Translate

Saturday, September 1, 2012

የውህደት መግለጫ፣ ከግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እና የኢትዮጵያ አንድነትና የፍትህ ንቅናቄ የተሰጠ የውህደት መግለጫ


የውህደት መግለጫ፣ ከግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እና የኢትዮጵያ አንድነትና የፍትህ ንቅናቄ የተሰጠ የውህደት መግለጫ

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እና የኢትዮጵያ አንድነትና የፍትህ ንቅናቄ :-
1. ተመሳሳይ ራዕዮች፣ ተልዕኮዎችና ግቦች ያሏቸው መሆኑ በመረጋገጡ፤
2. ተመሳሳይ የትግል ስልቶችን የሚጠቀሙ በመሆኑ፤
3. በአደረጃጀትም ሆነ በድርጅታዊ የሥራ ባህል በጣም የተቀራረቡ በመሆናቸው፤
4. በጥምረት ለነፃነት፣ለእኩልነት (ጥምረት) ውስጥ በትብብር በመሥራት በመካከላቸው ያለው የመተማመን መጠን በከፍተኛ ደረጃ በማዳበራቸው፤ እና
5. ይህ የውህደት ውሳኔ የሁለቱም ድርጅቶች መተዳደሪያ ደንቦች በሚደነግጉት መሠረት ለየድርጅቶቹ ከፍተኛ ውሳኔ ሰጭ አካላት ቀርቦ ሙሉ ተቀባይነት በማግኘቱ፤
ከዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 23 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ ሁለቱ ድርጅቶች፣ ማለትም
• ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ እና
• የኢትዮጵያ አንድነትና የፍትህ ንቅናቄ
ተዋህደዋል።
• የተዋሃደው ድርጅት “ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ” (በአጭሩ “ግንቦት 7”) ተብሎ እንዲጠራና የግንቦት7ን ዓርማና መተዳደሪያ ደንብ እንዲጠቀም ተስማምተዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ማክሰኞ ነሐሴ 23 ቀን 2004 ዓ.ም.

No comments:

Post a Comment