Translate

Wednesday, October 16, 2013

ለአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ፍትሕ አይቀሬ ናት

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
international criminal courtማስታወሻ ለአንባቢው፡፡ ባለፈው ሳምንት ሐተታዬ ‹‹የዘር አደን›› በሚል አሉባልታዊ ክስ  የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በተሰነዘረበት ክስ ደግፌው ተሟግቼለታለሁ፡፡ በዚህም ሳምንት ድጋፌን በመቀጠል እነዚህ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች የፈጠሙትን ግፍና በደል ጭቆና በመዘርዘር ራሳቸውን ነጻ በማድረግ የአይ ሲ ሲን (የኣለም ወንጀለኛ ፍርድ ቤት) ስም በማብጠልጠልና የቆመለትን ዓላማ የሳተ በማስመሰል ገዢዎችና አስፈጻሚዎ ቡችሎቻቸው ያነሱዋቸውን ማስረጃ ቢስ ውንጀላዎች በተጨባጭ ማስረጃ ድርጊቶታቸውንና ሸፍጣቸውን ይፋ ለማድረግ ወስኛለሁ፡፡ የኦክቶበር 11-12, 2013 የአፍሪካ አንድነት ‹‹መሪዎች›› የጨረባ ስብሰባ የተጠራውም ቴአትራዊ የልብ ወለድ ሴራ ለማካሄድና ነጻ ለመምሰል የሚያስችላቸውን ቅጥፈት ለማናፈስ ነው፡፡

Tuesday, October 15, 2013

ከ52 የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች በመልካም አስተዳደር ለተመረጡ የአፍሪቃ መሪዎች ለሚሰጠው ሽልማት በዚህ ዓመት መስፈርቱን ያሟላ መሪ አለማግኘቱን አስታወቀ

በመልካም አስተዳደር ለተመረጡ የአፍሪቃ መሪዎች ለሚሰጠው የሞኢ ኢብራሂም ሽልማት በዚህ ዓመት ተሸላሚ እንዳልተገኘ ድርጅቱ ዛሬ ለንደን ውስጥ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል ።
8u7
ሞኢ ኢብራሂም የተባለው ድርጅት በመልካም አስተዳደር ለተመረጡ የአፍሪቃ መሪዎች ለሚሰጠው ሽልማት በዚህ ዓመት መስፈርቱን ያሟላ መሪ አለማግኘቱን አስታወቀ ። ድርጅቱ ዛሬ ለንደን ውስጥ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በዚህ ዓመት ተሸላሚ እንደሌለ አስታውቋል ። ከ52 የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች መካከል የድርጅቱን መስፈርት ያሟላ መሪ አለመገኘቱ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አነጋጋሪ ጉዳይ ነበር ። ድርጅቱ ለአፍሪቃ ሃገራት የሰጠው የመልካም አስተዳደር ደረጃም ዛሬ ይፋ ሆኗል ።

በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተለቀቅን!!! ዜጎችን በፖለቲካ አቋማቸዉ ማሰርና ማዋከብ ይቁም!

ጓዶች ተመልሰና . . . ጉድ አይተን . . . ያዉ የኛ ጉዳይ ሲለመድ እስር እና ዱላ እንደ ተራ ነገር እያየነዉ ምንም አልመሰለኝም ነበር . . . ያሁኑ ግን እኛን እያዋከቡና እየሰደቡ ወደ ዉስጥ ሲያስገቡን ከዉጪ ሆነዉ እኛም ከነሱ ጋር ነን እኛንም ዉሰዱን ባሉ ጓደኞቻችን ላይ የደረሰባቸዉ ድብደባና ስድብ አፀያፊ ብቻ ሳይሆን ምን ያህል ፖሊስ ገለልተኛ እንዳልሆነ በይበልጥ ግልፅ አድርጎታል . . . አንዳንዶቹን በጃቸዉ የነበረ መፅሃፍና መፅሄት በመንጠቅ “አሁን እናንተ ስለፖለቲካ ምን ታዉቃላችሁ” እስከማለት የደረሰ የአምባገነን ወገንተኝነት አንፀባርቀዋል፡፡

Monday, October 14, 2013

ስንቱን አጣን! (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

እንደኢትዮጵያ ባለ ኋላቀር አገር አገር ውስጥ መሠልጠን ብዙ ችግር አለበት፤ እኔ ራሴ በኮምፒዩተር መጻፍ ከጀመርሁ ሠላሳ ዓመት ሊሆነኝ ነው፤ ታዲያ መብራት ጠፋና የምሠራው ባጣ የቆዩ ወረቀቶችን ሳገላብጥ አንድ እአአ በዲሴምበር 26 1965 ከዱሮ ተማሪዬ የተጻፈልኝን ደብዳቤ አገኘሁ፤ በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በነበረ ከአንድ በጣም ጎበዝ ወጣት የተላከልኝ ነበረ፤ ከተመረቀ በኋላ በአንድ ኩባንያ ውስጥ ተቀጥሮ ለጥቂት ዓመታት ሠርቶ ትምህርቱን ለመቀጠል ወደአሜሪካ ሄዶ በሎዝ አንጄለስ አካባቢ ከሚገኝ ትምህርት ቤት ገብቶ ነበር፤ ደብዳቤውን የጻፈልኝ ከዚያ ነው፤ ደብዳቤው ሰባት ገጾች አሉት፤ ከሰባቱ ገጾች አምስቱ ስለኢትዮጵያ ያለውን ስጋት የሚገልጽ ነው፤ በሎዝ አንጀለስ አካባቢ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት በሚያደርግበት ጊዜ ሁሉ ብዙዎቹ የሚያሳዩት የመንደረኛነት ስሜት እያበሳጨው የተማሩት ሰዎች በእንደዚህ ያለ ማኅበረሰባዊ ኋላቀርነት ውስጥ ሆነው ኢትዮጵያ የምትባለው አገር እንዴት መራመድ ትችላለች? እያለ ይሰጋ ነበር።

Prof. Mesfin Woldemariam
Prof. Mesfin Woldemariam
ደብዳቤውን ላቋርጥና ስለሰውየው ትንሽ ልናገር፤ ተማሪ ሆኖ ክፍል ውስጥ ምንም ነገር የማያሳልፍ በጣም ተከራካሪ ተማሪ ስለነበረ አደንቀው ነበር፤ አንድ ጊዜ እንዲያውም የዘውድ መንግሥት ደጋፊ ነኝ አልሁና አንዴት በትከሻው ላይ ጭንቅላት ያለው ሰው ዓመቱን በሙሉ የዘውድ አገዛዝ የሚያደርስብንን በደልና ችግር ሲነግረን ቆይቶ አሁን ደግሞ ያንን ደጋፊ ነኝ ይላል ብሎ ወረፈኝ፤ ልጁን ስለማውቀው አነጋገሩ አሳቀኝ እንጂ አላስቆጣኝም፤ ጥያቄህ ይገባኛል፤ ግን እኔን ሳትወርፈኝ መጠየቅ ትችል ነበር በዬ ቢቀበለውም ባይቀበለውም ለጥያቄው መልሱን ሰጠሁት፤ በኋላም ጥሩ ጓደኛዬ ነበር።

በ1ኪሎ ቁርጥ ሥጋ እና በ12 ድራፍት ብርጭቆ – እውነትና ከሕደት………(ከ ይድነቃቸው ከበደ)


(የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ሀላፊ)
ኪነ-ጥበብ ምኞታችን፣ደስታችን፣አዘናችንን እና ክፋታችን የምናይበት እና የምናዳምጥበት የህይወታችን ነፀብራቅ ነው፡፡ ኪነ-ጥበብ ህይወትን ቀለል አድርጎ ከማዝናናት ባለፈ በገለሰብ አስተሳሰብ ላይ የራሱ የሆነ በጎ ወይም በጎ ያልወነ አስታውጾ የሚያበረከት ጥበባዊ ሃይል ነው፡፡ይህ ሃይል በመልካም አስተሳሰብ ላይ ተመስርቶ ወደ ህብረተሰቡ ውስጥ ሲገባ የሚኖረው አገራዊ ፋይዳ እጅግ በጣም የበዛ ነው፤፤ በመሆኑም ኪነ-ጥበብ እንዲህ አይነቱ ጠቀሜታ እንዲኖረው የሚያደርጉት በጥበብ ሙያ ውስጥ የሚገኙ ባለሙያዎች ናቸው ፤እነኚህ ባለሙያዎች ሙያቸው ከመሬት የፈለቀ ሣይሆኖ በልምድና በት/ት የዳበረ ጥበባዊ ተስጥኦ ነው፡፡

የሀገሩን ችግር ሁሉ ለኦሮሞ ልጆች ብቻ እየሰጠ ሆድ የሚስብሰን ተስፍሽ… ተስፋው ምን ይሆን!

የሀገሩን ችግር ሁሉ ለኦሮሞ ልጆች ብቻ እየሰጠ ሆድ የሚስብሰን ተስፍሽ… ተስፋው ምን ይሆን!
መቅድም
ውድ የድረገጻችን ተከታታዮች ራሴን አሻሽላለሁ ብዬ ትምህርት ጀመሬ ስጠፋ ጊዜ ራሴን ያሸሸሁ መስሏችሁ ምነ ነካህ… ብላችሁ መጨነቃችሁን በተለያየ መልኩ አድርሳችሁኛል፤ ለተጨነቃችሁ እንደተጨነቃችሁልኝ አንድዬ ይጨነቅላችሁ!!! ብዬ መመረቅ እወዳለሁ፤ እነሆ ዛሬ በወዳጃችን ተስፍሽ ማስታወሻ ምክንያት ተከስቻለሁ አንብቡልኝማ፤
OromoWomanበ1992 ዓ.ም እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ማዕከላዊ ስታስቲክስ የሚባል መስሪያ ቤት እሰራ ነበር፡፡ ያኔ “ፈላ” ነበርኩ፡፡ በምሄድባቸው የገጠር ቀበሌዎች የሚያገኙኝ እናቶች በሙሉ መጀመሪያ የሚጠይቁኝ “እናት አለችህ…” ብለው ነበር፡፡ “አዎ” ስላቸው፤ “እንዴት አምና ላከችህ…” ብለው ቀጣይ ጥያቄ ያነሱ ነበር፡፡ አባቶቹም፤ “ይቺ እሳት የሆነች ልጅ” እያሉ የሚያደንቁኝ ከጩጬነቴ ጋር እያያዙ ነበር፡፡  እንደውም ይፋት ውስጥ የሚገኙ የዳውድ አምባ ቀበሌ ሰዎች፤ “በስምንተኛው ሺህ ሽንብራ ጥላ ስር ሆኖ የሚፈርድ ዳኛ ይመጣል” የተባልከው አንተ ነህ ይሉኝ ሁሉ ነበር፡፡ (ለእነርሱ የመንግስት ሰራተኛ ሁሉ ዳኛ ነው) …አስቡትማ የሽንብራን ተክል እንደዛፍ ጥላ የምጠለልበት ምን ያህል ሚጢጢ ብሆን እንደሆነ….!
ታድያ በዛን ወቅት አብዬ ዘውዴ የነገሩኝ መቼም አይረሳኝም፡፡
ለስራ አብዬ ዘውዴ ያሉበት ቤት ጎራ ስል ዕለቱ ሰንበት ነበርና በርካታ ሽማግሌዎች እና ሙሉ ሰዎች ተሰብስበው ወግ ይዘው ነበር፡፡ ታድያ ከመንገድ መሪዬ “ሚሊሻ”  ሙሉጌታ ጋር ሆኜ እነ አብዬ ዘውዴን ያሉበት ስደርስ “ኖር” ብሎ ከመቀመጫው ያልተነሳው ራቁቱን መሬት ላይ ቁጭ ብሎ ሲጫወት የነበረው ህፃኑ የአብዬ ዘውዴ የልጅ ልጅ ብቻ ነበር፡፡
እኛም በአካባቢው ባህል መሰረት በእግዜር ብለን ሰዎቹ ብዙ እንዳይቆሙ ፈጠን ብለን ተቀመጥን፡፡ እኔ የተቀመጥቁት ከአብዬ ዘውዴ አጠገብ ነበር፡፡
“ከአዲሳባ መምጣትህን ሰምተናል፡፡ መንግስት እንዲህ እንዳንተ ያሉ አአንድ ፍሬ ልጆችን አምኖ ስራ ብሎ መላኩ ይገርማል” አሉኝ፡፡

Sunday, October 13, 2013

መሐሙድ አህመድ የቴዲ አፍሮን ኮንሰርት አቋርጦ ሄደ

የኢትዮጵያውያን በመላው አለም መበተን ለአርቲስቶቻችን በተለይም በሙዚቃው ኢንዳስትሪ ለተሰማሩ ጥሩ የገቢ ምንጭ እየሆነላቸው ይገኛል፡፡ አቀንቃኞቻችን በውጪ የሚገኙ ዳያስፖራዎቻችንን ለማዝናናት፣ የአገር ቤት ፍቅራቸውን የሚቀሰቅሱና ስሜት የሚኮረኩሩ ዘፈኖችን በሙዚቃ አልበሞቻቸው በማካተት በአውሮፓ፣ በአውስትራሊያ፣ በመካከለኛው ምስራቅና በአሜሪካ በወኪሎች አማካኝነት ኮንሰርቶችን በማዘጋጀት ኪሳቸውን አደልበው ወደ አገር ቤት ይመለሳሉ፣ አንዳንዶቹም ዶላሩ ጥሟቸው በወጡበት ቀርተው ኑሯቸውን ይመሰርታሉ፡፡