Translate

Wednesday, August 31, 2016

ሰበር ዜና! የትግራይ ወጣቶች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ትእዛዝ ተሰጠ


የትግራይ ወጣቶች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ትእዛዝ ተሰጠ 
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱ እና ከፍተኛ የህወሓት ሹማምንቶች እምነት የሚጣልባቸው የፓርቲው ወጣት አባላትን ስብስበው ጠንካራ ትእዛዝ አስተላለፉ::

አገዛዙ በዐማራ ሕዝብ ላይ ይፋ ጦርነት አውጇል፤ በባሕር ዳር የሰባታሚት ማረሚያ ቤት ዐማሮች በጅምላ ተቀብረዋል


ዐማራ ዛሬ (ነሃሴ 25 ቀን 2008 ዓ.ም) 
Muluken Tesfaw #AmharaResistance
አገዛዙ በዐማራ ሕዝብ ላይ ይፋ ጦርነት አውጇል፤ በባሕር ዳር የሰባታሚት ማረሚያ ቤት ዐማሮች በጅምላ ተቀብረዋል
• የአብራጂራ ሕዝብ የመከላከያ ታንክ ላይ ሰንደቅ ዓላማ ተከለ 
• የዐማራ ተጋድሎ ከእለት ወደ እለት እየጨመረ ሒዷል፤ የጋይንት፣ የቋሪትና ግምጃ ቤት አካባቢዎች ከጠላት ቀጣና የጸዱ ናቸው 
• የትግሬ መከላከያ ሠራዊት በወገራ አውራጃ ሕጻናትና አቅመ ደካሞች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈጽሟል
• የደባርቅ፣ የመተማ፣ ሸኽዲና ሽንፋ ከተሞች በቃጠሎ ታፍነው ውለዋል
• በቡሬ ትንሳኤ ሆቴል ግቢ 2 አስከሬን ተደብቆ ተገኘ
• በወንበርማ ሽንዲ ወረዳ የዐማራ ተጋድሎ ሁለተኛ ቀኑን አስቆጥሯል
• በእጅባራ ሕዝብና መከላከያ ተፋጠዋል

ሕወሃት የትግራይ ልዩ ሃይል አባላትን የአማራ ልዩ ሃይልን የደንብ ልብስ አልብሶ አማራውን እንዲጨፈጭፉ አሰማርቷል - See more at: http://ecadforum.com/Amharic/archives/16861/#sthash.4zGhse80.dpuf

Ethiopia, special force members in the Amhara region
በማኅበራዊ ገጾች እየተሰራጩ ያሉ ታማኝነት ያላቸው መረጃዎች እንደሚያመለክቱት “የአማራ ልዩ ሃይል አቋም ይዟል” ተቃውሞ በማሰማት ላይ ባሉ ወገኖቹ ላይ አልተኩስም ብሏል። ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ሕወሃት) ይህ ነገር እጅግ አስደንግጦታል።

Tuesday, August 23, 2016

በቂሊንጦ ወህኒ ቤት ታስረው የሚገኙ እስረኞች የሶስት ቀን ብሄራዊ ሃዘን እንዲታወጅ ጠየቁ


ኢሳት (ነሃሴ 17 ፥ 2008) 
በተለያዩ ክልሎች ለዴሞክራሲ፣ ፍትህና ነጻነት ሲሉ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖችን ለማስታወስ ኢትዮጵያውያን ከነሃሴ 19 እስከ 21 ፣ 2008 የሚቆይ የሶስት ቀን ብሄራዊ ሃዘን እንዲታወጅ በቂሊንጦ ወህኒ ቤት ታስረው የሚገኙ እስረኞች ጠየቁ። 
በአቶ በቀለ ገርባ፣ ደጀኔ ጣፋ፣ አዲሱ ቡላላ፣ ጉርሜሳ አያኖ፣ ዮናታን ተስፋዬ፣ ፍቅረማሪያም አስማማው፣ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ እና ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በጋራ ተጽፎ ለኢሳት የደረሰው ደብዳቤ፣ “ብሄራዊ የሃዘን ቀን የሚታወጀው የዲሞክራሲና የፍትህ ጥያቄ አንግበው የተሰው ወገኖቻችንን በልባችን ውስጥ ህያው ሆነው እንደሚኖሩ ለማረጋገጥና እነሱም የወደቁለትን አላማ በትግላችን እንደምናሳካው ቃል ለመግባት እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸውም አጋርነታችንን ለማሳየት ነው” ሲል ያስረዳል። 

Sunday, August 21, 2016

ህወሃት በሕዝብ ላይ የደገሰው በዶ/ር ደብረጽዮን አንደበት

ህወሃት በሕዝብ ላይ የደገሰው በዶ/ር ደብረጽዮን አንደበት

(ክንፉ አሰፋ)
haile tplf debretsion
ባለፈው ሳምንት ጌታቸው ረዳ ከአልጃዚራ ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ ጋር ተጋፍጦ ነበር። አንድ ጥያቄ ቀረበለት። “በራሳችሁ የምትተማማኑ ከሆነ ለምን የተባበሩት መንግስታት ታዛቢዎች እንዳይገቡ ከለከላችሁ?”
ሚኒስትር ጌታቸውም። “የተባበሩት መንግስታት አያስፈልገንም። እኛው ራሳችን ከህዝቡ ጋር እንነጋገራለን።” ሲል ነበር የድፍረት መልስ የሰጠው።

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ቃለምልልስ ሰጠ “ከባለፉት 9 ወራት ብቻ ከ1 ሺህ በላይ ኦሮሞዎች በኢትዮጵያ ተገድለዋል – ወደዚያ አልመለስም”

 አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በሪዮ ኦሎምፒክ በማራቶን ውድድር የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ካመጣ በኋላ እጁን ወደላይ በማጣመር መንግስትን የተቃወመው ባለፉት 9 ወራት ብቻ ከ1 ሺህ በላይ ኦሮሞዎች በመንግስት ጸጥታ ኃይሎች በመገደላቸውና በርካቶችም በመታሰራቸው ነው አለ:: አትሌቱ በቃለምልልሱ ላይ እንዳለው ወደ ኢትዮጵያ ቢመለስ ለህይወቱ አስጊ በመሆኑ ወደ ኢትዮጵያ እንደማይመለስ አስታውቋል:: ቃለምልልሱን በቭዲዮ ይመልከቱት::

Saturday, August 13, 2016

ስለ ወያኔ መውደቅ ሳስብ(ሄኖክ የሺጥላ)

ስለ ወያኔ መውደቅ ሳስብ ፥ አይኖቼ በደስታ እንባ ይሞላሉ ። እንባውን የፈጠረው ይቺን ቀን ማየት ያልቻሉትን ብዙዎች ስለማስብ ነው ። ዛሬ ጎንደር ላይም ሆነ ኦሮሚያ ላይ የተነሳው ትግል ፥ ባንድም ይሁን በሌላ መልኩ የዛሬው ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት አእላፋት ህይወታቸውን ገብረውበታል ። እልፎች ታስረዋል ፥ ህልቆዎች ከስራ ፥ ከሃገር ተባረዋል ፥ ቆጥረን የማንጨርሳቸው ሊህቃኖች ተንገላተዋል ፥ ታድርደዋል ። ህፃናቶች ተገለዋል ፥ እናቶች ፀጉራቸውን ተላጭተው አሸባሪ ተብለው ታስረዋል ። ብዙዎች በርሃ ወርደዋል ፥ እጅግ ብዙዎች ሞተውለታል ፥ ብዙዎችም ሞተውበታል!

በደብረማርቆስ ንግድ ቆሟል | አልሞ ተኳሾች ብዙ ሰው አቁስለዋል

በደብረማርቆስ ንግድ ቆሟል | አልሞ ተኳሾች ብዙ ሰው አቁስለዋል
(ዘ-ሐበሻ) በጎጃም ደብረማርቆስ የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር አልሞ ተኳሽ (ስናይፐር) ፖሊሶችን መጠቀሙ ተሰማ:: እነዚህ አልሞ ተኳሾችም ያቆሰሏቸው ስዎች ቁጥር ከ20 እንደሚበልጥ ዘ-ሐበሻ በስልክ ያነጋገረቻቸው የደብረማርቆስ ነዋሪዎች ገልጸዋል::

በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ህዝብ ላይ የታቀደው ድቡቁ የህወሓት ሴራ ሲጋለጥ

A Quest for Identity and Geographic Restoration of Wolkait-Tegede, Gondar, Amhara, Ethiopia.
በቅድሚያ ይህንን ድብቅ የወያኔ ሴራ የሚያጋልጠውን ሰነድ ከነትርጉሙ የላኩልንን ወገኖች ከልብ እናመሰግናለን።

Friday, August 12, 2016

በጎጃም መንግስት ፈረሰ እየተባለ ነው

Alemnew Mekonnen
የአማራውን ሕዝብ “ልፋጫም” ብሎ የተሳደበዉና ሕወሃት ጉልበት ብቻ አመራር ላይ የተቀመጠው አለምነህ መኮንን ባረፈበት ሆቴል ድብደባ እንደተፈጸመበት መረጃዎች ይጠቁማሉ። አለመነህ በሕወሃት ታጣቂዎች ታጅቦ ሾልኮ ከአካባቢው ያመለጠ ሲሆን፣ ብዙዎች ሰዉዬው አይኑን በጨው አጥቦ በዚህ ወቅት ሕዝብ ፊት ለመቅረብ መድፈሩ አስገርሟቸዋል።
በጎጃም እነብሴ ሳር ምድር፣ቋሪት እና ሌሎች ደጋማ ቦታወች ያሉ አርሶ አደሮች መንግስት ፈርሷል የሚል ወሬ በመስማታቸው የቀበሌ ሊቀመንበር እና ፀሃፊወችን ቤታቸውን በድንጋይ እና በጥይት እንደደበደቡ እየተነገረ ነው። እስካሁን አራት የገጠር ሚሊሻወች የተገደሉ ሲሆን አቶ ቢያድጌ አለሙ የሚባል ሊቀመንበር መገደሉ ታውቋል።

የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች የመፍትሄ ያለህ እያሉ ነው


ነሃሴ  ፮ ( ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተቃውሞ እየተናጡ ባሉት የአማራ እና የኦሮምያ ክልሎች ዙሪያ የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና የክልል ስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም የፌደራል ባለስልጣናት የቪዲዩ ኮንፈረንስ  እያደረጉ ነው፤ ስብሰባው መፍትሄ ማመንጨት አልቻለም።

“ሲመረው የማይነሳ ህዝብ የለም ባለም፣” አለ አቦይ ስብሐት ነጋ! (ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የኢትዮጵያውያን የጸደይ አብዮት በ2016 የክረምት ወቅት መጀመሩ ነውን? 
አንድ ህዝብ ታምቆ ፣ ታምቆ ማለት ተጨቁኖ  በዘመንታ አይቆይም ። ዩኒቨርሳል universal  ማለት ነው ።  አንድ ህዝብ እንደ ህዝብ መጠን  በዓለም ታሪክ  አንዳስቀመጡት አንደፈለጉት  የሚቀመጥ አይደለም። ሲመረው ይፈነዳል።  ይሄ ዓለም አቀፋዊ  እውነታ /universal  truth  ነው። ሲመረው የማይነሳ ህዝብ የለም ባለም።  በታሪክም /historically።  አሁንም።  ለወደፊትም ። (አዛውንቱ የእንጨት ሽበት ባለቤቱ አቦይ ስብሀት ነጋ፣ የዘ-ህወሀት ጭንቅላት፣ ንጉስ፣ የክርስትና አባት፣ ተጽእኖ ፈጣሪ እና የአለቆች ሁሉ አለቃ (ካቦ) እ.ኤ.አ በ2015 ከተናገረው የተወሰደ።)  (ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ ።)
በዘ-ህወሀት ላይ የፍርዱ ቀን ደረሰ ማለት ነውን?
Protests in Ethiopia
እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 “የኢትዮጵያውያን የጸደይ አብዮት በበጋው ወቅት መጀመሩ ነውን በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ በመምጣት ላይ ስላለው የጸደይ አብዮት ትችት አቅርቤ ነበር፡፡“

Breaking News: A Breakthrough agreement between ODF and Patriotic G7

Memorandum of Understanding (MoU)
Oromo Democratic Front (ODF) and Patriotic Ginbot 7 (PG7)
lencho-leta-and-berhanu-nega
August 11, 2016

Thursday, August 11, 2016

በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን ተክትሎ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ደኅንነት ሁኔት አስጊ መሆኑን ሪፕሪቭ ገለጸ

በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን ተክትሎ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ደኅንነት ሁኔት አስጊ መሆኑን ሪፕሪቭ ገለጸ

ነሃሴ  ፬ ( አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ100 በላይ ሰላማዊ ዜጎች መብታቸውን በሰላማዊ ሰልፍ መጠየቃቸውን ተክትሎ በኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ተክትሎ ላለፍት ሁለት ዓመታት ከየመን ታፍነው የተወሰዱት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሞት ፍርድ ይፈረድባቸዋል የሚል ስጋት እንደፈጠረባቸው ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሪፕሪቭ  አስታውቋል።

በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ የተለያዩ አለማቀፍ ሚዲያዎች ሽፋን እየሰጡት ነው።


ነሃሴ  ፭ ( አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታላላቅ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃንና የሰብዓዊ መብት ተቋማት በኢትዮጵያ በተለይ በኦሮሚያና አማራ ክልል ውስጥ የተካሄደውን የጅምላ ግድያ በስፋት አትኩሮት ሰጥተው ዘግበውታል። በዋና ከተማዋ አዲስ አበባን ጨምሮ መላውን ኦሮሚያ ክልል በጎንደርና አካባቢው በባህርዳር የተካሄዱት ሰላማዊ ሰልፎች በጸጥታ አስከባሪዎች በግድያ ምላሽ መሰጠቱን ቢቢሲ ዘግቧል። ሁለቱ ታላላቅ የአገሪቱ ብሔረሰቦች  አነስተኛ ቁጥር ባለው አንድ ብሄት በመሳሪያ ሃይል በግዳጅ መገዛታቸውንም ቢቢሲ የኢትዮጵያን ሕዝብ ቁጥር በመቶኛ ስሌት ቀመር ይዞ በመውጣት አሰነብቧል። 6.1% የሚሆኑት የትግራይ ብሔር ተወላጆች 34.4% የሚሆኑትን ኦሮሞችና 27% የሚሆኑት አማራዎች ያገለለ አስተዳደር መመስረታቸውን፣  የስልጣን፣ የሃብት፣ ወታደራዊና ደኅንነቱ በህወሃት ቁጥጥር ስር መውደቁን ቢቢሲ በመረጃ አስደግፎ ዘግቧል። የኦሮሚያ ክልልን የመሬት ቅርምትና የወልቃይት ሕዝብን የማንነት ጥያቄዎችም  ሰፊ ሽፋን አግኝተዋል።

ወልቃይት የማን ነው? የማይረባ ጥያቄ | ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

ነሐሴ 2008
አንድ
በነገረ አስተሳሰብ ወይም በአስተሳሰብ ሕግ (ሎጂክ) ትምህርት ላይ አንድ የማስታውሰው ምሳሌ አለ፤ ‹‹ሚስትህን መደብደብ ትተሃል ወይ?›› የሚል ጥያቄ ነው፤ ጥያቄው የሚነሣው ጠያቂው አውቃለሁ ብሎ ከያዘው እውቀት ወይም እምነት ነው፤ ስለዚህም ጠያቂው የሚፈልገው ጥያቄ ለማስተላለፍና መልስ ለማግኘት አይደለም፤ ጠያቂው የሚፈልገው በጥያቄ መልክ የራሱን ‹‹እውቀት›› ወይም እምነት ለተጠያቂው ለማስተላለፍና ተጠያቂውን የጠያቂው ደቀ መዝሙር ለማድረግ ነው፡፡
Pro-Mesfin-300x2001.jpg
ሚስትህን መደብደብ ትተሃል ወይ? መልስ የሌለው ጥያቄ ነው፤ ‹‹አዎ›› የሚል መልስ ሰውዬው ሚስቱን ሲደበድብ እንደነበረ አመነ ማለት ነው፤ ‹‹አልተውሁም›› ከአለ በራሱ ላይ መሰከረ፤ ሁለቱም መልሶች ተጠያቂውን የሚያስወነጅሉ ስለሆኑ መልስ አይደሉም፤ ከዚያም በላይ ጥያቄው ትክክል አይደለም፤ የማይረባ መጥፎ ጥያቄ ነው፡፡
‹‹ወልቃይት የማን ነው?›› የሚለው ጥያቄ ትክክል አይደለም፤ የማይረባና መጥፎ ጥያቄ ነው፤ ጠያቂው የሚፈልገው መልስ የአማራ ነው፤ የጎንደር ነው፤ የትግሬ አይደለም፤ የሚል ነው፤ ነገር የሚገባው ተጠያቂ ጥያቄውን ጠያቂው በፈልገው መልክ አይመልስለትም፤ ሊመልስለትም አይገባም፤ ወልቃይት የኢትዮጵያ ነው የሚል መልስ አይፈለግም፤ የማይፈለግበትም ምክንያት ‹‹ወልቃይት የኢትዮጵያ ነው፤›› ማለት ወልቃይትን ከጎሠኛነት አጥር ስለሚያወጣ ነው፤ የትግራይ አይደለም፤ የአማራ አይደለም፤ የኢትዮጵያ ነው፤ አሁን ትግራይና አማራ የኢትዮጵያ ናቸው፤ ይህ ከተባለ በኋላ ወልቃይት የትግራይ ነው? ወይስ የአማራ? የሚለውን ጥያቄ ማንሣት የጎሠኛነት ጥያቄ ነው፤ የኢትዮጵያዊነት ጥያቄ አይደለም፤ ጥያቄው የማይረባ የሚሆንበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው፤ ሁለተኛው ምክንያት የጎሠኛ ጥያቄ በመሆኑ የወያኔን የጎሠኛ መመሪያ የሚያከብር መሆኑ ነው፡፡

Wednesday, August 10, 2016

እነ አባይ ጸሃዬ አሜሪካ ነበሩ፤ “ኦሮሞና አማራ ተባበሩብን፤ ሰግተናል”

አሜሪካ ህወሃትን ለማዳን ጥገናዊ ለውጥ እንዲደረግ ፈልጋለች

oromo and amhara

የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ከፍተኛ አመራር አባይ ጸሃዬ፤ ሳሞራ የኑስን ጨምረው ሌሎች ከፍተኛ የህወሃት ባልደረቦቻቸውንና በመያዝ አሜሪካ አገር አጭር ቆይታ አድርገው መመለሳቸውን ጎልጉል አረጋግጧል። አሜሪካ በግል የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማነጋገር ውሉ ባግባቡ የማይታወቅ የሽግግር ሃሳብ ለመተግበር ማሰቧ ተሰምቷል። የሽግግር ሃሳቡ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) የያዘውን ስልጣን በተወሰነ መልኩ የሚያስቀጥል በመሆኑ ለአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች ሃሳብ የሚያቀርቡ ተጽእኖ ፈጣሪዎች አሜሪካ ይህንን መሰሉን አቋም እንድትቀይር እየወተወቱ ነው። ለኦባማ አስተዳደር ፖሊሲ አውጪዎች ዕቅድ ለማቅረብ እነዚሁ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ዝግጅት አላቸው።