Translate

Monday, March 30, 2015

ሰማያዊ ቀን!

 ስቃይ፣ አፈና፣ ስደት፣ ይብቃን!

semayawi4
የሰማያዊ ፓርቲ እሁድ መጋቢት 20 ቀን በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ አካሂዷል፡፡ በትዕይንቱ የወጣው ሕዝብ ነጻነት እንደሚፈልግ፤ ስቃይ፣ አፈናና ስደት እንደበቃው ባሰማው መፈክር አሰምቷል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ ከፎቶዎች ጋር በማጀብ ከሰልፉ ዝግጅት ጀምሮ በየሰዓቱ በፌስቡክ በለቀቀው መረጃ መሠረት አዲስ አበባን ጨምሮ በጅማ፣ በአዲስ አበባ፣ በሶዶ፣ በአርባ ምንጭ፣ በጭሮ፣ በደብረ ታቦር፣ በወልቂጤና ሌሎችም ከተሞች ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡

Friday, March 27, 2015

ለዓመታት የስለላ ሠራተኛና የአዲስ አበባ ቀጠና ኦፊሰር የነበረች የህወሃት አባል መክዳቷ ታወቀ።


በኢትዮጵያ የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት መዋቅር ውስጥ ተመድበው የሚያገለግሉ የሰለላ ሰራተኞች በጽናት መስራት በማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው ተሰማ።
የጎልጉል ታማኝ የዜና ምንጮች አንዳሉት ድርጅቷ ህወሃትንና ታላቁን የአፈና ተቋም የስለላ ኦፊሰር የነበረችው የመክዳት ውጥኗ እውን የሆነላት ከስድስት ዓመት በኋላ ነው። በተደጋጋሚ ጊዚያት የዲፕሎማት ቪዛ እንዲሰጣት ፓስፖርቷን ለኢሚግሬሽን ብትልክም ያልተሳካላት ይህቺ የስለላ ኦፊሰር፣ በመጨረሻ የተሳካላት ስፔን አገር ለስለላ ስልጠና በማግኘቷ ነው።

Thursday, March 26, 2015

አርበኞች ግንቦት7 – ጉዞአችን ወደ ነፃነት ነው!! መዳረሻችንም የነፃነት አደባባይ ብቻ ነው!!

 
Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracyአለማችን አንባገነን ስታስተናግድ ወያኔ የመጀመሪያው አይደለም። ዘረኛንም እንዲሁ …….. እኛም ስለነፃነት ብለን ለትግል ስንነሳ የመጀመሪያዎቹ አይደለንም …… አለማችን እንደየዘመኑና እንደ የወቅቱ አንባገነኖች ያለ የሌለ የመሳሪያና ወታደራዊ ሀይላቸውን በመጠቀም ህዝብን በፍርሀት አሸማቀውና ረግጠው ለመግዛት ሲውተረተሩ በተደጋጋሚ ታይተዋል። በዚያው ልክ ህዝባዊ ሀይልን መመከት ተስኗቸው ሲንኮታኮቱ በተደጋጋሚ የታየ ወደፊትም አናባገነኖች እስከተከሰቱ ድረስ በህዝባዊ ሀይል ተጠራርገው መቀመቅ ሲወርዱ መታየቱ አይቀሬ ነው ። ህዝብ የወደደውን አስተዳዳሪ እንጂ ረግጦ ሊገዛው የሚፈልገውን አንባገነን ተቀብሎ አያውቅም ፤ዛሬም አልተቀበለም ፤ ነገም አይቀበልም ። ይህን በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ በተደጋጋሚና በጉልህ የሚታይ ግዙፍ እውነት መቼም ተቀብለውና ከታሪክ ተምረው ስለማያውቁ አሳፋሪው ውድቀታቸው በተደጋጋሚ ሲታይ አለ።
ሀገራችን የአለማችን አካል እንደመሆኗ አንባገነኖች ተፈራርቀውባታል። አንባገነኖችም በህዝባዊ ሀይል ተጠራርገውባታል። ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ ትልቅ ወታደራዊ ሀይል የነበረው የትናንቱ ደርግ እንደ እንቧይ ካብ ሲናድ ተመልክተናል። አንባገነኖች መናገር እንጂ መስማት የማችሉ፤ ማየት እንጂ ማስተዋል የተሳናቸው በመሆናቸው እነሆ ዛሬም የወያኔ ዘረኛው ቡድን ህዝባ ላነሳው የነፃነትና የፍትህ ጥያቄ ያለ የሌለውን ወታደራዊ ሀይል በጠራራ ጸሀይ በማሰለፍ መቼውንም ያልተቻለውን ህዝብን በሀይል አሸማቆ ለመግዛት መከራውን ሲያይ ይስተዋላል። ለዚህም ነው ….. ከሌላው የሀገራችን ክልሎች ከፍ ባለ ሁኔታ የህዝባዊ እንቢተኝነት እየታየ ባለበት ጎንደርና አካባቢው በሰራዊት ማጥለቅለቅ የተያያዘው።

የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ለ8ኛ ጊዜ ተመለሰ

• ኢብኮና የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት መልሰዋል
• ‹‹አማራጫችን እንዳናቀርብ እየተከለከልን ነው›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ‹‹አናስተላልፍም›› ብለው መመለሳቸውን ድርጅቶቹ ለፓርቲው በላኳቸው ደብዳቤዎች ገልጸዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ መጋቢት 16/2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የብሔራዊ ራዲዮ በአማርኛ ስርጭት የሚተላለፍ ‹‹መንግስታዊ አወቃቀር›› የሚል የቅስቀሳ መልዕክት ልኮ የነበር ሲሆን ባለፉት 24 አመታት ተግባራዊ የሆነው የጎሳ ፌደራሊዝም ለግጭት መንስኤ መሆኑን በመረጃ ዘርዝሮ ማቅረቡን የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
ይሁንና ኢብኮ ይህን የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ‹‹በተለያዩ ጊዜያት በብሔር ብሔረሰቦች መካከል ተከሰቱ ያሉትን ግጭቶች በመዘርዘር በህዝቦች መካከል ሌላ ግጭት እንዲቀሰቀስና እንዲባባስ የሚያደርጉና ግጭት የሚያራግቡ፣ አንዱን ብሔር ከሌላ ብሔር የሚያገጩ ናቸው፡፡›› በሚል እንደማያስተላልፍ ገልጾአል፡፡ ከዚህም ባሻገር በመልዕክቶቹ ውስጥ ‹የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት›፣ እንዲሁም ‹የህወሓት/ኢህአዴግ ስርዓት› የሚለው አገላለጽ የፓርቲውን ህጋዊ መጠሪያ የማይወክል በመሆኑ›› በሚል እንደማያስተላልፍ ገልጾአል፡፡
በሌላ በኩል እነዚህ ግጭቶች በአሁኑ ወቅትም የቀጠሉና የጎሳ ፌደራሊዝሙ እስካለ ድረስ ብዙ ዋጋ የሚያስከፍሉ መሆናቸውን የገለጸው የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ መልዕክቶቹ ከፓርቲው ማንፌስቶ የወጡ፣ ኢብኮ እንዳለው ለግጭት ሳይሆን ከግጭቶቹ መማር እንዲቻልና አሁን ያለው የጎሳ ፌደራሊዝም ከተስተካከለ ችግሮቹ እልባት እንደሚያገኙ በሚያሳይ መልኩ የተላለፈ መልዕክት ነው ብሎአል፡፡ ‹‹እኛ ያቀረብነው አማራጫችን ነው፡፡ አማራጫችን ስናቀርብ ደግሞ የጎሳ ፌደራሊዝም የፈጠረውም ቀውስም በማሳያነት ማቅረብ አለብን፡፡ ይህን እውነታ የአገር ውስጥና የውጭ ተቋማት ዘግበውታል፡፡ አብዛኛዎቹ መንግስትም ያመነባቸው ናቸው፡፡ ነገር ግን ስርዓቱ የሰራቸው ጥፋቶች ይፋ አውጥተን እንዳናቀርብ ስለተፈለገ መልዕክቱን መልሰውታል፡፡ በግልጽ አማራጫችን እንዳናቀርብ ተከልክለናል›› ሲል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
በተመሳሳይ የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት ‹‹ከሀገሪቱ ሰንደቅ አላማ ጋር የሚጻረር፣ ብሔር ብሄረሰቦችን ወደ አላስፈላጊ ግጭት እንዲያመሩ የሚገፋፋ፣ የሌላ ፖለቲካ ፓርቲን ስም የሚያጎድፍ ይዘት የተካተተባቸው›› ናቸው በሚል መልሷል፡፡ ይህ የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ሲመለስ ለ8ኛ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡

Wednesday, March 25, 2015

ድምፃችን ይሰማ 2ኛውን የሰላማዊ ተቃውሞ ይፋ አደረገ * “ሳንቲም በመሰብሰብ በራስ ላይ እቀባን በማድረግ ለመንግስት ተቃውሞን መግለጽ”

2ኛው አነስተኛ የትብብር መንፈግ ተቃውሞ መርሃ ግብር
ሳንቲም በመሰብሰብና በማጠራቀም ራስ ላይ የመቆጠብ እቀባ በማድረግ ለመንግስት የተቃውሞ መልእክት ማስተላለፍ
ረቡዕ መጋቢት 16/2007
በሰላማዊ ህዝባዊ ትግል ውስጥ ትብብር የመንፈግ እና የቦይኮት ተቃውሞ ከመንግስት ኃይሎች ጋር ሳይፋጠጡ እና አካላዊ ግጭት ውስጥ ሳይገቡ ትብብርን በመንፈግና የቦይኮት እንቅስቃሴዎችን በማድረግ በደል እያደረሰ ለሚገኘው አካል የተቃውሞ መልእክት የማተላለፍ ስልት ነው፡፡ የትብብር መንፈግ ተቃውሞዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ዓይነቶች ያሏቸው ሲሆን በአገሪቱ ውስጥ የሚገባንን የዜግነት መብት እስክናገኝ ድረስ ለመታገል ቆርጠን በገባንበት ታላቅ ህዝባዊ ትግል ውስጥ ካሁን ቀደም እምብዛም ሳይሞከር ቆይቷል፡፡
yisema
ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተቃውሟችን ወደቦይኮት እና ትብብር የመንፈግ ስልቶች እንደሚሸጋገር፣ ይህም አደባባይ ተኮር በሆኑ ተቃውሞዎች የገዛ ህዝቡ ላይ ጥይት ለመተኮስ የማያመነታው መንግስት ጡጫ እንዳያሳርፍብን ለመከላከል እንደሚያስችል መገለጹ ይታወሳል፡፡

Tuesday, March 24, 2015

ESAT Efeta 23 March 2015 Ethiopia | ESATTUBE

ESAT Efeta 23 March 2015 Ethiopia | ESATTUBE

ጎንደር ዝምታውን ሰብሯል – የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዘዋል

መጋቢት ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን በሰሜን ጎንደር አካባቢ የታየውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ የአገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ካለፈው ሃሙስ ቀን ጀምሮ በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዛዋል።Ethiopian soldiers in Barentu
የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአየር ሃይል አባላት ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ ከግቢ እንዳይወጡ ሲታዘዙ የተወሰኑት ደግሞ ከደብረዘይት እና ድሬዳዋ አየር ሃይል  ወደ መቀሌ አምርተዋል። ብዛት ያለው የእግረኛ ሰራዊትም ወደ ኤርትራና ሱዳን ድንበሮች አቅንቷል።
ወታደራዊ ልምምዶችና አዳዳስ ምልመላዎችም እየተካሄዱ መሆኑንም ምንጮች ገልጸዋል።
ማንነታቸው በውል ያልታወቀ የተቃዋሚ ሃይሎች ጎንደር ከተማ ውስጥ የሚሊሺያ አዛዥ የሆነውን ኮማንደር ተፈራን ገድለው  ካመለጡ በሁዋላ፣ እነሱን ለመያዝ መጋቢት 12 አርማጭ ልዩ ቦታው እንኮይ ተራራ ላይ በተደረገ ጦርነት ፣ ከተቃዋሚዎች በኩል ሻምበል ይርዳውና
አዲሱ የተባሉ  ሲገደሉ፣ ከመንግስት ታጣቂዎች በኩል ደግሞ  የልዩ ሃይል አባል የሆነው  እባበይ እንዲሁም አንድ ስሙ በውል ያልታወቀና ሁለት የሚሊሺያ አባላት ተገድለዋል። ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ጀምሮ እስከ ምሽት በቀጠለው የተኩስ ልውውጥ፣ አንድ ተማሪ በመንግስት
ሃይሎች ተገድሏል። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ምሽት ላይ አካባቢውን ጥለው መውጣታቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስትን አስተያየት ለማካተት የተደረገው ጥረት አልተሳካም።