Translate

Monday, December 30, 2013

የወገን ጩኸቱን አናፍነው! ጩኸቱን አንቀማው!

የማለዳ ወግ

ነቢዩ ሲራክ
ሰሞኑን ጠቃሚ መረጃ የምንለዋወጥባቸው ማህበራዊ ገጾቻችን በሙግት ንትርክ ማዕበል ተውጠው ተመለከትኩ … ከእምየ ምኒሊክ እሰከ በደሌ ቢራ ፣ ከድንቁ ትንታግ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ መግለጫ ፣ እርማት እስከተሰጠበት እንቁ መጽሔት ፣ ከታሪክ አዋቂው የሃገር ሽማግሌ ፕሮፊሰር ይስሐቅ የታሪክ ቀደምት ትንታኔ ታሪክ እስከ ማይጠቅመን የጁሃር መሃመድ ዘመቻ ሁሉም ሰሞነኛ ዝብሪት በየአይነቱ ሰማን ። ይህ ሁሉ ታዲያ በፈረንጆች አመት በዋዜማው ባይሆን ደስ ባለኝ! ይህም የእኛ ነገር ፣ የእኛ ኑሮ ነውና ምን ያደርጉታል?Ethiopians in Saudi Arabia suffering, December 2013
ባለሁበት የሳውዲ ምድር በአለም እንደ ጨው የተበተንን የዚያች ሃገር ዜጎችን ትኩረት ሳቢ ብቻም ሳይሆን አስጨናቂ ቀንን ተፋጦ ማወጫ ያጣ ወገን ጩኸት ደምቆ እንዳይሰማ የእኛ ነገር አልተመቸውም ! ሌላው ቀርቶ ጥቂት “ያገባናል” ያልን መረጃን በቀላሉ እየተለዋወጥን በምንገኝባቸው ማህበራዊ ገጾች ከአንድ የአለም ጫፍ ወደ ሌላው የአለም ጫፍ በብርሃን ፍጥነት የሚሰራጨው የጥላቻ ፖለቲካ የመረጃ ቅብብል መተንፈሻ ፣ ጉዳታችን ለአለም መንገሪያ ሜዳችን እንዳያጨልምብን ሰጋሁ ! ከሁሉም የሚያሳዝነው የምንወዳቸውና የምናከብራቸው የተማሩ የተመራመሩት ወገኖቻችን ሳይቀሩ በዝብሪቱ አዙሪት ተጠልፈው መግባታቸውን እየታዘብን ነው ።

የኢትዮጵያ ትንሣኤ! (ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም)

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
H.I.M. Haile Selassie and bronze statue of Ghanaian President Kwame Nkrumah
ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ: ፕሬዚደንት ንኩሩማ ሃዉልት
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (ኦ ኤ ዩ) የአፍሪካ ሕብረት (ኤ ዩ በየአፍሪካ አንድነትን የተካው) ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ከተማ  የወርቅ ኢዩቤልዩውን በማክበር ላይ ነው፡፡ በሜይ 1963 አፍሪካ አንድነት ሲመሰረት፤የጋናው ፕሬዜዳንት ክዋሚ ንኩርማ የመዝጊያ ንግግሩን የደመደመበት በተለይ በእድገት ላይ ያለችውንና ተቀኚ የነበሩትን የአፍሪካ ሃገራት ወደ ነጻነት ለመራችው ኢትዮጵያ ለክብሯ በመረጠውና ባዘጋጀው ግጥሙ ነበር፡፡ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን አስመልክቶ ንኩሩማ  ሲናገር: ‹‹ግርማዊ ሆይ! በጓደኞቼና በራሴ ስም የሚቀረኝ ለኢትዮጵያና ለሕዝቦቿ በተለይም ለግረማዊነትዎ ያለኝን አክብሮት በመግለጽ በዚህች ታሪካዊ ሃገር ባደረግነው ቆይታ የተቸረንን አቀባበልና መስተንግዶ ሳላመሰግን ማለፍ አይቻለኝም፡፡ ንኩሩማህ ዘወትር ባነበብኩት ጊዜ ትውስታ የሚያጭርብኝን ይህን የግጥሙን ስንኝ አሰማ፡፡  የራሱ የንኩሩማህ ቃላት እነዚህ ናቸው፡፡

ኢንጂነር ግዛቸው የዉህደት ጥሪ ለሰማያዊ/መኢአድ/መድረክ/አረና/ኢዴፓ አቀረቡ


UDJ
ኢንጂነር ግዛቸው የዉህደት ጥሪ ለሰማያዊ/መኢአድ/መድረክ/አረና/ኢዴፓ አቀረቡየአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ «በመድረክ ዙሪያም ሰፊ ዉይይት ያደረገ ሲሆን፣ አዲሱ ብሄራዊ ምክር ቤት፣ በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ፓርቲው ከመድረክና ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የጀመረውን ውህደት እልባት እንዲያበጅለት መመሪያ ሰጥቷል» ስንል መዘገባችን ይታወቃል።

Sunday, December 29, 2013

“ነፃ እስክትወጡ በደሌ አትጠጡ” ጃዋር መሀመድ

ሁኔ አቢሲኒያዊ

Ethiopian singer Teddy Afro, Bedele controversy
መቼስ ለአገር የሠራና የደከመ ቢያጠፋም እንኳን የቻለውን ያህል በመሞከሩ በክብር ማኖርና መንከባከብ የውዴታ ግዴታ ነው። የሚያሳዘነኝ ነገር ይሄ ሳይሆን እስካሁን እንዲህ ያለውን ነገር ሰምተንና አይተን ያለማወቃችን ነው ስንት የለፉላትን አገር በእነ መለስ እንዲህ መሆኗን ሳያዩ ማለፋቸው ሳይቀር ዛሬም ድረስ ቢያንስ ስራዎቻቸው በክብር እንደቅርስ አለመያዛቸው ሳያንስ በየጊዜው የሚነሱ የታሪክ ነቃፊዎች የትችታቸው ማሟሻ አድርገዋቸው ማየት ያስዝናል ለዚህም ይመስለኛል አገሪቷ የሠራላትን፣ የደከመላትንና የተቆረቆረላትን ማዋረድ እንጂ ማክበር እንደማታውቅ የሚለፈፈው። በዚያም ተዞረ በዚህ የውዷ ኢትዮጵያ ታሪክ ‘የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ’ በመሆኑ ምንም ማለት ልናዝን አይገባም።

ከሰሞኑ ደግሞ እነ ጃዋር መሀመድ ተከታዩን ስብከት ነጻ ሊያወጡት ቃል ገብተውለት ለነበረው ኦሮሞ የኢትዮጵያ ልጆች መንፈሳዊውን ስብከታቸው ጀባ ብለዋል፡፡

ከቴዲ አፍሮ የተሰጠ መግለጫ “ለሙዚቃ አፍቃሪዎቼ በሙሉ”

ከቴዲ አፍሮ የተሰጠ መግለጫ “ለሙዚቃ አፍቃሪዎቼ በሙሉ”


ከጥቂት ሳምንት በፊት የዳግማዊ ሚኒሊክን መቶኛ አመት የሞት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በእንቁ መጽሔት ተጋብዤ ቃለ ምልልስ አድርጌአለሁኝ። ይኸዉ Ethiopian Artist Teddy Afroዉይይታችን በ “አመጣጡን ያየ አካሄዱን ያዉቃል” እርዕስ ስር ለህዝብ እንደቀረበ አዉቃለሁ። ከዚህ ዉጪ እኔ በማላዉቀዉ ሁኔታ መጽሔቱ በሰራዉ ስህተት ፎቶዬን በሌላ አነጋገር አጅቦ ያወጣዉን ከኔ እምነትም ሆን ጉዞ ጋር የሚራመድ ጉዳይ አይደለም። ይህንኑ ለማረጋገጥ “አመጣጡን ያየ አካሄዱን ያዉቃል” በሚል ርዕስ ስር በወጣዉ መጽሔት መልክቶቼን በማየት ማረጋገጥ ይቻላል። ያም ሆኖ መጽሔቱ በሰራዉ ስህተት እርምት አድርጎ ይቅርታም ጠይቆናል። ጉዞዬ የፍቅር የአንድነት እና የይቅር ባይነት ነዉና ይህንንም ጉዳይ በዚሁ ስሜት ውስጥ እናስተናግደዋለን።
ፍቅር ያሽንፋል
ቴዎድሮስ ካሳሁን

በከፊቾ ዞን የጽላት ዝርፊያና ቀበኞቹ

"ባለሃብቶች በእድሳት ስም ቤተ መቅደስ ዘልቀው ጽላት ይቀይራሉ"

tabot


በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል በከፊቾ ዞን በጥንታዊ አድባራት ጽላት መዘረፉን እናውቃለን ያሉ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ገለጹ። የዜናው ምንጮች የዞኑ አገረ ስብከት በዞኑ በሚገኙ አድባራት ላይ ምርመራ እንዲያካሂድ ጠይቀዋል። ዝርፊያውን የሚያካሂዱት “ባለሃብቶች” መቀመጫቸውን አዲስ አበባና ጅማ ከተማ ያደረጉ የክልሉ ተወላጆች መሆናቸውን አስታውቀዋል።

Saturday, December 28, 2013

እኔ አላውቅም ፈራሁ ጁሃር (ከሄኖክ የሺጥላ )

የበደሌ ቢራ ፋብሪካ ከአዲስ አበባ 483 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ኢሉ-ኣባ-ቦራ ( Eloo The father of Holstein Friesian) ኢልባቡር ከተማ በሁለት መቶ ሃምሳ ሺ ስኩውር ሜትር ይዞታ ላይ ስራውን እንደ ኣውሮጳውያን ኣቆጣጠር በ 1993 ማከናወን የጀመረ ትልቅ የቢራ ማምረቻ ድርጅት ነው።

Poet Henok Yeshitela
ኢሊባቡር መልካም ምድራዊ ኣቀማመጡም ሆነ ምድራዊ ልምላሜው፥ እንደ በቆሎ ፤ ገብስ፤ ጤፍ፤ የቅባት እሎች፤ ማር፤ ከነ ቦራ ደሞ ወተት፤ ቅቤ እና ወዘተ የሚዘራባት፤ የሚታጨድባት፤ የሚቆረጥባት፤ የሚታለብባት ሃገር እንድትሆን ኣድርጉዋታል።
ኢሊባቡርን የጽሁፌ መንደርደሪያ አደረኩ እንጂ ዋናው ነጥቤ እሱ አይደለም። ዛሬ መናገር ወይም መጻፍ የፈለኩት ቴዲ አፍሮ በቅርቡ በመላው ኢትዮጵያ የሙዚቃ ዝግጅቱን እንዲያሳይ ወኪል የሆነውን የበደሌ ቢራን ያለመጠጣት አድማ ( boycotting) በመላው ኢትዮጵያ ይደረግ ዘንድ አንዳንድ ግለሰቦች የጀመሩትን ነገር ሰምቼ፤ ለምን በደሌን፤ ለምን ቴድን የሚል ጥያቄ ለሚጠይቁ፤ መልስ የሚመስለኝን ለመተየብ፤ ከተቻለም ለማሳየት መመኮር በመሻቴ ነው ።

ፖለቲካ ጨለማን ተገን አድርጋ ወንጌል ስትሆን !


(አሌክስ አብረሃም ) 

ወገኖቸ እሰብካችኋለሁ !! 
በደሌ ቢራ አትጠጡ እንደተባለ ሰምታችኋል...... እኔ ግን እላችኋለሁ ባጠቃላይ አልኮል መጠጥ አትጠጡ ! ለጤና ጠንቅ ነውና !! መጠሃፉ ‹‹ደሃ ድህነቱን እንዲረሳ የወይን ጠጅ ስጠው ›› ቢልም እኛ ኢትዮጲያዊያን <አስራ አንድ> በመቶ እያደግን ያለን ሃብታም ህዝቦች ነንና እኛን አይመለከትም ! አዎ ! መጠጥ አገር እያጠፋ ነው ትዳር እየበጠበጠ ነው ይሄ ሁሉ ያማረበት ጠጭ ብርጭቆውን በቄንጥ ይዞ ውሰኪውን የሚከነብል ይሄን ሆንኩ ሳይል ወጋኝ ፈለጠኝ ሳይል ድንገት የሚከነበለው ለምን ይመስላችኋል ......መጠጥ .....መጠጥ ነው ወገኖቸ !! 

ህዝቤ ቁሞ ይንከላወሳል እንጅ ጉበቱ እኮ የለም .....ሳንባውኮ በጥቃርሻ ተዥጎርጉሮ የሚያፈስ ኮርኒስ መስሏል ......ነብሱ አድፏል ! ይሄ ሁሉ የሆነው በምንድን ነው በመጠጥ !! መጠጥ እንዝህላል ያደርጋል ግዴለሽ ያደርጋል ዋጋ ቢስ ያደር .... ጋል ወገኖቸ ......ዛሬ እኮ ምፅአት ቀርባለችና ንስሃ ግቡ ሲባል ‹ሎ...ል› የሚል ወጣት ነው እያፈራን ያለነው ....

ትውልዱ በቀቢፀ ተስፋ የሚይዝ የሚጨብጠውን አጥቷል ቤተስኪያኖቻችን ርግብና ዋነስ ሰፍሮባቸው ካለሰው እየዋሉ ቡና ቤቱ በሰው ተጨናንቋል ..... ጭፈራ ቤቱ ካፍ እስከገደፉ ሞልቷል .....ስለሳምሶን ታሪክ ሰምታችኋል (ለነገሩ መቸ መጠሃፉን ታነቡና ፌስ ቡክ ላይ አፍጥጣችሁ እየዋላችሁ ) ሳምሶን ታላቅ የህዝብ ነፃአውጭ ነውና ሲረገዝ እናቱ የአልኮል መጠጥ በአፏ እንዳይዞር እግዜር አዟት ነበር ! 

Friday, December 27, 2013

የጁነዲን ባለቤት በድርድር ተፈቱ !!/ከኢየሩሳሌም አርአያ/

የቀድሞ የኦህዴድ/ኢህአዴግ አመራር አባልና ሚኒስትር የነበሩት አቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት በውስጥ በተደረገ ድርድር ከእስር እንዲለቀቁ መደረጉን የቅርብ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን ገለጹ። « ከሳኡዲ ኤንባሲ ገንዘብ ተቀብለው ሲወጡ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል» በሚል በሽብርተኝነት ወንጀል እንዲከሰሱ የተደረጉትና ለአንድ አመት የታሰሩት የአቶ ጁነዲን ባለቤት ወ/ሮ ሃቢባ መሐመድ ከሕወሐት መሪዎች በተላለፈ ቀጭን ትእዛዝ እንዲፈቱ መደረጉን የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም ይህ ሊሆን የቻለው በስደት ከሚገኙት አቶ ጁነዲን ሳዶ ጋር በተደረገ ምስጢራዊ ድርድር ላይ “መንግስት ከዚህ ቀደም በወሰዳቸው እርምጃዎች፣ ፖለቲካዊ ምስጢራዊ ጉዳዮችና ገዢውን ፓርቲ የሚመለከቱ ማንኛውም ነገሮች በየትኛውም ቦታ ላለማጋለጥ፣ ላለመናገር፣..” ከጁነዲን ጋር ከስምምነት ከደረሱ በኋላ ባለቤታቸው እንዲፈቱ መደረጉን አስታውቀዋል። በሙስና የተጨማለቁት አባዱላ ገመዳ እንዲሁም ደ/ፂዮንና ፀጋዬ በርሄ ከጁነዲን ጋር እንደተደራደሩ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።

በሳውድ አረቢያ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ውስጥ ዘረኝነትና ሙስና ተስፋፍቷል ተባለ

ታህሳስ ፲፰( አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከቆንስላው ባገኘው የውስጥ መረጃ በሃላፊነት ላይ የተመደቡት አምስቱ ዲፕሎማቶች በዘረኝነትና በሙስና ከመዘፈቃቸው ም በተጨማሪ ሊሴ ፓሴ ለማውጣት ወደ ቆንስላው የሚደውሉትን ስደተኞች በስብሰባ ሰበብ የሉም በማስባል ጉዳያቸውን እያስፈጸሙ እንደልሆነ ተመልክቷል። ከአንድ ወር በፊት ከ160 ሺ በላይ ህዝብ የተፈናቀለበትን ችግር ለማወቅ በቆንስላው የተገኙትና ከዲፕሎማቶች ውጭ ያሉ ሰራተኞችን ብቻ በመሰብሰብ ” የችግሩ ምንጭ ምንድነው በማለት?” የተወያዩት የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ ለዚህ ሁሉ ችግር መፈጠር መንስኤ በሆኑት ዲፕሎማቶች ላይ አፋጣኝ እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረው የነበረ ቢሆንም እስካሁን የወሰዱት እርምጃ አለመኖሩ ታውቋል።

“የመኖሪያ ፈቃድ የላችሁም” በሚል ምክንያት ኢትዮጵያውያን ከሳውድ አረቢያ እንዲወጡ ሲታዘዙ፣ ከዚህ ቀደም በቋሚነት ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ 24 የቆንስላው ሰራተኞችን የሚያግዙ በአገሪቱ የሚኖሩ 40 ድጋፍ ሰጪ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ህዳር 12 ቀን 2006 ዓም ለ3 ወራት በሚቆይ የኮንትራት ጊዜ ተቀጥረዋል። ከተቀጠሩት 40 ሰራተኞች መካከል 30 ዎቹ  ሰራተኞች የተቀጠሩት የዲፕሎማቶች የቅርብ ቤተሰቦችና ዘመዶች ናቸው። አብዛኞቹ ሰራተኞችም የተቀጠሩት የዘር ማንነታቸው እየታየ ሲሆን ከተቀጣሪዎቹ መካከል እንግሊዝኛ፣ አማርኛና አርበኛ ከማይናገሩት ጀምሮ ማስተርስ እና የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ይገኙበታል።

በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መንግስት እንዲታደጋቸው እየተማጸኑ ነው

ህሳስ ፲፰ አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዩኒቲ በሚባለው ግዛት ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያን በጦርነት አጣብቂኝ ውስጥ መገኘታቸውንና ህይወታቸው አደጋ ውስጥ መውደቁን ተናግረዋል።

በግዛቱ ውስጥ በአንድ የመንገድ ስራ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ 6 ኢትዮጵያውያን እንደተናገሩት በሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች መካከል የሚደረገውን የተኩስ ልውውጥ ለማምለጥ ያለፉትን ሁለት ቀናት በከባድ ማሽነሪዎች ውስጥ በመደበቅ ለማሳለፍ ተገደዋል። በአካባቢያቸው 2 ኢትዮጵያውያን መገደላቸውንና 3ቱ ደግሞ መቁሰላቸውን ተናግረዋል።

ትግሉ የሁሉንም ተሳትፎ የሚጠይቅበት ወሳኝ ምእራፍ ላይ ደርሷል


ራሱን የብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ብሎ የሚጠራው ድርጅት በከፍተኛ የፖለቲካ ኪሳራ ውስጥ ገብቷል። የህወሃትን ዙፋን ከመጠበቅ ባለፈ ምንም ሚና የሌላቸው የብአዴን አመራሮች ያለፉትን ሶስት ወራት በተለያዩ መንገዶች የድርጅቱን አባሎች ሲገመግም ከርመዋል። በግምገማዎች ላይ እንደተረጋገጠው ብአዴን የህወሀትን ዙፋን ሊሸከሙ የሚችሉ ወጣቶችን ኮትኩቶ ለማሳደግ አለመቻሉ ነው። በብአዴን ውስጥ ለሚታየው የውስጥ ትርምስ በድርጅቱ ውስጥ የሚገኙ የግንቦት7 አባላትና ደጋፊዎች እየተጫወቱት ያለው ሚና በሌሎች ድርጅቶች ውስጥ ላሉ የንቅናቄው አባላት ጥሩ ትምህርት የሚሰጥ ነው። የንቅናቄው አባሎችና ደጋፊዎች በድርጅቱ ውስጥ የታቀፉ ወጣቶችን የፖለቲካ ግንዛቤ ከማሳደግ ጀምሮ ፣ የንቅናቄውን መረብ እስከ ወረዳዎች በመዘርጋት ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ናቸው። ሰሞኑን በገሀድ በየግምገማዎች ላይ ሲነገር እንደነበረው ብአዴን እወክለዋለሁ ከሚለው የአማራ ህዝብ ሙሉ በሙሉ ተነጥሎ በአየር ላይ የተነሳፈፈ ድርጅት ሆኗል።
ይህን እውነታ ዘግይተው የተረዱት የብአዴን ዙፋን ጠባቂ አመራሮች የሚይዙትን የሚጨብጡትን በማጣት የተለያዩ ውሳኔዎችን እያሳለፉ ነው። ታማኝ የሚሉዋቸውን ካድሬዎች በየወረዳዎች በመላክ በግንቦት7 የሚጠረጠሩትን ወይም የግንቦት7 አባሎች ናቸው ተብለው ከሚገመቱ ሰዎች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት አላቸው ተብሎ የሚታሰቡትን ሰዎች በመያዝና በማሰቃየት ሌላው ወጣት ንቅናቄውን እንዳይቀላቀል ለማድረግ እቅድ ነድፈው ለመንቀሳቀስ አስበዋል።

Thursday, December 26, 2013

ረቡዕ ምሽት በመንፉሃ ዙሪያ መጠነ ሰፊ ጥብቅ ፍተሻ ተጀመረ!

ረቡዕ ምሽት በመንፉሃ ዙሪያ መጠነ ሰፊ ጥብቅ ፍተሻ ተጀመረ!

(ነቢዩ ሲራክ ከሳውዲ አረቢያ)
eth embassy saudi 1

ትንሽ ስለጃዋር መሀመድ

ትንሽ ስለጃዋር መሀመድ

ከዓለማየሁ መሀመድ

ሁለት ነገሮችን ላንሳ።

1.  የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ትግል መሬት አንቀጥቅጥ ሆኖ ለሁለት ዓመት ገደማ ዘልቋል። በዚህ ትግል ውስጥ በሀገር ቤት ከስርዓቱ ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው ደም ህይወታቸውን ገብረው ትግሉ በማይናወጥ ጽናት ላይ እንዲቆም ያደረጉት ብዙሃኑ ሙስሊሞች ዋጋቸው በክብር መዝገብ ላይ ምንጊዜም ወርቃማ በሆነ ቀለም ተመዝግቦ ይቀመጣል። ከእነሱ ባሻገር በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ትግሉ መሬት ይዞ  በሰከነ መልኩ እንዲጓዝ ያደረጉት አስተዋጽኦም የሚዘነጋ አይደለም። ጃዋር በዚህ ውስጥ ስሙ ሲጠቀስ ነበር። የሙስሊሞች ትግል ላይ ትንሽም ብትሆን አሻራው አርፎበታል። ያኔ ነው። በፊት። አሁንስ?Jawar Mohamed Muslim fundamentalist

2.  የኦሮሞ ህዝብ ጭቆና ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የተለየ ነው- አይደለም -የሚለው ክርክር ለጊዜው ይቆይና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ለ40 ዓመታት ሲያቀነቅነው የነበረውና ውጤት ሳይኖረው ዘመናት የቆየው ትግሉ አሁን ‘’የኦሮሞን ህዝብ ትግል በኢትዮጵያ ጥላ ስር’’ የሚለው ሀሳብ አሸንፎ ሲወጣ ጃዋር ብቅ አለ። መጀመሪያ ላይ በሳል በሆኑ፡ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ፡ የሰውን ልጅ በአንድ መነጽር የሚመለከቱ የሚመስሉ ሀሳቦች በጃዋር አፍ ውስጥ ይዋኙ ነበር። ይህም በተቀረው ኢትዮጵያውያን ዘንድም ጃዋር ምናልባት ያረጀውን የኦነግ ጠባብ ብሄርተኝነት ከመቃብር አስቀመጦ የኦሮሞን ህዝብ ከዕውነተኛ ድል የሚያቀርብ አዲስ መንገድ ይጀምራል የሚል ብጣቂ ተስፋ ውስጣቸው የነበሩ ጥቂቶች አልነበሩም። ከመነሻውም የተጠራጠሩት፡ የተደበቀው ማንነቱ አንድ ቀን ይወጣል ብለው በጥርጣሬ ሲመለከተቱት የነበሩት ቁጥራቸው የትየለሌ ነበር።

Monday, December 23, 2013

ከአቶ አያሌው መነሳት ጀርባ የአቶ ደመቀ ሚና

"የቆየ ቁጭትና ቁርሾ ነው"

ayalew n demeke


በአማራ ክልል የተካሄደውን ሹም ሽር ተከትሎ የተሰጠው ሹመትና የሹም ሽሩ አካሄድ መነጋጋሪያ ሆነ። “በቃኝ አሉ የተባሉትን ባለስልጣን አውርዶ እንደገና መሾም የተነቃበት የህወሃት የማረጋጊያ ጨዋታ ነች” ሲሉ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ተናገሩ። በሹም ሽሩ የአቶ ደመቀ መኮንን እጅ እንዳለበትና መንስዔውም “የቆየ ቁጭትና ቁርሾ” እንደሆነ ተጠቆመ።

በደም የተገነባ ተቋም የኢትዮጵያ አየር ኃይል (ለዳግመኛ ክህደት እንዳይዳረግ)


ግንቦት 83/91 ላይ የኢትዮጵያ ሰማይ ክፉኛ በሃዘን ሲመታ ፣ ደመናው ሲጠለሽ ፤ ወንዞች መደፈራረስ ሲጀምሩ ፤
የሰውን ልብ ባር ባር ሲለው …….. የክፉው ቀን ጅማሮ ፣ የውርደት ሃሌታ ፣ የሃገር አልባነት ስሜትና የዜግነት
ውርደት ደጃፍ ላይ መውደቃችን እውነት ነበር ።

የኢህአዴግ አዲሱ አሰላለፍ ፪ – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)


በድህረ-መለስ ኢትዮጵያ የፖለቲካው ሥልጣን በስርዓቱ ልሂቃን መካከል ከሚደረገው የኃይል መተናነቅ አንጻር፣ ዛሬም ከመፈራረቅ ጣጣው የተላቀቀ የማይመስልባቸው ምልክቶች መታየታቸው እንደቀጠለ ነው፡፡ ከአራት ወር በፊት በዚህ መፅሄት ላይ ‹‹አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ›› በሚል ባቀረብኩት ፅሁፍ በገዥው ፓርቲ ውስጥ ተፈጥሮ ከነበረው ክፍፍል የትኛው ቡድን የበለጠ ጉልበት አግኝቶ በአሸናፊነት መውጣት እንደቻለ ከገለፅኩ በኋላ ፅሁፉን የቋጨሁት እንዲህ በማለት ነበር፡- ‹‹የፓርቲው የታሪክ ድርሳን እንደሚነግረን ‹ይሆናሉ› የተባሉት ተቀልብሰው፣ ባልተጠበቁ ሁነቶች (የኃይል መገለባበጥ ተከስቶ) ፖለቲካው የሚመራበት አጋጣሚ ሊፈጠር የሚችልበት ዕድል ሊኖር እንደሚችልም መዘንጋት አያስፈልግም፡፡››
እነሆ በዚህ ፅሁፍ ደግሞ በቅርቡ በተጨባጭ የታዩትን አዳዲስ ኩነቶች እና ይህንኑ ተከትለው ሊመጡ ይችላሉ ብዬ የምገምታቸውን ‹የቢሆን ዕድሎች› (Scenarios) ለማየት እሞክራለሁ፡፡ 

Sunday, December 22, 2013

የመንግስት ሹማምንቶች ጅዳ ከተማ ውስጥ፡መሽገዋል ያሏቸው 80 ሺህ ኢትዮጵያውያን እጃቸውን በሰላም ካልሰጡ የመንፉሃው አይነት እልቂት እንደሚጠብቃቸው ሲያሞርቱ !

በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያነጣጠረው ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል !

=======================================================
በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ አንባሳደር ዘነበ ከበደ የሚመሩት የመንግስት ሹማምንቶች ጅዳ ከተማ ውስጥ፡መሽገዋል ያሏቸው 80 ሺህ ኢትዮጵያውያን እጃቸውን በሰላም ካልሰጡ የመንፉሃው አይነት እልቂት እንደሚጠብቃቸው ሲያሞርቱ ! ሪያድ በኢትዮጵያው አንባሳደር መሃመድ ሃሰን የሚመራው ቡድን የሚያሰማው « ጅብ ከሄድ ውሻ ጮህ ጥሪ » ድብቅ አጀንዳ ያለው መሆኑ ተገለጸ !

Friday, December 20, 2013

የኢህአዴግ መንግስት ሃላፊነት ስልጣን እየሰጠ እያወጣቸው ያሉ ባለስልጣናት በሙስና ለተጨማለቁት ነው

በመረጃው መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ በሙስና ተከሰው ጉዳያቸው እየተጣራ ከቆዩ የበላይ ባለስልጣኖች ውስጥ። ኩማ ደመቅሳና አለማዮህ ታፈሰ ክስ ህዳር 30/ 2006 አ/ም ያየው የወረዳው ፍርድ ቤት። ተከሳሽ ለሆነው አለማዮህ ታፈሰ ለ10 አመታት ፅኑ እስራት ፍርድ ሰጥቶ። ለኩማ ደመቅሳ በሌላ ቀን ቀጠሮ እንዲታይ በወሰነበት ግዜ። የፍርድ ውሳኔ የተሰጠው አለማዮህ የይግባኝ ጥያቄ በማቅረቡ። የወረዳው ፍርድ ቤት የወሰነውን በድጋሚ ያየው ምንም ነፃነት የሌለው የዞኑ ፍርድ ቤት። በላይኞቹ የስርአቱ ባለስልጣናት ውስጣዊ ትእዛዝና ተንኮል መሰረት። ወንጀሉ ኩማን እንዳይነካው በማለት ለተከሳሹ ነፃ ብሎ እንደለቀቀው ለማወቅ ተችለዋል፣

ሁለቱም ተከሳሾች ተከፋፍለው በልቶውታል ተብሎው የተከሰሱበት 70 ሚሊዮን የሚገመት ብር። ለተለያዩ የከተማው መሰረተ ልማቶች እንዲውል በማለት ከህዝብና ከሃገር ሃብት የተመደበው ባጀት።

‘ነውጥ አልባ ትግል’ – ጋዜጠኛ ኤልያስ ወንድሙ ስለ አዲሱ ዶክመንታሪ ፊልም ይናገራል – ሁሉም ሊያዩት የሚገባው

በአለም ዙርያ ተበታትነው ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከነ ጋንዲ ምን ይማራሉ? የሳውዲ አረቢያ መንግስት በዜጎቻችን ላይ እያደረሱ ያሉት ግፍና መከራን እንዴት መቋቋም ይቻላል? በሌሎችስ ላይ እንዳይደርስ እንዴት መከላከል ይቻላል? – ‘ነውጥ አልባ ትግል’ ለእነዚህና ሌሎች ተዛማች ጥያቄዎች ምላሽ አለው – ጋዜጠኛ ኤልያስ ወንድሙ ስለዚሁ አዲስ ዶክመንታሪ ፊልም ይናገራል። አስተናጋጁ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ነው።

Thursday, December 19, 2013

ከወያኔ ክፋትና እብሪት እንጂ ፍትህ አይጠበቅም

26351fb59e29fb0a1375427042
December 19, 2013
ወያኔ ባለፉት ሃያ ሁለት አመታት የአገራችንን የፍትህ ተቋሞች አንዴ አንደ ቂም መበቀያ ሌላ ግዜ ደግሞ እንደ ማጥቂያ መሳሪያ እየተጠቀመባቸዉ የፖለቲካ ተቀናቃኞቹንና ጥርስ የነከሰባቸዉን የህብረተሰብ አባላት እያሰረ፤ እያሳደደና እየገደለ ከርሞ ዛሬ ላይ ደርሷል። በተለይ ከግንቦት 1997ቱ ምርጫ በኋላ ወያኔ ብዕርና ወረቀት ይዘዉ በሃሳብና በአመክኖ የታገሉትን ሰላማዊ ዜጎች “ሽብርተኞች”፤ ድምጻችን ይሰማ ብለዉ የመብትና የነጻነት ጥያቄ አንግበዉ በሰላማዊ መንገድ የታገሉትን ኢትዮጵያዉያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ደግሞ “አክራሪዎች” እያለ ፍርድ ቤት በማቅረብ በፍትህ ተቋሞች በኩል የፖለቲካ ዉሳኔ በማሳለፍ ሠላማዊ ዜጎችን ለረጂም ግዜ እስርና እንግልት ዳርጓል።

ጎሰኝነት /የጎሳ ብሄርተኝነት ስነ ልቦና /the Psychology of Ethnic Nationalism

Aseged Tamene

ጎሰኝነት /የጎሳ ብሄርተኝነት ስነ ልቦና /the Psychology of Ethnic Nationalism

በጎሰኝነት የታጨቀ አስተሳሰብ የሰው ልጅ ህሊና በማሰወር ከሰውነት ደረጃ አውጥቶ ወደ አውሬነት በመቀየር ስብዕና የተላበሰ አስተሳሰብን ያጠፋል!!!
ጎሰኞች በአደባባይ እብደታቸውን የሚያሳዩበት ቀን ህዳር 29!!!

ምስጋና ለአያሌው ጎበዜ – አክባሪዎ አቢሲኒያዊ


እርስዎ ብዐዴን/ህወሀትን ወክለው የአማራን ህዝብ ሲመሩ መቆየትዎ ይታወቃል በዚህም የክልሉ ህዝብ ኤያሌው ጎበዜ ለዘላለም ይኑር እያለ እንዲኖር ማድረግዎትን የሚያስታውሱት ነው እርስዎ በጣም ያሳዘኑኝ ያ ወዳጅዎ ደመቀ መሬቱን ድንጋይ ያድርግለት እና በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ይገባሻል ብሎ መለስም ብራቮ እንዲህ ነው እንጂ ተላላኪ ብሎ ትምህርት ሚኒሰቴር ሲያደርገው ለእርስዎ ግን ቅንጣት ታህል አለመስጠቱ ሱዳኖች እንኴን እንዲታዘቡት አድርጔል፡፡

Wednesday, December 18, 2013

ከወያኔ ክፋትና እብሪት እንጂ ፍትህ አይጠበቅም

ወያኔ ባለፉት ሃያ ሁለት አመታት የአገራችንን የፍትህ ተቋሞች አንዴ አንደ ቂም መበቀያ ሌላ ግዜ ደግሞ እንደ ማጥቂያ መሳሪያ እየተጠቀመባቸዉ የፖለቲካ ተቀናቃኞቹንና ጥርስ የነከሰባቸዉን የህብረተሰብ አባላት እያሰረ፤ እያሳደደና እየገደለ ከርሞ ዛሬ ላይ ደርሷል። በተለይ ከግንቦት 1997ቱ ምርጫ በኋላ ወያኔ ብዕርና ወረቀት ይዘዉ በሃሳብና በአመክኖ የታገሉትን ሰላማዊ ዜጎች “ሽብርተኞች”፤ ድምጻችን ይሰማ ብለዉ የመብትና የነጻነት ጥያቄ አንግበዉ በሰላማዊ መንገድ የታገሉትን ኢትዮጵያዉያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ደግሞ “አክራሪዎች” እያለ ፍርድ ቤት በማቅረብ በፍትህ ተቋሞች በኩል የፖለቲካ ዉሳኔ በማሳለፍ ሠላማዊ ዜጎችን ለረጂም ግዜ እስርና እንግልት ዳርጓል።

ወያኔ ለኢትዮጵያና ለዜጎቿ ደንታ የሌለዉ እና ከስህተቱ የማይማር የግብዞችና የዘረኞች ስብስብ ስለሆነ አሁንም የአገሪቱን የፍትህ ተቋሞች እንደ ማጥቂያ መሳሪያ እየተጠቀመ የኢትዮጵያን ህዝብ በፍርሃት ጨለማ ዉስጥ ሸብቦ እየገዛ ለመኖር የቆረጠ ይመስላል።

Tuesday, December 17, 2013

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተመሰረተበትን አንደኛ አመት አስመልክቶ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ

Ginbot 7 Popular Force logo ታህሳስ 7  2006 ዓም የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከተመሰረተ  አንድ አመት ሞላው። አንድ አመት  በጭንቅና  በአሳር  ለተያዘች የዛሬይቱ ኢትዮጵያና ህዝቧ እጅግ ረጅም ግዜ እንደሆነ ህዝባዊ ሃይሉ በሚገባ  ይገነዘባል።

“ሕወሓት ከመለስ ሞት በኋላ እየተዳከመ ያለ ድርጅት ነው፤ ኢህአዴግ ለዘለዓለም መግዛት አለብኝ የሚል ድርጅት ነው” ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ

ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ ከህወሓት ጋር 17 ዓመታት በትግል ያሣለፉ እና ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዷ ነበሩ፡፡ በ1993 ዓ.ም ከፓርቲው ከተሰናበቱ አባላት አንደ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት የ“አረና” ፓርቲ አባል የሆኑት ወ/ሮ አረጋሽ በአጠቃላይ ጉዳዮች ዙሪያ ከ“ሎሚ” አዘጋጅ ቶማስ አያሌው ጋር ያደረጉት ቆይታ የመጀመሪያ ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-


ሎሚ፡- የኢህአዴግ ጭቆናና፣ አፈና፣ የተንሰራፈው በመላው ሀገሪቱ ነው የሚል አቋም ካላችሁ፣ ብሔር ተኮር ፓርቲ የመሰረታችሁበት ምክንያት ምንድነው;

Sunday, December 15, 2013

ሁለገብ-ገብ ትግል – ከኔልሰን ማንዴላ ጋር የምንጋራው የትግል ስትራቴጂ


ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄም በኔልሰን ማንዴላ ዜና እረፍት የተሰማውን ሐዘን በመግለጽ መግለጫ ያወጣ ቢሆንም የትግል ተሞክሯቸው ለአገራችን ስላለው ጠቀሜታ ተጨማሪ ቁም ነገሮችን ማንሳት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል።
ኔልሰን ማንዴላንና የትግል ጓዶቻቸው መሣሪያ እስከማንሳት ያደረሳቸው የደቡብ አፍሪቃ አፓርታይድ አገዛዝ ዋነኛው መገለጫው የባንቱስታን ሕግ ነበር። በዚህ ህግ መሠረት ደቡብ አፍሪቃ ዘርን መሠረት ያደረጉ አስር “ባንቱስታ” የተሰኙ “ራስ ገዝ” ግዛቶች ተቋቁመው ነበር። ያኔ በደቡብ አፍሪቃ አገዛዝ ሥር በነበሩ የደቡብ ምዕራብ ግዛቶች ደግሞ ሌላ አስር ባንቱስታዎች ነበሯቸው። በእያንዳንዱ ደቡብ አፍሪቃዊ መታወቂያ ባንቱስታው እንዲገልጽ ህጉ ያስገድዳል። የአንዱ ባንቱስታ ነዋሪ ያለልዩ ፈቃድ ወደሌላው ባንቱስታ መሄድ አይችልም። ከዚህም ሌላ ለነጮች ብቻ በተከለሉ ቦታዎች ጥቁሮች ለሥራ ካልሆነ በስተቀር ለሌላ ማናቸው ተግባር እንዳይገኙ ህጉ ያዛል። አፓርታይድ የደቡብ አፍሪቃ ዜጎችን በየዘር ክልሎቻው ውስጥ አጉሮ አገራቸውን እስር ቤታቸው እንዲሆን አደረገው። ይህንን ለመቃወም ኔልሰን ማንዴላ እና የወቅቱ ታጋዮች በመጀመሪያ ሰላማዊ ትግልን ሞከሩ፤ ያ አላዋጣ ሲል መሣሪያ አነሱ።
በአሁኑ ሰዓት ባንቱስታን መሰል የክልል አስተዳደር ያለው በአገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው። ልክ በአፓርታይድ ደቡብ አፍሪቃ እንደነበረው ሁሉ የኛም መታወቂያዎች ዘራችንና ክልላችንን ይገልፃል። በአፓርታይድ ደቡብ አፍሪቃ እንደነበረው ሁሉ እኛም ከክልላችን ውጭ ተንቀሳቅሰን መሥራትና መኖር አንችልም። ከቤንሻንጉል-ጉሙዝ እና ከደቡብ ክልሎች ተፈናቅለው ለጎዳና ኑሮ የተዳረጉት የአማራ አርሶ አደሮች የዚህ ፓሊሲ ሰለባዎች ናቸው።

ነጋሪቱም ተጎስሟል፤ፋኖም ተሠማርቷል !!!

           

ዛሬ ኢትዮጵያዊያን እያዩ ያሉት ውርደት ቃል የሚገልፀው አልሆነም። ኢትዮጵያ በታሪኳ ዛሬ እየደረሰ ያለ ዓይነት ውርደት ደርሶባት እንደሆነ በታሪክ የተመዘገበ ነገርም ተፈልጎ አልተገኘም። ይሄ ለኢትዮጵያዊያን የጨለማ ዘመን ነው። በኢትዮጵያ እንዲህ ስደትና እንግልት፤ ሃዘንና ዋይታ የበዛበት ዘመን ታይቶ አይታወቅም።
በዚህ ግዜ በኢትዮጵያችን መንግስት ነኝ እያለ ራሱን የሚጠራ ቡድን አለ።ይሄ ቡድን አገሪቷን ከተቆጣጠረ ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያ የገባችበት የውርደት አዘቅት ከባድ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በህወሃቶች አዝማችነት ተስምቶ የማይታወቅ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ግፍ በዜጎች ላይ ይፈፀማል። የተለየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸውን ሰዎች ይዘው ግብረ ሶዶም እንዲፈፀምባቸው ያደርጋሉ፤ ሴቶች ልጆችን በጋራ ሁነው ይደፍራሉ፤ በተቀደሱ ስፍራዎች ገብተው ቅዱሱን ስፍራ ያረክሳሉ፤ ዜጎችን ከእርሻ ማሳቸው አፈናቅለው በገዛ አገራቸው መፃተኛ ያደርጓቸዋል። በአጠቃላይ ዜጎች በአገራቸው ተስፋ አጥተው ሃዘንተኛ እንዲሆኑ ያደርጋሉ። ተስፋ የቆረጡ ዜጎች ኢትዮጵያ ውስጥ ከምኖር ሂጄ ብሞት ይሻለኛል ብለው እግራቸው በመራቸው መንገድ ይሰደዳሉ። በእንዲህ ሁኔታ ከኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ250ሺህ በላይ ወጣቶች ይሰደዳሉ።ገሚሱ በየበርሃው በውሃ ጥማት ወድቆ ይቀራል፤ ገሚሱም የባህር አዞ ቀለብ ሁኖ ዱካው ይጠፋል። ከሞት ተርፈው በየአርብ አገራቱ የደረሱ ዜጎች በሰው ልጆች ላይ ሊደርስ የማይገባ ወንጀል ይፈፀምባቸዋል።ባንዲራቸውን በአንገታቸው እንደጠመጠሙ ሬሳቸው ሜዳ ላይ ተጥሎ የአርብ መሳቂያ መሳለቂያ ይሆናሉ። በዚህ ሰሞን በሳውዲ ዓረቢያ እየተፈፀመ ያለው ግፍ ለኢትዮጵያዊያን ትልቅ ብሄራዊ ውርደት ሁኗል።

Saturday, December 14, 2013

አቶ ልደቱ ወደ ፖለቲካ ተመለሱ

አቶ ልደቱ ወደ ፖለቲካ ተመለሱኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቢሆንም ግን ፈተናውን ወድቋል የሚሉት አቶ ልደቱ አያሌው፤ የኢኮኖሚ እድገቱን መካድ ስህተት ነው፤ እድገቱ ዘላቂነት እንደሌለው አለመገንዘብም ስህተት ነው በማለት የኢዴፓ “ሦስተኛ አማራጭ” የተሰኘ የኢዴፓ አቋምን ይተነትናሉ፡፡ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች መዳከም አንዱ ምክንያት የመንግስት ተጽእኖ እንደሆነ አቶ ልደቱ ገልፀው፤ ነገር ግን ህዝቡን አሰባስቦ በመታገል የመንግስትን ተጽእኖ ማስቆምና ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡ ይልቅስ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ራሳቸውን ለመፈተሽና ስህተታቸውን ለማረም አለመዘጋጀታቸው ትልቅ እንቅፋት ሆኗል ይላሉ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ፣ በጭፍን ድጋፍና በጭፍን ተቃውሞ ለሁለት ስሜታዊ ጽንፎች ፖለቲካ እንደሰፈነ ጠቅሰው፤ ስር የሰደደውን የተሳሳተ የጽንፍ አስተሳሰብ በምክንያታዊ አስተሳሰብ በመተካት ሦስተኛ አማራጭ መያዙ ለአገሪቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ይላሉ፡፡

ኢህአዴግ ከብሔር “ተኮር” ተቃዋሚዎች ጋር ሊሸማገል ነው

ኢሳያስ ወደ ኢጋድ እየተሽኮረመሙ ነው

eprdf to reconcile


ኢህአዴግ በብሔርና በክልል ደረጃ ከተደራጁ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ለሚንቀሳቀሱት ቅድሚያ በመስጠት ለመደራደር የሚያስችለውን ቅድመ ሁኔታ በማመቻቸት ላይ መሆኑን የጎልጉል ምንጮች ገለጹ። ምንጮቹ እንደጠቆሙት ኢህአዴግ ለዚህ ተግባሩ ወዳጅ ጎረቤት አገሮችን፣ አንጋፋ የጎሳ መሪዎችንና ያፈገፈጉ የቀድሞ ተቃዋሚ መሪዎችን እየተጠቀመ ነው።

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ስለምኒሊክና ስለኢትዮጵያ


bulcha d


የአጼ ምኒሊክን መቶኛ የሙት አመት መከበር ምክንያት በማድረግ በ DW ሬድዮ በተደረገው ጥያቄና መልስ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፣ ዶ/ር ሓይሌ ላሬቦና ዶ/ር ሹመት ሲሳይ (የታሪክ ተመራማሪዎች) ቃለ መጠይቅ ተደርጎ በሚሰጠው መልስ ላይ ስለ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በተናገሩት ላይ አስተያየቴን አቀርባለሁ።

‘‘ፍርድ ሲዘገይ ሀገር እንደታሰረ መቆጠር አለበት’’ ተማም አባቡልጉ (የሕግ ጠበቃ)


Temam-Ababulgu

አቶ ተማም አባ ቡልጉ ከአዲስ ጉዳይ መጽሄት ቁጥር 128 ህዳር/2006 ዕትም ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ
አዲስ ጉዳይ፡ የሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ወደ ታህሳስ 3 ሲዛዋወር እንደ ጉዳዩ ዓቃቤነትዎ እንዲያውቁት ተደርገው ነበር?

Thursday, December 12, 2013

እምዬ ምኒልክ፡ የጥቁር ሕዝብ ኩራት!

ከነሐሴ 11 ቀን 1836 ዓ.ም. --

emiye menelikII

የጋምቤላ ክልል በህንድና በሳዑዲ ኩባንያዎች ላይ ዕርምጃ እንዲወሰድ ጠየቀ

የህንዱ ኩባንያ ‹‹ከቆመለት ዓላማ በተቃራኒ ከአካባቢው ደን ጣውላ በማምረት ሲያጓጉዝ በተጨባጭ ተይዟል››

timber log


የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት ሦስት የውጭ አገር ኩባንያዎች ከፍተኛ ችግር ታይቶባቸዋል፣ የፕሮጀክት አፈጻጸማቸውም ደካማ ነው በሚል የፌዴራል መንግሥት ዕርምጃ እንዲወስድ ጠየቀ፡፡
የክልሉ መንግሥት በቅርቡ ለግብርና ሚኒስቴር፣ በግልባጭ ደግሞ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በጻፈው ደብዳቤ የህንድ ኩባንያዎች የሆኑትን ካሩቱሪንና ቬርደንታ ሃርቨስት፣ እንዲሁም የሼክ መሐመድ አል አሙዲ ኩባንያ የሆነው ሳዑዲ ስታር የእርምትና የማስተካከያ ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቋል፡፡

“የወደፊቷ ደቡብ አፍሪካ ከማንዴላ ጋር መያያዟን እጠራጠራለሁ” ፕሬዚዳንት መንግሥቱ

ለማንዴላ የገንዘብ ድጋፍ ሰጥተናል፣ ታምመው አስታመናል

mengistu-hailemariam


የኔልሰን ማንዴላን ሕልፈት በማስመልከት አውስትራሊያ ከሚገኘው ኤቢኤስ ሬዲዮ የአማርኛ አገልግሎት ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡፡ መንግሥቱ ለሬዲዮው በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ በእሳቸው በትረ ሥልጣን ወቅት ማንዴላ የአገሪቱን ከፍተኛ የክብር ሽልማት ከመጎናፀፈቸውም ባሻገር፣ የአንድ መቶ ሺሕ ዶላር ገንዘብ ተበርክቶለቸዋል፡፡ ይህና ቀሪው ንግግራቸው እንዲህ ቀርቧል፡፡

Wednesday, December 11, 2013

በጅዳ ቆንስል በር ውላ የምታድረው እህት ክራሞት…

ነቢዩ ሲራክ

Ethiopian woman in Saudi Arabia, Jiddah Ethiopian embassy
ይህችን እህት በጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት በር ተቀምጣ ካየኋት ሳምንት አልፏል። አልፎ አልፎ ላነጋግራት ብሞክርም መልስ አትሰጥም። መጀመሪያ ያየኋት ቀን አካባቢ ከስራ ለተፈናቀሉ እህቶች አነሰም በዛ መጠለያ እያለ ፣ ለምን በር ላይ ትሆናለች? ብየ የጠየቅኳቸው የቆንስሉ ጸጥታ አስከባሪ “አንተየ የዚህች እህት ጉዳይ አስቸጋሪ ነው ።

Tuesday, December 10, 2013

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምን ይዋሻሉ? – ከዳዊት ሰለሞን

የአውሮፓ፣ የፓስፊክ፣የካሪቢያንና የአፍሪካ ፓርላማ አባላት ስብስባን ከሰሞኑ አዲስ አበባ ማስተናገዷ አይዘነጋም፡፡ በስብሰባው ለመካፈል በዛ ያሉ እንግዶች በከተማይቱ የሶስት ቀናት ቆይታ በማድረግ በአገሪቱ የፓለቲካ፣ የሰብአዊ መብት አያያዝና የሚዲያ ነጻነት ዙሪያ ከመንግስት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡ ዳዊት ሰለሞን ከእንግዶቹ ለኢትዮጵያ መንግስት ቀርበው ከነበሩ ጥያቄዎች መካከል አንዱን በመምዘዝ የተሰጣቸውን ምላሽ ያጠይቃል፡፡

በብሔር ፖለቲካ ሥር “የተቀበረው ፈንጂ”! – (ዳዊት ሰለሞን)

(ከዋለልኝ እስከ ህወሃት/ኢህአዴግ)

የብሔር ጥያቄ በኢትዮጵያ ምላሽ እንዳገኘ የሚያስተጋባው ኢህአዴግ “የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች” በዓልን ማክበር ከጀመረ ስምንት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በአንፃሩ “ተመልሷል” የተባለው ጥያቄ እንደተቀበረ ፈንጂ በየጊዜው በየቦታው እየፈነዳ በህይወት፣ በንብረትና በኢትዮጵያዊነት ላይ አደጋ ማድረሱን ዳዊት ሰለሞን ሁነቶችን በመጥቀስ ይሞግታል፡፡
ከአስርት አመታት በፊት
የኢትዮጵያ ተማሪዎች በለውጥ አብዮት ናፍቆት እየተናጡ ነው፡፡ እዚህም እዚያም በተፈጠሩ ቡድኖች የማርክሲስት-ሌኒንስት ፍልስፍናን የሚሰብኩ የርዕዮተ ዓለም ጽሁፎች ይነበባሉ፡፡ ተማሪው ይከራከራል፣ የሌኒኒዝም ፍልስፍና ቀለም ቀለም መሽተት ለጀመረው የ1960ዎቹ ትውልድ ልብ የቀረበ ሆኗል፡፡ ፍልስፍናውን በአገራቸው የፖለቲካ ግለት ለመተርጐም የቋመጡት ወጣቶች በሁለት ጠርዝ ተሰልፈው በኢትዮጵያ ያለው “የመደብ ወይስ የብሔር ጭቆና ነው” በሚል በጠረጴዛ ዙሪያ ይፋለማሉ፡፡
የብሔር ጭቆና በአገሪቱ መስፈኑን ለማሳመን ሽንጣቸውን ገትረው ይከራከሩ ከነበሩ ተማሪዎች መካከል የብዙዎችን ቀልብ ለመስረቅ የበቃው ዋለልኝ መኮንን በተማሪዎች መጽሔት “On the Question of Nationalities in Ethiopia” የሚል ጽሑፉን ማስነበብ ጀመረ፡፡ ዋለልኝ በጽሑፉ ኢትዮጵያ አንድ አገር ሳትሆን ብዛት ያላቸው ብሔሮች በአማራ የበላይነት ተጨፍልቀው የሚኖሩበት መሆኗን ሞገተ፡፡ የዋለልኝን መከራከሪያ የተቀበሉ ተማሪዎች የብሔር ጥያቄን ዋነኛ መፈክራቸው አድርገው አረፉት፡፡ በአገሪቱ የሰፈነው ጭቆና የመደብ መሆኑን በመግለጽ “አንዱን ብሔር ጨቋኝና ሌላውን ተጨቋኝ” በማድረግ የተነሱትን እነ ዋለልኝን የተቃወሙ ተማሪዎች የብሔር ጭቆናን በሚያስተጋቡ ተማሪዎች “የነፍጠኛ ልጆች” የሚል ተቀጥላ ተበጀላቸው፡፡

ተከብሮ ያላስከበረ ሕገ-መንግስት

ይድነቃቸው ከበደ
ህዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም ሕገ-መንግስቱ የፀደቀበት ቀን ነው፡፡ይህንንም ተከትሎ በመንግስት አሳሳቢነት እልፍ ሲልም አስገዳጅነት ህዳር 29 በየዓመቱ ከተለያዩ ጎሳ የተወጣጡ ሰዎች ተሰባስበው በመንግሰት ሹማምንቶች ፊት በአደባባይ ከበሮ የሚደለቅበት ቀን ነው፡፡ይሁን እንጂ የአብዛኛው ኢትዮጵያዊያን መልካም ፍቃድና ተሳትፎ ባልታየበት የፀደቀው ህገ መንግስት በብዙሃን ዘንድ ተቀባይነቱ ጥያቄ ውስጥ የገባ ነው፡፡በዚህም መሠረት ከቃሉ አጠቃቀም ጀምሮ እስከ አከባበሩ ክብረ በዓል አብዛኛዉ ሰው እኔንም ጨምሮ ግድ አይሰጠንም፡፡Ethiopian political commentator from Addis Ababa, Ethiopia. Ydnekachew Kebede
‹‹ይህ ህገ-መንግስቱን የመነዳ ተግባር ነው!!!›› ከገዢው መንግስት ተደጋግሞ የሚሰማ ለመፈረጅ ወይም ለመከሰስ የሚጠቀሙበት ቃል ነው፡፡ አንድ ወዳጄ እንዲህ አለኝ ‹‹ ይህ ህገ መንግሰት ዝም ብሎ የተደረደረ ብሎኬት ነው እንዴ የሚናደው ?›› በማለት ሲተች ሰምቸዋለው፡፡በመናድ እና ደግፎ በማቆየት ላይ የተመሠረተሁን  ህገ መንግስት እጅግ በጣም ብዙ ነገር ተብሎለታል፡፡
እየተንገዳገደ ያለው ህገ መንግስት ከአፀዳደቁ ጀምሮ የሚቀሩት ድንጋጌዎች መኖራቸው ለማንም ግልፅነው፡፡ ቢሆንም ፀድቆ በተግባር ላይ የሚገኘው ህገ መንግስት ዋጋ እንዳይኖረው እያደረገ ያለው የገዢው መንግስት አካሄድና ተግባር መሆኑ በአጭሩ ለማሳየት እሞክራለው፡፡

አቶ ሙሐመድ ኢብራሒም ማእከላዊ እስር ቤት ዉስጥ በደረሰባቸው ድብደባ ህይወታቸዉ ማለፉ፤ ሆድ-እቃቸዉ ተከፍቶ ኩላሊታቸዉ መሰረቁ ታወቀ

“አስክሬን ምንሊክ ሆስፒታል ሄደን እንድንወስድ ስልክ ተደወለልን፤ ለሞቱ ከደነገጥነዉ በላይ አስክሬኑን ስንመለከት ፍጹም ተረብሸናል፤ ከአዉሬ አፍ የተረፈ አስክሬን ነበር ሚመስለዉ…ሰዉነቱ ተቦጫጭቋል!” ጓደኞች

TPLF, EPRDF latest victimዋሽንግተን ዲሲ፤ ህዳር 30/2006 (ቢቢኤን) ፦ በአዲስ አበባ ዉስጥ በቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የነበሩት አቶ ሙሐመድ ኢብራሒም ቀደም ሲል በጥቅምት 4/2006 በአካባቢዉ ላይ ፈንድቶ ከነበረዉ ቦንብ ጋር በተያያዘ መልኩ ለምርመራ ማእከላዊ እስር ቤት መግባታቸዉ እና በማእከላዊ ቆይታቸዉ ምግብ እንዳይገባላቸዉ ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸዉ መከልከሉም ለማወቅ ተችሏል።
እንደ አቶ ሙሐመድ ጓደኛ አገላለጽ ግለሰቡ ለተጠረጠሩበት ወንጅል የሚያበቃቸዉ ጉዳይ ባይኖርም፤ከገቡበት ማእከላዊ እስር ቤት በደረሰባቸዉ ከፍተኛ ድብደባ በህይወት መዉጣት አልቻሉም።

ማንዴላን በተመለከት ለግማሽ ዓመታት የተደበቅ ምስጢር

ሻምበል ጉታ ዲንቃ የማንዴላን ህይወት ያተረፉ ጀግና

guta dinqa


ኔልሰን ማንዴላ የደቡብ አፍሪካ የፀረ-አፓርታይድ (የዘር-መድሎ) ተዋጊ አርበኛ መሆናቸው ይታወቃል። በደቡብ አፍሪካ ዘረኛ መንግስት ለእስር የተዳረጉት ኢትዮጵያ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው እንደተመለሱ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 1962 ዓም ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ኢትዮጵያ ፓስፖርት በመስጠት አጋርነቷን የገለፀች ብቸኛ ሀገር ነበረች።

በብሔር ፖለቲካ ሥር “የተቀበረው ፈንጂ”!

(ከዋለልኝ እስከ ህወሃት/ኢህአዴግ)

article 39


የብሔር ጥያቄ በኢትዮጵያ ምላሽ እንዳገኘ የሚያስተጋባው ኢህአዴግ “የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች” በዓልን ማክበር ከጀመረ ስምንት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በአንፃሩ “ተመልሷል” የተባለው ጥያቄ እንደተቀበረ ፈንጂ በየጊዜው በየቦታው እየፈነዳ በህይወት፣ በንብረትና በኢትዮጵያዊነት ላይ አደጋ ማድረሱን ዳዊት ሰለሞን ሁነቶችን በመጥቀስ ይሞግታል፡፡

Monday, December 9, 2013

ተከብሮ ያላስከበረ ሕገ-መንግስት …

(ይድነቃቸው ከበደ)

void


ህዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም ሕገ-መንግስቱ የፀደቀበት ቀን ነው፡፡ ይህንንም ተከትሎ በመንግስት አሳሳቢነት እልፍ ሲልም አስገዳጅነት ህዳር 29 በየዓመቱ ከተለያዩ ጎሳ የተወጣጡ ሰዎች ተሰባስበው በመንግሰት ሹማምንቶች ፊት በአደባባይ ከበሮ የሚደለቅበት ቀን ነው፡፡ ይሁን እንጂ የአብዛኛው ኢትዮጵያዊያን መልካም ፍቃድና ተሳትፎ ባልታየበት የፀደቀው ህገ መንግስት በብዙሃን ዘንድ ተቀባይነቱ ጥያቄ ውስጥ የገባ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ከቃሉ አጠቃቀም ጀምሮ እስከ አከባበሩ ክብረ በዓል አብዛኛዉ ሰው እኔንም ጨምሮ ግድ አይሰጠንም፡፡

Sunday, December 8, 2013

ተማሪዎች ‹‹የፍትህ ያለህ!›› እያሉ ነው!


ከ2005 አጋማሽ በኋላ የአወልያ ግቢን መሰረት ያደረገውንና 2004 ታህሳስ ወር የተጀመረውን የህዝበ ሙስሊሙን ተቃውሞ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መረከብ እንዳለባቸው የሚያስረዱ ጥሪዎች ከየአቅጣጫው ይሰሙ ጀመር፡፡ ይህ አስፈሪ አቅጣጫ ልቦናው ውስጥ ከፍተኛ ፍርሀት የፈጠረበት የኢህአዴግ መንግስት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በራሳቸው ጉዳይ (በሰላትና ሂጃብ ጉዳይ) እንዲጨናነከትሎ በጥር ወር 2005 መጀመሪያ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሊኖር የሚገባውን የቁ በማድረግ በህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞ እንዳይሳተፉ ለመግታት ማሰቡን ከአንድ ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣን የወጣ መረጃ አመለከተ፡፡ ይህን ውሳኔ ተአለባበስ፣ አመጋገብና አምልኮ ስነ-ስርአት አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር አውጥቶት የነበረውን ኢ-ህገ መንግስታዊ ረቂቅ ደንብ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በቀጥታ ተግባራዊ አደረገ፡፡ ይህ ገና በውይይት ላይ የሚገኝ ረቂቅ ደንብ ምንም እንኳ ሁሉንም የሃይማኖት ተከታዮች የሚመለከት ቢመስልም ቅሉ ግን ያነጣጠረው ድሮም በእናት አገሩ ኢትዮጵያ ፍዳውን እያየ በኖረው ሙስሊም ተማሪ ላይ ነበር፡፡ በውስጡም ሂጃብንና ሰላትን የሚገድቡ ህገ ወጥ ኢህአዴጋዊ ሴራዎች የተጎነጎኑበት ነበር፡፡

ወያኔ ቁጥርና ቀጠሮ አያውቅም

30ሺ አይሞሉም የተባሉት ስደተኞች ከ150ሺ በላይ ሆነዋል

ወያኔ እንደሚለው በየአመቱ ከ2ሚ. በላይ የስራ እድል ቢፈጠር፣ ከውጭ ሰራተኛ እናስመጣ ነበር፡፡
የአዲስ አበባ አስተዳደር ባለፈው ሳምንት ባሰራጨው ማስታወቂያ፣ በበርካታ አካባቢዎች ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሰኞ የውሃ አገልግሎት እንደሚቋረጥ ገልፆ ነበር፡፡ አዲስ መስመር ለማገናኘው ሦስት ቀን ሙሉ ውሃ ማቋረጥ፣ ግራ ያጋባል፡፡ ሁሉም ነገር ከተዘጋጀኮ፣ አዲሱን መስመር  በጥቂት ሰዓታት አገናኝቶ ሥራውን ማጠናቀቅ አያቅትም፡፡ ደግነቱ ቅዳሜ በቀጠሮው ውሃ አልጠፋም፡፡ እሁድ ግን ተቋረጠ። ሰኞና ማክሰኞም እንደዚያው፤ ረቡዕ  ሀሙስም… ትናንት አርብም አልመጣም፡፡ መንግስት ጋ ቀጠሮ አይሰራም፡፡ “የአገሪቱና የአህጉሪቱ መዲና” በምትባል ከተማ…ውሃ ከጠፋ ስድስት ቀን ተቆጠረ።

የመንግስት ወሮበላ ሚልዮነሮች ወይ ቢልዮነሮች እነማን ናቸው?


የኢትዮጵያ ‘ሚልዮነሮች’!አብረሃ ደስታ
ከአንድ መቶ ዘጠኝ ሺ በላይ ዜጎች ወደ አንድ ሀገር የሚሰደዱባት ሀገረ ኢትዮጵያ ባለ ብዙ ሚልዮነሮች ሆነች አሉን። ወጣት ዜጎቻችን ስደት የሚመርጡበት ምክንያት ምንድነው? እውን መንግስት እንደሚለን ‘ቸግሯቸው ሳይሆን ባቋራጭ ለመበልፀግ ፈልገው ነው’? ወይስ የወላጆቻቸው የማዳበርያ ዕዳ ተሰደው ሰርተው ለመክፈል ነው?

ከሳውዲ ተመላሽ ዜጎች ንብረታቸው በጉምሩክ እንደተወሰደባቸው ተናገሩ



ህገወጥ ናችሁ ተብለው ከሳውዲ አረቢያ ወደ አገራቸው የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን፤ ለበርካታ አመታት ለፍተን ያፈራነውን ንብረት ይዛችሁ መግባት አትችሉም ተብሎ ተነጥቀናል፡፡ የፍተሻ ሰራተኞች ሻንጣዎቻቸውን በመፈተሽ፣ ሞባይል ከአንድ በላይ ከያዙ ትርፉን በማስቀረት፣ አዳዲስ አልባሳት እና ኤሌክትሮኒክስ ቁሰቁሶች የተወሰኑትን ብቻ በመፍቀድ እና ያመጡትን ወርቆች ግራም በመቀነስ ንብረታቸውን እየወሰዱባቸው እንደሆነ ተመላሾቹ ገልፀዋል፡፡

Wednesday, December 4, 2013

ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወዳገራቸው የመመለስ ግዴታው የህወሃት/ኢህአዴግ ነው!

ኦባንግ ለቴድሮስ መልክት ላኩ

obang and tedros


ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን)
ኅዳር 23፣ 2006 ዓም
ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወዳገራቸው የመመለስ ግዴታው የህወሃት/ኢህአዴግ ነው!
ግልጽ ደብዳቤ ለሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ገ/የሱስ

ከሰማይ የራቀችው ምድር ከምድሪቱ የራቀው ሰማይ

(ሠዓሊ አምሣሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ethio saudi 16

Tuesday, December 3, 2013

የኢህአዴግ የድርድር ጥያቄና የግል እይታዬ – ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)

አንድ፣ ኢሳት ፣ ኢህአዴግን እና ግንቦት7ትን የተመለከተ ዘገባ ካቀረበ በሁዋላ አንዳንዶች ዜናውን ሲጠራጠሩት ተመልክቻለሁ፣ ያሽሟጠጡም አልታጡም። መጠራጠርም፣ ማሽሟጠጥም የሰውልጅ ባህሪ በመሆኑ አልገረመኝም። ትንሽ የገረመኝ አንዳንድ “ጋዜጠኞች” መረጃውን ካገኙ በሁዋላ በራሳቸው መንገድ አጣርተው ሀቁን ማውጣት ሲችሉ እነሱም እንደሌላው መልሱን በማንኪያ እንዲቀርብላቸው መፈለጋቸው ነው። ጋዜጠኛ “ጥቆማ” ከተሰጠው ተመራምሮ፣ የምርምር ስራውን ይጽፋል እንጅ እንደ አንባቢ መልሱ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብለት አይጠብቅም፣ ጥያቄ መጠየቅማ ማንም ይጠይቃል፣ ጋዜጠኛን ጋዜጠኛ ወይም ተመራማሪ የሚያደርገው ለጠየቀው ጥያቄ ላይ ታች ብሎ መልስ ማቅረብ ወይም በአሰባሰባቸው መረጃዎች ላይ ተንተርሶ ትንተና መስጠት ሲችል ነው ( በሁለተኛው መስፈርት መሰረት ተመስገን ደሳለኝን እና በእስር ላይ የሚገኘው ውብሸት ታየን አደንቃለሁ)።

የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄና ፈተናዎቹ በኢትዮጵያ

(ዳዊት ተሾመ)

Bridge


1. መግቢያ
ከደርግ የ17 አመታት የአገዛዝ ውደቀት በኋላ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች በስፋት ሲንጸባረቁ ከነበሩ ጥያቄዎች መካከል የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ ዋነኛው ነው:: በዚህ ወቅት ውስጥ ለብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ በፖለቲካ ኃይሎች የቀረቡት የመፍትሔ ሃሳቦች የተለያዩ ቢሆንም የመፍትሔ ሃሳቦቹ የሚመነጩት ግን በዋናነት ከሁለት ተገዳዳሪ አስተሳሰቦች ነው::

ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት የተደረገ ጽናታዊ ጉዞ፣ በሺዎች የሚቆጥሩ ተሳትፈዉበታል

የህወሃትን ማስፈራራትና ማፈራራት ችላ በማለት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ዛሬ ገና ጎሕ ሳይቀድ ወደ ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ተመሙ። የታሰሩትን የሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎችንና ሌሎችን የሕሊና እስረኞችን በመጠየቅ ህዝባዊ እንቢተኝነትንም አሳዩ።

Ethiopian Muslims on the way to Kilinto prison
ህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት በሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ በካንጋሮ ፍርድ ቤቱ ሊፈርድባቸዉ እያቅማማ ቢሆንም ዛሬ በነቂስ የወጣው ህዝብ “ዋ!.. በነርሱ ላይ መፍረድ በኛ ላይ መፍረድ ማለት ነዉ” በማለት ሰላማዊ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶታል።

የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)

Journalist Temasegan Dasalegአውሮፕላኑ ቅዳሜ ጠዋት ሶስት ሰዓት ላይ ድሬዳዋ አየር ማረፊያ ደርሶ ከተርሚናሉ ስወጣ፣ ተጠራጥሬ ሰዓቴን ተመለከትኩ፤ የድሬ የጠዋት ፀሐይ ከተለመደው ንዳዷ ጋር የአዲስ አበባን የቀትር መራራ ፀሀይን ታስከነዳለች፤ እናም አጥበርባሪ ጨረሯን ያለምህረት ስትለቅብኝ፣ ጓደኛዬ መኪና ይዞ እቦታው እስኪደርስ መጠበቁ በገዛ ፍቃድ መለብለብ ስለመሰለኝ፣ በቀጥታ ከተደረደሩት ታክሲዎች አንዱን ይዤ ወደ ከዚራ አመራሁ፤ ድሬ የሄድኩት በዋናነት ከማህበራዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ምክንያት በመሆኑ ሊቀበለኝ የተዘጋጀውን ጓደኛዬን ደውዬ ከማውቃቸው የአንዱን ሆቴል ስም ጠቅሼ እዚያ እንድንገናኝ ነገርኩት፡፡

የሆቴሉ ፍተሻ ከወትሮው ጠንከር፣ ጠጠር ያለ በመሆኑ ትዕግስትን ይፈትናል፡፡

Monday, December 2, 2013

አይ አበሻ! አበሻና ሆድ፤ ክፍል ሁለት (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም )

አበሻ ድግስ ይወዳል፤ ድግስ የሚወደው መብላትና ማብላት ስለሚወድ ነው፤ ለመብላት የአበሻ ምክንያቱ ብዙ ነው፤ ልጅ ተወለደ ብሎ መብላት ነው፤ ልጅ ክርስትና ተነሣ ብሎ መብላት ነው፤ ልጅ አገባ ብሎ መብላት ነው፤ ልጅ ሞተ ብሎ መብላት ነው፤ አበሻ ሰው ቀብሮ ሲመለስ በንፍሮ ይጀምርና ቀስ በቀስ ወደሌላው ይተላለፋል።

Prof. Mesfin Woldemariam
Prof. Mesfin Woldemariam
ሃይማኖትም ቢሆን ለመብላት ካልሆነ የነፍሱ ጉዳይማ በጣም ሩቅ ነው፤ ሕያዋን ለነገሥታት፣ ሙታን ለካህናት ይገብራሉ፤ በሚለው መመሪያ መሠረት
ግብር መቀበል ያለ ነው፤ ክርስቶስ ተወለደ መብላት ነው፤ ክርስቶስ ተጠመቀ መብላት ነው፤ ክርስቶስ ሞተና ተቀበረ መብላት ነው፤ ክርስቶስ ተነሣ መብላት ነው፤ ማርያም አረገች መብላት ነው።
ማኅበርም የሚጠጣው (የሚበላው ለማለት ነው፤) ለመብላት ነው፤ አምላክ በተለያዩ ስሞቹ፣ ቅድስት ማርያም በተለያዩ ስሞችዋ፣ መላእክት፣ ቅዱሳን፣ ሰማዕታት ሁሉ ለመብላትና ለማብላት ያገለግላሉ፤ ወደመንግሥተ ሰማያት ለመግባት አማላጅ ሊሆኑ የሚችሉ ሁሉ ማኅበር ለመብላት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፤ የሌሎች አገሮች ክርስቲያኖች በመብል አይመለሱም፤ ገበያቸው በጠገራ ብር ነው፤ ስለዚህም አብሮ መብላት ብሎ ነገር የለም።