Translate

Monday, October 15, 2012

ወ/ሮ አዜብ መስፍን ቤተ መንግስቱን ሊለቁ ተስማሙ !!!

ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከቤተ መንግስት እንዲወጡ የቀረበላቸውን ጥያቄ ቢቀበሉም ጥርሳቸዉን እንደነከሱ ነው::ለሃይለማርያም ቤተመንግስቱን አላስረክብም በማለት ብትደነፋም አስቸኩዋይ የሚል ደብዳብይ ከደረሳት በሁዋላ ደንግጣለች::በተለያዩ ምክንያቶች በመደርደር ላለመውጣት  አንድ ጊዜ ለደህንነቴ አይመችም ሌላ ግዜ ተዝካር ላውጣና …እያለች ምክንያቶች ብታበዛም ግፊቱ ስለጨመረባት ለመልቀቅ ተስማምታለች::ከቀረቡላት 3ቪላዎች ዉስጥ ከአራተኛ ክፍለ ጦር በታች ጠበንጃ ያዥ አከባቢ ወደ ዉስጥ ገባ ብሎ ከዚህ ቀደም የመለስ ዜናዊ አክስት ልጅ የጦር ጄኔራል የነበረው የዮሃንስ መኖሪያ ቤት 
azeb and her first son
ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከቤተ መንግስት እንዲወጡ ሊሰጣት እንደሆነ ምንጮች ተናግረዋል::

ይህ መኖሪያ ቤት ከዚህ ቀደም ያማር ክልል መሪ አያሌው ጎበዜ በቁም እስር ታስሮበት የነበር ሲሆን ባከባቢው በርካታ ባለስልጣናት ስለሚኖሩበት ጥበቃው ለደህንነት አያሰጋም ::
በቅርቡም ከቤተመንግስት ተወጣለች ተብሏል እንደምንጮቹ ዘገባ ከሆነ የቤተመንግስቱን መልቀቅ ቅሬታ ቢፈጥርባትም ከመልቀቅ ሌላ አማራጭ እንደሌላት ገልጠዋል 

የመጀመሪያው የኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያን ጉባኤ በቨርጂኒያ ተካሄደ


ኢሳት ዜና:-የመጀመሪያው የኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያን መራጮች ጉባኤ በአሌክሳንድሪያ ቨርጂኒያ ተካሄደ።
ትናንት እሁድ፤ መስከረም 4 ቀን በተካሄደው ጉባኤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከተለያዩ የአሜሪካን ከተሞች የመጡ ኢትዮጵያዊያን የተገኙ ሲሆን፤ ለኮንግረስና ለሲቲ ካውንስል የሚወዳደሩ እጩዎች ቀርበው ንግግር አድርገዋል።
ኮንግረስማን ሞራን ግሪፊዝ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ችግር እንደሚረዱ ገልጸው፤ ከኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያን ጎን እንደሚቆሙ ገልጸዋል።
የአሌክሳንድሪያው ከንቲባ ዊሊያም ዲ ኢዩልም ባደረጉት ንግግር፤ የኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያን በአካባቢያቸው በሚገኙ በተለያዩ የአስተዳደር እርከኖች ውስጥ በተለያዩ መልኮች መሳተፋቸውን እንዲጨምሩ አሳስበው፤ ከፕሬዚዳንት ኦባማ ጋር በሚገናኙባቸው የተለያዩ አጋጣሚዎች የኢትዮጵያን ጉዳይ እንደሚያነሱ ቃል ገብተዋል።

አቶ ብርሀነ ገ/ክርስቶስ ተጠባባቂ ጠ/ሚር ሆነዋል


ኢሳት ዜና:-የውጭ  ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ዕምባሳደር ብርሀነ ገብረክርስቶስ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ተደርገው እንደተሾሙ ታወቀ። የሹመት ደብዳቤው ተፈርሞ የወጣው ከጠቅላይ ሚ/ሩ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙክታር ከድር ቢሮ እንደሆነ ታውቋል።
በአቶ ሀይለማሪያም ሹመትና በሌሎች ሁኔታዎች ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ በኢህአዴግ ነባር ፓርቲዎች በተለይም፤ በኦህዴድ ውስጥ ያለው ልዩነት እልባት አለማግኘቱ አዲስ ካቢኔ እንዳይቆቆም እንቅፋት መሆኑም ተመልክቶል::
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ስፍራ ለኦሆዴድ አባል እንደሚሰጥ በአንዳንድ ወገኖች ቢገመትም፤ ሌሎች ወገኖች ደግሞ ስፍራውን ሕወሀት እንደሚይዘው ሲገልጡ ቆይተዋል::
የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህውሀት) ማእከላዊ ኮሚቴ አባል አምባሳደረ ብርሀነ ገብረክርስቶስ ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መሰየማቸው በአዲሱ የካቢኔ ድልድል ስፍራውን በሙሉ ስልጣን እንደሚይዙት አመላካች ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ቢናገሩም፤ አቶ ተቀዳ አለሙም ለውች ጉዳይ ሚንስትርነት እንደታጩ እንዳንድ ምንጮች ተናግረዋል::

ወ/ሮ ሚሚ ስብሀቱ ለወ/ሮ አዜብ መስፍን ያላቸውን ድጋፍ ገለጡ


ኢሳት ዜና:-ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሥነምግባር ችግር ከተባረሩ በኋላ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትዕዛዝ ያለጨረታ የደቡብ ክልል
መገኛኛ ብዙሃን የቴክኒክ ሥራን ተረክበው በአቋራጭ ከባለሃብት ጎራ የተቀላቀሉት ወ/ሮ ሚሚ
ስብሃቱ ፣ ዛሚ በተሰኘው ራዲዮ ጣቢያቸው ለወ/ሮ አዜብ መስፍን ከአጃቢ ጋዜጠኞች ጋር በመሆን ሲሟገቱ ውለዋል፡፡
ሰሞኑን የወጡ ጋዜጦች ወ/ሮ አዜብ ቤተመንግስቱን ለአቶ ኃይለማርያም አላስረከቡም በሚል ያወጡትን ተከታታይ
ዘገባዎች የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ በሚለው ዝግጅታቸው ጋዜጠኞችን ሲተቹና እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቀዋል።
ወ/ሮ ሚሚ “እንዲህ ዓይነቱ ጥያቄ ከአዲሱ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ዳሳለኝ መጥቶ ከሆነ የሚያሳዝን ነው በማለት ተናግረዋል።የወ/ሮ አዜብ የቅርብ ጓደኛ የሆኑት ወ/ሮ ሚሚ በጋዜጦቹ የቀረበው ዘገባ እውነትነትን ሳይክዱ አርባ እና ሰማንያ ሳይወጣ፣ የጠ/ሚኒስትሩ ውለታ ሳይረሳ እንዴት እንዲህ ይጻፋል ከማለት አንስተው ደርጊቱ በጠ/ሚኒስትሩ ሌጋሲና ውርስ ብቻ ሳይሆን በቀጣዩ ልማት ላይ የተቃጣ አደጋ ነው በማለት ገልጸዋል።

የበአሉ ግርማ ጆሮጠቢ


ከተስፋዬ ገብረአብ
በኛ ዘመን የብእር ሰው ሆኖ መፈጠር መረገም ሆኖ ይሰማኛል። ከቡቃያው የሚነጋገር፣ በሁዳዱ ላይ ሽምጥ ፈረስ የሚጋልብ፣ ውሎው ከዋልካው፣ ማምሻው ከመልካው የሆነ ገበሬA renowned Ethiopian novelist Bealu Girmaእንዴት እድለኛ ነው? የኛ ዘመን ብእረኛ ህይወቱ በሰላዮች የተከበበ ነው። ተፈጥሮው ነውና አለመፃፍ አይችልም። መፃፍ ደግሞ አደጋ ነው። በአሉ ግርማ እንዲህ ባለ ችግር ውስጥ አልፎ፣ በከንቱ ያለፈ ደራሲ ነበር። ደርግ ብዙ ሰላዮች መድቦበት ነበር።
በአሉ ግርማ ምንም እንኳ ከደርግ ሰዎች ጋር በቅርብ ይሰራ የነበረ ሰው ቢሆንም ህሊናው ግን ነፃ ነበር። የደርግ የፀጥታው መስሪያ ቤት የበአሉን ነፃ መንፈስ በማወቁ፣ ነፃ ለቆት አያውቅም። በሰላዮቻቸው ከበውት ኖረዋል። በአሉ ግርማን እንዲሰልሉ ከተመደቡት አንዱ አይነስውር ለማኝ ሆኖ ነበር የሚተውነው። በአሉ ግርማ መኪናውን ውቤ በረሃ አቁሞ፣ እዚያው መኪና ውስጥ ሆኖ ሲቀመቅም፣ አይነስውር መሳዩ ለማኝ ወደ በአሉ መኪና ጠጋ ብሎ ይለምናል፣

የሚያድግ ኢኮኖሚ ነገር ግን የማይታይ የማይዳሰስ!


(ፈቃዱ በቀለ)
seen but not seen

Sunday, October 14, 2012

መለስ ዜናዊ ስልጣን ላይ በቆየባቸዉ አመታት ያከናውናቸው የነበሩት በርካታ ጉዳዮችን ለፓርቲውም ሆነ ለሚንስትሮች ምክር ቤትም ወይም ለይስሙላ ፓርላማ እንደማያሳውቅ ምንጮች አጋለጡ


ኢትዮጵያ አገራችንን ለ21 አመታት የገዛው ዘረኛውና አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ከፍተኛ በጀት የሚጠይቁ ትላልቅ ውሳኔዎችን በዙሪያው ላሰባሰባቸው የካቢኔ ምንስትሮችም ሆነ ለፓርላማው ሳያሳውቅ በራሱ ፈቃድ ብቻ ያስተላልፍና ያስፈጽም እንደነበረ ጉዳዩን በቅርበት ይከታተሉ ከነበሩ ሚንስተሮች የተገኘ መረጃ አጋለጠ።
መለስ ዜናዊ በህይወት በነበረበት ወቅት ለማንም ሳያማክር በግል ሥልጣኑ አስጀምሮት ከነበሩ ፕሮጄክቶች አንዱ ለኤርትራ ተቃዋሚዎች ይሰጥ የነበረው የፋይናንስና የማቴሪያል እርዳታ እንደነበረ የገለጹ ምንጮች የርሱን መሞት ተከትሎ ተቃዋሚዎቹ  ከፍተኛ ችግር እንደገጠማቸው ገልጸዋል።