information for ethiopia
Translate
Saturday, December 16, 2017
የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ የሽግግር መንግስት ሰነድ ማዘጋጀቱን ገለጸ
አባይ ሚዲያ ዜና
ናትናኤል ኃይለማርያም
የኢትዮጵያን ጉዳይ አስመልክቶ በአውሮፓ ፓርላማ የተጠራ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ አመራሮች በቦታው በመገኘት ኢትዮጵያ አሁን ስለገጠማት ፈታኝ እና አስፈሪ ጉዳዮች በማንሳት ሰፊ ማብራሪያ መስጠታቸውን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለኢሳት በሰጡት ቃለ መጠይቅ ለማወቅ ተችሏል።
Read more »
Wednesday, December 13, 2017
ከ424 ዜጎች ጭፍጨፋ፤ ከ14 ዓመት መሬት ነጠቃ በኋላ የጋምቤላ “ኢንቨስትመንት” 9ቢሊዮን ብር ያህል ከስሯል
ጋምቤላን በረሃ አድርጎ፤ ሕዝቧን ገድሎ፤ በተለይ የአንድ ክልል “ዜጎችን” ብቻ ጠቅሞ በጋምቤላ የተተገበረው “ኢንቨስትመንት” ዘጠኝ ቢሊዮን ብር ያህል የማይከፈል ዕዳ ውስጥ መዘፈቁን ህወሓት/ኢህአዴግ አመነ።
Read more »
“እንጨርሳቸው፤ አንድም አኙዋክ መትረፍ የለበትም”
እነዚህም የህወሓት ነፍሰበላዎች ይፈለጋሉ!
የሰላም ሰዎች የሆኑት አኙዋኮች ከህወሓት ጋር መቃቃር ውስጥ የገቡት ገና ከጅምሩ ነበር። የቀድሞው የአኙዋክ ምክርቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ኦባንግ ሜቶ እንደሚሉት ችግሩ የተያያዘው ህወሓት የጋምቤላን ለም ምድር የራሱ ለማድረግ ከመፈለጉ ጋር ነው። ህወሓት ሥልጣን ላይ እንደተቆናጠጠ የጋምቤላን ብቸኛ ጄኔሬተር በመንቀል ከመውሰድ አልፎ በአሎሮ ግድብ ላይ የነበሩትን ወደ 400 የሚሆኑ ማሽነሪዎች እና የእርሻ መሣሪዎች በምሽት ወደ ትግራይ ነቅሎ ወስዷል ይላሉ አቶ ኦባንግ። በመቀጠልም ተዝቆ የማያልቀውን የጋምቤላን ድንቅ ሃብት በረኸኞቹ ህወሃቶች ለመዝረፍ ውሳኔያቸው
አደረጉ
።
Read more »
የተማሪዎች ዓመጽና የየአካባቢው አጫጭር መረጃዎች
አክሱም ዩኒቨርሲቲ
አክሱም ዩኒቨርሲቲ በየግማሽ ቀኑ ሲነሳና ሲበርድ ነው የሰነበተው። በካፌ ሰዓት ብዙ ጊዜ ድንጋይ ይወረወራል። ማምሻውን በራት ሰዓት በተፈጠረው ብጥብጥ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባትና መውጣት አይቻልም ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ቤተሰቦቻቸው ቢሔዱም እስካሁን መውጣት የሚፈልጉ ከሁለት ሺህ በላይ የዐማራ ተማሪዎች አሉ።
Read more »
Friday, December 8, 2017
በኢትዮጵያ ስም ህወሓት ከሻዕቢያ ጋር የመጨረሻውን የጠቅላይ ጨዋታ ጀመረ
አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት “የእምነት አባቶች” የክህደቱ ተዋንያን ናቸው
“… ይህ ዜና በተገለበ መልኩ መሰማት ከጀመረ ሰነባብቷል። ዜናው በደባና በተቀነባበረ ሤራ የሚካሄድ ቢሆንም ዜናውን በገደምዳሜ የሚያሰራጩት ክፍሎች ስለ ጉዳዩ የተጨነቁ አይመስሉም። ቅርብ ሆኜ እንደምከታተለው ይህ ዜና አደገኛና ኢትዮጵያን ዳግም ክህደት የሚያከናንባት፤ እንደ አገር የመኖር ኅልውናዋን አደጋ ላይ የሚጥል ነው። ይህንን የሚያውቁ የሃይማኖት አባት መስቀል ተሸክመው የዚህ ሸፍጥ ተዋንያንና አስፈጻሚ መሆናቸው ያሳፍራል። ጉዳዩ በአጭሩ ህወሓት ከሻዕቢያ ጋር በኢትዮጵያ ስም ሊታረቅ ዓለምአቀፍ ዕውቅና የተሰጠው ድርድር መጀመሩ ነው…”
Read more »
Wednesday, December 6, 2017
የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ፈጸምን ያሉትን ጥቃት በተመለከተ ህወሃት ጥቃቱ መፈጸሙን አምኗል
የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ህዳር 26 – ለህዳር 27/2010 ንጋት ላይ ለወያኔ (አጋዚ) ጦር ሊውል የነበረ ነዳጅ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ጭነው ከሱዳን ወደ ጎንደር ሲጓዙ በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ በጭልጋ ነጋዴ ባህር በሰነዘሩት ጥቃት ተሽከርካሪዎቹን ሙሉ ለሙሉ ማውደማቸውንና ተሽከርካሪዎቹን አጅበው የነበሩ ወታደሮችን መግደላቸውን ገልጸዋል።
Read more »
Friday, December 1, 2017
ህዝባችን ለፍትህ እያካሄደ ያለውን ትግል አቅጣጫ ለማስለወጥ ህወሃት የሚሸርበውን ሴራ ማምከን ጊዜ ሊሰጠው የማይገባው ተግባር ነው።
December 1, 2017
በመንደርና በዘር የተሰባሰቡ የትግራይ ልጆች ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ወይም የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር በሚል ሥም ተደራጅተው በነፍጥ የአገራችንን በትረ ሥልጣን ከተቆጣጠሩ ወዲህ ላለፉት 27 አመታት ከኛ ወዲያ ላሳር በሚል እብሪትና ትዕቢት እያንዳንዱን ማህበረሰብ አዋርደው ገዝተዋል ፤ አሁንም እየገዙ ነው።
Read more »
Newer Posts
Older Posts
Home
Subscribe to:
Posts (Atom)