Translate

Friday, October 31, 2014

“ይህ አገዛዝ በቃው! አንፈልገውም! 27 ዓመት + 1 አንቀበልም!”

ቡርኪናፋሶ ከአምባገነን ወደ አምባገነን?

burkina-faso-1

ቡርኪናፋሶን ያለገደብ ሲመሩ የነበሩት ብሌዝ ኮምፓዎሬ ለተጨማሪ ዓመታት ሥልጣናቸውን ለማራዘም ያደረጉት ሙከራ በመክሸፉ ከሥልጣናቸው እንደሚለቁ ገለጹ፤ ለአንድ ዓመት የመሸጋገሪያ መንግሥት ተመስርቶ ምርጫ እስከሚደረግ በሥልጣን እንደሚቀጥሉ አስታወቁ፡፡ ሕዝቡና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ግን ይህንን የሚቀበሉበት ትከሻ እንደሌላቸውና የኮምፓዎሬ አገዛዝ አሁኑኑ መውረድ እንዳለበት በተቃውሟቸው እየገለጹ ነው፡፡ ከ27ዓመት አምባገነናዊ ሥርዓት በኋላ ቡርኪናፋሶ ወደ ሌላ አምባገነናዊ ሥርዓት ልትሄድ እንደምትች ተጠቆመ፡፡

Thursday, October 30, 2014

ሰበር ዜና – ‹‹አቦይ ስብሐት ጎበዝ ነኽ አለኝ›› ያሉት ፓትርያርኩ የማኅበራትን ተጠሪነትና የገንዘብ እንቅስቃሴ በሚመለከተው የሕጉ ረቂቅ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ተፋጠው ዋሉ

  • ፓትርያርኩ የማኅበራት ገንዘብ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ገቢ ኾኖ በማእከል ካልተመራ በሚል ከማኅበራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጋራ የሚቃረን ግትር አቋም ይዘው ውለዋል፡፡
  • አቋማቸው ተቀባይነት ካላገኘ ስብሰባውን ለመምራት እንደሚቸገሩ በመግለጽ ምልአተ ጉባኤን ለማስገደድ ያደረጉት ሙከራ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ጽኑ አቋም ሳቢያ አልተሳካላቸውም፡፡
  • ጉዳዩ ‹‹ከአዲስ አበባ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ጋራ ብዙ የሠራኹበትና የደከምኩበት ነው፤ በቀላሉ የምተወው አይደለም›› በሚል ከአክራሪነት ጋራ የተገናኘ ጽሑፍ ሲያነቡ ውለዋል፡፡
  • ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ‹አቦይ› ስብሐት ተናገረኝ እንዳሉት፣ ‹‹አንተ ጎበዝ ነኽ፤ ጽናት አለኽ፤ እንዲኽ ዐይነት ፓትርያርክ አይተን አናውቅም፡፡››
ከተጀመረ ስድስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የመጀመሪያ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ በዛሬ፣ ጥቅምት ፲፯ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ሙሉ ቀን ውሎው፣ የ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. ሕገ ቤተ ክርስቲያን ለማሻሻል በቀረበውና የልዩነት አቋም በተያዘባቸው የረቂቁ አንቀጾች ላይ ጠንካራ ውይይት ሲያደርግ አምሽቷል፡፡

“ተፌ!”


tefera w

ታጋይ፣ ከንቲባ፣ መከላከያ ሚ/ር፣ ምክትል ጠ/ሚ/ር፣ አቅም ገንቢ፣ አቅም ተገንቢ … ከዚህ ሁሉ አልፈው አሁን አቅማቸው ተገንብቶ የስፔስ (ሕዋ) ሳይንስ “አቅም ግንባታ” ለመሆን የበቁት ጡረተኛው ተፈራ ዋልዋ “የኢትዮጵያን የሕዋ (ስፔስ) ሳይንስ ሶሳይቲን” ገንብተው በሪፖርተር በኩል ብቅ ብለዋል፡፡
“አቅም ገንቢ ሚ/ር” በነበሩበት ወቅት “ሂድና ከአባዱላ ተማር የአንተ አቅም ግንባታ እንኳን አቅም ሊገነባ ያለውንም ሊያስቀጥል አልቻለም” ተብለው በአቶ መለስ የተገመገሙት አቶ ተፈራ አቅማቸው ተገንብቶ ለስፔስ መድረሱን “ባለራዕዩ መሪ” ሳያዩና ሪፖርተር ላይ ሳያነቡ መሰዋታቸው አቶ ተፈራን እጀ ሰባራ አድርጓቸዋል፡፡
የአላሙዲን “ወዳጅ” ሪፖርተር የአቶ ተፈራን አንደበት ገድቦት ነው እንጂ ተፈራ “ሼኸ፣ ዶ/ር፣ አቅም አስገንቢ … አላሙዲንን” ባነሱበት አንደበታቸው በግል ጄታቸው ገስግሰን ሁለተኛውን ሙት ዓመት “ነፍስ ይማር” በማለት አክብረን “በባለራዕዩ መሪያችን ስም በዚያውም ዛፍ ተክለን እና ፓርክ አቋቁመን እንዲሁም አንድ ፕላኔት በስማቸው አሰይመን” ተመልሰናል እንዳሉ ይገመታል – የሕዋው “አቅም ገንቢ” ተፌ! (ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®)

Wednesday, October 29, 2014

አዲስ አበባ ውስጥ ሌሊት የሚለጠፉ ወረቀቶችን ተከትሎ ውጥረት ነግሷል

“መረጃ ለአንድ ለአምስት ማቀበል አለባችሁ” ፖሊስና ካድሬዎች

addis p

  • የበር መብራት ማጥፋት ክልክል ነው፤ በሕግ ያስቀጣል
  • “መውጫና መግቢያ ሰዓታችሁ መመዝገብ ይጀመራል ተብለናል” ነዋሪዎቹ
ከትናንት በስቲያ በጨርቆስ አካባቢ አንድ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ መገኘቱን እና ሌሊት ላይ በቦሌ አካባቢ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን የሚያስተጋቡ ወረቀቶች በየግድግዳውና የኤሌክትሪክ ምሶሶ ላይ ተለጥፈው መገኘታቸውን ተከትሎ በከተማዋ ውጥረት መንገሱን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ከሰማያዊ ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ

ከሰማያዊ ፓርቲ
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ
ሰማያዊ ፓርቲ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በሕብረተሰቡ ዘንድ የሚነሱ በርካታ መሰረታዊና ወቅታዊ ጥያቄዎችን ጥያቄዎቹ አድርጎ ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥም ፓርቲያችን በተለያየ መልኩ የተቻለውን ሁሉ በማድረግ እየታገለ በመንግስት ላይ ጫና ለማሳደርና ችግሮች መፍትሔ የሚያገኙበት አቅጣጫ ሲያመለክት ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ የሀገራችን አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሱና እየከፉ የመምጣታቸውን ያህል ገዢው ፓርቲ ቆም ብሎ ከማሰብ ይልቅ ወደ ማይወጣው አዘቅት ውስጥ ሀገሪቷን ጭምር እያንደረደራት ይገኛል፡፡ ይህም አልበቃ ብሎ ከዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት ፍፁም በማይጣጣም መለኩ ዜጎችን ለአንድ ሀሳብ ብቻ እንዲገዙ አስገዳጅ መንገዶችን ጭምር በመጠቀም አፋኛ መዋቅሩን በማናለብኝነት እያስፋፋ ይገኛል፡፡ ይህም አልበቃ ብሎ ለማናቸውም አስተዳደራዊም ይሁን ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ሀይልን በመጠቀም ለመደፍጠጥና ለማጥፋት ቆርጦ በመነሳት ፍፁም አምባገነንነቱን ገፍቶበት የበርካቶች ህይወት ተቀጥፏል፡፡
ለዚሁ እንደማሳያም:-

Tuesday, October 28, 2014

የማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ ግንባታ: እውነቱና አሉቧልታው!

ማኅበረ ቅዱሳንን የሚወቅሱ ወገኖች ማኅበረ ቅዱሳንን ከሚወቅሱበት ነጥብ አንዱ ማኅበሩ ያሰራው ባለ ሰባት ፎቅ ሕንጻ ነው:: ለመሆኑ ይሄ የማኅበሩ ጽሕፈት ቤት ሕንጻ እንዴትና ለምን ተሰራ የሚለውን ጉዳይ ማየቱ ጠቃሚ ስለሆነ ባጭሩ እንመልከት::
mahbere kidusan building
ማኅበሩ ዋናው ማዕከል በመላው ዓለም ላይ የሚገኙ አባላቱን ለማስተባበርና የሚሰሩ ስራዎችን ለማቀናጀት አዲስ አበባ ላይ ቢሮ ተከራየ:: የአዲስ አበባ ማዕከልም እንዲሁ:: ከዚህም ባሻገር ሥራቸውን ባግባቡ ያከናውኑ ዘንድ የማኅበሩ የልማት ተቋማትም የራሳቸውን ቢሮ መከራየት ነበረባቸው:: ለነዚህ ቢሮዎች ኪራይ በየወሩ የሚከፈለው ገንዘብ ግን እጅግ ብዙ ሆነ::
በዚህ ወቅት ነበር ” ለኪራይ ይሄን ያህል ወጭ ከምናወጣ ለምን የራሳችንን ጽ/ቤት አንሰራም የሚል ሀሳብ የተነሳው:: ይህ ምክረ ሀሳብ ለሚመለከታቸው አመራሮች ቀርቦ ስለታመነበት የጽሕፈት ቤት ግንባታው ሥራ ተጀመረ::

የማለዳ ወግ…. የተመስገን ደሳለኝ እናት…

የማለዳ ወግ … ይድረስ ለወዳጀ ወንድም ለወዳጀ ታሪኩ ደሳለኝ !

ወንድሜ ሆይ ማምሻውን ” … አሁን የማወራው ስለ ብትቱው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሳይሆን ስለ ሆደ ባሻዋ እና ርህሩዋ እናታችን ነው! ” በማለት ስለ እናትህ ጭንቀት የጻፍከውን ሳነበው ፣ ስለ እናትህ ልቤ በሃዘን ተጎዳ ፣ ስለ ጀግኖች ሳይሆን ስለ ጀግና እናቶች መከራ አነባሁ ፣ እንደ ሰው በእልህ ሰውነቴ ጋለ ፣ ተናደድኩ …በቁጭት ግን አልቆዘምኩም …!
yetemesgen enat
ምን እንደምል አላውቅም … ለተጎዱት እናታችን አዝናለሁ ፣ ብቻ ሳይሆን ለመስዋዕትነት ለቀረቡት ለዚህች ቁርጥ ቀን ግንባራቸውን እንደ ተሜ ለሰጡት ብርቱ የሃገሬ ልጆች እናቶች በሙሉ አዝናለሁ “..ልጅሽ ወንድሜ ታስሯል! ” ለምትለው የመርዶ ነጋሪው ያንተ ጭንቀት ቢገባኝም ወጣት ነህና እንባህን ጠራርገህ ወንድምህ የሰጠንን ቃል አክብር ፣ ተከተልም! የጀግና ዘር አያለቅስም ! ተሜ አልነገረህም ? ወንድ ልጅ አደኮ አያነባም … በቃ እንዲያ ነው !!!!

Monday, October 27, 2014

ተመስገን ደሳለኝ 3 አመት ጽኑ እስራት ተፈረደበት


temesgen1

የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዛሬው ቀን በዋለው ችሎት 3 አመት ጽኑ እስራት ተፈረደበት፡፡ ፍትህን ሲያሳትም የነበረውና ሁለተኛ ተከሳሽ የሆነው ማስተዋል ህትመትና ማስታወቂያ በ10 ሺህ ብር ቅጣት ተጥሎበታል፡፡
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጥቅም 3/2007 ዓ.ም የመንግስትን ስም ማጥፋት፣ ህዝብን ማነሳሳትና የህዝብን አመለካከት ማናወጽ በሚሉ ሶስት ክሶች ጥፋተኛ የተባለ ሲሆን አሁን የተፈረደበት በትኛው እንደሆነ ባይታወቅም በአንደኛው ክስ ነው ተብሏል፡፡ የጥፋነኝነት ክሱ በተነበበት ወቅት ግን ‹‹መንግስት ይገድላል፣ ያፍናል፣ ይጨቁናል ብሎ ጽፏል፡፡›› በሚል ጥፋተኝ ነው ተብሏል፡፡
አቃቢ ህግ የቅጣት ማክበጃ ያላቀረበ ሲሆን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝም ሆነ ጠበቃው የቅጣት ማቅለያ አላቀረቡም፡፡ በሌላ በኩል የጋዜጠኛው ጠበቃ አምሃ መኮንን ይግባኝ እንደሚጠይቁ አስታውቀዋል፡፡ (ምንጭ: ነገረ ኢትዮጵያ)

Sunday, October 26, 2014

ለቅድስት ቤተ-ክርስቲያን መልካም ሥራ የሚሠሩ ማኅበራትን ለማፍረስ መሞከር ቅድስት ቤተ-ክርስቲያንን ለማፍረስ እንደመሞከር ይቆጠራል

መግለጫ ፎቶ
ጥቅምት 10 ቀን 2007 ዓ.ም.
ቁጥር : 10102014/0038
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
ለቅድስት ቤተ-ክርስቲያን መልካም ሥራ የሚሠሩ ማኅበራትን ለማፍረስ መሞከር ቅድስት ቤተ-ክርስቲያንን ለማፍረስ እንደመሞከር  ይቆጠራል::
ለቅድስት ቤተ-ክርስቲያናችን ሕልውና ዘወትር በትጋት በማገልገል ላይ የሚገኘውን ማኅበረ-ቅዱሳንን ለማፍረስ እየተካሔደ ያለውን እንቅስቃሴ በመቃወም ከዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት የወጣ መግለጫ

Saturday, October 25, 2014

የወያኔ ወሮበላ ዲፕሎማሲያዊነት፣

Prof. Alemayehu G. Mariam
 ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ወያኔ እያለ በሚጠራው እና ትግሉን በሰለጠነ መልኩበጠረጴዛውይይት እናየሀሳብ የበላይነት ሳይሆን ከጫካ በመግባት ብረትን የኃያልነት ዋስትናበማድረግ በንጹሀንዜጎች ደም ላይ ተረማምዶየጫካ ባህሪውን ከነግሳንግሱ እንዳለ ተሸክሞከህዝቦች ፈቃድ ውጭ በኃይልበህዝቦች ጫንቃ ላይ ተፈናጥጦ በሚገኘውየሽፍታ ቡድን የበላይነትየሚመራው በኢትዮጵያ ያለው ገዥአካል በአፍሪካ ወደር የማይገኝለት አምባገነን እናአረመኒያዊስብስብ እንደሆነ በተደጋጋሚ ስገልጽቆይቻለሁ፡፡ ዴሞክራሲ በህዝብ ለህዝብ የተቋቋመ ህዝባዊአስተዳደርከሆነ የወሮበላ አገዛዝ መንግስትደግሞ በዘራፊዎች እና በወሮበላዎች ለዘራፊዎች እናለወሮበላዎች የተቋቋመ የማፊያቡድን ነው፡፡ 

ፓትርያርኩ: የቤተ ክርስቲያን ራስ ቅዱስ ሲኖዶስ ባልመከረበትና ‹‹ለቤተ ክርስቲያን የማይመጥን ነው›› በተባለው የመክፈቻ ንግግራቸው ተገሠጹ፤ ውሳኔም ተላለፈባቸው!

  • ቅ/ሲኖዶሱኻያ ኹለት የስብሰባ አጀንዳዎችን በማጽደቅ መወያየት ጀምሯል
  • በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያው ሥልጣናቸውን የማጠናከር ውጥን አላቸው
  • የማኅበረ ቅዱሳን ደንብ አጀንዳ እንዳይኾን መቃወማቸው ውድቅ ተደርጓል
  • ሊቃነ ጳጳሳቱን ባዘለፉባቸው ሕገ ወጥ ስብሰባዎች ይቅርታ ጠይቀዋል
  • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በራሱ የሚመራው ሊቀ ጳጳስ ይመደብለታል
  • በደቡብና ምዕራብ ኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን ጸጥታ ጉዳይና የተሐድሶ መናፍቃን የሚፈጥሯቸው ችግሮች በአጀንዳነት ተይዘዋል
  • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመጨረሻው ከፍተኛ ሥልጣን ባለቤትና ከማንኛውም መዋቅር ኹሉ የበላይ አካል የኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለምልአተ ጉባኤው መደበኛ ስብሰባ ያሰሙትን የመክፈቻ ንግግር ‹‹ለቤተ ክርስቲያን የማይመጥን ነው›› በሚል በጥብቅ ተቃወመው፡፡ ተቃውሞው የተገለጸው፣ ምልአተ ጉባኤው የስብሰባው ቁጥር አንድ አጀንዳ ባደረገውየፓትርያርኩ የመክፈቻ ንግግር ላይ በተወያየበት ወቅት ነው፡፡

Friday, October 24, 2014

ምጽዓት

የዝርፊያው ፉክክር የት ለመድረስ ነው?

goat-and-sheep
“በግዞትም ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፡– ሂድ ለኢትዮጵያዊውም ለአቤሜሌክ እንዲህ በለው፤ — የእሥራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤- እነሆ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ፤ በዚያም ቀን በፊትህ ይፈጸማል፤ በዚያ ቀን አድንሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም፤ ፈጽሜ አድንሃለሁ፤ ነፍስህም እንደምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፤ በበእኔ ታምነሃልና ይላል እግዚአብሔር፡፡” ትንቢተ ኤርምያስ 39/15-18

የአ.አ ከንቲባ ጽ/ቤት ጠባቂ ፖሊሶች ተታኮሱ

የአ.አ ከንቲባ ጽ/ቤት ጠባቂ ፖሊሶች ተታኮሱ

addis ababa M
ፖሊሶቹ የተታኮሱት በከንቲባው ጽ/ቤት ውስጥ የሚሰሩ ፖሊሶች በነበራቸው ግምገማ በተፈጠረ አለመግባባት እንደሆነ ታውቋል፡፡ ፖሊሶቹ የተታኮሱት ከስብሰባው እንደወጡ እንደሆነም ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡
በከንቲባ ጽ/ቤት ፖሊሶች በተታኮሱበት ወቅት የአትክልት ተራን ጨምሮ በአካባቢው የሚገኘው ማህበረሰብ በድንጋጤ ውስጥ እንደነበርና አብዛኛው ከተኩሱ በኋላ ወደ አስተዳደሩ ቢሮ በማቅናቱ በከንቲባው ጽ/ቤት አካባቢ በርከት ያለ ህዝብ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ጠቅሰዋል፡፡
ፖሊሶቹ በተታኮሱበት ወቅት ገላጋዮች መሃላቸው በመግባታቸው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለና ይህም በግምገማው ወቅት ለገላጋይ ያበቃ አጨቃጫቂ ጉዳይ እንደነበራቸው ያሳያል ተብሏል፡፡ (የዜናው ምንጭ እና ፎቶ: ነገረ ኢትዮጵያ)

ከምርጫ ’97 “የተማረው” ኢህአዴግና የሚጠበቀው ሀገራዊ ምርጫ

(በላይ ማናዬ)

elec tion

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫን በተመለከተ ከሰሞኑ ለመነሻ ያህል የቀረበ ነው በሚል ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ለፓርቲዎቹ ለማስተዋወቅ ሞክሮ ነበር፡፡ ይህን የጊዜ ሰሌዳና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ከፓርቲዎቹ ጋር ለመምከር በሶስት ዋና ዋና ከተሞች (አዲስ አበባ፣ አዳማ እና ሀዋሳ) ፓርቲዎቹን ከፋፍሎ ለውይይት ጠርቶ የነበረ ቢሆንም ጥቂት የማይባሉ ፓርቲዎች መድረኩን ጥለው መውጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡

የቴሌ “አገልግሎት” መስተጓጎል ከሳምንት በላይ አስቆጠረ

"ችግሩ ሙሉ በሙሉ ተቀርፏል" የቴሌኮም ዳይሬክተር

eth telecom

ኢትዮ ቴሌኮም ከ1.6 ቢሊዮን ዶላር የማስፋፊያ ፕሮጀክት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ የሞባይል ማስፋፊያ መጠናቀቁ ቢገለጽም፣ አገልግሎቱ አሁንም በሞባይል አገልግሎት ላይ የሚታየውን ችግር ሊቀርፍ ባለመቻሉ፣ በተለይ ሰሞኑን ከአገልግሎት ጥራት ጋር በተያያዘ ደንበኞች ምሬታቸውን እየገለጹ ነው፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በበኩሉ ችግሩ የተከሰተው በተወሰኑ ቦታዎች እንደነበረና በአሁኑ ወቅት ግን ሙሉ ለሙሉ ተቀርፏል ይላል፡፡
በተለይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የከተማዋ የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች፣ የሞባይል መቆራረጥና የጥሪ መስተጓጎል ከሳምንት በላይ ያስቆጠረ ቢሆንም ባለፉት አምስት ቀናት ግን ችግሩ ይበልጥ መባባሱን አመልክተዋል፡፡

Thursday, October 23, 2014

ባነሰ ወጪ ድልን መቀዳጃ አመቺ ጊዜ ላይ ነን – እንጠቀምበት!

በአለፈው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ በምንም የማይገናኙ እና የተመሰቃቀሉ የሚመስሉ፤ በጥልቀት ላያቸው ግን የተያያዙና የተደጋገፉ ከመሆናቸው አልፎ እንደከዋክብት ፈለግ አቅጣጫን የሚያመላክቱ በርካታ ክስተቶች ተስተውለዋል። የጊዜ ቅደም ተከተላቸውን ሳንጠብቅ አንዳንዱን ለአብነት ያህል እናንሳ።
በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የዘነበው የዘለፋና የዛቻ ውርጅብኝ ህወሓት በቀጥታ በማይቆጣጠራቸው ማኅበራት ላይ ሁሉ ሲደርስ የቆየው ነፃ ማኅበራትን የማፍረስ ዘመቻ አካል መሆኑን መገንዘብ ቀላል ነው። ህወሓት የእስልምና እምነት ተከታዮችን ነፃ ማኅበርን በቁጥጥሩ ውስጥ ካስገባ በኋላ ፊቱን ወደ ክርስትና በተለይም ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ማዞሩ የተረጋገጠ ነገር ሆኗል። ወያኔ በሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ ማንም ከጥቃት እንደማያመልጥ፤ ለምንም ጉዳይ ይቋቋም ወያኔ የማይቆጣጠረው ማኅበር እንዲኖር የማይፈልግ መሆኑ ከዚህ በፊት የሚታወቅ ቢሆን በድጋሚ ማረጋገጫ የሰጠበት አጋጣሚ ሆኗል።
በመዠንግር ከአስራ አምስት በላይ የሥርዓቱ ታጣቂዎች ከነመሣሪያዎቻቸው አገዛዙን ክደው ጠፍተዋል። የጠፉትን ለማደን የመጡ ወታደሮች ደግሞ ከሕዝቡ ጋር በፈጠሩት ግጭት በርካቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በዚህ ግጭት ብቻ ከ40 በላይ ወታደሮች መገደላቸው ይነገራል። በጋምቤላ እና በቤንሻንጉልና ጉሙዝ ወረዳዎች ውጥረት ሰፍኗል። ከመሃል አገር ሄደው ኑሮዓቸውን እዚያው ያደረጉ ዜጎች ላይ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚደርስባቸው አፈናና እንግልት ጨምሯል። ግድብ እየተሠራበት ነው በሚባለው አካባቢም ከአሁኑ የፀጥታ ችግር እየደረሰ መሆኑ መረጃዎች ይጠቅማሉ። ወያኔ በምሥራቅ ኢትዮጵያ ኦጋዴን ውስጥ የገባበት ዓይነት ማጥ በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያም እየመጣ መሆኑ አመላካች ነው። የመከላከያ ሠራዊት አባላት መፍለስና የነፃነት ታጋዮችን መቀላቀል የእለት ለእለት ትዕይንት እየሆነ ነው።

መልዕክት ስለተመስገን ደሳለኝ ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ

‹ተመስገን፣ ጥሩ ታጋይ እና ሰው ሆኖ ለእስር ይወጣል››
‹‹ተመስገን፣ የህዝብ ልጅ ነው፤ ነገም ከነገወዲያም የህዝብ ልጆች ይፈጠራሉ››
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ‹‹ስለተመስገን ደሳለኝ ሃሳቤን አስተላልፍልኝ›› ካለኝ የተወሰደ
ከትናንት በስትያ፣ ሰኞ ዕለት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ የሆነውን አቶ አንዷለም አራጌን በ2007 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ላገኛቸው ችዬ ነበር – ለአቤል አለማየሁ ጋር፡፡ ባለፈው ሳምንት የ‹‹ባንዲራ ቀን›› በተከበረበት ዕለት ቃሊቲ ከወዳጄ እዩኤል ፍስሐ ጋር ሄጅ እነስክንድርን መጠየቅ ሳንችል ተመልሰን ነበር፡፡
የሆኖ ሆኖ፣ ከእስክንድር ጋር ለ15 ደቂቃ ያህል ለማውጋት ችለን ነበር፡፡ እስኬው፣ ሁሌም መንፈሱ ጠንካራ ነው፡፡ ሰኞም ያ አስደማሚ ጥንካሬው፣ ትህትናው፣ እውነተኛ ቅንነቱ፣ ብርታቱ፣ ቀናኢነቱ…አብረውት ነበሩ፡፡
ሰዓት ደርሶ ከእስክንድር ጋር ቻው ከተባባልን በኋላ ‹‹ኤልያስ፣ አንዴ ላናግርህ›› ብሎ ከጠራኝ በኋላ ‹‹እባክህ አንድ መልዕክት ስለተመስገን ደሳለኝ አስተላፍልኝ›› አለኝ፡፡ እስንክድር፣ ሁሌ ሀሳቤን አስተላልፍልኝ ሲለኝ ግልጽነቱ እጅግ ይማርካል፡፡

የህዝብ ግንኙነት ካድሬዎች በማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ ሊዘምቱ ነው


በአቶ ሬድዋን ሁሴን የሚመራው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አሰልጥኖ በፌዴራል የመንግስት ተቋማት በህዝብ ግንኙነት ኃላፊነት ለመደባቸው ካድሬዎች የሁለት ቀናት የማህበራዊ ድረገጾች አጠቃቀም ስልጠና በመስጠት በተለይ በግንቦት ወር ከሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ እንዲሳካ የበኩላቸውን አዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱ አደራ ተጥሎባቸዋል፡፡
የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን እንደገለጸው የኮምኒኬሽን ጽ/ቤቱ በሚኒስትሮች ምክርቤት ደንብ ቁጥር 158/2001 ሲቋቋም በመንግስትና በሕዝቡ መካከል ቀልጣፋ ውጤታማ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ማስቻል አንዱና ዋና ዓላማው ያደረገ ቢሆንም በተግባር ግን የሰለጠኑና ልምድ ያካበቱ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎችን የአመለካከት ችግር አለባቸው በሚል በማባረርና በማንሳፈፍ ካድሬዎችን በለብለብ ስልጠና ሲመድብ ቆይቷል፡፡ ዘርፉ ልምድና በቂ ስልጠና በሌላቸው ካድሬዎች በመያዙ በመረጃ አሰጣጥ በኩል ያለው ችግር እንዲባባስ ምክንያት ሆኗል፡፡
ጽ/ቤቱ የመደባቸው ካድሬዎች በተለይ በማህበራዊ ድረገጾች አጠቃቀም ደካማ በመሆናቸው ምክንያት ሚኒስትሩ አቶ ሬድዋን በሰበሰቡዋቸው ቁጥር ከፍተኛ ብስጭት የኢህአዴግን አቁዋም እንኩዋን መናገር የማይችሉ በማለት እስከመዝለፍ ደርሰዋል፡፡

Wednesday, October 22, 2014

የእንግሊዝ መንግሥት ለኢትዮጵያ ያዘጋጀውን የደኅንነት ማኔጅመንት ፈንድ አቋረጠ

በእንግሊዝ መንግሥት ገንዘብ ለኢትዮጵያ የደኅንነት ኃላፊዎች ይሰጥ የነበረው የደኅንነት ማኔጅመንት ፕሮግራም ተቋረጠ:ሪፕሪቭ የተባለ ነፃ የሕግ አገልግሎት የሚሰጥ የእንግሊዝ ኩባንያና ሌሎች የሰብዓዊ መብት አቀንቃኞች፣ ካለፈው ዓመት አጋማሽ ጀምሮ የእንግሊዝ መንግሥት ይህንን ፕሮግራም እንዲያቋርጥ ግፊት ሲያደርጉ ነበር::
እነዚህ ወገኖች ይህንን ግፊት የጀመሩት የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ምክንያት ዜጐችን ከመኖሪያ አካባቢያቸው ያፈናቅላል በሚል ክስ ነበር:: ይሁን እንጂ የግንቦት ሰባት ጸሐፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመንና
በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች፣ ባለፈው ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ወደ ኤርትራ ለመጓዝ የመን በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች፣ ባለፈው ሐምሌ 1ቀን 2006 ዓ.ም. ወደ ኤርትራ ለመጓዝ የመንሰንአ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ሥር ውለው ወዲያውኑ ለኢትዮጵያ መንግሥት ከተላለፉ በኋላ፣ በእንግሊዝ መንግሥት ላይ ጫናው እንዲጠናከር ሲጥሩ ነበር::
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አሁን ያለውን የኢትዮጵያ መንግሥት በኃይልም ሆነ በተገኘው አማራጭ ለመለወጥ የሚታገለው የግንቦት ሰባት አመራር ይሁኑ እንጂ፣ ዜግነታቸው እንግሊዛዊ መሆኑ ተጨማሪ ግፊት ይፈጥራል ብለውም ነበር::

Tuesday, October 21, 2014

ዘጠኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ከአዲስ አበባ እንዘገበው ዘጠኝ የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ ጥቅምት 11/2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ፓርቲዎቹ ለረዥም ጊዜ ስለ ትብብር ሲመካከሩ የቆዩ መሆኑ የታወቀ ሲሆን፣ ዛሬ ሰባት ገጽ ያለው ሰነድ ላይ የትብብር ፊርማቸውን በማኖር ትብብሩን ሊመሩ የሚችሉ አመራሮችንም መምረጣቸው ታውቋል፡፡
ዘጠኙ ፓርቲዎች የትብብር ስምምነቱ ያስፈለገበትን ምክንያት በሰነዱ ላይ ገልጸዋል፤ በዚህም ‹‹ነጻ አሳታፊና ታአማኒ ምርጫ እንዲካሄድ በትብብር ለመስራት፣ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትና የዜጎችን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ በጋራ መታገል››ን በተመለከተ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
በዚህም መሰረት ፈራሚዎቹ ፓርቲዎች የሚከተሉትን አመራሮች ትብብሩን እንዲመሩ መርጠዋል፡-
1. ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ከሰማያዊ ፓርቲ
2. ምክትል ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርጌሎ ከከንባታ ህዝቦች ኮንግረንስ
3 ዋና ፀኃፊ አቶ ግርማ በቀለ ከኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
4. ምክትል ፀኃፊ አቶ ካሳሁን አበባው ከመኢአድ
5. ገንዘብ ያዥ አቶ ኑሪ ሙደሂር ከመኢዴፓ ሆነው ተመርጠዋል፡፡
በትብብር ለመስራት ሲወያዩ ከነበሩት 14 ፓርቲዎች መካከል አንድነትና መድረክ ውስጥ የታቀፉት ፓርቲዎች ትብብሩን ለመፈረም በየ ድርጅቶቻቸው ውሳኔ ባለመተላለፉ ያልፈረሙ ሲሆን ትብብሩ እስከ ቅዳሜ እንዲጠብቃቸው ጠይቀዋል፡፡ በመሆኑም በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ትብብሩ ስለ ቀጣይ የትግል ሂደትና ስለ ትብብሩ አጠቃላይ ሂደት ላይ ነገ ጥቅምት 12/2007 ዓ.ም ከጠዋቱ አራት ሰዓት በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Monday, October 20, 2014

በኢትዮጵያ ያለው “የለማኝ መንግስት” አነሳስና አወዳደቅ

በኢትዮጵያ ያለው “የለማኝ መንግስት” አነሳስና አወዳደቅ
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
በአሁኑ ጊዜ የረዥም ጊዜ አንባቢዎቼ አንደምያውቁት ሁሉ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ያሉኝን ሀሳቦች እና ማሳመኛ የሙገታ ትንታኔዎች ከፍተኛ በሆነ ግልጽነት፣ እርግጠኝነት እና ለየት ባለ አቀራረብ ሁኔታ በእራሴ ቃላት እና ሀረጎች ለመግለፀ አሞከራለሁ፡፡ በዚህ በአሁኑ ትችቴ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ስርዓት በአመጽ እና በኃይል ከህዝቦች ፍላጎት ውጭ በስልጣን እርካብ ላይ ተፈናጥጦ የሚገኘውን ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሐት) እየተባለ የሚጠራውን “የለማኝ መንግስት” ገዥ ቡድን የፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍልስፍና መሰረት የሆነውን ጽንሰ ሀሳብ በማስተዋወቅ ውስጣዊ ይዘቱን እና ባህሪያቱን ለመመርመር እሞክራለሁ፡፡
በተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ እና የደቡብ ኤስያ አገሮች ብዙ የመከሰቻ መገለጫዎችን ያካተተ “ልመና” (ወይም ባክሸሽ) የሚባል የተለመደ ባህል አለ፡፡

ያዲሳባ ባለሥልጣናትና ቀምጣላ ካድሬዎች--ዝግ ቤቶች

ያዲሳባ ባለሥልጣናትና ቀምጣላ ካድሬዎች--ዝግ ቤቶች


“በሬ ለምኔ” የፍየል ቁርጥና ጥብስ መለያ ማስታወቂያ ነው። ከኦሎምፒያ ወደ መስቀልፍላወር በሚወስደው መንገድ ላፓሬዚን አለፍ እንዳሉ ወደ ግራ ሲታጠፉ ያገኙታል። ለጉዳዬ የሚመቸኝን በሬ ለምኔ ላመላክት እንጂ ብዙ “በሬ ለምኔ” ቤቶች አዲስ አበባ ተከፍተዋል። ያዲሳባ ቀምጣላ ካድሬዎች፣ ልማታዊ ባለሀብቶች፣ አቀባባዮችና ባለጊዜዎችና አጫፋሪዎቻቸው እድሜ ለማራዘም ፍየል ይመገቡና ማታ ልቅ የግብረ ስጋ ለማድራት አይጨነቁም።
የሚዘጋባቸው ህጻናት – ዝግ ቤቶች
እጠቆምኩት ቤት ስትገቡ ፍየል የሚያገላብጡት የሚታወቁ ባለሥልጣናትና ታዋቂ ካድሬዎች ናቸው። ፍየል ከገባ በኋላ መኪና ተረክ እያደረጉ እዛው ሰፈር፣ ብዙም ሳይርቅ ወይም ቦሌ መሃል፣ ዝግ ቤቶች ይሰየማሉ። አንዱን “ሮዚና” ዝግ ቤት ላስተዋውቃችሁ። ሮዚና ዝግ ቤት ማንም ዘው ብሎ አይገባም። ሮዚና ሲደርሱ እንደ መኖሪያ ቤት ጥሩምባ አሰምተው ከተንበሪውን የሚያስከፍቱ ደንበኞች ብቻ ናቸው። “ደንበኞች” ስል እንግባባለን ብዬ አስባለሁ።

Breaking News: የቀድሞው የኦነግ መሪ ዶ/ር ዲማ ነገዎ ኢትዮጵያ ገቡ

ዶክተር ዲማ ነገዎ አዲስ አበባ መግባታቸውን የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች አረጋገጡ::
የኦነግ መስራቾችና አንጋፋ መሪዎች፣ እነ ዶ/ር ዲማ ነግዎ፣ አቶ ሌንጮ ለታ የመሳሰሉት፣ የኦሮሞ ጥያቄ የመገንጠል ሳይሆን የዴሞክራሲ ጥያቄ ነዉ በሚል፣ ራሳቸውን ከኦነግ አግልለው፣ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፎረም (ኦዴፍ) የሚባል ድርጅት ማቋቋማቸውን ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ መግለጹዋ ይታወሳል::

«ሰላማዊ ትግል የሚባል ነገር አይሰራም፤ ጫካ ገብታችሁ ሞክሩን።» የብአዴን አመራሮች


በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ ጫናው በርትቷል፤
በምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ከገዥው ፓርቲ ባለስልጣናት የሚደርስባቸው ጫና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ። የምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ጸሃፊ የሆነው ጠበቃ ሳሙኤል አወቀ በእሱና በሌሎች የፓርቲው አመራሮችና አባላት ላይ ዛቻ እንደሚፈጸምባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ ቢሮ በ2006 ዓ.ም የእቅድ ግምገማ እና የ2007 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም እቅድ በተወያየበት እና የሁሉም ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የስራ ሂደት ባለቤቶች በተገኙበት፣ «ሳሙኤል አወቀ የሚባል በጥብቅና ሽፋን የመሬት ፖሊሲውን የሚታገል፣ ለተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ደጋፊ አርሶ አደሮች ጥብቅና የሚቆም፣ ከአሸባሪ ጋር ግንኙነት ባለው ድርጅት አመራር የሆነን ግለሰብ በህግ ሽፋን እስር ቤት እንዲወርድ ያላደረገ አቃቤ ህግ አቃቤ ህግ አይደለም» ተብሎ በህግ ስም እርምጃ እንዲወሰድበት ትዕዛዝ መተላለፉን ጠበቃው ገልጿል። በተለይ የደብረማርቆስ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት አቃቤ ህጎች ዋነኛ ችግራቸው ጠበቃ ሳሙኤልን በህግ ስም ማስቀጣት አለመቻላቸው እንደሆነ ተገምግመዋል ተብሏል። ጠበቃው ወዲያውኑ የፈጠራ ክስ እንደተመሰረተበት፣ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ «ለፍትህ ስርዓቱ አጋዥ ባለመሆኑ» በሚል መከሰሱንና ባልተከራከረበት ፍርድ ሂደትም 8000 ብር ቅጣት እንዲከፍል እንደተወሰነበት ገልጿል።

Sunday, October 19, 2014

“የዲግሪና የዲፕሎማ ወፍጮ ቤቶች”

ተፈጭና ተመረቅ – አስተምሮ መለስ

degree mill


በእንግሊዝኛው አጠራር የዲፕሎማ/የዲግሪ ወፍጮ ቤት (diploma/degree mills) ይባላሉ፡፡ በርካታዎቹ ሠለጠነ በሚባለው ዓለም ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ “ወፍጮ ቤቶች” የ“ትምህርት መረጃ” ለማግኘት በጣም ቀላል ነው፡፡ ዋናው መስፈርት አስፈላጊውን “የትምህርት ክፍያ” መፈጸም ብቻ ነው ፡፡ ከዚያ በወርቅ ቅብ የተንቆጠቆጠ “የባችለር” ወይም “የማስተርስ” ወይም “የዶክትሬት (ፒ.ኤች.ዲ.)” ዲግሪዎችን ማፈስ ነው፡፡ በቀጣይ የሚሆነው የ…ሚ/ር ወይም የ…ሚኒስትር ደኤታ ወዘተ መሆንና “በሹመት መዳበር” ነው፡፡ ከዚያ ህዝብ አናት ላይ “በስያሜ” ተቀምጦ መጋለብ ነው።

ሰማያዊ፣ መኢዴፓና ኢብአፓ የምርጫ ቦርድን ስብሰባ ረግጠው ወጡ

ከደቡብ ኅብረት ፕሮፌሰር በየነ ተመሳሳይ እርምጃ ወስደዋል


eth election

ምርጫ ቦርድ በጊዜ ሰሌዳ ላይ ለመወያየት በጊዮን ሆቴል የጠራውን ስብሰባ “ጥያቄዎቻችን የሚመልስ አይደለም” በሚል የሰማያዊ ፓርቲ ተወካዮች ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ከሰማያዊ ፓርቲ በተጨማሪም የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኢዴፓ) እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ) ተወካዮች ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል፡፡

Thursday, October 16, 2014

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ወገንተኝነቱን የሚያሳይበት ወቅት አሁን ነው!

ዘረኛውና ፋሽስታዊው የህወሓት አገዛዝ የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት በዘርና በፓለቲካ ወገንተኝነት በመከፋፈል ሹመቱና ጥቅማ ጥቅሙን ለራሱ ወገን፣ ችግሩንና መከራዉን ግን ለሌላው ኢትዮጵያዊ ያደለ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ሳይማሩና ሳይሰለጥኑ የጄኔራልነት ማዕረጎችን በሙሉ ሰብስበው የወሰዱት የህወሓት አባላት መሆናቸው የአደባባይ ሚስጢር ነው።
በወያኔ መዳፍ ውስጥ እየተሰቃየች ባለችው ኢትዮጵያችን ውስጥ በዘርም ይሁን በፓለቲካ አመለካከት ከህወሓት የተለዩ ኢትዮጵያዊያን ቢማሩም ቢሰለጥኑም ለከፍተኛ አመራርነት እንደማይበቁ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ያየነው ነው። አገዛዙ ቅራኔ ውስጥ በገባባቸው ቦታ ሁሉ እየዘመቱ ሕይወታቸውን እየገበሩ ያሉት ግን በመካከለኛና ዝቅተኛ ማዕረጎች ያሉ ኢትዮጵያዊያን መኮንኖችና ብዙሃኑ የሠራዊቱ አባላት የሆኑ ወታደሮችናቸው። ብዙሃኑ የሠራዊት ክፍል አለቆቹን ከመጠበቅ ባለፈ ድምጹን ከፍ አድርጎ ለመናገር እንኳን የማይፈቀድለት ሎሌ ተደርጓል።
ለኢትዮጵያዊ ወታደር ለህወሓት ሎሌ ከመሆን በላይ የሞት ሞት የለም። ብዙሃኑ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊቱ አባላት በጥቂት የወያኔ ሹማምንት የሚረገጥ መሆኑ የሠራዊቱን አባላት የግል ስብዕና ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የሠራዊቱን ክብር ይነካል። የሠራዊታችን የህወሓት አገልጋይ መሆን የምንወዳት አገራችን ኢትዮጵያን ያዋርዳል። ይህ ዉርደት በዚህ ሁኔታ መቀጠል የለበትም።
ከእንግዲህ ጄኔራሎችና ሌሎችም የበላይ አዛዦች ሁሉ የአንድ አካባቢ ተወላጆች በሆኑበት ሠራዊት ውስጥ ተስማምቶ መኖር መቀጠል እያንዳንዱን የመከላከያ ሠራዊት አባል ሊያሰፍር ይገባል። የህወሓት ጄኔራሎች ጮማ በውስኪ ሲያወራርዱ፤ በህንፃዎች ግንባታ፣ በባንኮች ንግድ፣ በግብርናና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ተሰማርተው ቢዝነሳቸውን ሲያጧጥፉ፣ ምስኪኖቹ የሠራዊቱ አባላት በኦጋዴን፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በአማራና በሌሎች የአገሪቱ ግዛቶች እየተወረወሩ ወገኖቻቸውን የሚፈጁበት ሥርዓት ማብቃት አለበት። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ብዙሃኑ አባላት ቤተሰቦቻቸው በችጋር እየተቆሉ የአዛዦቻቸው ሀብት ጠባቂ መሆናቸው ማክተም አለበት።

በኢትዮጵያ ተከታታይ ፍንዳታዎች ይደርሳሉ የሚለው ስጋት አይሏል * ደህነቶች እና የኢምባሲ አታሼዎች(ተወካዬች) በስብሰባ ተወጥረዋል

በኤምባሲዎች የደህንነት አታቼዎች(ተወካዬች) እና በወያኔ የደህንነት ባለስልጣናት መካከል ስብሰባ እየተካሄደ ነው።


ምኒልክ ሳልሳዊ እንደዘገበው 
በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀማጭነታቸውን ያደረጉ ምእራባውያን ዲፕሎማቶች ዘንድ የሚደርሱ እናፈነዳለን መረጃዎች ከፍተኛ የሆነ ስጋት እየፈጠሩ መሆኑን በአዲስ አበባ የሚገኙ እና ለደህንነት አታቼዎች ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል።
ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ሰዎች እንደሚናገሩት መሃል አገርን እና ምስራቅ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪት ክልሎች ይደረጋሉ የተባሉ ፍንዳታዎች ከአልሸባብ የመጡ ማስጠንቀቂያዎች ናቸው ቢባልም በአልሸባብ ውስጥ በተደረገ የመረጃ ማጣራት አልሸባብ ይህንን መረጃ እንዳልበተነ በአዲስ አበባ የአሜሪካን የደህንነት አታቼ ለማረጋገጥ ያደረጉት ሙከራ በከፊል ባይሳካም የሁኔታውን አሳሳቢነት አስመልክቶ በምእራባውያን የኤምባሲ ዲፕሎማቶች የደህንነት አታቼዎች እና በወያኔ የደህንነት ባለስልጣናት ጋር ስብሰባ መቀመጣቸው ታውቋል።

Wednesday, October 15, 2014

የህግ የበላይነት፣ የፓለቲካ ምህዳር እና ሰብአዊ መብት – የጸረ ሽብር ህጉ ሲገመገም

“ጋዜጠኝነትን እና የፖለቲካ ድርጅትን ሽፋን በማድረግ የሀገሪቱንና የሕዝቦቿን ሰላም ለማደፍረስ ከሚያስቡና ከሚፈልጉ ‘ሀይላት’ ጋር ግንኙነት በማድረግ የተለያዩ  የሽብር ተግባራትን ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር አውለናቸዋል።“ 
ይህ መግለጫ (መልስ) የኢትዮጵያ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ 652/2001 ከወጣበት ከነሀሴ 2001 ዓ.ም. ጀምሮ ጋዜጠኞችና በሰላማዊ መንገድ ተመዝግበው የፖለቲካ ምህዳሩን የተቀላቀሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት በኢህአዴግ መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ከታሰሩ በኋላ በመንግስት አካላት የሚሰጥ የተለመደ አባባል ነው።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በእስር ላይ ሳለ ያስተላለፈው መል ዕክት + (የክሱን ዶሴ ይዘናል)


(ኢ.ኤም.ኤፍ) ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶ፤ በአምስተኛ ፖሊስ ጣብያ ከቆየ በኋላ ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት ሊወሰድ በዝግጅት ላይ እንደነበረ፤ ትላንት በስፍራው ሄደው የጠየቁት ጋዜጠኞች ገልጸዋል። ከነዚህ ጋዜጠኞች መካከል ኤልያስ ገብሩ ስለሁኔታው በአጭሩ እንዲህ ብሏል።
ጋዜጠኛ ተመስገን በፌዴራል ፖሊሶች ታጅቦ ሲወሰድ
‹‹ለእስረኛ ማልቀስ/ ማዘን ሳይሆን የእስረኛውን መንገድ መከተል ነው››
‹‹የእስክንድር ሃሳብ ትክክል ነው›› ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ከነገረን የተወሰደ
*******************************
‹‹ፍትሕ›› ጋዜጣ ላይ በተስተናገዱ ሶስት ጽሑፎች ተከስሶ ለሁለት ዓመት ያህል የክስ ሂደቱ ሲታይ ቆይቶ በትናንትናው ዕለት በከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ‹‹ጥፋተኛ›› ከተባለ በኋላ ከትናንት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ዛሬ ጥዋት ላይ ከእስከዳር አለሙ፣ ይድነቃቸው ከበደ እና ስለሺ ሀጎስ ጋር ሄደን ጠይቀነው ነበር፡፡
ከተሜ ጋር በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳቦችን ተወያይተናል፣ በተወሰኑ ሀገራዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በየግል እምነቶታችንን በማንሳት ሃሳቦችን ተለዋውጠናል፡፡ ጥያቄዎችን አንስተን ምላሾችን ተደማምንም ነበር፡፡ …

Tuesday, October 14, 2014

ተመስገን ደሳለኝንም አሰሩት

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ታዋቂው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታሰረ። ተመስገን ደሳለኝ ከትላንት ጀምሮ፤ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶበት የታሰረ መሆኑን ለማወቅ ችለናል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከዚህ በፊት በተከሰሰበት እና ፍርድ ቤት ሲመላለስባቸው በነበሩት ክሶች ነው አሁን ለእስር የበቃው።
Temesegen Desalegn
ጋዜጠኛ ተመስገንን ለክስ ካበቁት ጽሁፎች መካከል፤ “መጅሊሱ፣ ሲኖዶሱና የአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ማጥመቂያዎች”፣ “የፈራ ይመለስ” እና “የብሄረሰቦች መብት እስከ መጨፈር” በሚል ርእስ የጻፋቸው ጽሁፎች ናቸው። ሁሉም ጽሁፎች አሁን እንዳይታተም በታገደው ፍትህ ጋዜጣ ላይ የወጡ ነበሩ።  በነዚህ ጽሁፎች ምክንያት አቃቤ ህጉ የክሱን ጭብጥ የመሰረተው፤ መንግስትን በአመፅ ለመናድ ቀስቅሷል፣ የመንግስትን ስም አጥፍቷል፣ የህዝብን አስተሳሰብ አናውጧል፤ በሚል ሲሆን ጽሁፎቹም ሆኑ ክሱ ሁለት አመታትን አስቆጥሯል።

Monday, October 13, 2014

“መፈንቅለ ዓለም ባንክ!”

ኢትዮጵያን ኦባንግ በብቸኝነት ወክለዋል

o at w b

ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ያህል የዓለም ባንክ በተለይ ከሲቪል ማኅበረሰቦች ጋር ሲያካሂድ የነበረው ስብሰባ “በመፈንቅለ ዓለም ባንክ” ተጠናቅቋል፡፡ ኢትዮጵያን በተለያዩ ዓለምአቀፋዊ መድረኮች በመወከል ድምጻቸውን የሚያሰሙትኦባንግ “በመፈንቅሉ” ከተሳተፉት የዓለም ሲቪል ማኅበረሰቦች መካከል ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ነበሩ፡፡

ከሐይማኖታዊ ይዘቱ ይልቅ ፖለቲካ ለሚሸተው የቤተ ክህነቱ ስብሰባ የትውልዱ ፖለቲካዊ ምላሽም ያስፈልገዋል።


ቅዱስ ላሊበላ ቤተ ክርስቲያን 

የሰሞኑ በቤተክህነት በአቡነ ማትያስ ሰብሳቢነት የተደረገው ጉባኤ እና በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተሰነዘረው የፈጠራ ክስ፣በመቀጠልም በኢቲቪ ዜና ላይ የተላለፈው ስብሰባውን አስታኮ ''ምዕመናን ነቅታችሁ ጠብቁ'' መሰል ዜና ሁሉ አንድ ነገር ያሳያል - በቤተ ክርስቲያን ላይ አንድ የአደጋ ደወል ከቅርበት እየተሰማ መሆኑን።

Sunday, October 12, 2014

48 + 1 ደቂቃ ቢያልፍ ምን እንደሚከተል ግንዛቤ ነበር

“ወያኔዎቹ የተሰራላቸው ውለታ አልገባቸውም”

time is up


ከስያሜው ጀምሮ እያነጋገረ ያለው የኢህአዴግ የአሜሪካ ጽ/ቤት የጥበቃ ሰራተኛ፣ በኢህአዴግ አባባል “ዲፕሎማት” አገር ለቆ እንዲወጣ ከተሰጠው የጊዜ ገደብ አንድ ደቂቃ ቢዘገይ ምን ሊከተል እንደሚችል አስቀድሞ ከስምምነት ላይ ተደርሶ እንደነበርተጠቆመ። በስምምነቱ መሰረት ወዲ ወይኒ መባረሩ ከህወሃት ደጋፊዎችና አመራሮች ቅሬታ ማስነሳቱን አስመልክቶ አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ዲፕሎማት “ወያኔዎቹ የተሰራላቸው ውለታ አልገባቸውም ማለት ነው” ሲሉ መደመጣቸውን የጎልጉል ታማኝ ምንጭ ተናገሩ።

“አሻራ” – በአንዳርጋቸው ጽጌ ዙሪያ ያጠነጠነች ልዩ ዕትም መጽሔት (PDF)

andargacew ashara magazine cover page
በአውስትራሊያ የሚገኙት ጋዜጠኞች አብይ አፈወርቅ እና ሳምሶን አስፋው በአንዳርጋቸው ጽጌ ዙሪያ ብቻ ያጠነጠነች አሻራ የተባለች የተለያዩ ታዋቂ ግለሰቦችን ቃለምልልስ እና ወቅታዊ ጽሑፍ የያዘች መጽሔት አሳትመዋል:: በኦን ላይን ለማንበብ የምትሹ እነሆ ተካፈሉዋት::

የኢህአዴግ ባለስልጣናት ስጋት ጨምሯል። ስብሰባ ማብዛት መፍትሄ አልሆነም።

☞ «ተቃዋሚዎች ተንሰራርተዋል… ሕዝቡ እንዳይውጠን መጠንቀቅ አለብን»
☞ የተጀመረው ትግል ፍሬያማነቱ እየታየ ስለሆነ ተቃዋሚዎች እና ሕዝቡ በንቃት በጋራ መሳተፍ አለባቸው።
☞ የባለስልጣናቱ ተስፋ እየተመናመነ ስለሆነ ሕዝቡ ትግሉን ማጠናከር ይጠበቅበታል።
የወያኔ ባለስልጣናት በስልጣን የመቆየት ፍላጎታቸው ላይ የተደነቀረው የህዝብ አቤቱታ እና የተቃዋሚዎች መንሰራራት ስጋት እንደሆነባቸው ታውቋል። ህዝቡ በጎሪጥ እያየን ያለበት ሁኔታ ተቃዋሚዎች አንድ እርከን አንሰራርተው መታየታቸው እንዲሁም ዲያስፖራው ጥርሱን ነቅሶ በነቂስ እየተቃወማቸው እንደሆነ ከዚህም በተጨማሪ ስልጠና ብለው በጠሩበት ቦታ ላይ ሁሉ የደረሰባቸው ተቃውሞ ሕዝባዊ ጥያቄ እና አስተያየት እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ተወያይተዋል።

Friday, October 10, 2014

የዓለም ባንክ 600 ሚሊዮን ዶላር ለኢትዮጵያ በብድር አበድሪያለሁ ቢልም የኢትዮጵያ መንግስት ስለ ጉዳዩ የማውቀው ነገር የለኝም ብሏል፡፡

የዓለም ባንክ 600 ሚሊዮን ዶላር ለኢትዮጵያ በብድር አበድሪያለሁ ቢልም የኢትዮጵያ መንግስት ስለ ጉዳዩ የማውቀው ነገር የለኝም ብሏል የዓለም ባንክ 600 ሚሊዮን ዶላሩ አበድሪያለሁ ሲል የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ስለ ጉዳዩ የሰማሁት ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ የመገናኛ ብዙሃን ነው እያለ ነው፡፡

የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በ23 ዓመት ጉዞው ያፈራቸው ጄነራል መኮንኖች ከወታደራዊ አመራር ሳይንስ ትምህርት እና ስልጠና አንፃር ሲመዘኑ

የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በ23 ዓመት ጉዞው ያፈራቸው ጄነራል መኮንኖች ከወታደራዊ አመራር  ሳይንስ ትምህርት እና ስልጠና አንፃር ሲመዘኑ
የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በ23 ዓመት ጉዞው ያፈራቸው ጄነራል መኮንኖች ከወታደራዊ አመራር  ሳይንስ ትምህርት እና ስልጠና አንፃር ሲመዘኑ

‘አሸባሪ ብዕሮች’ክንፉ አሰፋ

ይህች አጭር ጽሁፍ የተወሰደችው በአውስትራሊያ ከምትታተም “አሻራ” ከተሰኘች መጽሄት ልዩ እትም ላይ ነው።
የፈረንሳዩ አንባገነን ገዥ የነበረው ናፖሊዮን ቦናፓርት በአንድ ወቅት ስለ ነጻ ፕሬስ ሲናገር “ከአንድ ሺህ ሻምላዎች ይልቅ አራት ጋዜጦች የበለጠ መፈራት አለባቸው።” ነበር ያለው።

Thursday, October 9, 2014

ወያኔ ሲያስር አሜን….ሲገድልም አሜን – በኤፍሬም ማዴቦ

police ethiopia
ወያኔ ሲያስር አሜን….ሲገድልም አሜን
በኤፍሬም ማዴቦ
ብዕር የያዘ ማንም ሰዉ በዘመናችን ደግሞ የኮምፒተር መክተቢያ ፊቱ ላይ የደቀነ ሁሉ ከሱ ዉጭ ያለዉን ማንንም ሰዉ “ሌባ”፤ “ባንዳ” ወይም “ከሃዲ” እያለ እንዳሰኘዉ መጻፍ ይችላል። በተለይ በእንደኛ አይነቱ ሀላፊነትም ተጠያቂነትም በሌለበት ህብረተሰብ ዉስጥ ደግሞ የጓደኛዉ ሀሳብ ያልተስማማዉ ሁሉ እየተነሳ የገዛ ጓደኛዉን ባንዳና ከሃዲ አድርጎ ስለሚስለዉ የላይ የላዩን ብቻ ለሚመለከት ሰዉ አገራችን በባንዳና በአገር ወዳድ መሳ ለመሳ ለሁለት የተከፈለች ትመስላለች።

ጋጠ ወጡ ማን ነው?


የህወሃት ጉጅሌና ሎሌዎቹ መቼም ራሳቸውን የሚያይ አይንም መስታዎትም ያላቸው አይመስሉም። ሀፍረትና ይሉኝታ የሚባሉ ነገሮች በአጠገባቸው የዘሩ የማይመስሉት ለዚህ ሳይሆን ይቀራል። ምናልባትም ብልግና፣ ጭካኔ፣ ግፍ፣ አውሪያዊ ስብእና፣ ወገን ካለህግ መግደልና ማዋረድ፣ የህዝብ ሃብት በጠራራ ጸሃይ መዝረፍ ለእነሱ የተፈቀደና የተሰጠ ጸጋ አድርገው ሳይቆጥሩት ይቀራሉ?
ባለፈው ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሰለጠነና የዳበረ ስርዓት አከባበር በሰፈነበት ከተማ ውስጥ ባልታጠቁ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ሲተኩሱና ሲያስተኩሱ በመዋላቸው ለደረሰባቸው ትዝብት የነውረኝነት ሀፍረት እንደማፈር ሰላማዊዎቹንና በሰላማዊ መንገድ እስከ ሲቪላዊ አልታዘዝም ባይነት መብት ያላቸውን ጠንቅቀው አወቀው የተንቀሳቀሱትን ዜጎች ጋጠ ወጥና ባለጌዎች ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል። ትንሽ ሲቀዠብርባቸው ደግሞ ኦባማ ስላነጋገረን የቀኑ ተቃዋሚዎች፣ ይህ አልበቃ ሲል ደግሞ የሻእቢያ ተላላኪዎች ሲሉም ተደምጠዋል። ከአውሬነት ብዙ ያልተለዩት ደጋፊዎቻቸው ተኩሱን ሲያንጣጣ የነበረው የቀድሞ የስዩም መስፍን የግል አሽከርና ሹፌር የነበረው ወዲ ወይኒ ግደይ ስለተባረረ ንዴታቸውን ከአደባባይ እንኳን መደበቅ አልቻሉም።