በሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ
በፌደራል ጠቅላይ ዓ.ህግ የወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸውን በእስር ሆነው እየተከታተሉ ያሉት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበርና የመድረክ ከፍተኛ አመራር ዶ/ር መረራ ጉዲና ለቀረበባቸው ክስ ባቀረቡት መቃወሚያ ላይ ዓቃቢ ህግ ዛሬ ሚያዚያ 26 ቀን 2009 ዓ.ም ምላሽ ሰጠ፡፡
የፈደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ ዶ/ር መረራ ጉዲና ያቀረቡትን መቃወሚያና ዓቃቢ ህግ የሰጠውን መልስ መሰረት በማድረግ በቀረበው መቃወሚያ ላይ ብይን ለመስጠት ለግንቦት 25 ቀን 2009 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በዚሁ መዝገብ ሌላው ተከሳሽ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ መቅረብ አለመቅረባቸውን ለማረጋገጥ የመሐል ዳኛው በችሎት ስማቸውን በተደጋጋሚ ቢጠሩም ተከሳሹ አልቀረቡም፡፡
No comments:
Post a Comment