Translate

Sunday, January 31, 2016

በዲሲ የአርበኞች ግንቦት 7 የቀጥታ ስብሰባ ይሄን ከፍተው ይከታተሉ jan 31 2016- watch live


ሰበር መረጃ – የአባይ ግድብ እና የቦንድ ገንዘብ ዘረፋ (ወያኔ)

dam-467
(Satenaw) — የአል ጀዚራ ባልደረባ የሆነዉ ሃሰን ሁሴን  (Hassen Hussein) እንደዘገበዉ ጃንዋሪ 8 ላይ ግብጽ የአባይ ግድብ ግንባታ እንዲቋረት ጠይቃለች ይህዉም በሁለቱ ሐገራት መካከል ዉስጥ ለዉስጥ እየተካረረ የመጣ ዲፕሎማሲያዊ ጸብ ወደ ተለያየ አቅጣጫ እንደሚሄድ ሲነገር ቆይቶ ሰንብቶ ነበር።

የኃይለማርያም ደሳለኝ ስድስተኛው አማካሪ ከትግራይ – ብርሃነ ገ/ ክርስቶስ (የአርከበ እቁባይ አማች)

arekebe
ከኤርሚያስ ለገሰ
እነሆ! ዛሬ ደግሞ ” በሚኒስትር ማእረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ መልእክተኛ ” የሚል ሹመት ሰማን። የአዲሱ ቦታ ስልጣን እና ሃላፊነቱ ባይገለጵም ሹመቱ ከተሰጠው ሰው ማንነት ተነስቶ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ቢያንስ ቢያንስ ” የዶሮ ወጥ መልእክተኛ” እንደማይሆን ይጠበቃል።

Thursday, January 28, 2016

ኢትዮጵያ “ነፃነት የሌለባት”፤ ኤርትራ “ከክፉዎች የከፋች” ተባሉ

በዓለም ዙሪያ የሚሰማው የምጣኔ ኃብት ድቀት እና የማኅበራዊ ነውጥ ፍራቻ አምባገነን መንግሥታት በአውሮፓ አቆጣጠር ባለፈው 2015 ዓ.ም ይበልጥ አፋኝና ጨቋኝ እንዲሆኑ ሰበብ ሳይሰጣቸው እንዳልቀረ ዛሬ የወጣ የዓለም የነፃነት ሁኔታ ሪፖርት አስታውቋል፡፡
ፍሪደም ሃውስ የሚባለው ነፃ ቡድን በዚህ ሪፖርቱ የሃገሮችን የዴሞክራሲያዊ የነፃነት ይዞታዎች ገምግሞ በደረጃ አስቀምጧቸዋል፡፡ አምባገነን አገዛዞች ባለፈው የአውሮፓ ዓመት በ2015 ዓ.ም ይበልጥ የከፉ መሆናቸውን ይህ ዛሬ የወጣ የዓለም የነፃነት ይዞታ ሪፖርት ይናገራል፡፡

ር'ዮት አለሙ እንደ ክርስቶስ ደሞ እንደ በላይ ( ሄኖክ የሺጥላ )

ር'ዮት አለሙ እንደ ክርስቶስ ደሞ እንደ በላይ ( ሄኖክ የሺጥላ )

ጋዜጠኛ 'ና መምህርት ር'ዮት ዓለሙ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋ ታሪኳን ( ያሳለፈችውን መከራ ፣ እንግልት ፣ ስቃይ እና አስር ) በቅንጭብ ካካፈለችበ የኢሳት ማህደር ውስጥ ገብቼ ቃለ ምልልሷን አደመጥኩ ። እኔ በግሌ ቃለ ምልልሱ ፥ ስለ ወያኔ ( ወይም የ ዘንድሮ ትግሬ ምንነት) ስላለኝ እምነት ( ኣቋም ) ማረጋገጫ ከመሆን ውጪ ሌላ ነገር አላገኘሁበትም ። እንደ ሰው ፣ እንዲሁ አንዳንዴ "እስኪ እኔ ትግሬ ብሆን ኖሮ ሄኖክ የሺጥላ የሚጽፈውን "ትግሬ ተኮር" ጽሑፎች እንዴት ነበር የማያቸው?" ብዬ ራሴን ደግሜ ደጋግሜ ጠይቄ ላገኘሁት መልስ የ ር'ዮት ቃለ ምልልስ ስጋ ለበስ ባለ እስትንፋስ ማስረጃ በመሆን ለወያኔ -ትግሬ ሊኖረኝ የሚችለውን ቅንጣት "ምናልባችን" ጠራርጎ የወሰደ ፣ የማንነታቸው ፍጹም ማረጋገጫ ሆኖም አግኝቼዋለሁ ።

Tuesday, January 26, 2016

ኢንሳ የአየር ላይ ፎቶ በማንሳት ላይ የሚገኘው ለሱዳን ተሰጥቷል የሚባለውን አልፋሽጋ ተብሎ የሚጠራውን አካባቢ መሆኑ ታወቀ

ጥር ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ካለፈው ጥር ወር መግቢያ ጀምሮ የአየር ላይ ፎቶ እየተነሳ ያለው አካባቢ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ” ኢትዮጵያ መሬቱ የእኛ መሆኑን እውቅና ሰጥታለች” በማለት ለአልጀዚራ የተናገሩት አልፋሽጋ እየተባለ የሚጠራው ቦታ መሆኑ ታውቋል።

Ethiopian Border Affairs Committee
ትናንት ኢሳት የመረጃና ደህንነት ኢንፎረሜሽን ባለሙያ በማናገር በሰራው ዘገባ ላይ በአሁኑ ሰአት የአየር ላይ ፎቶ ለማንሳት ምልክቶችን መሬት ላይ የማስቀመጡ ስራ የሚከናወነው 365 ኪሜ ርዝመት ባለው ቦታ ላይ መሆኑን ቢዘግብም፣ ይህ ርቀት ግን የአየር ላይ ርቀትን የሚያመለክት እንጅ የመሬትን እርቀት የሚያመለክት ባለመሆኑ ማስተከከያ እንዲደረግበት ጠይቀዋል። በመጀመሪያው ሂደት ድንበር የማካለሉ ሂዳት የሚከናወነው 725 ኪሜ ርዝመት ላይ ባለው መሬት ላይ ሲሆን፣ ይህም አካባቢ ሱዳን የኢትዮጵያ መንግስት የእኔ መሬት መሆኑን አምኖልኛል በማለት የገለጸችው አልፋሽጋ እየተባለ የሚጠራውን ለም መሬት የሚያካትት ነው።

የኢትዮጵያ ሙስሊም ፈተና በ224 ደቂቃዎች

(ዘላለም ክብረት)

የሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እና ተባብራችኋል ተብለው የተፈረደባቸው ኢትዮጵያዊያን 
© ማሕበራዊ ሚዲያ

ክፍሉ ከኮሪደሩ ላይ ከተንጠለጠለ አምፖል በሚመጣ ብርሃን ፈገግ ብሏል፡፡ እኔም ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ ወደ ክፍሉ ስገባ ከክፍሉ አንደኛው ጫፍ ላይ አንድ ቀጠን ያለ ሰው ድምፁን በትንሹ ከፍ አድርጎ ቁርዓን ‹እየቀራ› ነበር፡፡ በክፍሉ ሌላኛው ጫፍ ላይ ደግሞ አንድ ፍራሽ፣ አንድ የውሃ ጀሪካን እና ትንሽ ልብሶች በፌስታል ውስጥ ተቀምጠዋል፡፡ በሌላኛው የክፍሉ ጫፍ ደግሞ የሽንት ባልዲ – ሽታውን ለመቀነስ ሲባል በግማሽ ውሃ ተሞልቶ ተቀምጧል፡፡ ክፍሉ ውስጥ እንደገባሁ አንዱ ጫፍ ላይ ትንሽ ቆም ካልኩ በኋላ በክፍሉ ውስጥ ያገኝሁት ብቸኛው ሰው ፍራሹ ላይ እንድቀመጥ በእጁ ሲጠቁመኝ ቁጭ አልኩ፡፡ ፍራሽ ላይ እንደተቀመጥኩ በፍራሹ ጫፍ ላይ የጆን ግሪሻም ‘The Last Juror’ መፅሃፍ ተቀምጦ አየሁት፤ አንስቼ ስመለከተው ክፍሉ ውስጥ ያገኘሁት ሰው ቁርዓን መቅራቱን ጨርሶ እንግሊዝኛ እችል እንደሆነ ጠይቆኝ ማውራት ጀመረ፡፡

Sunday, January 24, 2016

የአውሮጳ ፓርላማ ኢህአዴግን “ልክ ሊያስገባ”?!

ውሳኔው “ውስጡ በብረት የተወጠረ የቦክስ ጓንቲ ነው”

eu p

* ውሳኔው “ማዕቀብና የዕርዳታ ቅነሳ አያስከትልም” አና ጎሜዝ
* የቴድሮስ አድሃኖም “ዲፕሎማሲያዊ ልመና” አልሰራም
የአውሮጳ ፓርላማ ሐሙስ ዕለት ባለ 19 ነጥብ ውሳኔ ህወሃት/ኢህአዴግ በሚገዛት ኢትዮጵያ ላይ አስተላልፏል፡፡ ጉዳዩ ኢህአዴግ “ልክ ሊገባ ይሆን” የሚል አመለካከት ጭሯል፡፡ ረቂቁ ለውይይት እንዳይቀርብ የቻሉትን ያህል የጣሩት ቴድሮስ አድሃኖም “ዲፕሎማሲያቸው” አልሠራም፡፡ ውሳኔው “ማዕቀብና የዕርዳታ ቅነሳ አያስከትልም” በማለት አና ጎሜዝ ተናገሩ፡፡ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ውሳኔው “ውስጡ በብረት የተወጠረ የቦክስ ጓንቲ ነው” ብለውታል፡፡

ርዕዮት ሆይ! ወኔ ቢሶቹን “እንካ መቀኔቴን – ቀበቶህን ስጠኝ” ብለሽ ገስጭልን!

አዜብ ጌታቸው

Ethiopian heroine journalist Reeyot Alemu
አቅም በፈቀደ መጠን በየጊዜው በሃገራችን ወቅታዊ ሁነቶችና ክስተቶች ዙሪያ የተሰማኝን ለመግለጽ ስሞክር ቆይቻለሁ።ታዲያ በእያንዳንዱ ጽሁፍ ላይ በርካታ አስተያየቶች ይደርሱኛል።አብዛኞቹ አበረታች፤ ጥቂቶቹም አርበትባች። አርበትባች ስል ማስፈራራት መሞከራቸውን ለመግለጽ ያህል እንጂ ተርበተበትኩ ማለቴ እንዳልሆነ ይጠፋችኋል አልልም። “እንኳን ለሙቅ ለገንፎ አልደነግጥ አሉ…”። መዳፋቸው ውስጥ ሆና ያርበተበታቻቸውን የርዕዮት ዓለሙን ገድልና ጀግንነት እያየሁ ! እየሰማሁ! እኔ ከ4 ኪሎ ቤተ መንግስት (ቤተ መጥምጥ) በስንት ሺህ ማይልስ ርቀት ላይ ሆኜ እንዴት ልርበተበት? ያውም በኤሜል? እ ተ ተ ተ ተ…. !

Friday, January 22, 2016

የወያኔ “የማንቂያ ደወል” ደኩሜንታሪ — ውሸት ሲገነፍል!

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት

ከመሰረታዊ የእምነት ተግባርና ምንጭ ከስግደትና ቁርዓን ጀምሮ መስጊድ መገንባትና መንፈሳዊ ሥራዎችን ማከናወን ወንጀል ነው በሚል የወያኔ መንግስት በሙስሊሞችና እስልምና ላይ የክተት አዋጅ ነጋሪት እያስጐሰመ ነው።UEMSG logo
“የማንቂያ ደወል” በሚል ስያሜ በቅጥፈት የታጀለው ደኩሜንታሪ 1ኛ-በሙስሊሙና በክርስቲያኑ መካከል ለ14 መቶ ክፍለ ዘመን የቆየውን መተማመንና አብሮነትን ለመናድ፣ 2ኛ- በራሱ በሙስሊሙ ሕብረተሰብ መካከል ቅራኔ ለመፍጠር 3ኛ- አብዛሃኛው የኦሮሞው ሕብትረተሰብ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ስለሆነ፣ ይህ ጀግና ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ በሚያካሂደው ሕዝባዊ አመፅ ላይ በጓዳ በር በመግባት ጥቃት ለመክፈት የተደረገ ከጅምሩ የተኮላሸ ሙከራ መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው። ከሁሉም በላይ ግን ደኩሜንታሪው የሚያንፀባርቀው ዘረኛው የወያኔ ሥርዓት የጣረሞት ፍርግጫ ላይ መሆኑንና አንድ ሓሙስ የቀረው መሆኑን ነው።

Thursday, January 7, 2016

የነጻነት ቀን ቀርባለችና ጸንታችሁ ቁሙ! (እየሩሳሌም ተስፋው — ከቃሊቲ ማጎሪያ ቤት፣ አዲስ አበባ)

እየሩሳሌም ተስፋው (ከቃሊቲ ማጎሪያ ቤት፣ አዲስ አበባ)

እነሆ በጨለማ ቤት ውስጥ ከታጎርን 311 ቀናት ሞሉን፡፡ ጊዜው እንዴት ይሮጣል ባካችሁ? የዛሬ አመት በዚህ ወቅት ከጓደኞቼ ጋር በዝዋይ እስር ቤት የሚገኙትን ጀግኖቻችንን ለመጠየቅና እንኳን አደረሳችሁ ለማለት የገና ዋዜማን በዝዋይ ወህኒ ቤት ተገኝተን ነበር፡፡ ግን ምኞታችን ቅዠት ሆኖ ያሰብነው ሳይሳካ አንድም የፖለቲካ እስረኛ ማግኘት ሳንችል በሩን ተሳልመን ተመለስን፤ መጠየቅ አትችሉም ተብለን፡፡Eyerusalem Tesfaw
የገና ዕለትም እንደለመድነው ከጀግኖቻችን ጋር ለማሳለፍ መጀመሪያ በቂሊንጦ ወህኒ ቤት፣ ቀጥሎ የስድስት ሰዓት ተጠያቂዎች ናቸውና የቃሊቲ ጀግኖቻችን ከእነሱ ጋር በማሳለፍ ለማስታወሻ ይሆነን ዘንድ እዚሁ ቃሊቲ በር ላይ ተሰባስበን ፎቶ ተነሳን፡፡ ያ በዓል ለእኔ እና ለአባሪዎቼ የመጨረሻ በዓላችን ነበር፡፡ ሆኖም በዓሁኑ ሰዓት በዚያ ፎቶ ላይ ተሰባስበን ከተነሳነው ስንት ሰው እንደሆነ በሰፊው እስር ቤት የቀረው እናንተው ማየት ትችላላችሁ፡፡ (ፎቶ ከተገኘ ማለቴ ነው)

Wednesday, January 6, 2016

ስደት የፍርሃት ውጤት ነው

መስፍን ወልደ ማርያም
ታኅሣሥ 2008
ከሁለት ቀኖች በፊት ስለበእውቀቱ ሥዩም አድናቆታቸውን በፌስቡክ ላይ የገለጹ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ለበእውቀቱ ያላቸውን አድናቆት እኔም እጋራቸዋለሁ፤ ነገር ግን የእነዚህ ሰዎች አድናቆት በእውቀቱ ራሱንና ማንነቱን እንዲከዳ ይቃጣቸዋል፤ አንዱን አውቀዋለሁ፤ ከፖሊቲካና ከትጥቅ ትግል ወደስደት ‹‹ነጻነት›› የተሸጋገረ ያሬድ ጥበቡ የሚል የሚያኮራ ስም ይዞ የስደት መምህር የሆነ ነው፤ ሁለተኛው ሚስተር ቴዲ ገብርኤል ይባላል፤ እነዚህ ሁለት ስደተኞች በእውቀቱ ሥዩምን በጣም ስለሚወድዱትና ስለሚያከብሩት በአሜሪካ ስደተኛ ሆኖ እንዲቀርላቸው ይፈልጋሉ፤ በዚህ ብቻ ለኢትዮጵያ ያላቸውን ስሜት መገመት በጣም የሚያሳዝን ነው፤ ወደዝርዝር አልገባም፡፡

ኢትዮጵያ፡ በዘ-ህወሀት የተገደበች ሀገር (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ   በዘ–ህወሀት የተወገዘችው ኢትጵጵያ
ባለፈው ሳምንት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እየተባለ የሚጠራው አዲስ ስምምነት የተፈረመበት የብዕር ቀለም ሳይደርቅ የግብጽ ፕሬዚዳንት ጀኔራል አብደል ፋታህ ኤል ሲሲ በአንድ ብሄራዊ የእርሻ ፕሮጀክት የምረቃ ስነስርዓት በዓል ላይ በመገኘት ለግብጽ ህዝብ እንዲህ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፣ “ውኃ የህይወት ወይም የሞት ጉዳይ መሆኑን  እና ይህም የግብጽ ህዝብ ጭንቀት መሆኑን ሙሉ በሙሉ እገነዘባለሁ፡፡ እነርሱም መኖር እንደሚፈልጉ ሁሉ እኛም መኖር እንደምንፈልግ ከወንድሞቻችን ከኢትዮጵያውያን ጋር ስምምነት አድርገናል፡፡ ከዚህ ቀደምም በተሳሳተው መንገድ አልመራኋችሁም፣ አሁንም በተሳሳተው መንገድ አልመራችሁም፡፡“

ቴሌን ደህና ሰንብት?

ዶ/ር ደብረጽዮን “አልረካንም” አሉ

ethiotelecom
የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ስሙን ቀይሮ “ኢትዮቴሌኮም” በሚል ከተሰየመ በኋላ አስተዳደሩን ለፈረንሳዩ ፍራንስ ቴሌኮም ማስረከቡን ተከትሎ ኢህአዴግ ለወደፊቱ ያቀደውን እቅድ ይፋ የሚያደርጉ መረጃዎች ለንባብ በቅተዋል። በዛሬው እለት የመገናኛና የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል “ቴሌ ከዚህ በኋላ ለውጪ ካምፓኒ አይሰጥም። በአገር ውስጥ ባለሙያዎች ይቀጥላል” ሲሉ የማሳረጊያ ንግግር አሰምተዋል። የሚኒስትሩን ንግግር ያደመጡ “ቴሌን ህወሃት ጠቀለለው” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።

Sunday, January 3, 2016

የመጨረሻዉ መጀመሪያ — አሜሪካ ለምን የአርባ ምንጭ የሰዉ አልባ አይሮፕላን ማስነሻ ጣቢያዋን መተዉ አስፈለጋት?

ከሳዲቅ አህመድ

US shuts down drone operation in Ethiopiaወደ አለም አቀፉ የዲፕሎማሲ መንደር ቀረብ ቀረብ ማለት ከጀመሩ ወራት ተቆጥረዋል። ከሐያላኑ አገራት ጋር የቀጥታ ሳይሆን የእጅ አዙር የዲፕሎማሲ ጉዞን ሳይጀምሩ አልቀሩም የሚሉም አሉ። በጠመዝማዛዉ መንገድ የሚጓዙት የዲፕሎማሲ ጉዞ ከሚፈልጉበት ቦታ እስኪያደርሳቸዉ ድረስ እምብዛም አትኩሮት አልሳቡም። እርሳቸዉ ግን እየተጓዙ ነዉ። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ  አፈርቂ።
ዜናዉ፦

የህዳሴው ገደል እምን ላይ ደረሰ? (በውቀቱ ስዩም)

በውቀቱ ስዩም

አውሮፕላን መጣ እየገሰገሰ
በዘፈን አንደኛ ሙሉቀን መለሰ
(እስከመቸ ድረስ ጥላሁን ገሰሰ)
የህዳሴው ገደል እምን ላይ ደረሰ? Lol
የህዳሴውን ግድብ ወደ “ህዳሴው ገደል” ያሸጋገረውን ስምምነት የፈረመው ሰውየ “እጁን ለቁርጥማት፤ ደረቱን ለውጋት” እንዲዳርገው በመመረቅ ወደ ሰላምታየ እገባለሁ፡፡ እንዴት ናችሁ፤ ያልታደላችሁ? እኔ በህይወቴ በተለያየ ጊዜ ተስፋ ቆርጫለሁ፡፡ እንደ ዘንድሮ ተስፋን፤ ከሻኛውና ከፍሪምባው አፈራርቄ የቆረጥሁበት ጊዜ አልገጠመኝም፡፡Ethiopian author and poet, Bewketu Seyoum
መንግሥትም ሃያ አመት ሙሉ አጥሮ፤ ሃያ ዓመት ሙሉ ቆፍሮ የተሳካለት ኣይመስልም ፡፡ “በየቦታው እንምሳለን፡፡ ለመጭው ትውልድ ነዳጅ ሳይሆን ጉዱጓድ እናወርሳለን” የሚል ነው የሚመስለው፡፡ የዛሬ አስራ አምስት አመት ገደማ ውሃ ማቆር የተባለ ፕሮጀክት ነድፎ ነበር፡፡ እናም ኅብረተሰቡ በየጓሮው ሮቶ ሮቶ የሚያክል ጉድጓድ እየቆፈረ የዝናብ ውሃ እንዲያቁር ትዛዝ ተላልፎለት ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ውጤቱ ምንድን ነበር? የየሰፈሩ ሰካራም በየጉድጓዱ እየገባ አለቀ ፡፡ ይሁን እንጂ መንግሥት፤ ስንት ሰካራም አጥንቱን የከሰከሰበትን ፤ ደሙን ያፈሰሰበትን ፕሮጄክት ድንገት ሰረዘ፡፡ በጊዜው የተወሰኑ ሰዎች ለዶማና ላካፋ መግዣ በሚል ወፍራም በጀት አስለቅቀው ከድህነት ተላቀቁ ፡፡ አገሪቱ ግን የግዜር ገበጣ መጫወቻ መስላ ቀጠለች፡፡ የውሃ ማቆር ፕሮጀክሩ ቢቀጥል ኖሮ ዛሬ የህዳሴውን ገደል ለመሙላት ግብጽን አንለማመጥም ነበር፡፡