Translate
Thursday, July 30, 2015
ኦባማ በአዲስ አበባ
ይገረም አለሙ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በአዲስ አበባ ጉብኝታቸው ከጠቅላይ ምኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ጋር በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት በሰላማዊ ምርጫ የተመረጠ ብለዋል በሚል ከተለያየ አቅጣጫ ተቃውሞና ነቀፌታ እየተሰነዘረባቸው ነው፡፡ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ባደረጉት ንግግር ምርጫው በሰላማዊ ሁኔታ ተካሂዷል ይህ ማለት ግን ዴሞክራሲያዊ ነው ማለት አንዳልሆነ ከአቶ ኃይለማሪያም ጋር መነጋገራቸውን ስም ጠቅሰው ተናግረዋል፡ ምርጫ ግዜ እየጠበቁ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ነጻና ፍትሀዊ መሆን አንዳለበትም አስረግጠው ገልጸዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረቱ ንግግራቸው እስካሁን ተቃውሞ አልተሰማበትም፡፡
የዚህች ጽሁፍ አላማ ኦባማ ስለተናገሩት ማውሳት አይደለም፤በተለይ ሀገር ቤት ያሉ ተቀዋሚዎች ሰላማዊ ምርጫ የሚለውን አገላለጽ ሲቃወሙ አንድም ትናንትን የረሱ ሁለትም በሚቃወሙት ድርጊት ውስጥ የእነርሱ ድርሻ መኖሩን ያልተገነዘቡ ሆኖ ስለተሰማኝ ይህን ለማመለከት ነው፡፡ ትናንትን መርሳትና ራስን ነጻ አድርጎ ሌላውን መውቀስና መኮነን ስር የሰደደ ችግራችን ነው፡፡ ከዚህ መላቀቅ ካልቻልን ደግሞ ለውጥ ናፋቂ ሆነን መኖራችን አይቀሬ ነው፡፡
Thursday, July 23, 2015
ህወሓት በፈጠራቸው ድርጅቶች ውስጥ ተኩኖ ህወሓትን ማዳከም አርበኝነት ነው!
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ለኢህአዴግ እና አጋር ድርጅቶቹ አባላት የሚከተለው መልዕክት ማስተላለፍ ይሻል።
Tuesday, July 21, 2015
የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጉዞ… (ክንፉ አሰፋ)
ክንፉ አሰፋ
“…ከዚህ በኋላ ህዝብ ሰብስቦ ማውራት ላቆም ነው። ጊዜው ተቀይሯል። ትግል ለደካማ መንፈስ አይሆንም። ትግል መውደቅን ይጠይቃል። ሲወድቁ ግን ለመነሳት መሞከርን ይጠይቃል። ስንወድቅ ልታዩን ትችላላችሁ ስንነሳ ግን ታዩናላችሁ … ” ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ይህንን የተናገሩት የአስመራ ጉዟቸው ከመሰማቱ ጥቂት ቀናት በፊት ነበር። ንግግሩ ለብዙዎች ግርታ መፍጠሩ አልቀረም። ከቀናት በኋላ የኤርትራን ምድር ሲረግጡ “ስንነሳ ግን ታዩናላችሁ…” ማለታቸው ግልጽ ሆነ።
ከምርጫ 97 በፊት ዶ/ር ብርሃኑ በፖለቲካ ስብእናቸው የሚታወቁት ለሰላማዊ ትግል ባላቸው የከረረ አቋም ነበር። በእስር ቤት ሆነው በጻፉት “የነጻነት ጎሕ ሲቀድ፤ …” መጽሐፋቸው ሰላማዊ ትግል ያለውን የሞራል፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ የበላይነት ምሳሌ እያስቀመጡ ዘርዝረዋል።
ለዚህም ነበር ከሰላማዊ ትግል ወጥተው “ሁለገብ ትግል” ለማካሄድ ማቀዳቸውን ሲገልጹ ለብዙዎች ድንገተኛ እና አስደንጋጭ የሆነው። የጦርነትን አስከፊ ገጽታ ሲነግሩን የነበሩ እኝህ ምሁር በአንድ ግዜ ወደ ተቃራኒው የትግል ስልት ሲዞሩ ያቀርቡት የነበረው ምክንያት በወቅቱ ብዙዎችን ሊያሳምን አልቻለም። ምክንያቱም አመጽ ወይንም ጦርነት ከባድ ነገር ነው። ገንዘብ እና ግዜን ይበላል። ከሁሉም በላይ የህይወት መስዋእነትን ይጠይቃል። የሰላማዊ ትግሉ ስልቶች ገና በደንብ አልተፈተሹም የሚሉም ጥቂቶች አልነበሩም።
Sunday, July 19, 2015
ሊቀመንበራችን ትግል ሜዳ ውስጥ ነው!- መግለጫ
ሊቀመንበራችን ትግል ሜዳ ውስጥ ነው!- መግለጫ
ሐምሌ 12 2007 ዓ.ም.
ህወሓት በኢትዮጵያዊያን እና በኢትዮጵያ ላይ ያሰፈነው ዘረኛና ፋሽስታዊ አገዛዝ እንዲያበቃ፤ በምትኩም ፍትህ፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሰፈኑበት የፓለቲካና የኢኮኖሚ ሥርዓት እንዲመሠረት እና የሀገራችን አንድነት በጠንካራ መሠረት ላይ ለማኖር አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ተገዶ የገባበት የመረረ የአመጽ ትግል መጀመሩን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያዊያን የነፃነት አርበኞች በጀግነትና በጽናት እየታገሉ ነው።
ይህ ትግል በባርነትና በነፃነት መካከል የሚደረግ ወሳኝ ትግል ነው። የዚህ ትግል ውጤት የእኛ የዚህ ዘመን ትውልድ ሕይወት ብቻ ሳይሆን የአገራችንን የወደፊት ታሪክ፤ የልጅ ልጆቻችንን ሕይወት ይወስናል። በዚህም ምክንያት ይህንን ትግል በድል መወጣት ግዴታችን ነው። በዚህ ወሳኝ ወቅት ለነፃነት ግድ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከጎናችን ሊቆም ይገባል።
Thursday, July 16, 2015
ፍርድ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ወሰነ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ወሰነ፡፡ የፌደራል አቃቤ ህግ ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር በአካል ተገናኝታችኋል›› የሚል ክስ የመሰረተባቸው ተከሳሾቹ ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር ተገናኝታችኋል ከተባለ አቶ አንዳርጋቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ታስረው የሚገኙ በመሆናቸው መከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ይታዘዝልን›› የሚል ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡
የፌደራል አቃቤ ህግ በበኩሉ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ እና በእነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ መዝገብ ላይ ክስ ቀርቦባቸው በእድሜ ልክና በሞት እንዲቀጡ ተወስኖባቸው የህዝባዊ መብታቸው የተሻረ በመሆኑ በምስክርነት ሊቀርቡ አይችሉም ብሎ ተቃውሟል፡፡ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ህዝባዊ መብት በመሻሩ ለፍርድ ስራ ልዩ አዋቂ ወይንም ነባሪ ሆነው መስራት አይችሉም ያለው የፌደራል አቃቤ ህግ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በተጨማሪ ምስክርነት ቀርበው መመስከር አይገባቸውም ሲል የተከሳሾቹ ጥያቄ ውድቅ እንዲሆን ለፍርድ ቤቱ አመልክቶ ነበር፡፡
Wednesday, July 15, 2015
አሻራ መጽሄት – ቁጥር 2 (ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም፣ ጸጋዬ ገብረመድህን አርአያ፣ ዩሱፍ ያሲን፣ ደረጀ ደስታ…)
– ጸጋዬ ገመዴህን አርአያ – “ጠፍአት አገርነ” ትናንት ማታ ጨረቃዋንም አዋልደናል!
– ዩሱፍ ያሲን – የአረቡ ዓለም መቆራቆስ ቀይ ባህርን ይሸጋገር ይሆን?
– ደረጀ ደስታ – ቆም በል! ህዝብ ከሚያልቅ ህዝብ ቢያልቅ ይሻላል!
– ቆይታ ከፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ጋር እና ሌሎችም…
Subscribe to:
Posts (Atom)