Translate

Friday, September 7, 2012

አስገራሚው የመለስ ዘመዶች (ኤርትራውያን) መልእክት

meles zenawi's relatives from Eritrea
ትርጉም ኢየሩሳሌም አርአያ
የሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ ስጋ ዘመድ የሆኑ ኤርትራውያን የጋራ “ሃዘን መግለጫ “በአይጋ ፎረም በኩል አስተላልፈዋል።
“የምናፈቅረው ወንድማችን እና ልጃችን “ሲሉ የገለጿቸውን መለስ ዜናዊ “ቅዱስ” በማለትም እነዚሁ ኤርትራውያን አሞኳሽተዋቸዋል ።እነዚህ ወገኖች መለስ ከኢትዮጵያ አልፈውለአፍሪካ “ሰሩ” ያሉትን አሳፋሪ ትንተና ለመስጠት ከመከጀላቸው ባሻገር ኢትዮጵያውያን የመለስን መንገድ መከተል አለባችሁ ሲሉ ሊያሳስቡ ሞክረዋል። ይህንን መግለጫ ያወጡት የመለስ ወላጅ እናት የሟቿ ወይዘሮ አለማሽ ገብረልኡል ቤተሰቦች ናቸው ።የሚገርመው የመለስ አያቶች በእናቱም በአባቱም ደጃዝማቾች ሲሆኑ የባለቤቱ አዜብ መስፍን አያት እንዲሁ ደጃዝማች ናቸው ።መለስ ብዙ ጊዜ ፊውዳሊዝምን ሲቃወሙ ይደመጡ እንጂ በእርግጥም የተጠናወታቸው እና እስከ ህልፈተ ሞታቸው ያራምዱት የነበረው መስመር የፊውዳል ስርአት ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው ።
አስገራሚውን “መግለጫ “እንደሚከተለው ተተርጉሞአል።

“የሃዘን ማፅናኛ መግለጫ “
“በኤርትራ ምድር እና በመላው አለም የምንገኝ የደጃዝማች ገብረልኡል ተስፋማርያም እና የአቶ ካህሱ መላ ቤተሰቦች የሆንን፤
በሞት በተለየን በምናፈቅረው፣ልጃችን እና ወንድማችን፣የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ የተሰማን መሪር ሃዘን እየገለጽን ፤ለዘመዶቹ ለቤተሰቡ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጽናቱን ይስጠን እንላለን።
አቶ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ እና አፍሪካ ታሪክ ርሃብን ከሰፊው ህዝብ ለመንቀል ፣የታመመው እንዲፈወስ ፣መሃይሙ እንዲማር፣መብቱ የተገሰሰው ፍትህ እና ነጻነት እንዲከበርለት እና እንዲረጋገጥለት ፣ለአንድ ቀን እና ሰአት ሳያርፍ እና እፎይ ሳይል ፣ተወዳዳሪ የሌለው ዘላለማዊ የታሪክ ሃውልት ማኖሩ ፣ለህዝቡ እና ለቤተሰቡ የማይረሳ የድል ችቦ ፣የማይናድ ቅርስ ፣የማይጠፋ መብራት ፣ተጠብቆ የሚኖር ዘላለማዊ ክብር ፣. . . . ወዘተ ትቶ በማለፉ ፣የተሰማንን ትልቅ ኩራት እየገለጽን ፤በተለይ ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ ህዝብ በተለይም ደግሞ ለመላው ቤተሰቡ የጀመረውን ስራ ሳይጨርስ ፣ገና በ57 አመት እድሜው ማለፉ ሃዘናችንን ጥልቅ መሪር እና በጣም ከባድ ሸክም አድርጎታል።
አቶ መለስ ዜናዊ እድሜውን ሙሉ ሲያከናውነው የቆየው ፣መልካም እና የተቀደሰ ተግባራት ባይኖር ያለምንም ማጋነን እና አድሎ የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት አሁን ላለበት ደረጃ ሊበቃ እንደማይችል በማመን ፣እርሱ የጀመረው ወደር የሌለው የአገር እና ህዝብ ግንባታ አጠናክረው እንደሚገፉበት እና እንደሚያጎለብቱት ያለንን እምነት እና ተስፋ በዚህ አጋጣሚ እንገልጻለን ።ለአቶ መለስ ደግሞ ያንን ሁሉ የህዝብ እና ቤተሰቡ ጸሎት እና መሪር ሃዘን ፈጣሪ አምላክ ሰምቶለት በመንግስተ ሰማያት ያኑረው ።
ከወይዘሮ አለማሽ ገብረሉልኡል ቤተሰቦች

No comments:

Post a Comment