Translate

Sunday, May 31, 2015

የጦማርያኑ እና የጋዜጠኞቹ የሃያ ዘጠነኛ የፍርድ ቤት ውሎ – ዞን9

የጦማርያኑ እና የጋዜጠኞቹ የሃያ ዘጠነኛ የፍርድ ቤት ውሎ – ዞን9

zone9-bloggers6ከትላንትና ወዲያ በምሰክሮች እና ሲዲ ውዝግብ በይደር ተቀጥሮ የነበረው የነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝግብ የፍርድ ቤት ውሎ ትላንትናም በተለያዬ ድራማዎች ታጅቦ ለግንቦት 25 እና ለሰኔ 8 ተቀጥሯል፡፡

Friday, May 29, 2015

ነጻነት በሌለባት ኢትዮጵያ ሕዝባዊ አስተዳደር መትከል ዘበት ነው!!! ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ


ሰማያዊ ፓርቲ 2007 . ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ ሲወስን በዚህች ሐገር ገለልተኛና ብቃት ያላቸው ተቋማት እንደሌሉና ገዥው ቡድንም እውነተኛ ምርጫ እንደማይፈቅድ እያወቀ መሆኑን ከዚህ በፊት በሰጣቸው የአቋም መግለጫዎች ግልፅ አድርጓል፡፡ በሒደቱም እንደታየው ገና ከመጀመሪያው ምርጫ ቦርድ የሰማያዊ እጩዎችን ከምዝገባ ሰርዟል፡፡

Thursday, May 28, 2015

አምስተኛው ዙር የድምጽ ዘረፋ . . .

(ክንፉ አሰፋ)

elect2007

Wednesday, May 27, 2015

ውዝግብን ያስተናገደው የዛሬው የጦማሪያኑ እና የጋዜጠኞቹ የፍርድ ቤት ዝርዝር ዘገባ

ውዝግብን ያስተናገደው የዛሬው የጦማሪያኑ እና የጋዜጠኞቹ የፍርድ ቤት ዝርዝር ዘገባ
በትናንቱ የቪኦኤ ዘገባ ላይ አቃቤ ሕግ ቅሬታ አቀረበ
ጦማሪ አቤል ዋበላ ችሎት በመድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ተባለ
‹‹ሥነ-ሥርዓት ያዝ!›› ዳኞች
‹‹እናንተ ራሳችሁ ሥነ-ሥርዓት ያዙ! ይህ ችሎት ነው፡፡ ግልጽ ነው›› አቤል ዋበላ
‹‹ውሳኔው ለሁሉም ከሆነ፣ ለአቃቤ ህጉም ሆነ ለአለቃው ጠ/ሚኒስቴርም መሆን አለበት፡፡››
‹‹ጓደኛዬ (አቤል) የሚቀጣ ከሆነ ውሳኔው እኔም ላይ ይታዘዝ››
ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ

United States on Ethiopia’s Recent Election

Press Statement by Marie Harf
Deputy U.S. Department of State Spokesperson, Office of the Spokesperson
U.S. Department of State logoThe United States commends the people of Ethiopia for their civic participation in generally peaceful parliamentary and regional elections on May 24. We acknowledge the National Electoral Board’s organizational efforts and the African Union’s role as the only international observer mission on the ground. We also note the importance of the nine televised party debates as progress in fostering open public discussion of the challenges facing the country. We encourage all candidates, political parties and their supporters to resolve any outstanding differences or concerns peacefully in accordance with Ethiopia’s constitution and laws.
The United States remains deeply concerned by continued restrictions on civil society, media, opposition parties, and independent voices and views. We regret that U.S. diplomats were denied accreditation as election observers and prohibited from formally observing Ethiopia’s electoral process. Apart from the election observation mission fielded by the African Union, there were no international observer missions on the ground in Ethiopia. We are also troubled that opposition party observers were reportedly prevented from observing the electoral process in some locations.

ፊታችንን ከምርጫ ፓለቲካ ወደ ሁለገብ ትግል እናዙር!- የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ

ፊታችንን ከምርጫ ፓለቲካ ወደ ሁለገብ ትግል እናዙር!- የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ

11099980_1577592662492909_6349225450290127644_n

ግንቦት 18 2007 ዓ.ም
ምርጫ 2007 ተጠናቆ ተወዳዳሪም አወዳዳሪም የሆነው ህወሓት ይፋ ውጤት እስኪገልጽ እየተጠበቀ ነው። ሁሉ በእጁ ነውና ባለሥልጣኖቹ ምን ዓይነት ውጤት እንደሚስማማቸው እስከሚነግሩን ጥቂት ቀናት ይወስዱ ይሆናል። ከፈለጉ ሁሉን የፓርላማ ወንበሮች ሊወስዷቸው ይችላሉ፤ ካሻቸው ደግሞ ጥቂቱን ለተቃዋሚዎች ሊሰጡ ይችላሉ። ወሳኞቹ እነሱ ናቸው። በዚህ የፓርላማ ወንበሮች እደላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ድምጽ አንዳችንም ሚና የለውም።
ምርጫ የሕዝብ የሥልጣን ባላቤትነት ማረጋገጫ ከሆኑ አቢይ ዲሞክራሲያዊ ተቋማት አንዱ መሆኑ የታወቀ ነው። ሆኖም ግን ነፃ ተቋማት በሌሉበት፤ በአምባገነኖች አስፈፃሚነት የሚደረግ ምርጫ የመራጮች ነፃ ፍላጎት መግለጫ በመሆን ፋንታ የገዢዎች ሥልጣን ማረጋገጫ መሣሪያ ይሆናል፤ ከአገራችን እየሆነ ያለውም ይህ ነው።

ገዢው ፓርቲ ምርጫውን ማጭበርበሩን ራሱም ማጋለጥ ጀመረ፣አቶ ሀይለማሪያም በቁጥር ተጋለጡ ፣ የሕዝቡን ድምጽ መዘረፍ ተከትሎ የተቃውሞ ድምጽ እየተሰማ ነው

Hailemariam_election_002

(ሕብር ሬዲዮ-ላስ ቬጋስ) በኢትዮጵያ ገዢው ፓርቲ በሙሉ ቁጥጥሩ ለአምስተኛ ጊዜ ባከናወነው የይስሙላ ምርጫ የሕዝብ ድምጽ መዝረፉ በግልጽ እተነገረ ሕዝቡ፣የተቃዋሚ መሪዎችና የምርቻ ታዛቢዎች እየገለጹ ባለበት ሁኔታ ይህንኑ ተግባር በሚያጋልጥ መልኩ ራሱ የሚለጥፋቸው የየምርቻ ጣቢያ ውጤቶች ዘረፋውን ማከናወኑን ጭምር የሚአጋልጡ መሆን ጀምረዋል። አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የስርዓቱ ጠ/ሚ/ር ተቃዋሚዎችን <<ቁጥር አያውቁም እያሉ >> በከሰሱ ማግስት በተወዳደሩበት በወላይታ ዞን ምርጫ ጣቢያ በአንዱ ለሕዝቡ በተለጠፈ ውጤት መቶ በመቶ ድምጽ አግኝተው አሸነፉ ተባለ።

Tuesday, May 26, 2015

የምርጫና ነጻነት ቁልቁለት

ያኔና ዛሬ

female mps


* ከ45 ዓመት በፊት የፓርላማ ምርጫን ያሸነፉት አራት ሴቶች
ሰማንያ አራት ዓመት ባስቆጠረው የኢትዮጵያ ፓርላማ የመጀመርያው ሕዝብ በቀጥታ የተሳተፈበትና እንደራሴዎቹን የመረጠበት ምርጫ የተካሄደው በ1948 ዓ.ም. ነበር፡፡
በቀዳሚው ምርጫ ካሸነፉት ተወዳዳሪዎች መካከል አንዷ ወ/ሮ ስንዱ ገብሩ ናቸው፡፡ በታሪክ እንደተመዘገበው ወ/ሮ ስንዱ የመጀመሪያዋ የሴት የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አባልና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ለአራት ዓመት አገልግለዋል፡፡

የአዲስ ድምጽ ሬድዮ አዘጋጅ ጋዜጠኛ አበበ በለው የወያኔ ማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊትን አጋለጠ

ከታዬ ብርሃኑ ቨርጂኒያ
Audio Player

በስደት ላይ የሚገኘው ህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ በባልቲሞር ሜሪላንድ 41ኛው ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ሲኖዶሱ ያወጣው መገለጫ ይጠቁማል።በዚሁ መገለጫ ላይ ሲኖዶሱ ራሱን አይሲስ ብሎ በሚጠራው ቡድን የተሰዉትን ወጣቶች የኢትዮጵያውያን ሰማዕታት በሊቢያ ምድር መሰየማቸው እንደዚሁም ቤተሰቦቻችው እርዳታ የሚያሰባስብ በሊቀ ጳጳስ የሚመራ ግብረ ኃይል መቋቋሙን ያስረዳል። በተጨማሪም በዚህ የፈተና ወቅት መለያየቱ እንደማይበጅ አስረድቶ ራሳቸውን በገለልተኛነት መድበው የሚንቀሳቀሱ አብያተ ክርስቲያናትን ከህጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር አብረው እንዲሰሩ ጥሪ ያቀርባል።ይህ በእንደዚህ እንዳለ ራሱን ለህጋዊ ሲኖዶስ ተቆርቋሪ በማስመሰል ግን ህጋዊውን ሲኖዶስ ላይ ማህበራዊ ሚዲያ መርዝ የሚረጭ ወጣት አሉባልተኛ ከወደ ላስቬጋስ ብቅ ብሏል።በሳውዝ አፍሪካ የወያኔ ኤምባሲ ተላላኪና ጉዳይ አስፈጻሚ የነበረው ጉደኛ ወደ ላስቬጋዝ ብቅ ብሎ ጃኬቱን ገልብጦ የወያኔ ተቋዋሚ የሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ደጋፊ ሆኖ ተገኝቷል። ህጋዊ ሲኖዶስ ደግሞ የሚደግፈው በሲኖዶሱ ጥላ ስር ሆነው በመላው ሰሜን አሜሪካ፣በአውሮፓ፣በአውስትራልያና በአፍሪካ እየተዘዋወሩ የተሰደደው ኢትዮጵያውያንን እንደዚሁም ህጋዊውን ሲኖዶስ በትጋት የሚያገለግሉትን የወንጌል ገበሬዎችን በመሳደብና በማዋረድ እንደዚሁም ህጋዊ ሲኖዶስ ያልወሰነውን ውሳኔ በማንበብ ነው።

Monday, May 25, 2015

የምርጫው ማግስት መቼ ነው ? ( ሄኖክ የሺጥላ )

የምርጫው ማግስት መቼ ነው ? ( ሄኖክ የሺጥላ )
ታሪክ በሕይወት ዑደትና ሂደት ፣ ድርጊት ና በጊዜ ቀመር ተለክቶ ፣ ነገ ፣ ትናንት ፣ አምና ፣ ካቻምና ፣ የዛሬ ወር ፣ የዛሬ ዓመት ይባላል ። ይህም ታሪክ ድርጊቱ የሆነበትን ወቅት ከመለካት አልፎ ፣ የዘመኑን እድገት ፣ ፍልስፍና ፣ የህዝቦች ስነ ልቦናና ፣ አኗኗር አስረጅ አማዳዊ እና እምርታዊ ፣ ስለ ያኔው በመንገር ዛሬን ምን እንደሚመስል እና መምሰል እናዳለበት መሪ መንገድ ይሆናል ።
ለምሳሌ የአድዋ ድል ታሪክነቱ ትልቅነትን የተላበሰው ፣ ድሉ ቀን ስለነበረው ነው ። ድሉ ስል እና ብልህ አርበኞች ስለነበሩት ነው ። ድሉን የሚመሰክሩ ቋሚ ምስክራን ስለነበሩን ነው ። ድሉ የህዝብ ስለነበረ ነው ። ድሉ በነጻነት እና በባርነት መሃከል ስለተደረገው ትግል ጀግንነት ምስክር ስለነበረ ነው ። የአደዋ ድል ቀን አለው ። የድሉ ማግስትም ይታወቃል ።
የአድዋ ድል መጽሐፍ ተጽፎለታል ፣ የውጭ ሀገር ጸሐፊያን ( እነ አሉላ ፓንክረስት ስለ እኔ አሉላ ገጥመዋል ፣ እነ ጆሴፍ ሬሞንድ ስለ እቴጌ ጣይቱ ጽፈዋል ) የሀገራችን ገጣምያን እና ጸሐፊያን ( እነ ጳውሎስ ኞኞ የማይነጥፍ ብእራቸው ቃላቱን እስኪያጥጥ ተርከውለታል ፣ እነ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ተቀኝተውለታል ፣ ብላቴናው ቴዎድሮስ ካሳሁን የጥበብ ጥንፋሱን እፍ ብሎለታል ፣ እነ ገብረክርስቶስ ደስታ ፣ እነ ፣ እነ ከበደ ሚካዔል ፣ እነ መንግሱ ለማ ፣ ራሳቸው አለቃ ለማ ፣ እነ ሐዲስ አለማየሁ ፣ እና ሌሎቹም ስለ አድዋ ድል መስክረዋል ፣ አመስግነዋል ፣ ዘምረዋል ) ። ለምን አድዋ ድል ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ድሉ ቀን ስላለው ፣ ድሉ ማግስት ስላለው ፣ ድሉ ከድልነት ባሻገር ለታሪክ በረከት ስለነበረ ፣ ድሉ ድል ስለነበረ ።

የአቶ አዳርጋቸው ጽጌ ምስል ለጨረታ ቀርቦ 22,300 የአሜሪካ ዶላር አውጥቷል

ኢትዮጵያ ውስጥ የወያኔን እድሜ ለማራዘም የሀሰት ምርጫ በሚደረግበት ቀን በመላው አለም ተበትነው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን “በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ” (Ethiopian Current Affairs Discussion Forum) ተሰብስበዋል።Ato Andargachew Tsige's Picture
አላማቸው ወያኔ እድሜውን ለማራዘም ከሚያከናውነው የሀሰት ምርጫ የተለየ ነው “አርበኞች ግንቦት 7ን ለማጠናከር ገንዘብ ማሰባሰብ” በእለቱ የአቶ አዳርጋቸው ጽጌ ምስል ለጨረታ ቀርቧል ኢትዮጵያውያኑ በቡድን ተከፋፍለው ጠንካራ ፉክክር ሲያካሂዱ ከርመው በመጨረሻም ለጨረታ የቀረበው የአቶ አዳርጋቸው ጽጌ ምስል 22,300 የአሜሪካ ዶላር አውጥቶ ለአሸናፊው ተሰጥቷል።
የገንዘብ ማሰባሰቡ በቀጥቃ ወደ አርበኞች ግንቦት 7 የባንክ አካውንት ገንዘብ መላክንም ያካትታል።
“በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ” እየተደረገ ያለው አርበኞችን በፋይናንስ የማጠናከር ተግባር “ለሚቀጥሉት ሳምንታትም ተጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል ጉዳዩን የያዙት ታዳሚዎች።
በተመሳሳይ በአውሮፓ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አርበኞች ግንቦት 7ን ለማጠናከር የገንዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራሞችን እያካሄዱ ነው።

Sunday, May 24, 2015

ሥልጣን ወደ ህወሃት?!

“በሃይለማርያም አፈርኩባቸው” - በየነ ጴጥሮስ

tplf haile debretsion
* “ግምገማ!” የኢህአዴግ ስድብ ሃይማኖት
“ምግባረ ብልሹዎች ናችው፤ የሚታፈርባቸው ናቸው። እነሱን ብሆን ራሴን እንዳዋረድኩ ነው የምቆጥረው” ሲሉ የመድረክ ሊቀመንበር በየነ ጴጥሮስ ሃይለማርያምንና “ሌሎችም ቢሆኑ” ሲሉ የገለጹዋቸውን ባለሥልጣናት ምግባር ተቹ። ነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ቢኖር ኢህአዴግ እንደሚሸነፍ ከ፱፭ በመቶ እርግጠኛ መሆናቸውንም አመለከቱ።

ህወሃትና ሌቦክራሲ በኢትዮጵያ፣ ምርጫ ሳይሆን ግዳጅ

ከቢላል አበጋዝ፡ ዋሽግቶን ዲሲ
ሌቦክራሲ የሚለው የፖለቲካ ስርዓት ስያሜ የወያኔን ከ “ነጻ አውጭ ነት” ወደ ሌብነት ስርዓት መመስረት ያደረገውን ሽግግር አመልካች ነው። የሌቦች አገዛዝ ለማለት ነው። ሌቦክራሲ በስልጣን የባለጉ፤በሙስና የተዘፈቁ የሚመሩት ስርዓት ነው። በኢትዮጵያ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ከስልጣን ወጥቶ እንዲህ የህዝብ ንብረት በድፍረት የዘረፈበት ታሪክ የለም።እንዲህም አድርጎ ህዝብ ያፈነ ስርዓት አልነበረም። ይህ ምርጫ የሌቦች ስም ማደሻ ሰልፍ ማስተካከያ እንጂ ሌላ አይደም።የዚህ ስያሜ የሰጠነው ስርዓት እሰነብትበታለሁ የሚለው ትዕይንት ነው።የምናውቀው እባብ አዲስ ቆዳ የሚለብስበት።Ethiopian Election
አፍ ተሸብቦ፤ በግድ ምረጥ ብሎ፤ ካልመረጥ ደግሞ “ይከተልሃል” ተብሎ ምን ምርጫ ይባላል? ግዳጅ እንጂ።የቀድሞ ታዛቢ ያፈረበት፤ የተቸበት ምርጫ በኢትዮጵያ እየተካሄድ ነው። ህወሃት መሩ መንግስት ያለሀፍረት ተመረጥኩ፤ ህዝቡ እምነቱን ሰጠኝ ብሎ ለመደንፋት እየተመቻቸ ነው።
መጀመሪያ ዲሞክራሲን ምርጫ፤መመረጥ፤በየአራት፡ አምስት ዓመት፡ የሚመጣ፤ የሚሄድ አድርገን እንዳናይ በኛው ታሪክ እንኳን ቢያንስ የሁለት ዓሰርት ዓመታት ልምዳችን በቂ ትምህርት ሰጥቶናል።ከወያኔ ስርዓት ሌላ የነበረውን ትተን ማለት ነው።በምርጫ መሪዎች ማውጣት፤በምርጫው ጊዜ በሙሉ ፍላጎትና ስሜት መካፈልን አስመስክረናል።ኢትዮጵያውያን የዲሞክራሲ ስርዓት ናፍቆታቸውን የሁለት መቶ ዓመታት ልምድ አለን ከሚሉት ለምሳሌ አሜሪካ እንደማናንስ አሳይተናል።ኢትዮጵያዊው መራጭ ማለዳ የወጣ ጀምበር እስክትጠልቅ ድምጹን ለመስጠት ተራውን በመጠበቅ ጽናቱን አሳይቷል።

Saturday, May 23, 2015

ኢህአዴግ ሆይ ነቄ ነን ተቀየስ! (ርዕዮት አለሙ – ከቃልቲ እስርቤት)

ርዕዮት አለሙ – ከቃሊቲ እስርቤት
አራት ሆነን ወደምንኖርበት የአሁኑ የማግለያ ክፍል ከመግባቴ በፊት በርካታ እስረኞች በተለምዶ የአራድኛ ቃላት የሚባሉትን በመጠቀም ሲነጋገሩ የመስማት እድል ነበረኝ፡፡ ለርዕሴ የመረጥኳቸው ቃላትንም ያገኘሁት ከነሱው መሆኑን መግለፅ ይኖርብኛል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፤Reeyot Alemu, the 31 year-2012 Courage in Journalism Award winner.
አንዳንድ እስረኞች የሚፈልጉትን አንዳች ነገር ለማግኘት በጉልበታቸው ወይም ጤፍ በሚቆላ ምላሳቸው ይጠቀማሉ፡፡ ሀይልን በመጠቀም ያስገድዳሉ ወይም ያታልላሉ ማለት ነው፡፡ እንዲህ አይነቶቹ እስረኞች እንደለመዱት ለማድረግ ሲሞክሩ አንዳንዴ ደፋርና የማይታለሉ እስረኞች ላይ ይወድቃሉ፡፡ እናም ለማታለል ወይ ለማስገደድ የሞከረች ባለጌ የሚጠብቃት መልስ “ነቄ ነን እባክሽ! ተቀየሽ! ንኪው!”የሚል ይሆናል፡፡ እኛን ማታለልም ሆነ ማስፈራራት ስለማትችይ ይቅርብሽ፡፡ ዞርበይልን እንደማለት ነው፡፡
ኢህአዴግም እያደረጋቸው ያለው የማታለል ሙከራዎችና ተገቢ ያልሆኑ የሀይል እርምጃዎች ተመሳሳይ ምላሽ ሊያሰጡት እንደሚገባ አምናለሁ፡፡ የዘንድሮውን ምርጫ ለማለፍ ከወትሮው በከፋ ሁኔታ እየሄደባቸው ያሉት እነዚህ ሁለት ጠማማ መንገዶች መጨረሻቸው አውዳሚ ነው፡፡ በመሆኑም “ኢህአዴግ ሆይ ነቄ ነን ተቀየስ!” በማለት እኛና ሀገራችንን ይዞ ወደጥፋት እያደረገ ያለውን ግስጋሴ መግታት ይገባል፡፡

Friday, May 22, 2015

የወያኔን የይስሙላ ምርጫ አስመልክቶ ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢትዮጵያ ህዝብ የተላለፈ ጥሪ

የተከበራችሁ እናቶቼና አባቶቼ፤ እህቶቼና ወንድሞቼ እንዲሁም ልጆቼ የምትሆኑ ወጣቶች!! አገራችን የምትገኝበትን አስጨናቂ ሁኔታ ሁላችንም እንረዳለን። የህወሓት/ኢሕአዴግ ፋሽስቶች ቡድን እየገረፈ፣ እያሰረና እየገደለ በካርዳችሁ መርጣችሁ የምርጫ ድግሴን ካላሞቃችሁልኝ እያለ ነው። እንኳንስ ዛሬ ታዛቢ በሌለበት፤ ታዛቢ እያለም እንኳን ወያኔ የሕዝብን ድምጽ በትክክል ቆጥሮ አያውቅም። ወያኔ ለህዝብ ድምጽ ምንም ደንታ የሌለው የኋላቀር ወሮበሎች ቡድን ነው::Dr. Berhanu Nega’s election message to the Ethiopian people
ለስንት አስርት ዓመታት ለወያኔ ባርነት እንገብራለን? ለሀያ አስምስት ዓመታት ተገዛን፣ ተገደልን፣ ተቀጠቀጥን፣ ታሰርን፣ ተሰቃየን፣ ልጆቻችን በአገራቸው ተስፋ ቆርጠው ሲሰደዱ በበረሀ ንዳድ አለቁ፤ በባህር ሰጥመው ቀሩ፤ በባዕዳን አረመኔዎች እንደከብት ታረዱ፤ ቤንዚን ተርከፍክፎባቸው ተቃጠሉ። ሀይማኖታችን ተዋረደ፤ ባህላችን ረከሰ፤ ታሪካችን ተናቀ። በልማት ስም ወልደን ከከበድንበት ተፈናቀልን፤ አገራችን አደገች እያለ ሕዝብ በኑሮ ውድነት ተሰቃየ። በልቶ ማደር ብርቅ ነው። እንደሙጫ የሚያጣብቀንን ማህበረሰባዊ ትስስር በስልጣን ለመቆየትና ህብረተሰቡን ለመዝረፍ ሲል ሆን ብሎ እያፈራረሰው ነው:: ይኽ ሁሉ አይበቃንምን? ይኸ ሁሉ አይመረንምን?
ወላጆቼ፣ እህት ወንድሞቼ!ውርደት ይብቃን። የተረገጥንና የተገደልን አንሶን ፍጹም ማንንም ሊያሞኝ በማይችል የለበጣ ምርጫ ወደን የተረገጥን፤ ፈልገን የተገዛን ለማስመሰል ወያኔ የሚያደርገውን ሩጫ እናክሽፈው:: ከፊታችን ያለውን ምርጫ ባለመሳተፍ ምሬታችንን እንግለጽ።

ኢህአዴግ ሆይ ነቄ ነን ተቀየስ! (ርዕዮት አለሙ – ከቃልቲ እስርቤት)

ርዕዮት አለሙ – ከቃሊቲ እስርቤት
Reeyot Alemu, the 31 year-2012 Courage in Journalism Award winner.አራት ሆነን ወደምንኖርበት የአሁኑ የማግለያ ክፍል ከመግባቴ በፊት በርካታ እስረኞች በተለምዶ የአራድኛ ቃላት የሚባሉትን በመጠቀም ሲነጋገሩ የመስማት እድል ነበረኝ፡፡ ለርዕሴ የመረጥኳቸው ቃላትንም ያገኘሁት ከነሱው መሆኑን መግለፅ ይኖርብኛል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፤
አንዳንድ እስረኞች የሚፈልጉትን አንዳች ነገር ለማግኘት በጉልበታቸው ወይም ጤፍ በሚቆላ ምላሳቸው ይጠቀማሉ፡፡ ሀይልን በመጠቀም ያስገድዳሉ ወይም ያታልላሉ ማለት ነው፡፡ እንዲህ አይነቶቹ እስረኞች እንደለመዱት ለማድረግ ሲሞክሩ አንዳንዴ ደፋርና የማይታለሉ እስረኞች ላይ ይወድቃሉ፡፡ እናም ለማታለል ወይ ለማስገደድ የሞከረች ባለጌ የሚጠብቃት መልስ “ነቄ ነን እባክሽ! ተቀየሽ! ንኪው!”የሚል ይሆናል፡፡ እኛን ማታለልም ሆነ ማስፈራራት ስለማትችይ ይቅርብሽ፡፡ ዞርበይልን እንደማለት ነው፡፡
ኢህአዴግም እያደረጋቸው ያለው የማታለል ሙከራዎችና ተገቢ ያልሆኑ የሀይል እርምጃዎች ተመሳሳይ ምላሽ ሊያሰጡት እንደሚገባ አምናለሁ፡፡ የዘንድሮውን ምርጫ ለማለፍ ከወትሮው በከፋ ሁኔታ እየሄደባቸው ያሉት እነዚህ ሁለት ጠማማ መንገዶች መጨረሻቸው አውዳሚ ነው፡፡ በመሆኑም “ኢህአዴግ ሆይ ነቄ ነን ተቀየስ!” በማለት እኛና ሀገራችንን ይዞ ወደጥፋት እያደረገ ያለውን ግስጋሴ መግታት ይገባል፡፡

Tuesday, May 19, 2015

“ለውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ” ከአንዳርጋቸው ጽጌ እህት (ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ)

ይድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ እንዳሸዋ ተበትናችሁ የምትገኙ ወገኖቼ እኔ የተጎዳሁትን ያህል እናንተም የተጎዳችሁ መሆናችሁን በተለያዩ ሀገሮች በተደረጉ ሰልፎች ፤ የዉይይት መድረኮች ላይ በንዴት፤ በቁጭት እና በእልኸኝነት በእንባ ስትራጩ በመሃላችሁ ተገኝቼ ያየኻችሁ ሲሆን ይህም በጣም በኢትዮጵያዊነቴ እንድኮራ አድርጎኛል። አንዳርጋቸውም በወያኔ የጨለማ እስር ቤት እየከፈለ ያለውን መከራና መስዋትነት የትም እንዳልወደቀና እንዳልቀረ በማሰብ እጽናናለው።Letter from Andargachew Tige’s sister
ዛሬ አንዳርጋቸው ፅጌ በመላው ኢትዮጵያዊያን ዘንድ  “የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ“፤ “የኢትዮጵያ ልዩ አፈር“፤ “የኢትዮጵያ የበኩር ልጅ ” ወዘተ…. የሚሉ መገለጫዎችን እና መጠሪያዎችን የተጎናፅፈው ታናሽ ወንድሜ አንዳርጋቸው ፅጌ በእኔ እይታ ደግሞ የቤተሰባችን ልዩ ልጅ ነው።
አንዳርጋቸው የቤተሰባችን የመጀመረያ ወንድ ልጅ ስለነበረ ብርቅዬ መሆን  የጀመረው የካቲት 1 ቀን 1947 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው ቀዳማዊ  ኃይለ ስላሴ ሆስፒታል ከእናታችን ከወ/ሮ አልታዬ ተሰማ  ሮቢ እና ከአባታችን ከአቶ ፅጌ  ሀብተማርያም ጨሜሳ ከተወለደ ቀን ጀምሮ ነው።

Monday, May 18, 2015

የመሪዎች እምባ

የመሪዎች እምባ

hailemariam d


ከስም ልጀምር፣ የዛሬ ወጣቶች በተለይ ዘፋኞች ስማቸው በመጠኑ ተቆርጦ ወይም አንሶ ሲጠሩ እየሰማን ነው፤ ቴዎድሮስ – ቴዲ ብዙ ባያስከፋም ተያይዘው የቀጠሉት ዘፋኞች ግን እስከ አባታቸው ስለሚያሳንሱት ኢትጵያዊ ስም መሆኑ ራሱ አጠራጣሪ የሆነብኝ ጊዜ አለ። እስቲ አሁን ጃህ ሉድ አጥሮ ነው ወይስ ተቆርጦ ቻቺ፣ ጃኪ፣ ጂጂ፣ አቢ፣ ኢሚ፣ ዮሲ፣ ጃኪ-ጎሲ፣ ሚሊ፣ ሚኪ፣ ዮኒ፣ … ልተዋቸው።

መሸነፍን በአሸናፊነት የተቀበሉ መሪዎች

“ሕዝብን መታዘዝ ይገባል!”

eth election


በቅርቡ በሥልጣን ላይ እያሉ በምርጫ መሸነፋቸውን ባመኑበት ጊዜ ሥልጣናቸውን ያስረከቡት የናይጄሪያው ጉድላክ ዮናታን በአፍሪካ የ65 ዓመታት የምርጫ ዴሞክራሲ ጉዞ ከሚጠቀሱ ጥቂቶች መካከል አንዱ ሆነው ሰንብተዋል፡፡ ይህም ተግባራቸው በናይጄሪያ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ ታላቅ ሥፍራ የሚሰጣቸው የፖለቲካ ሰው አድርጓቸዋል፡፡

ኢትዮጵያና አሜሪካ (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
ዱሮ ዱሮ ምዕራባውያን የሶቭየት ኅብረትን ኮሚዩኒዝም መስፋፋት ለመቋቋም ከእሥራኤል ሌላ አጋር ሊሆኑ የሚችሉ አገሮችን ሲያስሱ፣ ኢትዮጵያ፣ ቱርክና ፋርስ እየታጩ ነበር፤ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር የተወዳጀበትና በአስመራ ቃኘው ጣቢያን የተከለበት አንዱ ምክንያት ይኸው ነው፤ የፋርስ ጉዳይ ከንጉሠ ነገሥቱ መፈንቅለ መንግሥትና ሞት ጋር አበቃ፤ ቱርክ እያንገራገረም ቢሆን የሰሜን አትላንቲክ አገሮች ማኅበር ውስጥ አለበት፤ እሥራኤል በአረቦች አካል ላይ እሾህ እንደሆነች ጥጋበኛ የአሜሪካ ቅምጥል ሆናለች።Prof. Mesfin Woldemariam : is an Ethiopian Human Rights activist and philosopher
የፋርሱ ጉዳይ ከፋርሱ ንጉሠ ነገሥት ጋር እንደተያያዘው ሁሉ የኢትዮጵያም ጉዳይ ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ጋር የተያያዘ ነበር፤ የእውቀት ጥበብ (ቴክኖሎጂ) እያደገ ሲሄድ የቃኘው ጣቢያ ለአሜሪካ አማራጭ የሌለው መሆኑ ቀረ፤ አሜሪካ ኮተቱን ይዞ ወደህንድ ውቅያኖስ ሲሄድ ኢትዮጵያን ችላ ማለት ተጀመረ፤ መቃቃሩ እየበረታ ሲሄድ የአሜሪካ እብሪትና የኢትዮጵያ ኩራት ተጋጩ፤ አጼ ኃይለ ሥላሴ የአሜሪካኑን አምባሳደር አስከማስወጣት ደረሱ፤ ጨዋታ ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ ያኔ ተጀመረ፤ የፋርሱ ንጉሠ ነገሥት ሲገለበጥ ቀጣዩ አገዛዝ ከአሜሪካ ጋር ጠላት እንደሆነው የአጼ ኃይለ ሥላሴም አገዛዝ ሲገለበጥ ቀጣዩ አገዛዝ ከአሜሪካ ጋር ጠላት ሆነ።

Saturday, May 16, 2015

Ethiopia Travel Alert: U.S. Department of State


U.S. Deeply Concerned by Sentence of Ethiopian JournalistThe State Department alerts U.S. citizens residing in or traveling to Ethiopia of the upcoming elections scheduled for May 24, 2015. U.S. citizens are urged to exercise caution and remain abreast of the security situation throughout the electoral period. This Travel Alert expires on June 30, 2015.
The State Department recommends U.S. citizens maintain a high level of security awareness during the electoral period and avoid political rallies, polling centers, demonstrations, and crowds of any kind as instances of unrest can occur. Review your personal security plans; remain aware of your surroundings, including local events; and monitor local news stations for updates. Although there have been no specific incidents of violence targeting U.S. citizens, U.S. citizens are urged to exercise caution and stay current with media coverage of local events. Election results are scheduled to be announced June 22, 2015.

Friday, May 15, 2015

ግንቦት 7ን በማስመልከት የወጣ የጋራ አቋም መግለጫ – አገራችንና ሕዝባቸን ማዳን ግባችን አድርገን በአንድነት አንሰራለን

አገራችንና ሕዝባቸን ማዳን ግባችን አድርገን በአንድነት አንሰራለን

Ginbot 7 Statement
የአንድነት፣ የመከባበር፣ የመቻቻል እና የነፃነት ምሳሌ የሆነችው አገራችን እኩይ አላማቸውን ለማሳካትና የስልጣን እድሜያቸውን ለማራዘም በሚንከላወሱት የወያኔ ቡደን አገራችንና ሕዝባችን ከምንግዜውም በከፋ ደረጃ ላይ አድርሰዋታል።

አይሲስን ስንቃወም ህወሓትን አለመርሳት!


def-thumbበአይሲስ በግፍ በታረዱብን ወገኖቻችን የተሰማን ሀዘንና ቁጭት ከፍተኛ ቢሆንም እንኳን ከአዕምሮዓችን መውጣት የሌለበት ሀቅ አለ። ይህ ሀቅ “ያስጠቃን፣ ያሳረደን ወያኔ ነው” ከሚለውም ያለፈ ነው። መረሳት የሌለበት ሀቅ፣ ከአይሲስ የከፋ ጨካኝ በአገራችን የመንግሥት ሥልጣን የተቆጣጠረ መሆኑ ነው።
የህወሓት ፋሽስት ጦር በበደኖ፣ በአዋሳ፣ በሀረር፣ በጋምቤላ፣ በጎንደር፣ በኦጋዴን፣ በአዲስ አበባ፣ በሸካና መዠንገር፤ እንዲሁም በሚታወቁም በማይታወቁም የማሰቃያ እስር ቤቶች አይሲስ እየፈፀመ ካለው የባሱ ወንጀሎች በወገኖቻችን ላይ ፈጽሟል፤ አሁንም እየፈፀመ ነው። ባሳለፍነው ሣምንት እንኳን በሁመራ ወገኖቻችን የራሳቸውን መቀበሪያ ጉድጓድ ቆፍረው በጅምላ ተገድለዋል። በአይሲስና በህወሓት መካከል ያለው ልዩነት አይሲስ ነውረኛና አረመኔዓዊ ተግባሩን በቪዲዮ እየቀረፀ ለዓለም ሲበትን ህወሓት ግን እነዚሁኑ ነውረኛና አረመኔዓዊ ተግባሮችን እየፈፀመ መረጃዎች አፍኖ መያዙ ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ግን ህወሓት ሰዎችን ከነሕይወታቸው ጉድጓድ ውስጥ የቀበረ አረመኔ፣ እኩይ ድርጅት ነው።
ስለሆነም ለዓለም ሰላም ስጋት የሆነውን አይሲስን ስንቃወም የራሳችንን አይሲስ – ህወሓትን – አለመርሳት እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ ህወሓት፣ የአይሲስን እኩይ ተግባራት ከኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጋር እና ከዲሞክራሲያዊያዊ ፓለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ጋር ለማገናኘት እያደረገ ያለው ጥረት ምን ያህል አደገኛ ተግባር እንደሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲረዳው ያስፈልጋል። ዓይን አውጣ ሌባ ንፁሁን ሰው “ሌባ” እንደሚለው ሁሉ የኛው አይሲስ ራሱን ንፁህ አስመስሎ ሌሎችን “አይሲስ” ማለቱ ሊነቃበት ይገባል።

Thursday, May 14, 2015

ኢትዮጵያ፡ የምንወድሽ ሀገራችን ደግመሽ አልቅሽ! (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የኢትዮጵያውያን/ት ህይወት ያሳስበናል!
እ.ኤ.አ በ2005 ልክ የዛሬ 10 ዓመት በያዝነው ወር ገደማ አሁን በህይወት የሌለው እና እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አድራጊ ፈጣሪ አምባገነን መሪ የነበረው መለስ ዜናዊ በዚያን ዓመት ተካሂዶ የነበረውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ሁከት የደህንነት እና የጦር ኃይሉን በእራሱ ቁጥጥር ስር በማዋል በሰላማዊ እና ባልታጠቁ ንጹሀን ዜጎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት እልቂት እና መከራን ያዘለ ዘመቻ አካሂዷል፡፡Cry Once Again, Our Beloved Country
እ.ኤ.አ ግንቦት 16/2005 መለስ ዜናዊ የፖሊስ፣ የደህንነት እና ወታደራዊ ኃይሉን በእራሱ ቁጥጥር ስር በማደረግ እና የአዲስ አበባ ከተማን የፖሊስ ኃይል ከፌዴራል ፖሊስ እና ከልዩ ኃይል ጋር በማቀናጀት ሁሉንም የህዝብ ስብሰባዎች ህገወጥ ናቸው በማለት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ ነበር፡፡ በቀጣዮቹ ሳምንታት የመለስ የጭፍጨፋ ኃይሎች አረመኒያዊ ጭፍጨፋ በማካሄድ 193 ሰላማዊ ንጹሀን ዜጎችን ግንባራቸውን እና ደረታቸውን በጥይት እያነጣጠሩ በመምታት የገደሉ ሲሆን ሌሎች 800 የሚሆኑ ወገኖቻችንን ደግሞ በጽኑ እንዲቆስሉ አድርገዋል፡፡

Wednesday, May 13, 2015

በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላይ ዘለፋ አዘል ግምገማ ተካሄደ

ኢሳት ዜና :- /ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በሰብሳቢነት የሚመሩት ኢህአዴግ፣ ከፍተኛ የግንባሩንና የመንግስት አመራሮችን በመገምገም ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የመንግስት ስልጣን የሚይዙትንና ድርጅቱን የሚመሩትን ሲመርጥ ከርሟል። ሁሉም የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹሞች የተገመገሙ ሲሆን፣ የመንግስት ስልጣን ያልያዙ ነገር ግን በግንባሩ ውስጥ ያገለገሉ ነባር ታጋዮችም በግምገማው ተሳትፈዋል። አቶ ሃይለማርያም ግምገማውን በሰብሳቢነት ሲመሩ ቆይተው፣ የመጨረሻው ተገምጋሚ ራሳቸው ሆነዋል።

የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጉዳይ ፤ ለ15 ሰዓታት እንደተገመገሙ ተገለጸ

የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጉዳይ ፤ ለ15 ሰዓታት እንደተገመገሙ ተገለጸ
አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ላለፉት ሁለት አመታት ሕወሃትን በታማኝነት ሲያገለግሉ እንደነበረ የሚታወቅ ነው። ከጅምሩ አንድ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሲሞት፣ ቦታዉን የሚይይዘው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተሩ ነበር። አቶ መለስ ሲሞቱ ምክትል ጠ/ሚኒስተር የነበሩት አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስተር ለማድረግ ፓርላማ ቀጠሮ ያዘ። ተጠባባቂ ጠ/ሚኒስተር መባል ጀመሩ። አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠ/ሚኒስተር እንደሚሆኑም ተገለጸ።
ሆኖም ሕወሃቶች ተቃወሙ። ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚመርጠው ፓርቲው እንጂ ፓርላማው አይደለም አሉ። በዚህም ምክንያት አቶ ኃይለማሪያም ጠ/ሚኒስትር እንዳይሆኑ ብሎክ አደረጉ። አቶ ኃይለማሪያም ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር መባላቸው ቀረና ምክትል ጠ/ሚኒስተር ወደ መባል ተመለሱ። ሕወሃቶች ከነርሱ ዉጭ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት እንዲያዝ አይፈልጉምና የነርሱን ሰው ለማስቀመጥ ደፋ ቀና ማለት ጀመሩ። ወ/ር አዜብም ከቤተ መንግስት አልወጣም አሉ። አቶ ኃይለማሪያም በዚህ ምክንያት ሌሊት በጠዋቱ እየወጡ ማታ ነበር ወደ ስራቸው የሚሄዱት።
አቶ ኃይለማሪያምን በቅርበት ለመከታተል፣ አቶ ጸጋዬ በርሔ እና አባይ ጸሃዬ የጠቅላይ ሚኒስተር አማካሪ ሆነው እንደሚሾሙ፣ አቶ ድበረ ጽዩን ደግሞ ፣ ከአቶ ደመቀ መኮንን እና ዘረኛ የኦሮሞ አክራሪውና የአናሌና ጨለንቆ የጥላቻ ሐዉልት አስገንቢው ሙክታር ከድር ጋር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር እንደሚሆኑ፣ ዶር ቴድሮስ በዉጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት እንደሚሰሩ ስምምነት ሲደረስ፣ ሕወሃቶች የአቶ ኃይለማሪያምን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ተቀበሉ። (በነገራችን ላይ ለአቶ ደመቀ እና ለዶር ቴድሮስ አክብሮት አለኝ)

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲንቅናቄ ከውህደቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን አርበኛ ታጋዮችባለፈው እሁድ ግንቦት 2 2007 ዓ.ም ደማቅናታሪካዊ በሆነ ስነ-ስርዓት አስመረቀ፡፡

አርበኞች ግንቦት 7

 አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከውህደቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን አርበኛ ታጋዮች ከትናንት በፊትእሁድ ግንቦት 2 2007 . ደማቅና ታሪካዊ በሆነ ስነ-ስርዓት አስመረቀ፡፡
Ginbot 7 and EPPF
እነዚህ በርካታ ቁጥር ያላቸው የመጀመሪያ ዙር ተመራቂ አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ተከታታይ ወራት የተሰጣቸውን የፖለቲካ፣ የወታደራዊ እናእንዲሁም የመረጃና ደህንነት ስፋትና ጥልቀት ያላቸውን ትምህርቶች በመውሰድ በብቃት የተወጡና በተግባር የተፈተኑ መሆናቸውን የአርበኞችግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ታጋይ ተስፋሁን ተገኘ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግርገልፀዋል፡፡