Translate

Thursday, September 6, 2012

ዜና በጨዋታ፤ ኢህአዴግ መለስን ሳይተካ ስብሰባውን ቋጨ

Abe Tokchaw

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትላንት እና ከትላንት በስተያ በስብሰባ ተወጥሮ ነበር የዋለውና ያመሸው።
በርካቶች ከስብሰባው በኋላ ቀጣዩን የኢህአዴግ ሊቀመንበር ለማወቅ በጉጉት ሲጠብቁ ቢቆዩም ስራ አስፈፃሚው ግን ሊቀመንበሩን ሳይተካ ስብሰባውን ጨርሷል። ኢህአዴግ በድረ ገፁ ላይ የመሪውን ሹመት አስመልክቶ፤ “የተጓደለው አመራር በሚሰየምበት አቅጣጫ ዙሪያ…  የአመራር ምደባ ጉዳይ ለጋራ ዓላማ በሚደረግ ትግል ውስጥ አንድን ጓድ ይበልጥ መስዋዕት ይከፍል ዘንድ ከመመደብ ያለፈ ትርጉም የሌለው ቀላል ጉዳይ…” ሲል የገለፀው ሲሆን፤ በመስከረም የመጀመሪያው ሳምንት የኢህአዴግ ምክር ቤት በሚያደርገው ስብሰባ ላይ ሊቀመንበሩን እንደሚያሳውቅ አትቷል።

በነገራችን ላይ 1
በአቶ መለስ መሞት ሳቢያ፤ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የጦር ሃይሎች አዛዥ፣ የኢህአዴግ ሊቀመንበር፣ የህውሃት ሊቀመንበር እና ሌሎችም እኔ ደክሞኝ ወይም ረስቼ የተውኳቸው ቦታዎች ክፍት ሆነው እየጠበቁ ነው።
በነገራችን ላይ 2
በጋና ፕረዘዳንቱ አቶ ሚልስ የሞቱ ጊዜ ምክትላቸው ቃለ ማህላ ፈፅመው ቦታቸውን የተኩት ከቀብር በፊት ነበር። ምክንያቱን ስንጠረጥር በጋና ከቀብር ይልቅ ሀገር ይበልጣል! በኢትዮጵያስ…!? ተብሎ አይጠየቅም…!
በመጨረሻም፤
በአንድ ወቅት የኤርትራው ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የነበሩት አሊ አብዶ ሞቱ። አቶ ሲሳያስ እና ጓደኞቻቸውም ለእኒህ ሰው ትልቅ አክብሮት ነበራቸው አሉ። ለክብራቸው መገለጫም ሲሉ ለሁለት አመታት ያኽል ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳይሾሙ ቀሩ። አሁንም በነገራችን ላይ ለኤርትራ ቅርበት እንዳላቸው የሚነገርላቸው አቶ በረከት ስምዖን ምነውሳ ጠፉ…!? እስቲ በቅርብ የምታገኘቸው ጠይቁልኝ ይሄንን የኤርትራ ልምድ ለኛም ሀገር ይጠቀሙት ይሆንን!

No comments:

Post a Comment