Translate

Wednesday, November 30, 2016

ሰበር ዜና — ፕ/ር መረራ ጉዲና ታፍነዋል

ክንፉ አሰፋ
30 ኖቬምበር 2016 – የመድረክና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ዛሬ ረቡእ ማምሻውን በደህንነት ሃይሎች ታፍነው መወሰዳቸውን ለማረጋገጥ ችለናል።
Dr. Merera Gudina
ዶ/ር መረራ ጉዲና
በዛሬው እለትፕ/ር መረራ ጉዲና መኖርያ ቤት በደህንነቶች እና ከባድ መሳርያ በጣጠቁ የአጋዚ አባላት ተከብቦ መዋሉን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ብእር ብቻ ለያዘ አንድ ሰላማዊ ሰው ይህን ሁሉ ሃይል ማሰማራት ስርዓቱ ምን ያህል እንደተብረከረከ የሚያሳይ መሁኑን እማኞቹ ጨምረው ገልጸዋል።

በአውሮፓ ህብረት ጥሪ ተደርጎላቸው ሃገሪቱ ስላለችበት መስቀለኛ መንገድ ገለጻ አድርገዋል። ከዚያም በሆላንድ፣ በጀርመን እና በስዊዘርላንድ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ስለ ሃገሪቱ ሁነታ መወያየታቸው ይታወሳል።

Tuesday, November 29, 2016

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ: “አገራዊ ንቅናቄው የድርጅቶች እንጅ የብሄር ውክልና የለውም”


በቅርቡ በ4 የፖለቲካ ድርጅቶች የተመሰረተው የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ትናንት እሁድ በስቶክሆልም ከተማ የተሳካ ስብሰባ ማድረጉን ገልጿል። የአርበኞች ግንቦት7 መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር መሪ አቶ ሌንጮ ለታ እንዲሁም የአፋር ህዝብ ፓርቲ መሪ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ በስብሰባው ላይ የተገኙ ሲሆን፣ ስብሰባው በስቶክሆልም /ስዊድን የንቅናቄው አስተባባሪ አቶ ዘለሌ ጸጋ ስላሴ ንግግር ተከፍቷል። ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ባቀረቡት ሰፊ ንግግር፣ ሁሉም የንቅናቄው አባል ድርጅቶች ኢትዮጵያን እንደ አንድ ሉአላዊ አገር የሚቀበሉ መሆናቸውን እና ችግሮቻቸውን በዲሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት እንዳለበት ስምምነት ላይ የደረሱ በመሆኑ ተቀራርበው ለመስራት ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል። 

Monday, November 28, 2016

አርበኞች ግንቦት 7 በግጨው እና ማይለሚን በተባሉ ቦታዎች ባካሄደው ውጊያ በሕወሃት ጦር ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት በወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
Patriotic Ginbot 7 fighters in action
ኢትዮጵያንና ኢትዮጲያዊነትን ለማዳን ብሎም የተጨቆነውን ህዝባችንን በጫንቃው ላይ የተጫነበትን የባርነት ቀንበር አሽቀንጥሮ በመጣል ህዝብ ቀና ብሎ እንዲሄድና የዴሞክራሲ ተጠቃሚ እንዲሆን መራራና እልህ አስጨራሽ የትጥቅ ትግል እያካሄደ የሚገኘው ጀግናው የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ከወያኔው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይልና መከላከያ ሰራዊት ጋር ባደረገው ተከታታይ የማጥቃት እርምጃ የወያኔን ሹማምንቶች አንገት ያስደፋ አንፀባራቂ ድል ማስመዝገቡን አርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን ከስፍራ ባደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሰበር ዜና: አርበኞች ግንቦት7 በወያኔ ላይ በከፈተው ጦርነት የበላይነት ተቀዳጀ።

ኢትዮጵያንና ኢትዮጲያዊነትን ለማዳን ብሎም የተጨቆነውን ህዝባችንን በጫንቃው ላይ የተጫነበትን የባርነት ቀንበር አሽቀንጥሮ በመጣል ህዝብ ቀና ብሎ እንዲሄድና የዴሞክራሲ ተጠቃሚ እንዲሆን መራራና እልህ አስጨራሽ የትጥቅ ትግል እያካሄደ የሚገኘው ጀግናው የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ከወያኔው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይልና መከላከያ ሰራዊት ጋር ባደረገው ተከታታይ የማጥቃት እርምጃ የወያኔን ሹማምንቶች አንገት ያስደፋ አንፀባራቂ ድል ማስመዝገቡን አርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን ከስፍራ ባደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከፍተን ብናየው? ሻአቢያና ኦነግ መስተፋቅር!

አስፋ ጫቦ
Dallas Texas USAImage result for assefa chabo
እንደመግቢያ
ዛሬ ትንሽ መጻፍ የፈለኩት በኦሮሞ ነፃነት ግንባርና (ኦነግ) በኢሳይያስ አፈወርቂ መካከል ያለውን የቆየ ጥብቅ ትስስር በመጠኑ ለመፈተሽ ነው። መነሻ የሆነኝ እንግሊዝ አገር ሎንዶንና አሜሪካ፤ አትላንታ፣ ጆርጂያ የኦሮሞ “ምሁራንና ብሔርተኞች” ያደርጉት ስብሰባና የሰጡት መግለጫ ነው። ያ ራሱን ችሎ መነገር ያለበት ስለሚመስለኝ እመለስበታለሁ። የዚህኛው አላማ እዚያ ሰበሰባ ላይ ተካፋይ ከነበሩት “ነፃ አውጭዎች” አንዱን ኦነግን በጨረፍታ ለመታዘብ ነው።

Sunday, November 27, 2016

በሰሜን ጎንደር ከፍተኛ ጦርነት ሲካሄድ ዋለ

ኅዳር ፲፮ (አሥራ ስድስትቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ታች አርማጭሆ  ሳንጃ እና በጠገዴ ወረዳ ግጨው እንዲሁም ልዩ ስሙ ሃመረ በተባለ ቦታ ላይ የነጻነት ሃይሎች እና በገዢው ፓርቲ ወታደሮች መካከል ሲካሄድ በዋለው ጦርነት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የህወሃት /ኢህአዴግ ወታደሮች መገደላቸው ታውቛል።

ከሁመራ ወደ ቀራቀር በሚወሰደው መንገድ ላይ ቁስቋም ማሪያም አካባቢ በሚገኝ ዳገት ላይ፣ በወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አባል በነበረውና ሊያዝ ሲል በማምለጥ ጫካ በገባው ጎቤ መልኬ በሚመራው የነጻነት ሃይሎች ጦርና በአገዛዙ ወታደሮች መካከል በተደረገው ከፍተኛ ውጊያ በርካታ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል።

ህወሃት እጅ ላይ የንጹሃን ደም እየተንተከተከ ነው!! የምትኮሩ በዚህ ኩሩ

ሁሉም ደጅ እሳት አለ!!

tplf-and-blood

ህወሃት የታሪኩ ካስማና ማገር ከአስከሬን ጋር የተጣበቀ ስለመሆኑ የሚመሰክሩበት የሩቅ ሰዎች አይደሉም። አብረውት በበረሃ የነበሩ፣ አብረውት አመራር ሲሰጡ የኖሩ፣ “በሚያራምዱት አቋም” ከድል በፊትና በኋላ የተለዩት በተለያዩ ሚዲያ ላይ እንደመሰከሩት ህወሃት ደም ምሱ፣ አስከሬን ትራሱ ነው። በነዚሁ የቅርብ ሰዎቹ የተሰሙት ምስክርነቶች ስም፣ ቦታ፣ ጊዜ በመጥቀስ በወቀቱ እዚያው እንደነበሩ በማረጋገጥ እንጂ እንዲሁ በመላ አልነበረም። እነሱ ለአብነት ተነሱ እንጂ ሰለባዎችበየጊዜው አዳዲስ መረጃ ይዘው ብቅ ማለታቸው የተለመደ ነው። እዚህ ላይ ሌሎችም አይረሱም። ቅድሚያ ስለ ሌሎቹ።

Saturday, November 26, 2016

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በወያኔ ጦር ላይ በተለያዩ ቦታዎች በተደጋጋሚ ጥቃት በመፈፀም ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ፡፡

የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ነበልባል የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ህዳር 10 ቀን 2009 ዓ.ም ለሊት ጎንደር ዳንሻ ከተማ ልዩ ስሙ አዲስ አለም በተባለ ቦታ ሰፍሮ ከሚገኝ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ላይ በፈፀመው ድንገተኛ ማጥቃት ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ አጥቅቶ ተሰውሯል፡፡ በወሰደው ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃም 15 የወያኔ ቅጥረኛ ወታደሮችን በመግደል ቁጥራቸው ያልታወቀ ደግሞ ማቁሰሉን አርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን ከስፍራው ባደረሰን ዘገባ አስታውቋል፡፡

Thursday, November 24, 2016

የአርበኞች ግንቦት 7 ነበልባል ሰራዊት በዳንሻ፣ አዲስ አለም ጥቃት ሰንዝሮ መሰወሩን ንቅናቄው አስታወቀ

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በወያኔ ጦር ላይ በተለያዩ ቦታዎች በተደጋጋሚ ጥቃት መፈፀሙን በመቀጠል ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ታወቀ 
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) 
Patriotic Ginbot 7 fighters in action
የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ነበልባል የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ህዳር 10 ቀን 2009 ዓ.ም ለሊት ጎንደር ዳንሻ ከተማ ልዩ ስሙ አዲስ አለም በተባለ ቦታ ሰፍሮ ከሚገኝ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ላይ በፈፀመው ድንገተኛ ማጥቃት ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ አጥቅቶ ተሰውሯል፡፡ በወሰደው ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃም 15 የወያኔ ቅጥረኛ ወታደሮችን በመግደል ቁጥራቸው ያልታወቀ ደግሞ ማቁሰሉን አርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን ከስፍራው ባደረሰን ዘገባ አስታውቋል፡፡

የአርበኞች ገንቦት 7 ትላንት በጎንደር ዳንሻ ኣዲስ ኣለም ኣካባቢ ባድረገው ውጊያ ወደ 30 ሚድረሱ የወያኔ ወታደሮችን መግድሉን ምንጮቻችን ገልጸዋል።

Breaking News:-
የአርበኞች ግንቦት 7 ትላንት በጎንደር ዳንሻ ኣዲስ ኣለም ኣካባቢ ባድረገው ውጊያ ወደ 30 ሚድረሱ የወያኔ ወታደሮችን መግድሉን ምንጮቻችን ገልጸዋል።
የኣርበኞች ግንቦት 7 ሰሞኑን ተደጋጋ

Tuesday, November 22, 2016

ሰበር ዜና:-በጄኔራል ሲራጅ ፈርጌሳ የሽፋን ስእል በጄኔራል ሳሞራ የኑስ የበላይነት ቁጥጥር ስር የወደቀዉ የወታደራዊ ደህንነት የመከላከያ ሰራዊቱ ላይ አደገኛ እርምጃ በመዉሰድ አተኩሯል።

ልሁል አለም
world news
በመሆኑም ያለ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ኮማንድ ፖስቱ በስዉር እንዲያጠቃ ትእዛዝ ተላልፎለት
የኮማንድ ፖስቱ ደህንነትን ተገን ያደረገዉ ዉሳኔ በ8 የመከላከያ አባላቱ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በማዘዙ
ትናንት በ11/03/2009 በመላዉ ሐገሪቱ የተነሳዉን ህዝባዊ እንቢተኝነት ይደግፋል ያደራጃል የተባለዉ የመካከለኛዉ እዝ ባልደረባ የም/መቶ አለቃ አለበል ትእዛዙ የዉሳኔዉ ሰለባ ሲሆን በተጨማሪ ከሰሜን እዝ ወታደራዊ መምሪያ ክፍል ወታደር ቅጣው ቢያድግልኝ ላይ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
ወታደር ቅጣዉ ቢያድግልኝ ሐሙስ ከሰሜኑ እዝ ክፍለ ጦር መምሪያ ትፈለጋለህ ተብሎ ከተወሰደ ወዲህ በጥይት ተደብድቦ መረሸኑን የአይን እማኝ የነበሩ አባላቶች በከፍተኛ ቁጭት ለምንጫችን የትናገሩ ሲሆን።

Monday, November 21, 2016

የሕወሃት ኮማንድ ፖስት በመከላከያ አባላት ላይ የግድያ እርምጃ እየወሰደ ነው

በልኡል አለም
Ambo Must Unite Ethiopians or Nothing Will & TPLF’s Killer Machine ...
 በጄኔራል ሲራጅ ፈርጌሳ የሽፋን ስእል ተሰጥቶት በጄኔራል ሳሞራ የኑስ የበላይነት ቁጥጥር ስር የወደቀዉ የወታደራዊ ደህንነት የመከላከያ ሰራዊቱ ላይ አደገኛ እርምጃ በመዉሰድ ላይ አተኩሯል።

 በመሆኑም ያለ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ኮማንድ ፖስቱ በስዉር እንዲያጠቃ ትእዛዝ ተላልፎለት የኮማንድ ፖስቱ ደህንነትን ተገን ያደረገዉ ዉሳኔ በ8 የመከላከያ አባላቱ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በማዘዙ፣ ትናንት በ11/03/2009 በመላዉ ሐገሪቱ የተነሳዉን ህዝባዊ እንቢተኝነት ይደግፋል ያደራጃል የተባለዉ የመካከለኛዉ እዝ ባልደረባ የም/መቶ አለቃ አለበል ትእዛዙ የዉሳኔዉ ሰለባ ሲሆን በተጨማሪ ከሰሜን እዝ ወታደራዊ መምሪያ ክፍል ወታደር ቅጣው ቢያድግልኝ ላይ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።

Friday, November 18, 2016

ጎሠኛነት በባዶ ሜዳ (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም)

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

Mesfin Woldemariam በተለያዩ የኢትዮጵያ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ሁሉ የሚደረገው ውይይትና ክርክር እንደተጠናቀቀ ተቆትሮ የአማራና የኦሮሞ ጎሠኛነት ትልቁ አንገብጋቢ ጉዳይ እየሆነ ነው፤ (ስለኢትዮጵያ ለማያውቅ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ ከጠሩና ከጸዱ አማራና ኦሮሞዎች በቀር በአገሪቱ ውስጥ ሌላ ሰው ያለ አይመስልም!) ጎሠኛነት ጉዳያችን ያልሆነው ኢትዮጵያውያን የዳር ተመልካች መሆኑ እየሰለቸን ነው፤ ምንም እንኳን አማራና ኦሮሞ የተባሎት ጎሣዎች በብዛት ከሁሉም ቢበልጡም ከሰማንያ በላይ የሚሆኑ ጎሣዎች እንደሌሉና በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ቃል እንደሌላቸው ተደርጎ የሚጎነጎነው የሚስዮናውያንና የስለላ ድርጅቶች ታሪክ ለኢትዮጵያውያን ባዕድ ነው፡፡

Thursday, November 17, 2016

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች በቃፍታ ሁመራ ከሕወሃት ሰራዊት ጋር እየተፋለሙ ነው

Patriotic Ginbot 7 fighters attacked TPLF
የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ከሕወሃት ሰራዊት ጋር ከፍተኛ ውጊያ ሲያደርጉ ውለው ከርሰሌት በምትባል ቦታ የሚገኘውን የአደባይ ተራራን ተቆጣጥረዋል።

Monday, November 14, 2016

ኢትዮጵያን የሚጠቅማት ”እኛ” እና “እነሱ” ሳይሆን “እኛ” ብቻ ነዉ (ኤፍሬም ማዴቦ)

ኤፍሬም ማዴቦ
Ephrem Madebo with Patriotic Ginbot 7 fightersእንደኔ አንዴ ሲቆጥቡት አንዴ ሲደብቁት በድንገት ዕድሜያቸዉ ወደ ሃምሳዎቹ የገባ ሰዎች አንድ የምንጋራዉ እምነት አለ- እሱም የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች አንድ ነገር መጀመር እንጂ መጨረስ አያዉቁበትም የሚል እምነት ነዉ። በፍጹም ሊፈረድብን አይገባም። ከልጅነት ወደ አዋቂነት የደረስነዉ ጥንስስ ሲጠነሰስ እንጂ እንጄራዉን ሳናይ ነዉ። ፓርቲ ሲፈጠር እንጂ ዉጤቱን ሳናይ ነዉ። የፖለቲካ ህብረቶች ተፈጥረዉ ፈረሱ ሲባል ነዉ እንጂ እንዲህ አደረጉ ሲባል ሰምተንም አይተንም አናዉቅም። ባጠቃላይ የፖለቲካ ትግል ሲባል ነዉ እንጂ ድል ሲባል ሰምተን አናዉቅም። ድል የረጂም ግዜ ትግል ዉጤት እንደሆነ ይገባናል፥ ሆኖም ግን ዛሬ የሚረግጡን ሰዎች በረሃ ገብተዉ አዲስ አበባን እሲኪቆጣጠሩ ድረስ የወሰደባቸዉን ግዜ ሁላችንም የምናስታዉሰዉ ይመስለኛል። እኔ ይህንን ሁሉ ጉድ በአይኑ እያየ ያደገ ትዉልድ አካል ነኝ። ግን ይህንን ዕድሜ ልኬን ሲደጋገም ያየሁትን የአገሬን በሽታ መድሐኒት እፈልግለታለሁ እንጂ “ከመሳሳት እራሴን ላድናት” እኔን ምን አገባኝ የ”እነሱ” ጉዳይ ነው ብዬ እጆቼን አጣጥፌ አልቀመጥም። ጉዳዩ የኔ ነዉ . . .. ጉዳዩ የኛ ነዉ። “እነሱም” “እኛም” አንድ ላይ “እኛ” ነን። ሰዉ የመሆኔ ትልቁ ሚስጢር የሚነግረኝ በአካባቢዬ ካሉ ሰዎች ዉጭ መኖር የማልችል ማህበራዊ ፍጡር መሆኔን ነዉ። አንዳንዶቻችን መሳሳትን እንደ ጦር እንፈራለን፥ መሳሳትን ፈርተን እጃችንን አጣጥፈን ከምንቀመጥ እየተሳሳትንና ከስህተታችን እየተማርን የምንሰራዉ ስራ ነዉ አገራችንን ነጻ የሚያወጣት። ስለዚህ በእኔ እምነት ምንም ይሁን ምን ከኢትዮጵያ ፖለቲከኞች የሚጠበቅ ምንም ነገር የለም ብለን እጅና እግራችንን አጣጥፈን መቀመጡ የበሽታ ምልክት ነዉ እንጂ የጤንነት አይመስለኝም።

Thursday, November 10, 2016

“አዲስ አበባ ሆይ! አስር ጋሽ ቆፍጣናው እና ሁለት እያዩ ፈንገሶች ይኑሩሽ!!”

ኤርሚያስ ለገሰ
Ethiopian comedian, Eyayu Fungusእሁድ አመሻሽ:: በፈረንጆቹ አቆጣጠር ታህሳስ 06 ቀን 2016:: የአሜሪካን ክረምት የገባ የማይመስል ብርሃናማ ቀን ነበር። የዋሽንግተን ዲሲና አከባቢዋ ነዋሪ የሆንን ኢትዮጵያውያን በኮሎምቢያና 16ኛው ጎዳና መገጣጠሚያ ላይ በሚገኘው (ኮሎምቢያ ሃይት የትምህርት ማዕከል) የማይቀርበት ቀጠሮ ይዘናል። ወደ አደራሹ የምንሄደው የጣይቱ የባህልና የትምህርት ማዕከል ከሌሎች አገር ወዳጆች ጋር በመሆን ከኢትዮጵያ ያስመጡትን ቴያትር ለማየት ነበር። አብሬአቸው የምሄደው የቅርብ ወዳጆቼ የቴያትሩ ደራሲ እና ተዋንያን ጋር የቀረበ ግንኙነት ያላቸው በመሆኑ፤ ዘወትር ስለ ቴያትሩ ሲነግሩኝ የማዳምጣቸው ጆሮዬን እንደ ጥንቸል አቁሜ ነበር። በተለያየ ጊዜ ወግ ቢጤ ስንጭር ወደ ስደት ከመምጣታቸው በፊት ከአምስት ጊዜ ያላነሰ ተመላልሰው ቴአትሩን እንደተመለከቱት ሲያጫውቱኝና ከድራማው እየቀነጨቡ አባባሎችን ሲያጎኑት እኔ ቴያትሩን ባለመመልከቴ መንፈሳዊ ቅናት ያድርብኝ ነበር። “ማነው እያዩ ፈንገስ?…..ማነው ጋሼ ቆፍጣናው?” እያልኩ እራሴን እጠይቅ ነበር። በእያዩ ፈንገስ ፌስታል ውስጥ የተዶለተው ሰምና ወርቅ ምን እንደሆነ ለማወቅ መሻቱ ነበረኝ። “ሜዳ ጠፋ ተብሎ ተራራ የሚናድበት ሃገር” አይነት ፍርድና ቅጣት እየተሰጠ እንደሆነ በቴያትር ሲገለጥ ለማየት ፍላጎት ያሳድራል።