Translate

Wednesday, June 29, 2016

“የአማራና የኦሮሞ ምሁራን መነጋገር አለባቸው” – ጀዋር መሐመድ አዲስ ቃለምልልስ ከሕብር ራድዮ ጋር

<…በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚቃወምና የድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ ወደፊት ተጽዕኖ የሚያሳድር የሕግ ረቂቅ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ንዑስ ኮሚቴ በሁለቱም ፓርቲ አባላት ሙሉ ድጋፍተቀብሎት ለሴኔቱ ተመርቷል ።ይህ ሕግ ሆኖ ሲወታ የአሜሪካና የሕወሓትን ግንኙነት ይለውጣል። ይህ እንዲሆን ግን የተደረገው ስትራቴጂ..በእርግጠኝነት የምናገረው በወልቃይት፣በቅማንት ፣ለሱዳን በተሰጠው መሬት ሳቢአ የተገደሉት ንጹሃን ቁጥር በኦሮሚያ ተቃውሞውን ተከትሎ ከተገደሉት በእጥፍ ይበልታል።ይህን ግን ተከታትሎ በኦሮሚያ እንደተደረገው የእያንዳንዱ ሟች ብቻ ሳይሆን በተለይ የአካባቢው ፖሊስም ሆነ ልዩ ሔኢል በግድያ ሲሳተፍ የገዳዩ ማንነት ጭምር ቢወታ ኖሮ ከኦሮሚአው ጋር አንድ ላይ ማቀናጀት ይቻል ነበር ግን ያ አልሆነም። በአማራ የተፈጸመውን ግድያ ተከታትሎ የዘገበው የለም። ስራ አልተሰራም ይሄ ቢሰራ ኖሮ…> ጃዋር መሐመድ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ዳይሬክተር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
ጃዋር
የአማራና የኦሮሞ ምሁራን መነጋገር አለባቸው ይላል
ሕዝቡ ለሺህ ዓመት አብሮ የኖረ አንዱ ከአንዱ ጋር የተሳሰረ የአንዱ ችግር ሌላውን የሚመለከተው ነው
የረቂቁን ወደ ሴኔት ማለፍ ተከትሎ የዌአኔ ባለስልታናት አሁንም የጀመሩትን ሩጫ አጠናክረው ይቀጥላሉ እና ሌሎችንም ሀሳቦች በቃለ መጠይቁ ተካተዋል።

በአ.አ. 17 የፖሊስ አባላትና 1 የወረዳ ባለስልጣን ተገደሉ – መንግስት የሞተው 1 ፖሊስና 1 ባለስልጣን ብቻ ነው እያለ ነው

(ዘ-ሐበሻ) በመላው ኢትዮጵያ ገዢው የሕወሓት መንግስት ሕዝብን በየፊናው እያሰቃየ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሕዝብ የራሱን እርምጃ በባለስልጣናቱና ጠመንጃን በታጠቁ ሰዎች ላይ መወሰድ ጀምሯል:: ዛሬ በአዲስ አበባ የነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 17 የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት እና አንድ የወረዳ ከፍተኛ ባለስልጣን መገደላቸው ታውቋል::
በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ በተለምዶው ሃና ማርያም አካባቢ የሕዝብን ቤት ለማፍረስ የተያዘውን እቅድ ለማስፈጸም የከተማው አስተዳደር ከሕዝቡ ጋር በተፋጠጠበት ወቅት ከሕወሓት ደህንነት ቢሮ የተላኩ ሰምቶ አደሮች ባነሱት ግርግር የተነሳ; ተነሳ በተባለው ግጭት ፖሊሶች ወደ ህዝብ መተኮስ በመጀመራቸው ህዝቡ የራሱን እርምጃ በመውሰድ በ17 የፖሊስ አባላት እና በወረዳው ባለስልጣን ላይ እርምጃ ወስዷል::

ከህዝቡም ወገን በርካታ ሰዎች እንደቆሰሉ የተሰማ ሲሆን ፖሊሶችም እንዲሁ እንደተጎዱ መረጃው ይጠቁማል::
ይህንን ብጥብጥ ህዝብ እንደጀመረው ለማስመስል የደህንነት አባላቱ ተንኩሰው መሰወራቸውን የሚናገሩት የአይን እማኞች ሆን ብሎ ቤቴ አይፈርስብኝም ያለውን ህዝብ ለማሸማቀቅ ነው ብለዋል::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ መንግስት በዛሬው ብጥብጥ 1 ፖሊስ እና አንድ የወረዳ ባለስልጣን መገደሉን ገልጾ ጥቃቱን ሕገወጦች ያደረሱት ሲል ወንጅሏል:

Tuesday, June 28, 2016

“የትግራይ ሰዎች ተፈናቀሉ” አጉል የወያኔ ጩኸት በሽንፋ – ጎንደር

ሊቁ  እጅጉ እና አዳነ አጣናው
ላለፉት 40 ዓመታት አገርን  በማፈራረስ አባዜ  የተጠመደው  ወያኔ  በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ምክንያቶችን  በመፍጠር  ሲፈልግ  የትግራይ  ሕዝብ  ልጆቹን  ስለሰዋ  የትግራይ  ግዛት መስፋት አለበት፣ በሌላ  ጊዜ ደግሞ አባላቶቹን  አደራጅቶ  በተለያዩ   የሀገሪቱ  ክፍሎች በማስፈር፣ ብሎም  ከባንክ ብድር  በገፍ እንዲያገኙ በማድረግ  በሰፈሩባችቸው  አካባቢዎች ሁሉ  የንግድና  የእርሻ ሥራዎችን  በበላይነት እንዲይዙ አድርጓል። ስለሆነም  ወያኔዎች ተደራጂተው በሰፈሩባችው አካባቢዎች  ሁሉ  የአካባቢው ተወላጅ  በራሱ ቀዬ የበይ  ተመልካች  እንዲሆን  ተደርጓል ። በአጭሩ  ወያኔዎች ለ25 ዓመታት በመላ  ሀገሪቱ  የሚያካሂዱት  ዘረፋና የማያባራ የግዛት ተስፋፊነት ሌላው ቀርቶ በራሳቸው አምሳል የፈጠሯቸው  አጫፋሪ  የጎሣ  ድርጅቶች  እንኳ  ገደብ  የለሹን የወያኔ  ሁሉም  የኔ ይሁን በሽታ  ሥራ ላይ ለመትግበር ከአቅማቸው በላይ እየሆነ መጥቷል።
“<በጅብ  ጅማት  የተሰራ ክራር  ዜማው ሁልጊዜም  እንብላው> እንደሚባለው  ወያኔ ዛሬም እንዳመሰራረቱ ታላቋን  ትግራይ  የመፍጠር  በሽታው በተጠናከረ  መልኩ  ቀጥሏል። ወያኔ በጠባብነት ታዉሮ  አትዮጵያን  በስፋትና በአኩልነት ሊመራ  ቀርቶ እወክለዉ አለሁ የሚለውን  ትግራይን  እንኳ በአግባቡ በእኩልነት መወከል የተሳነው  የአንድ  አካባቢ ስብስብ  ነው፡፡. ለይስሙላ የትግራይ  ሕዝብ  ወኪል  ነኝ  ቢልም  እውነቱ  ግን በበላይነት እና በዋናነት የሚመራው  ከአርባ ዓመት በፊት አሽአ ማለትም አድዋ፣ ሽሬ፣ አክሱም ብሎ የመገንጠል ዓላማ አንግቦ  በሕቡእ  የተደራጀው ከሦስት አውራጃዎች በመጡ እጅግ በጣም ጠባብ  ግለሰቦች ሲሆን  ከኢትዮጵያ ጎሳዎች ያልተቀላቀልን  ‘ንጹሕ ትግሬ  እኛ  ነን የሚሉ በዝምድና  እና በጋብቻ የተሣሰሩ የአውራጃ አንጀኞች ናቸው።

Wednesday, June 22, 2016

ሰበር ዜና… እስከ አፍናጫቸዉ የታጠቁ ከ20 እስከ 25 ሺ የሚጠጉ የአርበኞች ግንቦት7 እና የትህዴን ወታደሮች በጾረና ግንባር ነበሩ

በልኡል አለም

Patriotic Ginbot7 attacked TPLF troopsበህወሃት አመራር እና በሰሜኑ እዝ ዉስጥ በሚገኙ የወታደራዊ ደህንነት መረጃ ክንፎች በተለይም ወታደራዊ እግረኛ ቃኘዉ መረጃ፣ የቴሌስኮፕ ምልከታ ቃኘዉ መረጃ፣ የሬዲዮ ጠለፋ አገልግሎት መረጃ፣ የሳተላይት ቅኝት መረጃ፣ የአስተኳሽ አስተላለፍ መረጃ፣ የመግቢያና መዉጫ ኮድ ሚስጥር አሳላፊ አመራር መረጃ ምድቦች ባጠቃላይ ወደ ግምገማ እንዲገቡ ከመከላከያ ሚኒስቴር ቀጥታ ትእዛዝ ቢተላለፍም የወታደራዊ ደህንነቱ አጣብቂኝ ዉስጥ መግባቱን ታማኝ ምንጮች ጠቅሰዋል።

ህወሃት “አምባሳደሮችን” በታማኞቹ ሊተካ ነው!

“የማይታመኑ ከሆነ [አለመታመናቸውን] ማሳየት አለባቸው”

ambassadors

በተለያዩ አገራት የሚገኙ አምባሳደሮች በወሳኝ የህወሃት ሰዎች ሊተኩ እንደሆነ ተነገረ፡፡ በህወሃት ውስጥ ያለው ፍርሃቻና አለመረጋጋት ለሁኔታው አስገዳጅነት ምክንያት ሆኖ ቀርቧል፡፡ ህወሃት ለዓመታት ያገለገሉትን ሎሌዎች የማያምናቸው ከሆነ እነርሱም “አለመታመናቸውን” ማሳየት ይገባቸዋል፡፡

Wednesday, June 15, 2016

ኤርትራውያን ጥላችን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሳይሆን ከወያኔ ጋር ነው አሉ

(ECADF)— ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ሕወሃት) ሰኔ 7 ቀን 2008 በጾረና ግምባር ወደ ኤርትራ ግዛት ተንቀሳቅሶ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የኤርትራ ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ባወጣው አጭር መግለጫ “የሕወሃት አገዛዝ በፆረና ማዕከላዊ ግንባር ጦርነት ከፍቶብናል” ነበር ያለው።Eritrea says the TPLF Regime launches an attack
የኤርትራ መንግስት “ኢትዮጵያ ጥቃት ፈጸመችብኝ” አለማለቱ ኤርትራውያን የኢትዮጵያን ሕዝብ በዘረኛና አምባገነን አፋኝ ሥርዓት ስር ደፍጥጦ እየገዛ ያለው በሕዝብ ያልተመረጠና ከአንድ አነስተኛ የህዝብ ብዛት ካለው ብሄር የወጣ እራሱን የብሄረሰቡ ነጻ አውጪ እያለ የሚጠራ አናሳ ቡድን ሕወሃት እንደሆነ በሚገባ ስለሚያውቅ ነው።

የህወሀት ወንጀለኞች ያልተመዘገበ ቦንድ ባሜሪካ ሲሸጡ ማጅራቸዉን ተያዙ!

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
T-TPLF Criminals Nabbed in America Selling Unregistered Bonds!
ባለፈው ሳምንት የዩኤስ አሜሪካ የቦንድ እና አክስዮን ልውውጥ  ኮሚሽን/U.S Securities and Exchange Commission (SEC) በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) ለአራት ዓመታት ያልተመዘገበ ህገ ወጥ የቦንድ ሽያጭ በማካሄድ ያገኘውን 6.5 ሚሊዮን ዶላር እንዲመልስ  (ዲስጎርጅመንት ወይም በትክክል ስተርጎም “ማስተፋት”)  ቅ ጣት  በይኖበታል ።

ሰበር ዜና… ዛሬም ቁስለኞች ወደ ትግራይ እየተጋዙ ነዉ!!

ልኡል አለም
በትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን የተለኮሰዉን የጦር ጸብ አጫሪነት ኤርትራ በቀላሉ አልተመለከተችዉም! በመሆኑም በኢትዮ ኤርትራ አዋሳኝ ድንበሮች ዙሪያ ከፍተኛ መጠን ያለዉና ዘመናዊ የሆነ ሰራዊት ማለትም የአየር ወለድና ባሕር ሐይል አጠቃላይ ፊቱን ወደ ትግራይ ነጻ አዉጪዉ ጦር በማዞር ለግዳጅ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን መረጃዎቻችን ተናግረዋል።
ወያኔ ጦርነቱ ጋብ ብሏል የሚል ማስተባበያ ቢስጥም በኤርትራ በኩል ከፍተኛ የሆነ የበቀል እርምጃ በመዉሰዱ የወያኔ የቦርደር ሆስፒታሎች በቁስለኛ ወታደሮች ከመጨናነቃቸዉ በተጨማሪ ሌሎች ቁስለኞች ዛሬም ወደ ትግራይ ሆስፒታል መወሰዳቸዉን ምንጮች አሳዉቀዋል።
በባሕር ላይ ዉትድርና እረጅም አመታትን በእስራኤልና በግብጽ ሲሰለጥኑ የነበሩ የኤርትራ ሰራዊቶችን ወደተፈለጉበት የጥቃት ወረዳ እንዲፈነጠሩ በሚያስችል የወደብ ከተማዎች ላይ እያሰማራ የሚገኘዉ የኤርትራ አየር ሐይል ጦርነቱን እጅግ የሚፈልገዉ ይመስላል ያሉት መረጃዎች አክለዉ እንደገለጹት ዘመናዊ የሮማኒያ፣ ሩሲያ፣ እስራኤል ሰራሽ የሆኑ የጦር ጀቶች ትንኮሳ በተደረገባቸዉ ስፍራዎች ላይ እያንጃበቡ መሆኑን ገልጸዋል።
ዝግጅቱ በወያኔ በኩልም የቀጠለ ሲሆን የትግራዩ ነጻ አዉጪ ቡድን በአየር ሐይሉ ላይ ባለዉ ጥርጣሬ ምክንያት እንቅስቃሴዎች ብዙም እንደማይታዩ ምንጮች ሲገልጹ አያይዘዉ የወያኔ ሰራዊት ይህን ጦርነት ሆን ብሎ ለፍተሻ እንዳደረገዉ እና ኤርትራ ድብቅ የዉጊያ ስልቶችን፣ሐይሎችን እና ብቃትን በሙሉ ባለማዉጣት ወታደራዊ መረጃዎቿን እንድትጠብቅ አሳስበዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

Monday, June 13, 2016

አ. ግንቦት 7 መግለጫ አወጣ “ወያኔ ከገባበት ለመውጣት በከፈተው ጦርነት ትኩረታችን አይቀለበስም”

በጥጋብና እብሪት የተወጠረው የህወሃት አገዛዝ በትናንትናው ዕለት ዕሁድ ሰኔ 5 ቀን 2008 በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በኩል ከኤርትራ ጋር በሚያዋስኑ የድንበር ቦታዎች ላይ ጦርነት ጀምራል፤ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንም ይህን ዜና አረጋግጠው ዘግበዋል። ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ በወያኔ በኩል ስለጦርነቱ ምንም የተሰጠ መግለጫ ባይኖርም የኤርትራ መንግሥት በጾረና ግንባር በኩል ጥቃት እንደተፈጸመበት ትናንት ማምሻውን ይፋ ባደረገ መግለጫ አረጋግጦአል።
የህወሃት ዘረኝነት በፈጠረው ኢፍትሃዊነትና አፈና የተማረረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በአገዛዙ ላይ ተቃውሞውን እያጠናከረ ባለበት በዚህን ሰዓት በሙስና የተጨማለቁ የህወሃት የጦር ጀነራሎችና በሲቪል ማዕረግ አስተዳደሩን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሩ ሃይሎች ለምን ይህንን ጦርነት መጫር እንደፈለጉ ግልጽ ነው። በኦሮሚያ የተነሳውን የመብት ጥያቄ ለማፈን ከ400 በላይ ሕዝብ መጨፍጨፉና በሺዎች የሚቆጠሩ እስር ቤት መታጎራቸው የህወሃትን ዕድሜ ለማራዘም እንደ አንድ መሣሪያ ሆኖ ላለፉት 25 አመታት ሲያገለግል በኖረው ኦህዲድ ውስጥ እንኳን ከከፍተኛ አመራር እስከ ተራ ካድሬ ያሉትን አስኮርፎአል። የወልቃይት ህዝብ ያነሳው የማንነት ጥያቄ ሌላኛው የህወሃት አጋር በሆነው ብአዴን ውስጥ የማያባራ ክፍፍል ፈጥሮአል። የነጻነት ታጋዮች በቅርቡ አርባምንጭ ከተማ አቅራቢያ የፈጸሙት የጀግንነት ገድል የደቡብ ኢትዮጵያን ሕዝብ የሚያንቃቃና ለትግል የሚያነሳሳ አርአያነት እንደፈጠረ የህወሃት አገዛዝ ተረድቶአል።

ሰበር ዜና… የትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን የመጨረሻዉ የሞት መንገድ ላይ!


ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን ለሁለት አስርት አመታት በቀኝ ግዝት ይዞ የቆየዉ ይህዉ የወያኔ ቡድን በተለያየ የሐገሪቷ ክፍሎች ከገባበት የጦር አጣብቂኝ ዉጥረት የተነሳ ሲሸሸዉና ሲሸሽገዉ የነበረዉን ጦርነት ሳይወደዉ በግዱ እየተጋፈጠዉ ይገኛል።
በሰሜናዊ የሐገራችን ክፍል በጾረና አካባቢም የወያኔ ቡድን ያደረገዉ ትንኮሳ መክሸፉን ምንጮች የጠቆሙ ሲሆን፡ የኢትዮጵያና የኤርትራ ድንበር ጋሽ ባርካ እና ላ ኢላይ ጋሽ አዋሳኝ ስፍራዎች ላይ ጦርነት ተቀስቅሷል!
በዚህ ጦርነት ወያኔ ከፍተኛ አደጋ እንደደረሰበት የተረጋገጠ ሲሆን የ 25ኛ ክፍለ ጦር የደጀን ጦርን ለማጠናከር በሚል ወደ አዉድማዉ ተጠግቷል።
በጦርነቱ የደረሰዉ የጉዳት መጠን ያልተረጋገጠ ከመሆኑ ባሻገር ከትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን መከላከያ ዘመቻ ስምሪት መምሪያ አካሎች የተገኘዉ መረጃ እንደሚጠቁመዉ በወያኔ በኩል የተሞከረዉ ትንኮሳ በተዘዋዋሪ መንገድ በኤርትራ ከሚገኙ የነጻነት ሐይሎች ጋር እንደሆነ የሚያሳይ ሲሆን ድንበር ዘለልነቱ የኤርትራ ወታደሮችንም ተሳታፊ እንዳደረጋቸዉ እንዲሁም እንደሚያደርጋቸዉ በጉልህ ያሳየ ነዉ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
( ጉድሽ ወያኔ )

Sunday, June 12, 2016

20 የሚሆኑ የሕወሓት ደጋፊዎች በአውስትራሊያ ኢትዮጵያዊውን የመንግስት ተቃዋሚ ደበደቡ | ቪዲዮ ይዘናል


(ዘ-ሐበሻ) ሕወሓት የሚመራው መንግስት በሜልበርን አውስትራሊያ የጠራውን ሕዝባዊ ሰብሰባ ለመቃወም ከወጡ ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ 20 በሚሆኑ የትግራይ ተወላጅ የሕወሓት መንግስት ደጋፊዎች ደበደቡት:: ኒውስ 7 የተሰኘው የአውስትራሊያ የመረጃ ቴሌቭዥን የተጎጂውን ኢትዮጵያዊ ፊት በደም ተለውሶ አሳይቶታል::

የሰሜኑ ጦርነት እንደገና ሊጀመር ነው! (የዳዊት ከበደ ወየሳ ሪፖርታዥ – ኢ.ኤ.ኤፍ)

በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል… በኤርትራ እና በትግራይ ድንበር አካባቢ ጦርነት መቀስቀሱ እየተሰማ ነው። ጦርነቱ በተለይ የተቀሰቀሰው በኤርትራ እና በትግራይ ክልል፤ በጾረና ግንባር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። እሁድ ንጋት ላይ የተጀመረው አዲስ ጦርነት አሁንም ድረስ እንደቀጠለ መሆኑን ነው የአካባቢው ነዋሪዎች የሚገልጹት።
ጾረናነዋሪዎቹ እንደሚሉት ከሆነ፤ ከባድ የተኩስ ልውውጥ መሰማት የጀመረው ንጋት ላይ ነው። የከፍተኛ ተኩሱ ድምጽ እስከ ምስራቅ ዛላ’ምበሳ ድረስ ተሰምቷል። የጦርነቱን መነሻ በተመለከተ የተለያዩ ወሬዎች በአካባቢው ሰዎች ዘንድ ይናፈሳል። ከትላንት በስትያ የተሰማው ወሬ፤ “የመከላከያ ሰዎች ኳስ እየተጫዌቱ ሳለ፤ የሽምቅ ተዋጊዎች በከፈቱት ተኩስ የተወሰኑት ሲሞቱ ቀሪዎቹ ደግሞ መቁሰላቸው የጸቡ መነሻ ነው።” ይላሉ።
ሌሎች ደግሞ የሚሉት፤ “ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት የህወሃት ትግራይ ወታደሮች የኤርትራን ድንበር አልፈው ሰላማዊ ሰዎችን በመያዝ፤ ወደ ድንበር ከተማዋ ገሩ-ሰርማይ አምጥተው ማሰር ከጀመሩ በኋላ ነው” ይላሉ ሌሎቹ ምንጮች። በዚያም ተባለ በዚህ ግን ጦርነቱ የተጀመረ ይመስላል። ለዚህም መረጃ የሚሆነው፤ ዛሬ ከሰአት በኋላ በትግራይ የጦር ካምፖች የሚገኙ ወታደሮች በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆኑ ትእዛዝ መሰጠቱና በመቀሌ የሚገኘው ሜካናይዝድ ጦርም ወደ ሥፍራው እንዲንቀሳቀስ መደረጉ ነው።

Saturday, June 11, 2016

ህወሃት ጉሮሮውን ሳይታነቅ የበላውን በ30 ቀን “እተፋለሁ” አለ

“ህወሃት ሲፈጠርም ጀምሮ ዓለምአቀፋዊ ወሮበላ ነው”

dollar-
ህወሃት በቦንድ ስም ህግ ጥሶ ሲሰበስብ የነበረውን ገንዘብ ክስ ተመስርቶበት ጉሮሮው ሳይታነቅ ወዶ ለመትፋት መስማማቱ ታወቀ። ድርጊቱ ኢትዮጵያን መሳቂያ፣  የምትተዳደረው በህገ አራዊት መሆኑን የሚያረጋግጥ መሆኑንና የህወሃትን የወሮበላነት ባህሪ እርቃን ያወጣ ነው ተባለ። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እንደሚሉት ከውጭ ምንዛሬ  ገበያ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ምርመራ ሊካሄድ የሚችልባቸው በርካታ አግባቦች እንደሚኖሩ ነው።

በጀርመን አ.ግንቦት 7 የተሳካ ስብሰባ እያደረገ ነው | ሕወሓቶች በር ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ወጥተዋል

አርበኞች ግንቦት 7ን ለመደገፍ አዳራሽ ውስጥ የሚገኘው ህዝብ
አርበኞች ግንቦት 7ን ለመደገፍ አዳራሽ ውስጥ የሚገኘው ህዝብ
                                   አርበኞች ግንቦት 7ን ለመደገፍ አዳራሽ ውስጥ የሚገኘው ህዝብ
(ዘ-ሐበሻ) የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር በተገኙበት በጀርመን በርሊን ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ሕዝብ አዳራሹን ሞልቶ እየተመለሰና ከውጭ ሆኖ እየተከታተለ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከበርሊን ዘገቡ:: ባልተለመደ መልኩ የሕወሓት ኢምባሲ ሰራተኞችና ለትምህርት ወደዚያው የተላኩ የባለስልጣናት ዘመዶች “አርበኞች ግንቦት 7 የ እናት ጡት ነካሽ ነው” የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮችን ይዘው ከአዳራሹ ፊት ለፊት ተቃውሞ እያሰሙ ነው::

Friday, June 10, 2016

በእነ አቶ በቀለ ገርባ ላይ የቀረበውን ክስ የፌዴራል ፍርድ ቤት እንዳያይ ተቃውሞ ቀረበ

የሽብር ተግባር ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው በእስር ላይ የሚገኙት እነ አቶ በቀለ ገርባ (22 ተከሳሾች) የክስ ሒደት፣ የፌዴራል ፍርድ ቤት ‹‹የማየት ሥልጣን የለውም›› ሲሉ የመጀመርያ የክስ መቃወሚያቸውን ክሱ ለተከፈተበት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት አቀረቡ፡፡

የኖርዲክ ሐገራት አርበኞች ግንቦት 7 ሕዝባዊ ውይይትና ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በኦስሎ ኖርዌይ ተካሄደ፡፡ ጁን 4/2016 የኖርዲክ ሐገራት የአርበኞች ግንቦት ሰባትሕዝባዊ ስብሰባና የገቢ ማሰባሰቢያ አጠቃላይ ሪፖርት(ዘገባ) ።

Patriotic Ginbot 7 Public Meeting in Oslo
ፕሮግራሙ ለነፃነት በረሐ የወረዱት የንቅናቄው መሪ አርበኛ ፕሮፌሰር ብርሐኑ ነጋ፣ / ጌታቸው በጋሻው ከቪዥኝ ኢትዮጵያ የክብር እንግዶች እና በብዙ መቶ የሚቆጠሩ የንቅናቄው አባላት እና ደጋፊዎች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከናውኑዋል።
በተለይ  ከኖርዌይ ውጭ ከስዊድን የመጡት የንቅናቄው አባላት እና ደጋፊዎች ለዝግጅቱ ድምቀት ከፍተኛ አስተዋፆ ያደረጉ ሲሆን ከስዊድን ወጣቶች የተገኘውን የሜዳልያ ሽልማት በበረሐ ለሚገኙ ታጋዮች እንዲደርስ ለንቅናቄው ሊቀመንበር ለአርበኛ ፕሮፌሰር ብርሐኑ ነጋ  ከስውዲን የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር አበርክተዋል።

Wednesday, June 8, 2016

ዛሬ ዳባት ከተማ በህዝባዊ ተቃዉሞ ስትናጥ ውላለች

የሙሉነህ ዮሐንስ ዘገባ
*ከጎንደር ከተማና ከትግራይ አቅጣጫ የሚመጡ ከ200 በላይ መኪናዎች ታግተው ውለዋል።
*ያስተዳደር የፍትህና መሰል የመንግስት ህንፃዎች በድብደባ ተሰባብረዋል።
*ከፍተኛ የሆነ የተኩስ እሩምታ ቀኑን ሙሉ ውሏል።
*አመፁ ባካባቢው ከሰፈረው ታጣቂ አቅም በላይ ስለሆነ የፌደራል ሃይል እየገባ ነው።
*ብዙ ሰውና ንብረት ላይ መጠኑ ያልታወቀ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።
*ትራንስፎርመር ጭና የነበረችው መኪና በእሳት ጋይታለች።
*ትራንስፎርመር ነቃዮቹ 25 ኪ.ሜ. እርቀው በደባርቅ ፖሊስ ጥበቃ ስር እንደሚገኙ ታውቋል።Dabat

አልሸባብ የገደላቸውን የኢትዮጵያ ወታደሮችን ፎቶ ግራፎች ለቀቀ

የልዑል ዓለሜ ዘገባ
በሶማሌያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች በተለይም የ44ተኛ ክፍለ ጦር እየተዳከመ መምጣቱን ምንጮች እየገለጹ ይገኛሉ::
ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች በአልሸባብ በአሰቃቂ ሁኔታ እየተገደሉ የሚገኙበት ኢል ቡር ( El bur ) የተባለዉ አካባቢ ሲሆን ከመከላከያ ሰራዊቱ መካከል አንዱ የላከልን መረጃ እንደሚያመላክተዉ ሰላም የማስከበሩ ሂደት በወያኔያዊያን አመራሮች ወደ ሰራዊት ማስጨረሱ ሁናቴ መሸጋገሩን ነዉ::
” የአልሸባብ አፈ ቀላጤ የሆነ አሊ መሃመድ ራጌ Ali Mahmud Rage የተባለ ግለሰብ በስፍራዉ ለሚገኙ መከላከያ ሰራዊት አዛዦች እና ወታደሮች በተለያየ መንገድ ማስጠንቀቂያ እየሰጠ የጥቃት አደጋ መፈጸሙን ከተያያዘዉ ሰንበትበት ብሏል! የሚል መልእክት ያሳለፈዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባል… የጥይት ድምጽ በተሰማበት ስፍራ ሁሉ በአፋጣኝ እየተወሰድን የምንማገድበት ሁኔታ እየተባባሰ ከመምጣቱ በላይ የ44ተኛ ክፍለ ጦር እየተመናመነ መጥቷል ሲል በምሬት አሳስቧል።
አል ሸባብ የኢትዮጵያ መከላከያ አባል የሆነ ኮማንደርን ጨምሮ ብዛት ያልቸዉ ወታደሮችን መግደሉን በተለያየ ወቅት የሚለፍፍ ሲሆን በሳለፍነዉ ሳምንት ዉስጥ ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላትን በሞት ፍርድ መቅጣቱንም ከስፍራዉ አንድ የወያኔ ከፍተኛ አመራር ተናግረዋል ።

በዲምክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አዘጋጅነት ቅዳሜ ጁን 4 – 2016 በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ የአርበኞች ግንቦት7 ታላቅ ህዝባዊ ስብስባ እና የገቢማሰባስቢያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ

በሕዝባዊ ስብሰባው ላይ ቁጥራቸው በብዙ መቶወች የሚጠጉ የንቅናቄው አባሎችና ደጋፊወች ለድርጅቱና ለመሪያችው አጋነታቸውን ለማሳየት ከኦስሎ እና ከመላው ኖርዌይ እዲሁም ከተለያዩ አገራት ተገኝተዋል በተለይም ክስቶኮልም የመጡ የድርጅቱ አባሎች ና ደጋፊወች ለዝግጅቱ ታላርትልቅ ድምቀት ስተውታል !!
የእለቱ የክብር እንግዶች
• የአርበኞች ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀምበር አርበኛ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ
• ፕ/ር ጌታቸው በጋሻው ከቪዥን ኢትዮጵያ
• ዶ/ር ሙሉአለም አዳም በኖርወዌይ አርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር
• ወ/ሮ ብዙአየሁ ጽጌ
Patriotic Ginbot 7 Public Meeting in Osloየእለቱ እንግዶች በተገኙበትሕዝባዊ ስብሠባው በኖሬጅያውያን የሰአተ አቆጣጠር ከቀኑ 16:15ተጀምሮ እስከ ምሽቱ 00:00 ሰዓት የተካሄደ ሲሆን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አቢ አማረ የለቱን ፕሮግራም በማስተዋወቅ ለዝግጁት ታዳሚውች እንኮን ደህና መጣችሁ በማለት ለዝግጅቱ መሳካት ክተለያየ ቦታ እርቀት ሳይገድባቸው ረጅም መንገድ ተጉዘው ለተገኙ እንግዶቻችን በድርጅታቸው ስምና ታላቅ ምስጋ ና አክብሮት ክአቀረቡ ቡሀላ የለቱ ፕሮገራም የመክፈቻ ንግግር በማድረገ አስጀምረዋል አያይዘውም በኢትዮጵያ ውስጥ በመላ የሀገራችን ህዝቦች በወያኔ አረመናዊ ስርአት በጭካኔ በግፍ ለተገደሉ እና በተለያዩ አስር ቤቶች በፖለቲካ ኣስተሳስባችው ምክንያት ያለወንጀላች የሚስቃዩ ውድ ኢትዮጵያዊን ወገኖቻችን በማስብ እንዲሁም አስቃቂ የኣካል ጉዳት ለተፈጸባቸው ኢትዮጵያዊን የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማስደረግ ስብሰባውን አስጀምረውታል::

Wednesday, June 1, 2016

መረጃ… ዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም ግምገማ ላይ ወድቀዋል!!

914e2-tplf_failingእጆቹን አስረዝሞ ለመዝረፍ ይመቸዉ ዘንድ የአለም ጤና ድርጅትን ለመምራት አዲስ አቅጣጫ የቀየሰዉ የትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ የዉጭ ሐገራት በመዘዋወወር የአለም ጤና ርጅትን ለመምራት ቅስቀሳ ሲያደርግ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።
ቅዳሜ እለት ወደ አዲስ አበባ የተመለሰዉ ቴድሮስ አድሐኖም ሁለት ቀላል መሳሪያ የታጠቁ ወጣቶች የሚጠብቁት ሲሆን የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 2_69183 አአ የሆነ ዘመናዊ ላንድ ሮቨር አዉቶሞቢል ተመድቦለት ይንቀሳቀሳል።
አምባሳደር ሙሌ የካቢኔ ዋና ሹሙና አምባሳደር ቦጋለም ከቴድሮስ አድሐኖም ጋር አብረዉ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን አቶ ህላዌ ዩሱፍ እና የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ከቴድሮስ አድሐኖም ጋር በአንድነት ሆነዉ በዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዙሪያ እየደረሰ ያለዉን የአገልግሎት ኪሳራ በተመለከተ ዉይይት ከማድረጋቸዉ በተጨማሪ በህዝቦች ሽግግር ዙሪያ ከእስራኤል ዲፕሎማኦች ጋር ተወያይተዋል።
የመላዉ ሐገራችንን አንጡራ ሐብት ከግል ጥቅማቸዉ አንጻር እንዳሻ ሲጠቀሙበት ማየት እጅግ ያሳዝናል በማለት ቁጭታቸዉን የገለጹልን ባለስልጣን ከእንግዲህ ወዲህ የትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን ሐገራችንን የመምራት ብቅት እንደሌለዉና የሐገሪቷ ብሔራዊ ደህንነት አደጋ ላይ መዉደቁን አሳስበዉ!!
ኢትዮጵያን ከአደገኛ ችግር ከመታደግ አንጻር ወያኔ ስልጣኑን ለሰፊዉ ህዝብ እንዲያስረክብ አስጠንቅቀዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
( ጉድሽ ወያኔ )