ተፃፈ በወፉ
ሌላው አሰገራሚው የእርስዎ ስም ነው፡፡ ሃይለማሪያም የሚለው ምንም ይሁን ምን መለኮታዊ ሃልን ያስገባ ስም ነው፡፡ የመጀመሪያው የሃይለማሪያም ልጅ (የትልቁ ሃይለመሪያም ልጅ ትዝ ይበለዎት መንግስቱ )፣ ሃይለ ስላሴ(ተፈሪ) ሃይለ መለኮት እያለ የሚቀጥል ነው፡፡ እንኳን ሥዩመ እግዚአብሔር ተጨምሮበት ስማችሁ ውስጥ ሃይል አለና ጥንቃቄ ያሻዋል፡፡በርግጥ እግዚአብሔር ባይረዳዎት ይህንን ሁሉ ወያኔ ጥሰው ወደ ስልጣን ይመጣሉ የሚል ግምት የለኝምና የእርስዎም ሹመት በእግዚአብሄር ምርጫ ነው ብየ አምናለሁ፡፡እግዚአብሔር በረከት ስምዖንን ተጠቅሞ በረከት ሆኖለዎታል፡፡ በረከት ለኢትዮጲያ የጠቀመው አንዴ ጫካ ገብቶ በመሰቀዋትነትና በቁርጠኝነት ሲታገልና እርስዎን ወደ ዙፋን ግንባሩንና ሽንጡን ገትሮ ግንባሩን ሲዋጋ ነው፡፡ በረከት ዙፋን አረጋጊና አንጋሽ ነው፡፡ መለስ ስልጣኑ እንዲረጋ በ1993 ቆራጥ እርምጃ ወስዷል አሁን ደግሞ ሃይለማሪያምን ወደ ስልጣን አምጥቷል፡፡ በረከት king maker ነው፡፡
ጥያቄው በመለኮታዊ ሃይል የተሸሙት እርስዎ ሃይለ ኢህአዴግ ወይስ ሃይለ መለኮት (ማሪያም) መሆን ይፈልጉ ይሆን? ሃይለ ማሪያም ሆይ ሃይል ይቀንሱና እንደ ድሮው (ምናልባት) ለሃያሉ እግዚአብሔር እየተገዙ እንደ እርስዎ ለስልጣኑ አዲስ ለሆኑት ለሶማሌው አቻዎት እንደመከሩት የተሰጠዎትን ጊዜ ሳያባክኑ ይግዙን፡፡
ከዚሁ ጋር ሳልረሳ አንድ ነገር ልምከረዎ፡፡ ጉዙፍ ሳይሆኑ ብመክረዎ ይሰሙኛል፡፡ መለስ መጀመሪያ የትህትና ቆዳ ለብሶ ( ትህትና የተባለውን ተኩላ ቆዳውን ለብሶት )ነበርና ከልምዴ ነው የማወጋዎት፡፡ ከገዘፉ በኋላ አይታወቅምና ምክሬ የቱን አስተሳሰብ ሊከተሉ ነው? አብዮታዊ ዴሞክራሲ ወይስ እንደስምዎ በመለኮታዊ ሃይል እየታገዙ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ለመፈፀም ሁሉንም እያሳተፉ ወይንም ሃሉን፣ ማሪያምን፣ ደሳለኝን ሆነው በማሳተፍ (ሱታፌ የሚበዛበት) መድብለ ፓርቲ ሊያቃቃሙ አሰቡ?
አብዮታዊ ዴሞክራሲ የአመጽ ዴሞክራሲ (በዴሞክራሲ ላይ ያመፀ ዴሞክራሲ) ይመስላልል በኢትዮጲያ የተያዘው፡፡ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ እንደሚያውቁት ሁሉ፡
- ቅጥ አምባሩ የጠፋ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ፣
- አምባ ገነናዊ ስርዐትና ስብዕና ግንባታ፣
- ጨቛኝ ፣አፋኝ ስርዓትን ግንባታ እና ዘረኛ ጅረት የሚፈስበት መንገድ፣
- ከድጡ ወደ ማጡ የመጣንበትን አሰተሳሰበ መለስ ነው ያተረፍነው፡፡
በሃይማኖታዊ ፀሎት ውስጥ
- የሰው ክቡርነት (እኩልነት፣ዴሞክራሲ፣ የዜጎች ልዕልና)
- ፈርሃ እግዚአብሔር (ትህትና፣ ቅድሰና)
- እርቀ ሰላምና ወይይት( ብሔራዊ እና የፖለቲካ ልሂቃን እርቅም እዚህ ጋ ይገባል)
- እንደርስዎ( የሰማሁትን ነው) ከሙስና የጸዳ ተቛምና ግለሰብ ይወጣሉ፡፡ አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግስት ፈልጉ …ይላልና አስቀድመው በፈጣሪዎ እግዚአብሄር መመሪያ ይዠዎታለሁ (በህገ አምላክ እንዲሉ) በልብዎ ውስጥ ሃይማኖታዊ ፀሎት ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ ይቅደም!
ተፃፈ በወፉ9/18/2012
No comments:
Post a Comment