Translate

Saturday, April 29, 2017

ኦባንግ ሜቶ ከከፋ አደጋ ተረፉ!

ኦባንግ ሜቶ ከከፋ አደጋ ተረፉ!


  • “ዳግም የመኖር እድል ተሰጠኝ፤ ተማርኩበት፤ እናንተም ተማሩ”
“ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ ሜቶ በሁሉም ስፍራ፣ በየትኛውም አጋጣሚ ለሚፈልጋቸው ሁሉ “አለሁ” የሚሉ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ዘረኝነትን፥ ዘውገኝነትን፥ ጎሠኝነትን አጥብቀው ይዋጋሉ። ይጸየፉታል። ከዘር ቆጠራና ከቂም የጸዳች ኢትዮጵያን ማየት ህልማቸውና የመጨረሻ ግባቸው ነው።

Tuesday, April 18, 2017

የቴዲ አፍሮ ዜማ ገምጋሚዎች ሲገመገሙ! (አዜብ ጌታቸው)

አዜብ ጌታቸው
Teddy Afro, Ethiopian singer, song writer
ሰላምና ጤና አብዝቶ ይስጣችሁ!
በቅድሚያ ይህን አስተያየት የምሰጠው የቴዲ አፍሮ ቲፎዞ ሆኜ እንዳልሆነ ያዙልኝ። በእርግጥ ከቴዲ አፍሮ ዘፈኖች ሁሉንም ባይሆን ጥቂት የማይባሉትን እወዳቸዋለሁ። ለኔ ከዘፈኑ ይልቅ አርቲስቱ ለህዝቡ ባለው ክብርና ለሃገሩ ባለው ፍቅር ላይ መሰረት ያደረገው ድንቅ ስብዕናው ከሙያ ብቃቱ በላይ ግዝፈት አለው። የአስተያየቴም ዙሪያ ይኽው ነው።መነሻዬ ደግሞ ባለፈው እሁድ በጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ርዕዮት ፕሮግራም የተደረገው ውይይት ነው። ወደ ውስጥ ዘለቅኩ፦

የቴዲ ‘መሠረታዊ ችግር’ ኢትዮጵያ ናት (ካሳሁን ይልማ)

ካሳሁን ይልማ
Teddy Afro New Single 2017 ‘Ethiopia’
Teddy Afro New Single 2017 ‘Ethiopia’
“ቴዲ የጎዳና ተዳዳሪ ገጭተህ ገድለሀል፣ የተገጨውንም ሰው አልረዳህም…” በሚል በቃሊቲ የታሰረበት ወቅት ነበር። የሀገሩ ርዕስ ሁሉ ቴዲ አፍሮ ነበር።
“ያቺ 17 መርፌ ናት፣… አይደለም ባክህ ሼኹ አላሙዲ ነው። ሸራተን አልዘፍንም ስላለ… ኧረ ሸራተን አይደለም.. ለሚሌኒየሙ ሼኹ ጋር እምቢ ብሎ ስታዲየምና ጅማ ስለዘፈነ ነው… ኖ ወያኔዎች እኮ በቀለኞች ናቸው። እናኳን ለቴዲ ለራሳቸውም የትግል ጓዶች የማይመለሱ አረመኔዎች…” አራት ኪሎ የነበርንበት ቦታ በክርክር ሞቅ ብሏል።እኔ እንግዳ ስለነበርኩ አስተያየት ሳልሰጥ አደምጣለሁ።
በዚህ መሐል አንድ ከፍ ያለ ድምጽ “ማን ግጭ አለው?” ሲል ተስተጋባ። ሁሉም በድንገት በመብረቅ እንደተመታ በክውታ ፀጥ ብሎ እርስ-በርስ ተያየ። እኔም ደነገጥኩ። ወዳጄ ደገመው! “ማን ገጭተህ አምልጥ አለው?!” ሲል በአለቅነትና በውስጥ-አዋቂነት ስሜት በትዕቢት ተናገረ።ታዋቂ ጋዜጠኛ እንጂ ታዋቂ ካድሬ መሆኑን አላውቅም

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይና ዋልድባ ገዳም


የዋልድባ ገዳም በህዋሓት መሪዎች በዓይነ ቁራኛ የወደቀው ገና ትግሉ እንደተጀመረ ነው። የዋልድባ ገዳም የህወሓት መሪዎች እንዲወድም ሃሳብ ያቀረቡት በ1973 መጨረሻ አካባቢ ሲሆን፣ አቅማራ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በወቅቱ የህወሓት መናኸሪያ ነበር። በተመቤን ውስጥ የሚገኘው ቦታ በፕሮፓጋንዳ ጽ/ቤት ተሰብስበው ወሰኑ፤ በስብሰባ የነበሩት አመራር ፖሊት ቢሮው በሙሉ ነበር። እነሱም፣ ስብሃት ነጋ፣ አረጋዊ በርሄ፣ ገደይ ዘርአጽዮን፣ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስን እና መለስ ዜናዊ ነበር። በወቅቱ ማ/ኮሚቴ የነበሩ ናቸው።

Thursday, April 13, 2017

ማዕከላዊ፤ የዜጐች ዋይታ ማማ! የስቃይ ማዕከል!


  • በማዕከላዊ ስቃይ ተፀንሶ ይወለዳል፤ ጡት ጠብቶ ዳዴ ብሎ ጐልምሶ ያረጅበታል!! እንደገና አዲስ የማሰቃያ ስልት ይወለዳል!!
  • በማዕከላዊ በንጹሐን ዜጐች ደም የጨቀዩ ገራፊዎች ይርመሰመሱበታል!!