Translate

Wednesday, May 13, 2015

በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላይ ዘለፋ አዘል ግምገማ ተካሄደ

ኢሳት ዜና :- /ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በሰብሳቢነት የሚመሩት ኢህአዴግ፣ ከፍተኛ የግንባሩንና የመንግስት አመራሮችን በመገምገም ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የመንግስት ስልጣን የሚይዙትንና ድርጅቱን የሚመሩትን ሲመርጥ ከርሟል። ሁሉም የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹሞች የተገመገሙ ሲሆን፣ የመንግስት ስልጣን ያልያዙ ነገር ግን በግንባሩ ውስጥ ያገለገሉ ነባር ታጋዮችም በግምገማው ተሳትፈዋል። አቶ ሃይለማርያም ግምገማውን በሰብሳቢነት ሲመሩ ቆይተው፣ የመጨረሻው ተገምጋሚ ራሳቸው ሆነዋል።

የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጉዳይ ፤ ለ15 ሰዓታት እንደተገመገሙ ተገለጸ

የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጉዳይ ፤ ለ15 ሰዓታት እንደተገመገሙ ተገለጸ
አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ላለፉት ሁለት አመታት ሕወሃትን በታማኝነት ሲያገለግሉ እንደነበረ የሚታወቅ ነው። ከጅምሩ አንድ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሲሞት፣ ቦታዉን የሚይይዘው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተሩ ነበር። አቶ መለስ ሲሞቱ ምክትል ጠ/ሚኒስተር የነበሩት አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስተር ለማድረግ ፓርላማ ቀጠሮ ያዘ። ተጠባባቂ ጠ/ሚኒስተር መባል ጀመሩ። አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠ/ሚኒስተር እንደሚሆኑም ተገለጸ።
ሆኖም ሕወሃቶች ተቃወሙ። ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚመርጠው ፓርቲው እንጂ ፓርላማው አይደለም አሉ። በዚህም ምክንያት አቶ ኃይለማሪያም ጠ/ሚኒስትር እንዳይሆኑ ብሎክ አደረጉ። አቶ ኃይለማሪያም ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር መባላቸው ቀረና ምክትል ጠ/ሚኒስተር ወደ መባል ተመለሱ። ሕወሃቶች ከነርሱ ዉጭ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት እንዲያዝ አይፈልጉምና የነርሱን ሰው ለማስቀመጥ ደፋ ቀና ማለት ጀመሩ። ወ/ር አዜብም ከቤተ መንግስት አልወጣም አሉ። አቶ ኃይለማሪያም በዚህ ምክንያት ሌሊት በጠዋቱ እየወጡ ማታ ነበር ወደ ስራቸው የሚሄዱት።
አቶ ኃይለማሪያምን በቅርበት ለመከታተል፣ አቶ ጸጋዬ በርሔ እና አባይ ጸሃዬ የጠቅላይ ሚኒስተር አማካሪ ሆነው እንደሚሾሙ፣ አቶ ድበረ ጽዩን ደግሞ ፣ ከአቶ ደመቀ መኮንን እና ዘረኛ የኦሮሞ አክራሪውና የአናሌና ጨለንቆ የጥላቻ ሐዉልት አስገንቢው ሙክታር ከድር ጋር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር እንደሚሆኑ፣ ዶር ቴድሮስ በዉጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት እንደሚሰሩ ስምምነት ሲደረስ፣ ሕወሃቶች የአቶ ኃይለማሪያምን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ተቀበሉ። (በነገራችን ላይ ለአቶ ደመቀ እና ለዶር ቴድሮስ አክብሮት አለኝ)

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲንቅናቄ ከውህደቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን አርበኛ ታጋዮችባለፈው እሁድ ግንቦት 2 2007 ዓ.ም ደማቅናታሪካዊ በሆነ ስነ-ስርዓት አስመረቀ፡፡

አርበኞች ግንቦት 7

 አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከውህደቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን አርበኛ ታጋዮች ከትናንት በፊትእሁድ ግንቦት 2 2007 . ደማቅና ታሪካዊ በሆነ ስነ-ስርዓት አስመረቀ፡፡
Ginbot 7 and EPPF
እነዚህ በርካታ ቁጥር ያላቸው የመጀመሪያ ዙር ተመራቂ አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ተከታታይ ወራት የተሰጣቸውን የፖለቲካ፣ የወታደራዊ እናእንዲሁም የመረጃና ደህንነት ስፋትና ጥልቀት ያላቸውን ትምህርቶች በመውሰድ በብቃት የተወጡና በተግባር የተፈተኑ መሆናቸውን የአርበኞችግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ታጋይ ተስፋሁን ተገኘ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግርገልፀዋል፡፡

Tuesday, May 12, 2015

ኃይለማርያም ደሳለኝ እምባ እስኪተናነቃቸው ድረስ በአርከበ እቁባይና ስብሃት ነጋ ተተቹ

ኢሳት ዜና :- ጠ/ሚኒስትሩ ሚኒስትሮችንና የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናትን በሙሉ ሲያስገመግሙ ከከረሙ በሁዋላ በመጨረሻ ራሳቸው 15 ሰአታት በፈጀ ግምገማ ተገምግመዋል። አብዛኞቹ በአቶ ሃይለማርያም የስራ ችሎታና አመራር ላይ ዘለፋ ቀረሽ ሂስ አቅርበውባቸዋል። አቶ ሃይለማሪያም የቀረበባቸውን ሂስ ለመቀበል ዝግጁ አለመሆናቸው ግምገማው ረጅም ጊዜ እንዲወስድ አድርጓል። ግምገማው ከምርጫው በሁዋላ የሚቀጥሉና የማይቀጥሉ ባለስልጣናትን ለመለየት እና ግድፈታቸውን አርመው ሰርተው እንዲጠብቁ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተነግሯል።
HaileMariam
አቶ ሃይለማርያም ከህወሃቶቹ ከአቶ አርከበ እቁባይ፣ አቶ ስብሃት ነጋና አስመላሽ ወልደስላሴ የሰላ ትችት ሲቀርብባቸው፣ ከራሳቸው የደህዴን አባላት ከሆኑት ከአቶ ሬድዋን ሁሴንና ሙፈሪያት ከሚልም ዘለፋ ቀረሽ ትችት አስተናግደዋል። አብዛኞቹ ብአዴኖች፣ አቶ በረከት ሳይቀሩ የአቶ ሃይለማርያምን ቁርጠኝነት ጥያቄ ውስጥ አስገብተዋል። በመጠኑም ቢሆን የራሩላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ብቻ ናቸው።
አቶ ሃይለማርያም እንቅስቃሴያቸውንና የሌሎችን ሰዎች እንቅስቃሴዎች የሚቆጣጠሩ የስለላ ካሜራዎች እንዳይተከሉ፣ በጽህፈት ቤታቸው ያለውም እንዲነሳ ማድረጋቸው ከደህንነት ሃይሉ ጋር አጋጭቷቸው እንደቆየና ውዝግቡ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ መሆኑ ተወስቷል።
አቶ ሃይለማርያም አንዳንድ መልሶችን ሲሰጡ እንባ ይተናናቃቸው ነበር። በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ደግሞ በእልህና በወኔ ተሟግተዋል። አቶ ስብሃት ነጋ በአቶ ሃይለማርያም ላይ ለሰነዘሩት ትችት፣ አቶ ሃይለማርያም ” ስብሃት በጣም ይጮሃል፣ እንዳሞራ ሁሉ ይዞረኛል፣ እዚህ ሳወያይም ይጮሃል፣ አለቃ መሆን ችግር ነው ብየ ዝም አልኩ። ንግግር ከመልክ ያምራል ይባላልና ያሳሳትኩት ነገር ካለ አርማለሁ። በአባባል ክፍተት ካለ ይቅርታ” በማለት መልሰዋል።
የግምገማውን ዝርዝር ሪፖርት በነገው ዘገባ የምናቀርብ መሆኑን ለመግለጽ እናወዳለን።

የቀድሞ የመኢአድ የሕዝብ የህዝብ ግኑኙነት ሀላፊን ጨምሮ በርካታ ወጣቶች ኤርትራ ለትጥቅ ትግል መግባታቸውን ገለጹ

Hiber Radio 

 ፣<<ወያኔን በሰላማዊ ትግል አይወድቅም ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ በትጥቅ ትግል መታገል ነው>>
ወጣት ተስፋሁን አለምነህ 
የቀድሞ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው ወጣት ተስፋሁን አለምነህ በአገር ቤት የወያኔን አገዛዝ በሰላማዊ ትግል ታግሎ መጣል አይቻልም ብሎ በመወሰን እሱና ሌላው የመኢአድ አባል ደሳለኝ ሲሳይ ከበርካታ ወጣቶች ጋር ኤርትራ የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ሰሞኑን መግባታቸውን ለህብር ሬዲዮ ከስፍራው በሰጠው አጠር ያለ ቃለ ምልልስ ገለጸ።

<በአስቸጋሪ ሁኔታ አልፈን የቀድሞው መኢአድ ግማሹ ክንፍ ኤርትራ ገብተናል>> በሚል አርዕስት ለህብር የላከውን ማስታወሻ እውነተኛነት ለማጣራት ባቀረብነው ጥያቄ የኤርትራ ስልኩን ልኮልን እሱም ሆነ ሌሎቹ በትጥቅ ትግል ስርዓቱን ለመጣል ኤርትራ የገቡ ወጣቶች መኖራቸውንና  ገልጿል ።
በአገር ቤት በሰላማዊ ትግዩ አምንን በተደጋጋሚ ስንታሰርና መከራ ሲደርስብን ነበር ያለው ተስፋሁን ሰላማዊ ትግሉ መሪያችን ፕሮፌሰር አስራትን ጨምሮ ብዙዎችን ከማስበላት ያለፈ ስርዓቱን ለማዳከም ባለመቻሉ የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ኤርትራ መግባታቸውን አረጋግጦልናል ።
<<ወያኔን በሰላማዊ ትግል አይወድቅም ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ በትጥቅ ትግል መታገል ነው>> ያለው ወጣት ተስፋሁን አለምነህ ስርኣቱን በሰላማዊ መንገድ ብቻ ታግሎ መጣል አለመቻሉን ጠቅሷል።
ከወጣት ተስፋሁን አለምንህ ጋር ያደረግነውን አጠር ያለ ቃለ ምልልስ ዘግይተን እናቀርባለን።
http://www.hiberradio.com/archives/500

Monday, May 11, 2015

አቶ ስንታየሁ ቸኮል ስድስት ወር ተፈረደበት – ሰማያዊ ፓርቲ

Semayawi party member
ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም መንግስት አይ. ኤስ. አይ. ኤስ ሊቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ በመቃወም የጠራው ሰልፍ ላይ በተነሳበት ተቃውሞ ሰበብ ሰልፉ ካበቃ ከሁለት ቀን በኋላ ከቤቱ ተይዞ የታሰረው የቀድሞው የአንድነትና አሁን የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አቶ ስንታየው ቸኮል ስድስት ወር ተፈረደበት፡፡
ዛሬ ግንቦት 3/2007 ዓ.ም ቄራ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የቀረበው አቶ ስንታየሁ ፖሊስ በሰልፉ ወቅት ድንጋይ ወርወሯል በሚል ባቀረበበት ክስ ምስክሮች ያሰማ ሲሆን የስድስት ወር እስር ተፈርሶበታል፡፡ አቶ ስንታየሁ መቃወሚያና የክስ ማቅለያ እንዲያቀርብ ተጠይቆ የነበር ቢሆንም ‹‹የከሰሰኝ ኢህአዴግ ነው፡፡ እየመሰከሩብኝ ያሉትም ኢህአዴጎች ናቸው፡፡ የወሰነብኝም ኢህአዴግ ነው፡፡ በመሆኑም ፍትህ አገኛለሁ ብዬ መቃወሚያም ማቅለያም አላቀርብም›› በሚል መቃወሚም ማቅለያም ሳያቀርብ ቀርቷል፡፡ ይህን አቋሙን በጽሁፍ እንዲያቀርብ የተጠየቀው ስንታየሁ መቃወሚያም ሆነ ማቅለያ እንደሌለው በጽሁፍ አቅርቧል፡፡

ከሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ !


የስም ማጥፋት ዘመቻው ከጀመርነው ትግል ፍፁም አያንበረክከንም!
ሰሞኑን በህውሓት/ኢህአዴግ ቁጥጥር ስር ባሉ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሰማያዊ ፓርቲ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዘመተ ያለውን የስም ማጥፋት ፕሮፓጋንዳ በአትኩሮት ሲከታተለው ቆይቷል፡፡ በዚህም የህዝብ ንብረት የሆኑ ሚዲያዎች፤ ለህዝብ አገልግሎትና በህዝብ ግብር በሚሰበሰብ ገንዘብ የሚተዳደሩ የማህበረሰቡ የአገልግሎት ተቋማት ጭልጥ ብለው የሰማያዊ ፓርቲ ስም በማጉደፍ እና በማብጠልጠል ላይ ተሰማርተው መገኘታቸውን በትዝብት ተመልክተናል፡፡