንድም ጊዜ እንኳን ከህዝብ የመነጩ አይደሉም።

የወያኔ ጉጅሌ በአገዛዝ ዘመኑ ሁሉ ብሄር ብሄረሰቦችን ከሚያይዟቸው የጋራ ማህበራዊ ቅርሶችና ህልሞች ይልቅ ካለመታከት ልዩነቶቻችን ላይ ያተኮረ ፖለቲካ እያካሄደ እንዳለ ግልጽ ነው።

ጎሠኛነትና ሽብርተኛነት (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)

Prof. Mesfin Woldemariamየጎሠኛነት አጭር ትርጉም ዓለምን በራሱ ጠባብ ኢምንትነት የሚለካ ሰው ነው፤ ለኪው መለኪያው ነው፤ መለኪያውም ለኪው ነው፤ ጎሠኛነት የዘረኛነት የባሕርይ ልጅ ነው፤ ዘረኛነትም ሆነ ጎሠኛነት መሠረታቸው ድንቁርና ነው፤ የድንቁርናው ዓይነተኛ መገለጫ ‹‹ንጹሕ›› የሚለው ቃል ነው፤ ለዚህ ዋና ምስክር አድርጌ የማቀርበው አዶልፍ ሂትለርን ነው፤ ስለ‹‹አርያን ዘር›› ማንነትና ‹‹ንጹሕነት›› የሂትለር Mien Kampf የሚለውን መጽሐፍ ነው፤

የሰው ልጆች ባህል የሚባለው ሁሉ፣ ዛሬ የምናየው የሥነ ጥበብ፣ የሳይንስና የሳይንስ ጥበብ (ቴክኖሎጂ) ውጤት ሁሉ የአርያን ዘር የፈጠራ ውጤቶች ናቸው፤ … ‹ሰው› የሚባለውም እሱ ብቻ ነው።

ኑ! እንዋቀስ፤ ኢህአዴግንም እናፍርሰው! (ተመስገን ደሳለኝ)

(ይህ “ኑ! እንዋቀስ” የሚለው ስር ነቀል የለውጥ ጥሪ ቀጥታ የሚያነጣጥረው በኢህአዴግ አባላት ላይ ብቻ ነው፤ አመራሩን በፍፁም አይመለከትም)

ኢህአዴግ ራሱ በይፋ ሲናገር እንደተደመጠው፣ በአሁኑ ጊዜ የአባላቱ ቁጥር ወደ ሰባት ሚሊዮን ገደማ ደርሷል፡፡ ይህም የአገሪቱ ቁጥር አንድ ግዙፍ የፖለቲካ ፓርቲ ያደርገዋል፡፡ በርግጥ ግዙፍ እንጂ ጠንካራ እንዳላልኩ ልብ ይሏል፡፡ ምክንያቱም ጥንካሬ የሚለካው በአባላት ቁጥር ሳይሆን በድርጅት ፍቅር፣ በዓላማ ፅናትና በሚሰጡት ልባዊ አበርክቶ ነው፡፡Journalist Temasegan Dasaleg
እንዲህ ያለ አቋመ-ብርቱነት ደግሞ ድሮ በያ ትውልድ ጊዜ ቀርቷል፡፡ በዘመነ-ኢህአዴግ የተንሰራፋው ጥቅመኝነት (በእነርሱ ቋንቋ ኪራይ ሰብሳቢነት) ብቻ ነው፡፡ ለዚህም በደቡባዊቷ አዋሳ ከተማ ስድስተኛው የድርጅቱ ጉባኤ በተካሄደበት ወቅት፣ አቶ በረከት ስምኦን በብስጭት እየተትከነከነ በደፈናው ለጥቅም ድርጅቱን የተቀላቀሉ አባላት በርካታ መሆናቸውን አምኖ በአደባባይ መናገሩ አስረጂ ሊሆነን ይችላል፡፡ ይህን ንግግሩንም አፍታተን ስናብራራው እንደሚከተለው ሆኖ እናገኘዋለን፡- የግንባሩ አባላት ቁጥር ሰባት ሚሊዮን ገደማ የደረሰው በጥቅም በመደለል፣ በአንድ ለአምስት የጥርነፋ መዋቅር በፍርሃት ተጠፍንጎ በመያዙና በመሳሰሉት ነው (መቼስ አቶ በረከት ከድርጅቱ ጉምቱ መሪዎቹ አንዱ ነውና ዘርዝሮ እንዲያስረዳን አይጠበቅበትም)

Thursday, March 27, 2014

ዓባይና የአሜሪካ ጨዋታ (ፕ/መስፍን ወልደ ማርያም)

አሥራ ዘጠነኛው ምዕተ-ዓመት አስተሳሰብ ከዚህ ቀጥሎ የተጠቀሰው ዓላማ ለአውሮፓ ቄሣራውያን ዋና ግባቸው ሆኖ እስከሃያኛው ምዕተ-ዓመት ዘልቆአል፤ አሀን ፈጽሞ በተለየ ዘመን አሜሪካ ይህንን አስተሳሰብ ይዞ የተነሣ ይመስላል።
ኢትዮጵያን የተቆጣጠረ ዓባይን ይቆጣጠራል፤ ዓባይን የተቆጣጠረ ግብጽን ይቆጣጠራል፤ ግብጽን የተቆጣጠረ ኃይልቀይ ባሕርን ከመግቢያና መውጫው 
ጋር ይቆጣጠራል፤ቀይ ባሕርን ከመግቢያና መውጫው ጋር የተቆጣጠረ ኃይልዓለምን ይቆጣጠራል።

በአዲስ አበባና አካባቢዋ የጅብ መንጋ ሰዎችን መብላቱ በምልኪነት እያነጋገረ ነው

ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)

ሙከራውን ማድረጉ ቢያንስ ኪሣራ የለውም፡፡ ውጤታማነቱን ግን እጠራጠራለሁ ብቻ ሣይሆን እንዲያውም መሣቂያ እንዳያደርጉን እሰጋለሁ፤ ክፉዎችና በሰው ስቃይ የሚደሰቱ ስለሆኑ በእሪታችን ቢሣለቁብን ማን ይከሳቸዋል? ከስም ባለፈ የሰላምን ምንነት ከማያውቅ ወያኔ በሰላማዊ መንገድ ችግርንHyena's in Addis Ababa causing problems ማስረዳትና መፍትሔ ለማግኘት መመኘት ከምኞትና ከህልም አያልፍም፡፡ እናም ወያኔን በእሪታ ለማስበርገግ የሚቻል አይመስለኝም፤ ተስፋ ለማስቆረጥ አይደለም – ተስፋ ብሎ ነገር ቀድሞውንም ከሀገራችን ከጠፋች ሰንብታለችና ማንም ማንንም ተስፋ ሊያስቆርጥ አይቻለውም፡፡ መቼም የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ነውና ወደአእምሯችን የመጣልንን ዘዴ ሁሉ አሟጠን መጠቀሙን የመደገፍ የሞራል ግዴታ ስላለብን እንጂ በአራት ከተሞች አይደለም በአራት መቶ ከተሞች እሪታችንን ብናቀልጠው ወያኔ ንቅንቅ አይልም፤ በጩኸታችን ከማላገጥም በዘለለ አንጀቱ በሀዘኔታ አይላወስም፡፡ የጅቦች ስብስብ በጩኸት እሩምታ ሣይሆን በአልሞ ተኳሽ አናብስት ነው የማያዳግም እርምጃ ሊወሰድበት የሚገባ፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር – 5 ቁልፍ አገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮችን ይዛ እነሆ በPDF ያንብቧት

Negere Ethiopia Semayawi Party Newspaper Issue5

ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር – 5 ቁልፍ አገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮችን ይዛ እነሆ በPDF ያንብቧት


- መዝሙረ ኢህአዴግ! (በላይ ማናዬ)
- የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ከአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት በተደረገላቸው ግብዣ ወደ አሜሪካ ያመራሉ፡፡ በጉዞው ዓላማና በተለያዩ የአገራችን ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
-  ኢትዮጵያና የዩክሬኑ ግጥምጥሞሽ
- ባለ ቀለሙን አብዮት ማን ይመራዋል? (በጌታቸው ሺፈራው)
- አዲስ ጠብመንጃ በምንሽር፤
አገዳደሉ ሆድ የሚያሽር፡፡
(በዝክረ ታሪክ አምድ፡- አቶ ታዲዎስ ታንቱ)
- “የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት ዘመቻ” (ግርማ ሞገስ)
- ኑሮ ሆነብን እሮሮ (ጋሻው መርሻ)
- የኢትዮጵያ ፖለቲካና የሴቶች ተሳትፎ (ኤልሳቤት ወሰኔ)
- ሰላማዊ ትግሉ መሪዎቹን ይሻል (ታምራት ታረቀኝ)
- ኢትዮጵያዊነት ለእኔ! (አፈወርቅ በደዊ)
- እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ፕሮግራሞች የሚተዋወቁበት ገጽ አለልዎት
መልካም ንባብ!

“ለውጡ እንደቀረበ ጥርጥር የለኝም” ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር

ነገረ-ኢትዮጵያ፡- ከሁለት ወር በፊት ወደ አሜሪካና የአውሮፓ አገራት ለስራ ጉብኝት ሄደው ነበር፡፡ አሁንም ወደ አሜሪካ ጉዞ ሊያደርጉ እንደሆነ ሰምቻለሁ፡፡ የአሁኑ ጉዞ አላማ ምንድን ነው?


ኢንጅነር ይልቃል፡- መጀመሪያ ያደረኩት ጉዞ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የፓርቲውን አላማና ፕሮግራም፣ የሰራናቸውን እንዲሁም ወደፊት ልንሰራቸው ያሰብናቸውን ስራዎች፤ ሰማያዊ እንደ አዲስ ኃይል ሲመጣ የቆመላቸው ሀሳቦችና እምነቶች ምን እንደሆኑ ለማስተዋወቅ ታስቦ የተደረገ ነበር፡፡ የአሁኑ ግን ከበፊቱ የተለየና ለሰማያዊ ሊቀመንበር በሚል በቀጥታ በአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት የተደረገ ግብዣ ነው፡ ፡ የአሁኑ ወጣት የአፍሪካ መሪና ወደፊትም ለአገራቸው መሪ ሊሆኑ የሚችሉ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ጥሩ ስራ የሰሩ፣ በውድድር ከተመረጡ በኋላ በአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት በሚደረግ ምርጫ መመዘኛዎቹን ለሚያሟሉ ሰዎች የሚሰጥ እድል ነው፡፡

Wednesday, March 26, 2014

እውነተኛው አ.ኢ.ግ.ተ. (EITI) ወይስ የማዳም ክላሬ የሙስና ማጋበሻ ቡድን? (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ማዳም ክላሬ አሸንፈዋል! እንኳን ደስ ያለዎት፣ ማዳም ክላሬ!
EITI board chairwomanባለፈው ሳምንት የ “አምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) ሊቀ መንበር የሆኑት ማዳም ክላሬ ሾርት ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም እና በማስፈራራት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የሙስና ማጋበሻ ቡድናቸው አባል እንዲሆን ለማስቻል የEITI የቦርድ አባላት ድምጻቸውን እንዲሰጡ በማድረጉ ጥረት ሲያካሂዱት የቆዩት ዥዋዥዌ ጨዋታ ተሳክቶላቸዋል፡፡ ማዳሟ አሮጌውን እና ያረጀ ያፈጀውን የአሰራር ሂደትን ማለትም እጅ በመጠምዘዝ፣ በኃይል በማስፈራራት፣ ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም በማስገደድ፣ ከኋላ ሆኖ በማስተኮስ፣ ስልጣንን መከታ በማድረግ ከህግ አግባብ ውጭ በግድ እንዲያምኑ በማድረግ፣ አሰልች እና የምጸት ቃላትን በመጠቀም እና የህጻናት ዓይነት እሽሩሩ ዘይቤ ቁጣን በመከተል ለርካሽ ጥቅም ሲባል የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ሀቅን በመደፍጠጥ በሸፍጥ ለጊዜውም ቢሆን ሀሳባቸውን አሳክተዋል፡፡ ማዳሟ በእንደዚህ ዓይነት እኩይ ምግባራቸው የተካኑ ናቸው፡፡

Tuesday, March 25, 2014

የእሳት ፖለቲካ በኢትዮጵያ (Fire Politics in Ethiopia)

ይሄይስ አእምሮ፣ አዲስ አበባ

This is the third time Harar experienced a deadly fire.በሃይማኖት መሪዎችና አገልጋዮች ዙሪያ ሰሞኑን አንዲት መጣጥፍ ጽፌ ለድረ ገፆች ልኬ ነበር፡፡ ለኅሊናቸው ተገዢ የሆኑ አወጡት – አስነበቡን፤ እግዚአብሔር ይስጣቸው፡፡ ለባህልና ለይሉኝታ ያደሩት እንዲሁም እነሱ በሚፈልጉት ሙዚቃ ብቻ ታንጎና ማሪንጌ መደነስ የሚፈልጉት ወደቅርጫታቸው ከተቱት – ይክተቱት፡፡ ሁሉም የመሰለውን የማድረግ መብት አለውና ያነበበም ያስነበበም፣ ያፈነም ያሳፈነም የኅሊናው ዳኝነት ይፍረደው ከማለት ውጪ በዚህ በውዥንብር ዘመን መወቃቀሱም ሆነ መካሰሱ ፋይዳ የለውም፡፡ ግን ግን የእውነት አምላክ ለሁላችንም እውነተኛውን የልቦናና የኅሊና ሚዛን እንዲሰጠን እጸልያለሁ፡፡ ሁለትና ሁለት ሲደመር አራት ብቻ የሚሆንበት ሃቀኛ ዘመን እንዲመጣልንም እንዲሁ፡፡ በተረፈ የልጆቼ ልጆች “Mother stomach is ranger.” ሲሉ እሰማለሁና በዚያ “ሜጀር” የተቃኘ የቅሬታ ዘፈኔን ጋብዣቸው በገዢዎቻችን አነጋገር ንቅድሚት እላለሁ፤ ሕይወት እንዲህ ናትና፡፡

የመስዋዕትነት ወንጌል (ከጸጋዬ ገ/መድኅን አርአያ)

ከጸጋዬ ገ/መድኅን አርአያ

በአጤ ኀይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት (በ1960 አካባቢ) ኤድመንድ መሪ የተባለ አሜሪካዊ የዕለታዊው ኢትዮጵያ ሔራልድ ጋዜጣ አማካሪ ሆኖ ይሰራ ነበር። እኛም እንጠረጥረው እንደነበረ ሁሉ የአሜሪካ ስለላ ድርጅት ሠራተኛ (ኮንታክት ማን) ነው። (እግዜሩ ይይላቸውና ለካ በእኛም መሐል ሰዋቸውን ይተክሉ ነበር) ኤድ መሪ የሥነ ጽሑፍ ሰው ስለሆነ በማስታወቂያ ሚኒስቴር “ተረፈ ዜና” የምንለውን – የማይታተመውንና የማይታወጀውን (በራዲዮና በቴሌቪዥን) በንጥረ ነገሩ መውሰጃ ሥፍራ የተነፈስነውን ሁሉ ሰብስቦ ካገጣጠመው በኋላ ወደ አሜሪካ ሲመለስ Kulubi የሚል መጽሐፍ አወጣ። እንግዲህ ተረፈ ዜና የገባችሁ ይመስልኛል። ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ብዙ ሳንርቅ- ጠባያችንን ወደማያውቁ ሰፈሮች በወረራ መልክ ሳንዘምት እዚያችው ከባዕታችን እንደልማዳችን እንቀማምስና (ከቢራ አያልፍም) ቶሎ ወደ ማተሚያ ቤት እንመለሳለን። እንግዲህ ደግሞ ወደ ማተሚያ ቤት እንመለሳለን። “ምሳችንን እንጠጣ” ይላሉ አንዳንዶቻችን። ቀስ ብሎ ሁላችንም እንዲህ እንደምንል ተደርጐ ተወርቶብናል።

የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት በተፈናቃዩች ተጥለቀለቀ

ፍኖተ ነጻነት

ተፈናቃዩቹ ከጎንደር አካባቢ ተነስተው ከዛሬ 20 ዓመት በፊት ወደ ምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ዳኖ ወረዳ በመውረድ በእርሻ ስራ የተሰማሩ ገበሬዎች ናቸው፡፡ከ1996ዓ.ም ጀምሮ በተለያየ ደረጃ ‹‹ክልላችንን ለቅቃችሁ ውጡ››ሲባሉ ቆይተዋል፡፡Displaced Amharas from Ambo
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማስፈራሪያው ወደ ግድያ፣ድብደባና ወከባ በማደጉ ለአቤቱታ አካባቢያቸውን ጥለው አዲስ አበባ ለመግባት ተገደዋል፡፡ከተፈናቃዩቹ መካከል የተወሰኑት ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ካሳ ተ/ብርሃን ጽ/ቤት በማምራት አፈ ጉባኤውን ለማናገር ቢሞክሩም ሊያገኟቸው አልቻሉም፡፡የአፈ ጉባኤው ጸሐፊ ጉዳያችሁ ታይቷል ወደ መጣችሁበት ተመለሱ››ያለቻቸው ቢሆንም ተፈናቃዩቹ ‹‹ብንመለስ ሊገድሉን ስለሚችሉ አንመለስም››የሚል አቋም ይዘዋል፡፡

የግብጽ ፍርድቤት 530 በሚሆኑ የሙስሊም ወንድማማች አባላት ላይ ሞት ፈረደ

ተከሳሾቹ ለአንድ ፖሊስ ኃላፊ መሞት ተጠያቂዎች ናቸው

egypt 5


* ውሳኔው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን አስደንግጧል
በሕዝብ ከተመረጡ በኋላ በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣናቸው የተወገዱትን የቀድሞ የግብጽ ፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲን በመደገፍ በፖሊስ ጣቢያ ላይ አደጋ አድርሰው የነበሩ 529 ተጠርጣሪዎች ትላንት ሰኞ ዕለት የሞት ቅጣት ተበየነባቸው፡፡ የብይኑ ፍጥነትና የተፈረደባቸው ተከሳሾች ብዛት አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጨምሮ በርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን አስደንግጧል፡፡ አሶሺየትድ ፕሬስ እንደዘገበው ከሆነ ውሳኔው ለይግባኝ የሚቀርብ ሲሆን በሙስሊም ወንድማማች ላይ ሆን ተብሎ የተነጣጠረ ጥቃት እንደሆነ ዘግቧል፡፡

Monday, March 24, 2014

Lower Omo: Local Tribes Under Threat


ኢህአዴግ ባደባባይ የወደቀውን ፈተና “በጓሮ” አለፈ

ግልጽነትና ተጠያቂነት ፈረዱ ወይስ ተፈረደባቸው?

short eiti eprdf


ለግልጽነትና ለተጠያቂነት ብሎም ለህዝቦች ጥቅም ቅድሚያ እንደሚሰጥ ህግ ደንግጎ የተቋቋመው ዓለም ዓቀፋዊ ተቋም ኢህአዴግ ያቀረበውን የይግባኝ ማመልከቻ ተቀብሎ ማጽደቁ አነጋጋሪ ሆኗል። በ2009 ኢህአዴግን “ያወጣሁትን መስፈርት አታሟላም” በማለት እውቅና የከለከለው ይህ ተቋም፣ ኢህአዴግ በሚከሰስባቸው ዋና ጉዳዮች ለውጥ ሳያደርግ የራሱን ውሳኔ የገለበጠበት አካሄድ እየተመረመረ እንደሆነ የጎልጉል ምንጮች ጠቁመዋል።

Sunday, March 23, 2014

ሃያ ሦስት የስቃይ፤ የሰቆቃና የእልቂትና ዓመታት

የኢትዮጵያ ህዝብ በፋሽስቱ ህወሓት ብልሹ አስተዳደርና አምባገነናዊ አገዛዝ ስር ወድቆ በኑሮ ውድነትና በረሃብ አለንጋ እየተገረፈ፣ ሰብኣዊና ዲሞክራሲያዊ መብቱ ተነጥቆ ለአፈናና ለእስራት እየተዳረገ፣ ሉዓላዊ ክብሩ ተደፍሮ ለም መሬቱንና አንጡራ ሃብቱን እየተሸነሸነና እየተቦረቦረ ለባዕድ እየተሸጠ፣ በገዛ ሀገሩ ተፈናቃይና የውጭ እጅ ተመልካች ሆኖ ለስደትና ለእንግልት እየተዳረገ እነሆ ዛሬ ከ23 ዓመት በላይ የሰቆቃ፣ የእልቂትና የመከራ ዓመታት ተቆጠሩ።
ለአለፉት 23 ዓመታት የደፈረሰው ፖለቲካችን ወደ ጭቃነት እየተቀየረ ስለመሆኑም ምንም ምስክር አያሻውም።ፋሽስቱ ወያኔ ከሀገር ሉዓላዊነት እስከ ታሪካችን፣ ከባንዲራችን እስከ እንደ ሕዝብና እንደ ሀገር ያለን ደረጃ መቀመቅ አውርዶታል። አንዳንዶቻችን እንደዚህ ዘመን ትውልድ አባልነታችን ያለፈውን መለወጥ፣ ዛሬን የሰውነት ደረጀችን በጠበቀ ሁኔታ መኖርና ነገንም ላልተወለዱ ልጆቻችን መልክ አስይዞ ለማውረስ ከቁጥጥራችን እየወጣ መሆኑን በግልጽ እንመለከታለን። በሌላ ወገን ወያኔዎቹ የአለፉት 23 ዓመታት የአንድ ጀምበር ያህል አጥረውባቸው፤ ተጨማሪ 40 አመታትን ለመግዛት በማለም ሲንፈራገጡና በቀቢጸ ተስፋ ህዝብን ለማማለል ሲሞክሩ እያየንና እየሰማን ነው። ስንራብ መጥገባችንን ይነግሩናል። ስንታረዝ ደራርበን መጎናፀፋችን ይታያቸዋል። ሀገራችን ከአለም ሀገሮች ተርታ በሁሉም መስኮች ለማለት በሚያስደፍር ደረጃ በማይታመን ፍጥነት እየወጣች ወደ ግርጌ ስትወረወር፤ ወንበዴዎቹ ወያኔወች ግን ሀገራችን ተሞሸረች አማራች ይሉናል። የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲረግጡት የሚደቅን ቅጠል ያህል በመቁጠር ከህግና ከአመክንዮ ውጭ በማን አለብኝነት ሕዝባችንን በንግድ ድርጅቶቻቸው እየገፈፉ እርቃኑን አስቀርተውታል።

“ውሃ፣ መብራት፣ ኔትዎርክ የለም ፤ ኑሮ ከበደን” ሰሚ ጆሮ ያጣ የሕዝብ እሮሮ

“ውሃ የለም፤ መብራት፤ ኔትዎርክ የለም፤ መብት የለም፤ ፍትህ የለም፤ ኑሮ ከበደን” እያሉ ስለኑሮዓቸው የተሰማቸውን በሀቅ የተናገሩ ልጃገረዶች በጋጠወጥ የህወሓት ካድሬዎችና ታጣቂዎች እጅ መከራና ስቃይ እየደረሰባቸው ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በእነዚህ ለጋ ወጣቶች ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ በዝምታ ያልፋል ተብሎ አይታመንም።
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮን ጨምሮ በወያኔና የጥቅም ተጋሪዎቹ ሥር የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙሃን በየዕለቱ ያለማቋረጥ ከሚዘገቡት የልማትና የዕድገት ዘገባዎች ከፍተኛውን ስፍራ የሚይዘው በአገራችን ውስጥ እየተሠሩ ስላሉ ትላልቅ የሃይድሮ ኤለክትሪክ ማመንጫ ግንባታዎች፤ በየከተማው ስለተዘረጉ የውሃ መስመሮች፤ የስልክ አገልግሎት ለማዳረስ ስለተወሰዱ እርምጃዎች፤ ስለ ረጃጅም የባቡር መስመሮች ግንባታ እና ስለ አገር አቋራጭ የመንገድ ሥራዎች የሚቀርቡ የተጋነኑ ዘገባዎች ናቸው።
እነዚህ የልማት አውታሮች ግንባታ በአብዛኛው የሚካሄዱት ከምዕራባዊያን መንግሥታት በሚሰጡ የገንዘብ እርዳታና ዕዳው ለልጅ ልጆቻችን በሚተርፍ አለም አቀፍ የገንዘብ አበዳሪ ድርጅቶች ወለድ እያስከፈሉ በሚሰጡት የረጅም ጊዜ ክፍያ ብድር እንደሆነ ግልጽ ነው።

የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን ምክር ቤት ስብሰባ በመንግስት ካድሬዎች በሀይል ተደናቀፈ

የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን ምክር ቤት ስብሰባ በመንግስት ካድሬዎች በሀይል ተደናቀፈ

Update:
ከ32 የሚበልጡ የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን ምክር ቤት አባላትና አመራሮች ንብረቶቻቸው ተቀምቶ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እየተጋዙ ነው፡፡ የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ እና ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሺበሺ ከፓርቲው የተላኩ መሆኑን የሚያሳየውን ደብዳቤ ጨምሮ መታወቂያቸው ሳይቀር በካድሬዎቹ ተነጥቋል፡፡
————————-
የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ እና ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሺበሺ ደህንነታቸው አደጋ ላይ ነው፡፡
የሟቹን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊ ምስል ያለበት ቲሸርት የለበሱ ከ10 የሚልቁ የመንግስት ካድሬዎች በወላይታ ሶዶ እየተደረገ የነበረውን አንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን ምክርቤት ስብሰባን በሀይል ማደናቀፋቸውን ከስፍራው ለፍኖተ ነጻነት የደረሰው ዘገባ አመለከተ፡፡

Saturday, March 22, 2014

ለነፃነት የምናደርገው ትግል በህገ ወጥ እስርና ማስፈራሪያ አይደናቀፍም! (በሰማያዊ ፓርቲ)

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

“ማርች-8″ የሴቶችን ነጻነትና እኩልነት እንዲሁም ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ የሚከበር የሴቶች ቀን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህን በዓል አስመልክቶ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ባለፈው ዕሁድ የካቲት 30/2006 ዓ.ም ሴቶች ብቻ የሚሳተፉበት የጎዳና ላይ ሩጫ ማዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡ በዚህ የሐገራችንም ሆነ የዓለም ሴቶች የነጻነት ቀናቸውን በሚያከብሩበት ዕለት እንደሌሎች ሴቶች ሁሉ የሰማያዊ ፓርቲ አአባላትም አላማውን ደግፈው በዕለቱ ቀኑን አስመልክቶ በተዘጋጀው ሩጫ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ በዚህ በሴቶች የነጻነት ቀን በስርዓቱ ላይ የሚነሱ ብሶቶችን ካሰሙት ተሳታፊዎች ውስጥ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሚገኙበት ሲሆን፣ በተለየ መልኩ በእነዚህ አባላቶቻችን ላይ ያነጣጠረ የአፈሳ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እንደዚህ አይነት ህዝባዊ መድረኮችን ላይ ብቻ ሳይሆን ሁሌም ህዝብ ላይ የሚደርሰው በደል በማጋለጥ መብት እና ለአገራችን ብሄራዊ ጥቅም በመቆም በገዥው ፓርቲ ተደጋጋሚ ህገ ወጥ እርምጃ ሲወሰድበት ቆይቷል፡፡ የተደረገው ህገ ወጥ ድርጊት ከዚሁ ፓርቲው ለህዝብና ለአገር መቆሙን ተከትሎ እየደረሰበት ያለው የከፋ የጭቆና አካል ነው፡፡

Semayawi party press conference, Addis Ababaህገ ወጥ ድርጊቱን የበለጠ አስገራሚ የሚያደርገውም አባላቶቻችን የታሰሩበት ምክንያት “የጣይቱ ልጅ ነን” ፣ ህወሓት/ኢህአዴግን ምን ያህል ከታሪክ ጋር የተጣላ መሆኑን ከማሳየቱም በተጨማሪ አባላቶቻችን ለማስር እንግልት ወቅት በአባላቶቻችን ላይ የደህንነት አካላት ነን በሚሉ ግለሰቦች ማስፈራሪያና ዛቻ ተፈፅሞባቸው፡፡

Friday, March 21, 2014

ለአልሙዲ “ማፅናኛ” (ከጋዜጠኛ ተስፋዬ ተሰማ)

ከጋዜጠኛ ተስፋዬ ተሰማ

Ethiopian-born al-Amoudi
በቅርቡ ባህርዳር ላይ በተካሄደው የኢትዮጵያ ስፖርት በአል ሼኽ አልሙዲ በክብር እንግድነት ተጋብዘው ነበር። የበአሉን መክፈቻ በቲቪ ስከታተል አንድ ጥያቄ ወደ በአእምሮዬ መጣ። አልሙዲንን የክብር እንግዳ አድርጐ መጋበዙ ለምን አስፈለገ?..ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ።

በመኢአድ በኩል የቀረበው ቅድመ ውህደት ያለመፈረም ሰበብ አሳዛኝና የህዝቡን ጥያቄ ያኮሰሰ ነው!!

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የሰጠው መግለጫ

Andenat Party UDJየአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ለረዥም ዓመታት የህዝብ ፍላጎትና አንገብጋቢ የሆነው ተቃዋሚዎች ” ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ ” ጥያቄ ለመመለስ በስትራቴጂ አምስት ዓመት እቅድ ውስጥ በማካተት መንቀሳቀስ ከጀመረ ዓመታት አስቆጥረዋል:: የውህደቱ ጉዳይ ለአንድነት ፓርቲ የአንድ ሳምንት ጥያቄ ሳይሆን ስትራቴጂ ግብ ነው:: የዚሁ አካል የሆነው እንቅስቃሴ በመኢአድና በአንድነት ፓርቲዎች መሐከል መካሄድ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል:: ሂደቱን ለመቋጨት በርካታ ድርድሮችና የደብዳቤ ልውውጦችም ቢከናወንም እነሆ አሁንም ተጨባጭ ውጤት በተግባር አለመታየቱ የሁለቱም ፓርቲ አባለት በጅጉን እያሳዘነ ነው::
በተለይ በቅርቡ እየተካሄደ ከነበረው ተግባር መካከል ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) መጋቢት 1 ቀን 2006 ዓ.ም የተፃፈልንን ደብዳቤ መሰረት በማድረግ የሁለቱ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲገናኙ የተጠየቀው ጥያቄ በደስታና በላቀ መንፈስ ተቀብለነዋል::

Thursday, March 20, 2014

የአባ በላ ፍቅር እስከ መቃብር (ማህሌት ነጋ)

በማህሌት ነጋ

“ሃይለማሪም ደሳለኝ አብዩዝድ ነው። እንደውም ማታ ማታ (በህወሃቶች) ሳይገረፍ አይቀርም!” ብሎ ነበር ብርሃኑ ዳምጤ ከጥቂት ወራት በፊት በፓልቶክ ላይ።….
ESAT brings Aba Mela as a political analyst“ስለ አንድ ሰው ስንጽፍና ስንናገር ቢቻል አዎንታዊና መልካም ከሆኑ ነገሮች መጀመር ጥሩ ነው” ይሉ ነበር “የኔታ” በሚል ቅጽል ስም እንጠራቸው የነበሩ የዘጠናኛ ክፍል የአማርኛ አስተማሪያችን። ቀጭንና የዋህነት የተላበሰ ፊታቸው ላይ ችፍ ብሎ የማርክስን ግርማ ሞገስ ያጎናጸፋቸውን ገብስማ ሪዝ በእጃቸው እየዳበሱ ያስተማሩኝ ትዝ አለኝ።
ነገሩ የድሮ ትምህርት ቢሆንም የተማርኩትን በማሰብ እንደ አዞ ደንዳና ቆዳ ስለ ታደለው ብርሃኑ ዳምጤ ለመጻፍ ስነሳ ከልቅ አፉ ባሻገር ከማደንቅለት ባህሪው ብጀምር መልካም ነው ብዬ አሰብኩ።

የኢትዮጵያ ተተኪ ሴቶች ትውልድ መነሳሳት! (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

“ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል!”

ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ እንደገና ወኔ የተሞላበት የትግል መንፈሱን በማደስ ጥንካሬውን አሳየ !
Semayawi party female youth activists released
እ.ኤ.አ ማርች 9/2014 የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች በዓል ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ ተዘጋጀቶ በነበረው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶችም ተሳትፎ አድርገው ነበር፡፡

Wednesday, March 19, 2014

“ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል!” – ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ እንደገና ወኔ የተሞላበት የትግል መንፈሱን በማደስ ጥንካሬውን አሳየ!

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
እ.ኤ.አ ማርች 9/2014 የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች በዓል ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ ተዘጋጀቶ በነበረው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶችም ተሳትፎ አድርገው ነበር፡፡ ከዴሞክራሲያዊ ምርጫ ባፈነገጠ መልኩ በኃይል በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጥጠው ስልጣንን የሙጥኝ በማለት ከህግ አግባብ ውጭ በህዝብ ላይ ደባ በመፈጸም ላይ የሚገኙትን የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ዕኩይ ምግባር የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲገነዘበው በማሰብ ወጣት ሴቶቹ እውነታውን ያለምንም መሸፋፈን በማጋለጥ እምቢ አሻፈረኝ በማለት ተቃውሟቸውን ለዓለም በይፋ አሰምተዋል፡፡ እንዲህ በማለትም ተቃውሟቸውን አጠናክረዋል፣

አባ መላ ሳይበላ ተበላ !

ሆዳም! ስለሚበላው እንጂ ስለሚባለው አይጨነቅም!

አዜብ ጌታቸው
አባ መላ ነኝ የሚለው የፓልቶኩ ብርሃኑ ዳምጤ ሰሞኑን የሰራው ስራ ከማንም በላይ የጎዳው እራሱን ነው።  ከአንድ ድርጅት ውልቅ ብለው በዚያው ጀንበር ሌላው ድርጅት ጥልቅ የሚሉ፤ ያም ሳይጥማቸው ወይም ሳይመቻቸው ይቀርና ወዲያው ደሞ ወደ ሌላ 3ኛ 4ኛ….. ድርጅት ጥልቅ ውልቅ የሚሉ ጥቂት የማይባሉ ቅብዝብዞችን አውቃለሁ።እነኚህ አይነቶቹ የቻሉትን ያህል እንደ ፌንጣ ዘለው ዘለው በመጨረሻ እዩኝ እዩኝ ያለ ……እንዲሉ፦ ራስን ብቻ አባል በሚያደርገው ዲፕሬሽን ወደ ተሰኘው ድርጅት ይገቡና ፍጻሜያቸውም እዛው ይሆናል።
ሰሞኑን በአባ መላ የታየው ዝላይ ግን በፌንጣ ተምሳሌት ከተገለጹት ቅብዝብዞች የተለየ ነው፡፡ አባ መላ ውልቅ ካለበት የወያኔ ጓዳ ያሞሌ ተመኑን ቀንሶ ዳግም ጥልቅ ብሏል። ስለዚህ ለአባ መላ ተግባር በተምሳሌነት የምትጠቀሰው ፌንጣ ሳትሆን የተፋውን መልሶ የሚውጠው ጉማሬ ይመስለኛል ።

ውዳሴ መስከረም ወጽዮን

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

woman flag


በብዙ አገሮች እንዲሁም በኢትዮጵያ የሴቶችና የወንዶች ቁጥር ብዙም አይለያይም፤ እኩል ለእኩል ይሆናሉ፤ ነገር ግን ይህ የቁጥር እኩልነት በኑሮአችን ላይ አይታይም፤ በ1983 የወያኔ ሠራዊት በየመንገዱ ይታይ በነበረበት ጊዜ አንድ ቀን ወደሂልተን ሆቴል ስገባ አንዲት ልጅ ከቁመትዋ የሚረዝምና ከክብደትዋ የበለጠ ጠመንጃ ይዛ አየሁና ዕድሜዋን ብጠይቃት አሥራ አራት አንደሆነ ነገረችኝ፤ ይቺ ልጅ በዚህ ዕድሜዋ ስንት መከራ እንዳየች እግዚአብሔር ይወቀው፤ በዚያን ጊዜ እንደስዋ ያሉ ብዙ ሴቶች ወያኔዎች አይቻለሁ።

ሁለቱ ተፎካካሪ ነገስታቶች

(ቁምላቸው ገ/መስቀል አምቦ)

ካፊ አቲዮ ጋኬ ሻረቾ (አጼ ጋኪ ሻረቾ)

ምኒልክ ሁሉን አስገበሩ። ጣሊያንንም አድዋ ላይ አሸነፉ። አንድ ስጋት ብቻ ቀረ ከወደ ደቡባዊ ከፍታዎች የመሸገ ባላንጣ። ከአርሲ ዘመቻ በፊት ምኒልክን በአንድራቻ ደጅ ያስጠና ጌታ።

ነገረ-ኢትዮጵያ ርዕሰ አንቀጽ የህዝብ የአገልግሎት ጥያቄ አስቸኳይ ምላሽ ያሻል!

“ነገረ-ኢትዮጵያ” የሰማያዊ ፓርቲ ጋዜጣ (ቅፅ 1 ቁጥር 4)

Negere Ethiopia Issue 4ነገረ-ኢትዮጵያ ርዕሰ አንቀጽ የህዝብ የአገልግሎት ጥያቄ አስቸኳይ ምላሽ ያሻል!

…በውሃ እጥረት ምክንያት ተማሪዎችና አዛውንቶች ካለ አቅማቸው ከሰፈር ሰፈር እየተንከራተቱ በጀርባቸው ለመሸከም ተገደዋል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ምክንያት ህዝብ ስልክና ኢንተርኔት መጠቀም አልቻለም፡፡ ባልታቀዱ ግንባታዎች ምክንያት የሚፈራርሱት መንገዶች ህዝብ በሰዓት ወዳሰበበት ቦታ እንዳይደርስ አድርገዋል፡፡ እነዚህ አገልግሎቶች የሰማይ ያህል በራቁበት ወቅት ሙስና፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ህዝብ ሊያገኘው በሚገባው አገልግሎት ላይ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆነውበታል… 
[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

Tuesday, March 18, 2014

በነፃነት ቀን ነፃነት ማጣት!

ይድነቃቸው ከበደ

Young semayawi party female activists
ሰብአዊ መብቶች እያንዳንዳችን ሰው በመሆናችን ብቻ የሚገቡን ከሰብአዊነታችን ተለይተው ሊታዩ የማያችሉ መብቶች ናቸው፡፡ መንግስታት እነዚህን በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጣቸውን ሰብአዊ መብቶች ለማክበር ለማስከበርና ለማሟላት በቀዳሚነት ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በዚህም መሰረት ኃላፊነት ከፈረሙ ቀደምት አገራት መካከል ኢትዩጵያ ትገኝበታላች፡፡

መንግስት ስለ ጣይቱ ልጆች ጨንቆት ዋለ (Semayawi Party Update)

መንግስት ስለ ጣይቱ ልጆች ጨንቆት ዋለ (Semayawi Party Update)

Semayawi Party- Ethiopia (Update)
semayawi-female-free1ምንም የረባ መከራክሪያ ያላቀረበው ፖሊስ መናገር አቅቶት ሲንተባተብ ነው የዋለው በተጨማሪ ሌሎች መያዝ የልቻልናቸው 20 እሩጫው ላይ የነበሩ ሴቶች ስላሉ በማለት የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል ሲጀምር ችሎቱ የታየው በጽ/ቤት ነው የነበረው የሰዉ ብዛት ያስጨነቀው መንግስት ሰዉ በችሎት እንዳይታደም ክርክሩን እንዳይሰማ በጣም ጠባብ በሆነችው ቢሮ ከአቅሙዋ በላይ የሆኑ ተከሳሾችን ለማሰተናገድ ተገዳለች ውሳኔ መስጠት የማይችለው ዳኛ ለነገ መጋቢት 10/2006 በመደበኛ ይታይ በሚል ተልካሻ ምክንያት ቀጥሮአቸዋል የጣይቱ ልጆችግን በጣም በሚያሰድሰት ሞራልና የትግለ ሰሜት ላይ ሆነው ለማየት ችለናል፡፡

Free the young women of Blue Party (Norway)

DCESON PRESS RELEASE

Ethiopians’ struggle for justice, freedom and democracy is continuing today in and outside of the country. Democratic change in Ethiopia support organization-Norway (DCESON) is one of the organizations formed in Norway to support the struggle.Ask a Semayawi Party woman
The objective of DCESON is to support and to encourage the oppositions in and outside of Ethiopia which are believed to bring the real democratic change, peace and stability in the country as well as in the region.
It is on the basis of this fundamental principle that DCESON strongly oppose the intimidation, imprisonment and beatings of Semayawi party members following March 9, woman’s day in Ethiopia.

Monday, March 17, 2014

[የሃረሩ ቃጠሎ ጉዳይ] መቃጠል መቃጠል መቃጠል – ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)

ከአስራ ምናምን ዓመታት በፊት ፔሩቪያዊው ኢኮኖሚስት ሄርናንዶ ደ ሶቶ ስለ “ኢንፎርማል” ኢኮኖሚ በጻፈው መጽሃፍ ውስጥ ፣ በአለም ላይ በህጋዊ መንገድ ያልተዘመገበ ከ10 ትሪሊየን ዶላር በላይ ሃብት መኖሩን፣ ይህን ሃብት መዝግቦ የባለቤትነት ህጋዊ መብት በመስጠት ብዙ ዜጎችን ከድህነት ማውጣት እንደሚቻል ገልጾ ነበር። ደ ሶቶ እንደሚለው በደሃ አገራት ሁለት አይነት ኢኮኖሚ አለ። አንደኛው ጥቂቶች የሚያንቀሳቅሱትና በመንግስት እውቅና የተሰጠው ኢኮኖሚ ሲሆን ሌላው ደግሞ መንግስት የማያውቀው በአብዛኛው ህዝብ የሚንቀሳቀሰው ኢኮኖሚ ነው ፤ ይህ ኢኮኖሚ በመንግስት እውቅና ያልተሰጠው በመሆኑ በዚህ ስር የታቀፉ ዜጎች ከባንክ ተበድረው ቢዝነሳቸውን ለማስፋፋት አይችሉም፤ መንግስትም ከእነዚህ ሰዎች ተገቢውን ታክስ አያገኝም። በደሃ አገራት ውስጥ መንግስታት እውቅና ሳይሰጡት የሚንቀሳቀሰው ሃብት እውቅና ከተሰጠው ሃብት ይበልጣል። ደ ሶቶ እንደሚመክረው ህጋዊው የኢኮኖሚ ስርአት የማያውቃቸውን ሀብቶች በመመዝገብና ህጋዊነት በማላበስ ዜጎች ሃብትና ንብረት እንዲያፈሩና ድህነትን እንዲሻገሩ ማድረግ ይቻላል።

የጠፋውን የማሌዥያ አውሮፕላን የበላው ጅብ አልጮህ አለ፤ (ከዚህ በፊት 5 አውሮፕላኖች ጠፍተው እንደነበር ያውቁ ኖሯል?)

ከአትላንታው አድማስ ራድዮ

ስለ ማሌዢያው የበረራ ቁጥር 370፣ የተሰወረ አውሮፕላን መዘገብ እጅግ ከባድ ነው። ምክንያቱም ነገሮች በየደቂቃው ይቀያየራሉና።

የቁልቁለት መንገድ! – ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

Temesgen… በማስመሰል ታጥሮ መሆን በጠፋበት
ምን አገባኝ የሚል በተከማቸበት
የባይተዋር መንፈስ ከሞላ ባገሩ
ዘመኑን ማወቂያ ይሄ ነው ሚስጥሩ
ይሄን ጊዜ ጠርጥር እንደጠፋ ዘሩ፡፡
(ገጣሚ ደምሰው መርሻ/ያልታተመ)
አዎን፣ ገጣሚ ደምሰው እንዳለው እኔም በዚህ ዘመን “ዘሩ እንደጠፋ” አሊያም ሊጠፋ እንደተቃረበ እጠረጥራለሁ፡፡
ስለምን? ቢሉ …በኢትዮጵያችን ለህሊናው፣ ለሕዝብና ለሀገሩ የሚቆረቆር፣ የእውነት ተሟጋችና የሞራል ልዕልናን የተቀዳጀ ሙሉ ሰው ፈልጎ ማግኘት እጅግ አተካች ሆኗልና፡፡

በአሜሪካ የሚኖረው የሕወሐት ወንጀለኛ

ከኢየሩሳሌም አርአያ

The Ethiopian author, former TPLF torture czar and spymaster “Professor” Bisrat Amare
Bisrat Amare former head of TPLF Intelligence
የሕወሐት አባል የሆነውና በአሜሪካ የሚኖረው ብስራት አማረ በርካታ ወንጀሎችን እንደፈፀመ የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። ሕወሐት በረሃ እያለ የባዶ 6 እስር ቤት ዋና ሃላፊ የነበረው ብስራት አማረ የኢ.ህ.አ.ፓ አባላት የነበሩት እነ ፀጋዬ ገ/መድህን (ደብተራው) ጨምሮ በሕወሐት የተያዙትን በሙሉ ወረኢ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በነበረ እስር ቤት በጅምላ አሰቃይቶ እንደገደላቸው ምንጮቹ አረጋግጠዋል። በሺህ የሚቆጠሩ የትግራይ ሰዎች « ኢዲዩና ፊውዳል..» በሚል ባዶ 6 ተብሎ ይጠራ በነበረው እስር ቤት ተሰቃይተው እንዲገደሉ የተደረጉት በብስራት አማረ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮቹ ከዚህ በተጨማሪ የድርጅቱን በርካታ አባላት እንዳስገደለ አያይዘው ገልፀዋል። እነተክሉ ሃዋዝ በዚህ ወንጀለኛ ከተገደሉት ይጠቀሳሉ ሲሉ ያክላሉ።

በዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ዝክር፤ በእህቶቻችን ኮርተናል! (ግንቦት 7)

March 17, 2014

Ginbot 7 weekly editorialለዘንድሮው ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን መታሰቢያ በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገው የሩጫ ትዕይንት ላይ ወጣት ሴቶች ባሳዩት ልበ ሙሉነት ኮርተናል። የሩጫውን ትዕይንት አስታከው፣ በአብዛኛው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እንደሆኑ የተነገረላቸው ወጣት ሴቶች ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለህሊና እስረኞች መፈታት እና ለሀገር አንድነት ድምፃቸውን ከፍ አድረገው ጮኸዋል፤ ዘምረዋል። እነዚህ ወጣት ሴቶች በሥርዓቱ ምን ያህል እንደተማረሩ በቃላትም በአካል ንቅናቄም አሳይተዋል። ዘረኛውና ፋሽስቱ ወያኔ ግን “ለምን ተቃወማችሁኝ” ብሎ አስሯቸዋል፤ ከፊሎቹም የደረሱበት አይታወቅም። በእህቶቻችን ቆራጥነት ኮርተናል፤ በወያኔ የፈሪ ዱላ ደግሞ ተቆጥተናል። በ1997 እና 98 “የወላጆቻችን ድምጽ ይከበር” ያሉ ሕፃናትን የጨፈጨፈው ወያኔ በ2006 ወጣት ሴቶችን ከማሰቃየት ይመለሳል ብለን አናምንም። ወያኔ እስካልተወገደ ድረስ የፈሪ ዱላው የማይቀር ነገር ነው።

Sunday, March 16, 2014

የኢህአዴግ ማመልክቻ ድጋሚ ውድቅ መደረግ አለበት!

በመጀመሪያ አፋኝ ሕጎች መሠረዝ አለባቸው!

eiti

የተፈጥሮ ሃብትን በትክክለኛ መንገድ ለሕዝብ ጥቅም መዋሉን በመከታተል ለአገራት እውቅና የሚሰጠው The Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) ለተሰኘ ዓለም ዓቀፋዊ ተቋም ኢህአዴግ በድጋሚ ያቀረበው የእውቅና ጥያቄ ማመልከቻ ውድቅ መደረግ እንዳለበት ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት (Human Rights Watch) ድርጅት አስታወቀ፡፡ ኢህአዴግ የእውቅና ማመልከቻ አስገብቶ ውድቅ ተደርጎበት የነበረ ሲሆን በኢትዮጵያ ላይ የታወጁት አፋኝ ሕጎች እስካልተወገዱ ድረስ ድጋሚ ማመልከቻው ውድቅ ሊደረግ እንደሚገባው ጨምሮ ተነግሯል፡፡

በአዲስ አበባ ውሃ እስከ 20ቀናት ይጠፋል

መፍትሔ ያጣው የውኃ ችግር ተባብሶ ቀጥሏል

waterline


* “የውኃ ምርት ችግር የለብንም የኤሌክትሪክና የማሰራጨት እንጂ” የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን
የፌዴራል መንግሥት መቀመጫና የአፍሪካ መዲና በሆነችው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ፣ ለሁለትና ሦስት ቀናት ይጠፋ የነበረው የውኃ ችግር እስከ 20 ቀናት እየጠፋ  መሆኑንና ችግሩ ተባብሶ መቀጠሉን ነዋሪዎች እየገለጹ ነው፡፡