ነቢዩ ሲራክ
የጠ/ሚኒስትር መለስን ሞት ተከትሎ ያነጋገርኳቸው እዚህ ሳውዲ አረቢያና በተለያዩ አረብ ሃገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸውልኛል፡፡ በተለይም በትናንትናው እለት በጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ውስጥ በሚገኘው የጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት አዳራሽ በተቀመጠው የሃዘን መገለጫ ሲያስቀምጡ ያገኘኋቸው ኢትዮያውያን የተሰማቸውን ሃዘን ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትሩን ነብስ ይማር ከማለት ባለፈ በስልጣን ዘመናቸው በአርረ ሀገር ስደት ባለነው ከመቶ ሽዎች የምንቆጠር ኢትዮጵያውያን ላይ በመንግስት ተወካዮች እየደረሰብን ያለውን የአስተዳደር በደልና የመብት ጥበቃ ጉድለት አንጻር አስተዳደራቸው የሰመረ ነው ለማለት እንደማይችሉ በመጠቆም ለደህንነታቸው ሲባል በድምጽ አስተያታቸውን ለመስጠት የተቆጠቡ አንዳንድ ነዋሪዎችም አጋጥመውኛል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ቆስንሉ ባስተላለፈው ጥሪ መሰረት የስንብት ስነስራቱ ለመከታተል ዛሬ ማለዳ በቆንስሉ ጽህፈት ቤት ብገኝም ወደ አዳራሹ እንዳልገባ የጸጥታ ሃላፊዎች የእገዳ ጥብቅ ትዕዛዝ መተላለፉን ገለጸውልኛል፡፡
ከጸጥታ አስከባሪዎች አንዱ ወንድምም ” የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት እንደተሰማ ለምን መጥተህ አልዘገብክም?” በማለት ላቀረቡልኝ ጥያቄ በጊዜው በአካባቢው አለመኖሬን ባስረዳቸውም መልሴ አሳማኝ እንዳልሆነ በመግለጽ ከዚህ በፊት በራዲዮው የማቀርባቸው ዘገባዎች ሚዛናዊ እንዳልሆኑ ሃይለ ቃል በማከል ተነግረውኛል፡፡ ይሁንና እገዳውን የጣለው እንዲነገሩኝ በተደጋጋሚ ላቀረብኩት ጥያቄ ስነ ስርአቱ ሲጠናቀቅ መጠየቅ እንደምችል በመግለጽ እኒሁ በኢሕአዴግ ደጋፊነታቸው የሚታወቁት የጸጥታ አስከባሪ ክችም ያለ መልስ ሰጥተውኛል፡፡ ከሳምንት በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ ” ለምን ለቅሶውን አልዘገብክም ?” በሚል “ተቃዋሚ የግንቦት አባል ነህ !” ከሚል ውንጀላ ጀምሮ ” እርምጃ ይወሰድብሃል ! ” እስከሚል ማስጠንቀቂያ የደረሰኝ መሆኑን በመንግስት ደጋርፊዎች በኩል ደርሶኝ ነበር፡፡
No comments:
Post a Comment