ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !
Translate
Thursday, September 29, 2016
የህወሃት መከላከያ ሰራዊት እጁን እየሰጠ ወደ ኤርትራ እየገባ ይገኛል
በልኡል አለም ሰበር መረጃ ! !
ከምእራብ ትግራይ ወደ ኡምሃጅር የተወረወረ የህወሃት መከላከያ ሰራዊት የግንባር ጦር በገጠመዉ ድንገተኛ የተኩስ ልዉዉጥ ምክንያት እጁን እየሰጠ ወደ ኤርትራ እየገባ ይገኛል። ከሰሜኑ እዝ ከመከላከያ አባላቱ ዉስጥ ያፈተለከዉ መረጃ እንደሚጠቁመዉ ከሆነ የመዋጋት ፍላጎት የሌላቸዉ የህወሃት ወታደሮች በትናንትናዉ እለት ወደ አል-ፉሽቓ (Al fushqa) ሱዳን ድንበር በኩል አምርተዉ ለነጻነት ታጋዮች እጃቸዉን መስጠታቸዉ ታዉቋል። ብዛት ያላቸዉ ቀላልና ከባድ የጦር መሳሪያዎች በምርኮ መግባታቸዉንና የህወሃት መከላከያ ሰራዊት አባላትም መቀላቀላቸዉን የገለጸልን ምንጫችን በምርኮ የሚገቡትን ወገኖች የኤርትራ ወታደሮች ወደ መደበኛ ማረፊያ ማዘዋወራቸዉን ምንጮች አረጋግጥጠዋል፡፡
Thursday, September 22, 2016
በአልሞ ተኳሽ እና በመሬት ስርቆት የታወቀው ህወሓት ለኢትዮጵያ አደጋ ተጠያቂ ነው – አክሎግ ቢራራ (ዶር)
አክሎግ ቢራራ (ዶር)
“እኛ ጠንካራ ለመሆን የምንችለው በመተባበር ብቻ ነው፤ በተጻራሪው፤ እኛ ደካማ የምንሆነው በመከፋፈል ነው።” ጀሪ ሮሊንግ፤ የቀድሞው የጋና ፕሬዝደንት
ብራቮ ሸገሮች፣ ብራቮ ጋዜጠኛ ሕይወት ፍሬ ስብሐት!!
በፍቅር ወርቁ
ለአብነት ያህል ከሸገር ሬዲዮ ወጪ በመንግሥት ስር የሚገኙትም ሆነ የግሎቹ ኤፍ ኤም ሬዲዮኖች በስብሰባው የመጀመሪያ ቀን መንግሥት ለስብሰባው አጀንዳ ይሆን ዘንድ ባሰራጨው ሰነድ ላይ ፈጽሞ ለእኛ የማይመጥንና አገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ፖለቲካዊ ትኩሳትን ከግምት ውስጥ ያስገባ ባለመሆኑ በሚል- በተቃውሞ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የስብሰባው ተሳታፊ ምሁራን አዳራሹን ለቀው እንደወጡ የዘገበው የሸገር ሬዲዮ ብቻ ነው። በአጠቃላይ ከጅማሬው ቀን ጀምሮ የስብሰባውን ድባብ በሚዛናዊ መልኩ መረጃዎችን ለሕዝብ እያቀረባችሁ ነውና ሸገሮች ምስጋና እና አድናቆት ይገባችኋል። ለዚህ ለዛሬው የቁጭት ስሜት ለተቀላቀለበት አስተያየቴ ምክንያት የሆነኝ ግን፤
Thursday, September 1, 2016
የሕወሃት ብጥብጥ እና ሽሽት- ከውስጥ አዋቂ ምንጭ (ክንፉ አሰፋ)
ክንፉ አሰፋ
“Whoever sows injustice will reap calamity.”
“አመራሩ ክፉኛ ከመከፋፈሉ የተነሳም የርስበርሱ ችግራቸው ላይ ተወጥረዋል።” ይላል መረጃው። ቀንደኞቹ የህወሃት አባላት ስርዓቱ እንዳበቃለት ስለተገነዘቡ ንብረት እና ልጆቻቸውን በማሸሽ ላይ ናቸው።
ሕዝቡ ሁሉ እንደተፋቸው በግልጽ እየነገራቸው ስለተገነዘቡ፤ የህወሃት የደህንነት አባላት ሕዝቡን ተተው የራሳቸውን ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሰልሉ ተነግሯቸዋል። “ተጠርጣሪ” የኦህዴድ እና ብአዴን አባላት በነዚህ ሰላዮች ስለተከበቡ በፍርሃት መወጠራቸውን ከራሳቸው አንደበት እየተሰማ ነው።
Subscribe to:
Posts (Atom)