Translate

Saturday, May 31, 2014

ለውጥን ፈልገን ለውጥንም ፈርተን በጭራሽ አናመጣውም

ዳዊት ዳባ

Revolution coming to Ethiopia
የለውጥ አስፈላጊነት ላይና ወያኔ መራሹ መንግስት ይበቃው ዘንድ ባብዛኛው ዜጋ ከተቻለ የሚለው እንዳለ ብዥታ የለም። ይህ ፍላጎት የብዙ ስረአቱ ውስጥ ያሉ ዜጎችም ጭምር መሆኑን የተለያዩ መረጃዎችን ጨምቆ ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል። በርግጥ የለውጡ አስፈላጊነት ላይ የሚስማሙና አይቀሬነቱን የሚያውቁ ነገር ግን ለውጡ የተረጋጋና ችግሮች ያልበዙበት እንዲሆን ይረዳል ብለው አገዛዙ ድርሻ በሚያደርግበት እንዲከወን የሚመኙ አሉ። ፈራ ተባ እያሉ ሀሳቡን አንዳንዴ ያነሱታል። ይህ ሀሳብ ክፋት ባይኖረውም ጥሩ ምኞት ብቻ ነው የሆነው። በትንሹ እንኳ ተቀባይነት እንዲያገኝ አይደለም እንዲሰማ ለማድረግ አገዛዙ ጉልብት አልሰጠው እያለ ብለጭ ድርግም ይላል። አውቆ የሚያደርገው በሚመስል ገና እነዚህ ጥሩ አሳቢ ዜጎች ቁምነገሩን ሲያነሱት አገዛዙ አንጀት ቁርጥ የሚያስደርግ ሰማይ ሰማይ የሚያካክል አጋረዊ ጥፋቶችን አከታትሎ እየፈጸመና እያላገጠበት ያስቸግራል። ለምን ብሎ ለሚጠይቅ?። ቀንደኛ ለሆኑት የስርአቱ ሰዎች ከኛ በላይ ይህ መንገድ እንዳማያዋጣቸውና እድሜያቸውን ማሳጠር ብቻ እንደሆነ አሳምረው ስለሚያውቁ ነው። እውነት ለመናገር ትክክልም ናቸው። የትኛውም ለውጥ የሚመጣበት መንገድ የመጨረሻ ውጤቱ ለነሱ መቶ በመቶ ፍፁም ተመሳሳይ ነው። አስፍተንና እርቀን አስበን፤ ሆደ ሰፊ ሆነን፤ ይቅር ብለናል ብለን መጫኛ ነክሰን ብንለምንም ልንሳምናቸውና ሀሳብ እንዲቀይሩ ለማድረግ አይቻለንም። የሰሩትን ያውቁታል። ስለዚህም ላልቆረጡ ይቁረጥ።

አገራዊ ስሜት ለምን ይጎድለናል?

በተክሉ አባተ

ከበርካታ ሳምንታት በፊት ከጓደኞቼ ጋር ኢትዮጵያ ስላለችበት ወቅታዊ ሁኔታ እየተወያየን ነበር:: ሁሉም ተሳታፊ የተስማማበት ጉዳይ ቢኖር ኢትዮጵያ ከምንም ጊዜ በላይ እጅግ ከባድ ማኅበራዊ ምጣኔ ሃብታዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ መግባቷን ነበር:: ለዚህም በግንባር ቀደምነት ተጠያቂው መንግስት እንደሆነ ቢሰመርበትም ህዝቡም ላለንበት ሁኔታ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ታላቅ አስተዋጽዖ እያደረገ እንደሚገኝ ተወስቷል::እንዲያውም ኢትዮጵያውያን ለአገርና ለለውጥ ያላቸው ስሜት እንደ በረዶ የቀዘቀዘ እንደሆነ ተነገረ:: ለዬት ያለና ታላቅ አገራዊና ወገናዊ ጉዳይ ሲነገር ህዝቡ ጸጥ ረጭ ብሎ ሰምቶ ሃሳቡን ሳይሰጥ ሹልክ እያለ እንደሚወጣ ሁሉም የታዘበውን እያነሳ ተናገረ:: ብዙዎች ለወገናቸው ጥልቅ ስሜት ስለሌላቸውና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በንቃት ስለማይሳተፉም መንግስት በጭቆናው እንዲቀጥል ሞራልና ጉልበት እየሰጡት እንደሆነም ተጨመረበት::
ከቀናት በኋላ በሌላ መድረክ ፋንታው የሚባል ወንድሜ ለኦስሎ ነዋሪዎች ከላከው ደብዳቤ ውስጥ “ለነገሩ ብዙ ኢትዮጵያዊ ሰው ለብዙ ነገር ስሜት የለውም” የሚል ትችት አገኘሁ:: ይህ በቀላሉ የማይታለፍ ጉዳይ እንደሆነና ውይይት እንደሚያስፈልገው በማመን ጸሃፊውን ቀጥለው በተዘረዘሩት ጥያቄዎች ዙሪያ ልምዱንና እውቀቱን እንዲያካፍለን ተማጸንኩት::
  • ሰው ስሜት የለውም ስንል ምን ማለታችን ነው?
  • የስሜት አለመኖር ምክንያቱና መንስዔው ምንድን ነው?
  • የስሜት አለመኖር የሚያስከትለው ጉዳት ወይም ጣጣ ምንድን ነው?
  • ስሜት-አልባነትን እንዴት ማጥፋት ወይም መቀነስ ይቻላል?
  • ስሜት-አልባነትን ለማጥፋት ወይም ለመቀነስ በሚደረግ ትግል ዋና ተዋንያን እነማን ናቸው?

Thursday, May 29, 2014

40 – 23 የኢህአዴግ የጎሳና የመጥበብ ሰረገላ ሐዲዱ ላይ ነውን?

“ኢትዮጵያን በጎሳ ሳጥን ቆልፎ የሚጓዘው ህወሃትና ድግሱ”



40 - 23
ህወሃት በነጻ አውጪ ስም ታግሎ ኢትዮጵያን መግዛት የጀመረበትን 23ኛ ዓመት በዓሉን እያከበረ ነው። ወዳጆቹና መሪዎቹ ባስቀመጡት እቅድ መሰረት ኢትዮጵያን “በመተካካትና በተሃድሶ” ስም ራሱን እያገላበጠ ለመግዛት የቆረጠው ጊዜ በትንሹ 40 ዓመታት እንደሆነ ይታወቃል። አሁን ባለው የሰረገላው ጉዞ ኢህአዴግ ከ40 – 23 ከመቀነሱ ውጪ አሰበበት ስለመድረሱ መገመት የሚያስችል ምልክት የለም። እንደውም ስጋት እንጂ።

የሰማያዊ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ

(ነገረ-ኢትዮጵያ) – የሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 20/2006 ዓ.ም ባደረገው የብሄራዊ ምክር ቤት ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ፡፡ ምክር ቤቱ በሊቀመንበሩ የቀረበውን የ6 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያጸደቀ ሲሆን ብሄራዊ ምክር ቤቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ቀጣይ ውሳኔዎችም ተላልፈዋል፡፡

Ethiopia's Semayawi (Blue) party logo
ከዚህም በተጨማሪ በሊቀመንበሩ የቀረበለትን የስራ አስፈጻሚዎች የቦታ ሽግሽግም ተቀብሎ ያጸደቀ ሲሆን በሽግሽጉ መሰረትም አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ፣ አቶ ዮናታን ተስፋዬ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ አቶ ጌታነህ ባልቻ የጥናትና ስትራቴጅ ኃላፊ እንዲሁም አቶ እያስፔድ ተስፋዬ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ አጽድቋል፡፡

Related Posts:

ዓባይ እንደዋዛ፤ ግድቡን ከጥላቻ አንጻር ማየት አደገኛ ነው (ዶ/ር አክሎግ ቢራራ፣ ክፍል አራት)

Click here for PDF

የዚህ ተከታታይ ፅሁፍ መሰረታዊ ሃሳብና ትንተና፤ ኢትዮጵያ ዓባይንና ሌሎች ወንዞቿን የራሷን ኢኪኖሚ ዘመናዊነት፤ ለሕዝቧ የምግብ ዋስትና ስኬታማነት፤ እያደገ ለሄደው ወጣት ትውልድ የስራ እድል የመፍጠር ወዘተ መብት ያላት መሆኑን የሚያጠናክር ነው። The Nile is African and Ethiopia is its hub በሚል አርእስት ለአለጀዚራ ያቀረብኩት ፅሁፍ ይኼን ይገባኛልነት በማስረጃ ተደግፎ ያሳያል። በአረብኛ የተተረጎመው ትንተና የብዙ አንባቢዎችን አስተሳሰብ እንደቀሰቀሰ ሰምቻለሁ፤ አሉታዊና ነቀፋ ያለበት ትችት አልደረሰኝም። የኢትዮጵያን ይገባኛልነት ሌሎች የጥቁር አፍሪካ ተፋሰስ አገሮች እንደሚደግፉም አሳይቻለሁ።
Ethiopia's dam on Abbay/Nile riverአከራካሪ ሆኖ ያየሁትና በተከታታይ ለመተንተን የሞከርኩት የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅምና ይገባኛልነት ከጥያቄ ውስጥ ለማስገባት አይደለም፤ ለማጠናከር ነው። ገዢውን ፓርቲ መቃወምና የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም መደገፍ የተለያዩ ነገሮች መሆናቸውን አሳይቻለሁ። የኢትዮጵያ ይገባኛልነት፤ ዘላቂ ጥቅምና ደህንነት ከጥያቄ ውስጥ መግባትና ለፖለቲካ መንደርደሪያና መጠቀሚያ ሊሆን አይገባውም እላለሁ። ኢትዮጵያ የባህር በሯን አጥታ ዓባይንም ማጣት ለተከታታይ ትውልድ በደል ነው። ለማስታወስ አፄ ኃይለሥላሴና ደርግ ለማልማት የሞከሩትን ዓባይ ዛሬ እድል ተገኝቶ የተሃድሶ ግድብ ስራ መጀመሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው ሂደት የተገኘ ነው። ሕዝቡ በመንፈሱም፤ በጉልበቱም፤ በገንዘቡም እንደሚደግፈው እንሰማለን። ለኢንቬስትመንቱ የሚፈሰው ኃብት የህወሓት/ኢህአዴግ የግል ኃብት አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ኃብት ነው። ጥቅሙም ለኢትዮጵያ ሕዝብ መሆን አለበት።

Tuesday, May 27, 2014

በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የሚፈፀመው ኢሰብአዊ ወንጀል

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

Crimes Against University Students and Humanity in Ethiopia
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
እ.ኤ.አ ሜይ 2/2014 ቢቢሲ/BBC እንደዘገበው በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ እንደመዥገር ተጣብቆ የሚገኘው ገዥ አካል የጸጥታ ኃይሎች ከመናገሻ ከተማዋ ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ በኩል በ80 ማይሎች ርቀት ላይ በምትገኘው የአምቦ ከተማ ላይ ቢያንስ 47 የዩኒቨርስቲ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ ረሽነዋል፡፡ ስብዕናው በውሸት እና በሀሰት ውንጀላ የበከተው ገዥ አካል ይህንን እልቂት እንደተለመደው ሽምጥጥ አድርጎ በመካድ “ጥቂት ጸረ ሰላም ኃይሎች በቆሰቆሱት እና በአስተባበሩት አመጽ“ ምክንያት የሚል የሀሰት ፍረጃ በመስጠት በግፍ የተገደሉትን ወገኖቻችንን ቁጥር ለማሳነስ ጥረት አድርጓል፡፡ ይህ በወጣት ተማሪዎች እና ህጻናት ላይ የተፈጸመው የማንአለብኝነት የእብደት አሰቃቂ እልቂት በዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች ዘንድ ሰፊ ሽፋን አልተሰጠውም፡፡

Monday, May 26, 2014

አቶ ስብሃት ነጋ – የእንደራደር ጥያቄዎን በታማኒ ተግባር ይጀምሩት!

ከአቢቹ ነጋ

ከዚህ በፊት የግንቦት ሰባት ድርጅት የንደራደር ጥያቄ ከኢትዮጵይ መንግሥት አንደደረሰው በአፅኖት አውርቶናል። ብዙ ሕዝብ የግንቦት ሰባትን ዜና በማድቤት የተፈበረከ እራስን የመካቢያ ወሬ አድርጎት አንደነበር አይዘነጋም። እኔ ግን ዜናውን አንደወረድ መቀበል ብቻ ሳይሆን ደስተኛም ነበርሁ። ኢትዮጵያን አግዚአብሔር አንደሚጠብቃትም ያመንሁበት ወቅት ነበር ማለት ይቻላል። የዋህ ላገር ቅን አሳቢ ስለሆንህ እንጅ ከእባብ የርግብ አንቁላል እንዴት ትጠብቃለህ ብባልም የባብ መርዝም መዳህኒት ሊሆን እንደሚችል ይታወቅ ብያለሁ።TPLF power broker, Sibehat Nega
ከሁልም ያስደስተኝ ግን ግንቦት ሰባት ጥያቄውን በሕዝባዊ መግለጫው ያስተናገደበት ዘዴ ነበር። አንዳንድ ሰዎች ድርጅቱ በኢሃዴግ ተጠይቆ ከሆነ ጉዳዩን በምስጢር ይዞ ማካሄድ ነበረበት ብለዋል። የሕዝብን ጉዳይ ይፋ ማድረጉ የሚአስመሰግነው እንጅ ሊአስወቅሰው አይገባም። ከሁሉም በጣም የሚአስደስተው ደግሞ ድርጅቱ ከመንግሥት ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ለመወያየትና ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን ጠቅሶ ለድርድሩ ታማኒነት መንግሥት በቅድሚያ ማድረግ ያለበትን ነገሮች ይፋ ማድረጉ ነበር። በመሰረቱ ይህ ከፍተኛ የሆነ ያገር ጉዳይ ለህዝብ ምስጥር የሚሆንበት ምክንያት ውሃ የሚቋጥር አይሆንም። ድርድሩ ቢጀመር ግን ሂደቱን የሚአደናቅፉ ሁኔታውች አንዳይከሰቱ ሲባል በምስጢር ሊያዙ የሚችሉ ጉዳዮች ግን ይኖራሉ። በዚህ ድርጊቱ ግንቦት ሰባት የመንግሥትን ሀቀኝነት ፈትሾታል ቢባል ማጋነን አይሆንም።

የዞን ዘጠኙ በፍቃዱ፣ እንደ ሀገር ወዳድ ዜጋ… (ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጎዳና)


Befekadu Zone9
በመጋቢት ወር 2005 ዓ.ም ከጋዜጠኛ እና ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ ጋር በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘነው ዕንቁ መጽሔት ላይ ነበር እሱ ማኔጂንግ ኤዲተር እኔ ደግሞ ዋና አዘጋጅ ሆኜ፡፡ ከትውውቃችን ቀን ጀምሮ በፍቄ እንጂ በፍቃዱ ብየው እንኳን አላውቅም፡፡ በፍቃዱ ሳውቀው በጣም ረጋ ያለ፣ ትሁት፣ ሰውን በአክብሮት ብቻ የሚያናግር፣ አስተዋይ፣ ሰውን የሚረዳ፣ የራሱን ሀሳብ፣ አቋምና ዕምነት በቀላሉ የሚያስረዳ፣ የተለየ የሰዎችን ሀሳብ፣ አቋምና ዕምነት በጨዋ ደንብ የሚያከብር (ይሄን ዐይነት ባህሪ ብዙ ሰዎች ጋር መመልከት አልቻልኩም)፣ በሀሳቦች ላይ ውይይት የሚወድ፣ ጊዜውን በአግባቡ ከፋፍሎ ለሚወዳቸው ሥራዎቹ የሚሮጥ፣ ራሱን በዕውቀት፣ በወቅታዊ መረጃዎችና በተለያዩ ሥልጠናዎች ማበልጸግ የሚወድ እጅግ ቅን ልጅ ነው፡፡
በመጽሔቷ ላይ ለአምስት ወራት ያህል አብረን ሰርተን ነበር፡፡ በእነዚህ ጊዜያቶች ሀታታዊም ሆነ ግለ-ሃሳባዊ ጽሑፎችን ለማሰናዳት ጠቃሚ ወቅታዊ መረጃዎችን መሰብሰብ ይወዳል፡፡ በመረጃዎቹ ላይ ከባልደረቦቹ ጋር መደበኛም ሆነ መደበኛ ባልሆኑ ስብሳባዎች ላይ ውይይት ከፍቶ ሐሳቦችን መለዋወጥም ልምዱ ነበር፡፡ ይህን ዓይነት ልምድ ለየትኛውም ነጻ ጋዜጠኛ ወሳኝ ነው የሚል ጠንካራ እምነት አለኝ፡፡ በቢሮ ጠረጼዛ ላይ ተጀምረው በቢሮ ጠረጼዛ ላይ የሚጠናቀቁ ጽሑፎችን የሚያሰናዱ፣ ለመስክ ሥራ መልፋት የማይወዱ “ጋዜጠኞች” እና ጸሐፊያን በሀገራችን መኖራቸውንም አውቃለሁ፡፡

ያለ በቂ ማስረጃ በሕገ ወጥ መንገድ ከአራት ሳምንት በፌት ከተያዙት ስድስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በተጨማሪ በአንድ ጦማሪ አባል መኖሪያ ቤት ላይ ፖሊስ ለ7 ሰአት የቆየ ብርበራ አካሄደ

Zone9

ያለ በቂ ማስረጃ በሕገ ወጥ መንገድ ከአራት ሳምንት በፌት ከተያዙት ስድስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በተጨማሪ በአንድ ጦማሪ አባል መኖሪያ ቤት ላይ ፖሊስ ለ7 ሰአት የቆየ ብርበራ አካሄደ፡፡Zone 9 bloggers
በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ በዞን ዘጠኝ ጦማሪና መስራች ሶልያና ሽመልስ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ፖሊስ ብርበራ ያካሄደ ሲሆን የጸረ-ሽብር ሕጉ ይፈቅድልናል የሚል ምክንያት ሰጥተው ያለ ፍርድ ቤት የብረበራ ማዘዣ ከካሜራ ቀራጭ ጋር የተገኙት ሰባት ፖሊሶች በጦማሪዋ ክፍል እና ሌሎች አስፈላጊ ነው ባሉዋቸው ክፍሎች ሲያካሂዱ ነበረውን ብርበራ ጨርሰው ይጠቅመናል ያሉትን የዶ/ር መረራ ጉዲና የመጨረሻ መጽሀፍ እና ሌሎች ወረቀቶች ወስደው ቤት ውስጥ የነበሩትን የጦማሪዋን ወላጅ እናት አስፈርመው ከጠዋቱ 4 ሰአት አካባቢ ቤቱን ለቀው ወጥተው ነበር፡፡ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ተመልሰው በመምጣት ተጨማሪ ፍተሻ በዋናው መኖሪያ ቤት መካሄድ እንፈልጋለን ብለው ሁለተኛ ዙር ብርበራ በምግብ ማብሰያ ክፍል ውስጥ እናካሂዳከን በሚል ሰበብ ትንሹ ክፍል ውስጥ የጦማሪዋን እናት እነዲወጡ በማግለል ከማቀዝቀዛውን አንቀሳቅሰው አፍታም ሳይቆዩ 19 ገጽ የግንቦት ሰባት ፕሮግራም አግኝቻለሁ ሲል አንዱ ፈታሽ ተናግሯል፡።

Sunday, May 25, 2014

<< ለሰፊው ህዝብ ጥቅም >> የተቆጣጠርነው ሬዲዮ ጣቢያ የት ሄደ ?

( አሌክስ አብርሃም )
Photo: << ለሰፊው ህዝብ ጥቅም  >> የተቆጣጠርነው ሬዲዮ ጣቢያ የት ሄደ ?
( አሌክስ አብርሃም )

የዛሬ 23 አመት (ጊዜው እንዴት ይሮጣል ) የአንድ ታጋይ አጭር ንግግር የኢትዮጲያን  አየር ሞላ  እንዲህ ሲል ….
‹‹ የጭቁን ህዝብ ብሶት የወለደው  ጅግናው  የኢህዴግ ሰራዊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የአዲስ  አበባ የሬዲዮ ጣቢያ ለ(((ሰፊው ህዝብ ጥቅም )))ተቆጣጥሮታል !! ግንቦት 20  ሽ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት  ዓመተ ምህረት ! ›› ወዲያው ‹‹አሳ በለው በለው ›› የሚል ሙዚቃ ተከተለ (አሳና የትጥቅ ትግል ምን እንደሚያገናኛቸው ባይታወቅም አሳ በለው ሞቅ ብሎ ተሰማ . . . ምናልባትም እንደባህር የሰፋችው አዲስ አበባ ውስጥ  ታጋዮች አንደአሳ ነባሪ በነፃነት መዋኘታቸውን ለመጠቆም እንደሆነም እንጃ  ) 

እንግዲህ ኢህዴግ  የሬዲዮ ጣቢያውን  ለሰፊው ህዝብ ከመቆጣጠሩ በፊት  ሬዲዮ ጣቢያው ‹‹የሰፊው ህዝብ ›› እንደነበር ደርግም ሲናገር ነው የኖረው ! ከሰፊው ህዝብ መጠቀሚያነት ወደሰፊው ህዝብ መጠቀሚያነት የተላለፈው ሬዲዮ ጣቢያ ግን ከሰፊ የመንግስት ፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያነት ወደ በጣም ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ድምፅ ማጉሊያነት ከመተላለፍ ያለፈ ምንም ለውጥም እድገትም አላሳየም !   
  

በደርግ ጊዜ  ‹‹ልጅህን  ለብሄራዊ ውትድርና  ላክ ›› ሲባል ህዝቡ እንዲህ ይል ነበር  ‹‹እኛ ልጆቻችንን እሳት ውስጥ መማገድ አንፈልግም ››  ሬዲዮው  ግን  ህዝቡ ያላለውን  እንዲህ በማለት ዜና ያውጅ ነበረ  ‹‹ ሰፊው የኢትዮጲያ ህዝብ  ተገንጣይ ወንበዴን ለማደባየት ልጆቹን  ሃብቱን ለመስጠት ቃል ገባ !! ›› 
‹‹ ምንም የማያውቁ ልጆቻችንን በግፍ ረሸናችሁብን ›› ሶል ህዝቡ ሬዲዮው ‹‹ ፀረ አቢዮተኞች ላይ የህዝብና የአቢዮት ጠላት የሆኑት ላይ ርምጃ ተወሰደ ›› ህዝቡ ግራ ገባው !  ሃቁን ፍለጋ  ደበቅ ብሎ ከጫካ የምትተላለፈውን  የ‹‹ትሃት ››ን ሬዲዮ ማዳመጥ ጀመረ  እሷ መቶ ገደልኩ  ሶስት መቶ ማረኩ ስትል ያምናታል ….አገር የሚያስተዳድረው መንግስት ውሸታም ነበራ ! ገዡ ከዋሸ  ማንም ተነስቶ ህዝብን ውሸት ቢነግረው ያምናል ! ውሸት እንዲያምን የሚገደድ ህዝብ የሌሎችንም ውሸት የማያምንበት ምክንያት የለማ ! 

ኢህዴግ ስልጣን ላይ ወጣ …. ሬዲዮው ከአልጋ ስር ወጥቶ ጠረጴዛ ላይ ተቀመጠና  ህዝቡም ያለመሳቀቅ ማድመጥ ጀመረ ! ምን ያደርጋል  ህዝቡ ‹‹ኧረ ልጆቻችን ስራ አጡ ›› ሲል ሬዲዮው ‹‹ ወጣቱ ስራ ፈጥሮ ሃብት በሃብት ሆነ›› ማለት ጀመረ ! በቃ ይሄ ነገር ከቤቱ ነው ሬዲዮ  ጣቢያውን ጠበል እንርጨው   ወይም  ብሄራዊ ሬዲዮ ጣቢያችን  መሳሪያውን ነቅሎ ጫካ ይግባና  ከጫካ  ፕሮግራሙን  ያስተላልፍልን  እግራቸው ከተማ ሲረግጥ ነገር እየተበላሸ ነው ያሉም ነበሩ . . . 

በዛም በዚህም ሬዲዮው የሚያወራው  የመንግስትን ጉዳይ እንጅ የህዝብን እውነት አልሆን ቢለው ህዝቡ መለስ ብሎ ሰውየውን   ማሰብ ጀመረ የቱን ሰውየ  ? ኢሃዴግ  ሬዲዮ ጣቢያውን  ሲቆጣጠር  ብስራቱን ለህዝብ ያደረሰውን ነዋ ! እስቲ ይሄን ነገር እንስማው እያለ አባባሏን ተመልሶ አጤናት !
 የጭቁን ህዝብ ብሶት የወለደው ………..ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን አዲስ  አበባ የሬዲዮ ጣቢያ ለ(((ሰፊው ህዝብ ጥቅም )))ተቆጣጥሮታል !! 
‹‹ ወራጅ አለ››  እውነቱን እንነጋገር ከተባለ  ሰፊው ህዝብ  እስካሁንም ብሶቱን የሚናገርበት  ሬዲዮ ጣቢያ  የለውም ! የህዝብ የራሱ ልሳን   የሆነ  ቴሌቪዥን ጣቢያ የለውም !  ለሰፊው ህዝብ  ጥቅም  ኢሃዴግ የተቆጣጠረው ጣቢያ ሰፊውን  ህዝብ  በሰፊው የሚያጉርበት   ፖሊስ ጣቢያ ብቻ ነው !  እንደውም የሰፊው ህዝብ ጣቢያ ግንቦት 20 ሽ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት ‹በሽብር ተጠርጥሮ › የታሰረና  መንግስት ምርመራውን ስላልጨረሰ የሃያ ሶስት አመት የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀበት ተቋም ይመስላል !  

በእርግጥ መንግስቱ ሃይለማሪያም   ግልፍተኛ መሪ ነበሩ  ! ኢሃዴግ ግን የተረጋጋ መንግስቱ ሃይለማሪያም ሆነ !ፊት ለፊት ባያፍንም  አፋኝ ህግ ያወጣል …በማን አለብኝነት ያፀድቃል ! ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ መጥፎ ታሪክ  እየፈጠረና  ጥላቻ ይዘራል …ይህም ታሪካዊ ሃላፊነቱን የመወጣት ብቃት እንዳነሰው የሚያሳይ ድርጊት ነው ! ደርግ ‹‹በምስራቅ አፍሪካ አንደኛ የሆነ ጦር ገነባንልህ ›› እያለ ህዝቡ ጭቆናውን እንዳያነሳ ዝም ለማስባል የብድር መሳሪያ ሰልፍ እያሳየ እንደልጅ ህዝብን ሊያታልል እንደሞከረው ኢህዴግም በብድር የተሰራ  መንገድና ድልድይ እያሳየ አፈናውን በህዝብ ስም በሚመጣ የትውልድ እዳ ሊሸፍን ይሞክራል ! እና ኢህዴግ እንደስርአት የደርግን ስርአት ናፋቂ ሆኖብናል ! 

አሁንም ካለምክንያት ማሰር ምክንያት እያፈላለጉ ዜጎችን ስር ቤት መወርወርና ማንገላታት፣ማሸማቀቅ ፣ እና ማስፈራራት  በሰፈነበት  አገር ‹‹ሰፊው ህዝብ›› በብሶት የተረገዘ እንጅ ብሶት የወለደው ነፃነት አላጣጣመም ! መንግስት የጎረምሳ እድሜ ያለው ስልጣን ላይ ተፈናጦ ከትላንቱ ካልተማረ እየተድበሰበሰ  በሚታለፍ መሰረታዊ ችግር ውስጥ ፣ህዝብ በማይተማመንበት የፍትህ ስርአት ውስጥ ፣ የኑሮ ውድነት ሰማይ በነካበት ድህነት ውስጥ ሁነን ግንቦት ሃያን ስናስብ ….ትዝ የሚለን መስከረም ሁለት ነው !

አዎ  ግንቦት ሃያ የኢህዴግ መስከረም ሁለት ነው !! መንግስት  እራሱ  የደርግ ስርአት ናፋቂ ሆነብን እኮ !   ለማንኛውም ወደሰፊው ህዝብ  ሬዲዮ ጣቢያ የበአለ ዝግጅት አዘጋጆች ደውለን እንዲህ ማለት እያማረን ነው  ‹‹ ሃሎ  በአሉን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ለማስተላለፍ ነው . . . ለጓድ መንግስቱ ሃይለማሪያም ባሉበት . . . የተገረሰሱ ሳይሆን በምትከዎት ሰው አስቀምጠው ረፍት የወጡ ስለመሰለን እንኳን ስሙን ለቀየረው መስከረም ሁለት በአልዎት በሰላም አደረሰዎ  …አሳ በለው  በለው የሚለውን ዘፈን ይጋበዙልን ማ  ››የዛሬ 23 አመት (ጊዜው እንዴት ይሮጣል ) የአንድ ታጋይ አጭር ንግግር የኢትዮጲያን አየር ሞላ እንዲህ ሲል ….
‹‹ የጭቁን ህዝብ ብሶት የወለደው ጅግናው የኢህዴግ ሰራዊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የአዲስ አበባ የሬዲዮ ጣቢያ ለ(((ሰፊው ህዝብ ጥቅም )))ተቆጣጥሮታል !! ግንቦት 20 ሽ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት ዓመተ ምህረት ! ›› ወዲያው ‹‹አሳ በለው በለው ›› የሚል ሙዚቃ ተከተለ (አሳና የትጥቅ ትግል ምን እንደሚያገናኛቸው ባይታወቅም አሳ በለው ሞቅ ብሎ ተሰማ . . . ምናልባትም እንደባህር የሰፋችው አዲስ አበባ ውስጥ ታጋዮች አንደአሳ ነባሪ በነፃነት መዋኘታቸውን ለመጠቆም እንደሆነም እንጃ )
እንግዲህ ኢህዴግ የሬዲዮ ጣቢያውን ለሰፊው ህዝብ ከመቆጣጠሩ በፊት ሬዲዮ ጣቢያው ‹‹የሰፊው ህዝብ ›› እንደነበር ደርግም ሲናገር ነው የኖረው ! ከሰፊው ህዝብ መጠቀሚያነት ወደሰፊው ህዝብ መጠቀሚያነት የተላለፈው ሬዲዮ ጣቢያ ግን ከሰፊ የመንግስት ፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያነት ወደ በጣም ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ድምፅ ማጉሊያነት ከመተላለፍ ያለፈ ምንም ለውጥም እድገትም አላሳየም !

Saturday, May 24, 2014

ስብሃት “እርቅን” እንሞክራለን፤ ከባልደረቦቼ ጋር እመክራለሁ አሉ

እርቅ ላይ የምትሰሩ የት አላችሁ?

reconciliation

ባለፈው ሳምንት የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ የተቃዋሚ ፓርቲ ወኪሎችንና አቶ ስብሃትን ባንድነት በየተራ አናግሮ ነበር። ከውይይቱ የተለመደ ክርክር በዘለለ አቶ ስብሃት እርቅ አስፈላጊ መሆኑንን ማመናቸው የተለየ ጉዳይ ነበር። እንደ እርሳቸው አነጋገር አሁን የተጀመረውን መልካም የልማት ስራ ለማስቀጠል እርቅ አስፈላጊ ነው። የእርቅን አስፈላጊነት በማመን ከባልደረቦቻቸው ጋር በመምከር የእርቅ ጉባኤ ለማዘጋጀት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

በኢትዮጵያ የኤርትራ ስደተኞች የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ወሰኑ


eritrean refugees
በሺህ የሚቆጠሩ የኤርትራ ስደተኞች የፕሬዚዳንት ኢሳያስን አስተዳደር በትጥቅ ትግል ለማስወገድ ጠመንጃ ካነሱ ተቃዋሚዎች ጋር ለመቀላቀል መወሰናቸውን ሱዳን ትሪቢውን ገለጸ። ውሳኔው የተላለፈው ኤርትራ ለ23ኛ ዓመት ድል በዓልን ተንተርሶ ነው።

Thursday, May 22, 2014

ይሻል መጣ ብዬ ምርኩዝ አስጨበጨ መንገድ ያሳየሁት፣ ለካ ሌላም አይደል ‘ደርጉ’ን ኖሯል እና ‘ኢህአዲግ’ ነው ያልኩት


DERG

ይሻል መጣ ብዬ ምርኩዝ አስጨበጨ መንገድ ያሳየሁት፣
ለካ ሌላም አይደል ‘ደርጉን’ ኖሯል እና ‘ኢህአዲግ’ ነው ያልኩት።
የደርግ እና የኢህአዲግ መመሳሰል ታወሰኝ እና  የኢትዮጵያ ገበሬ ምን ብሎ ያስብ ይሆን? እያልኩ ሳስብ የመጣልኝ ግጥም ነው።

እየሳቁ ማልቀስ! (የማለዳ ወግ)

ነቢዩ ሲራክ

Nebyu Sirak Ethiopian journalist in Saudi Arabiaበለጋ እድሜዋ ትዳር መስርታ ሁለት ትጉህ መንታ ልጆች የታደለች እህት ከትዳር ጓደኛዋ ችግር ገጠማት። የ “ተበዳይ ነኝ!” ባይ ወዳጀን ምሬት ደጋግሜ ብሰማም ከቀናት በፊት “በደለኝ!” ያለችው የትዳር አጋሯ በኮሚኒቲው ሽምግልና ኮሚቴ በኩል ክስ መስራቱን እና የክስ ጥሪ እንደደረሳት ሰማሁ። ከአሰር አመት በፊት እድሜዋ ገና የ17 አመት እያለ የዛሬ የ12 አመት እድሜ የሆነውን ትልቁን ልጀን ያሳደገችውን እህት የቆየ አብሮነት ትውስታ እያሰብኩ የአለመግባባቱን ሽምግልና ወደሚከወንበት የጅዳ ኮሚኒቲ ሽምግልናውን ለመታዘብ መጓዝ ጀመርኩ። የያኔዋ ጉብል በኮንትራት ስራ መጥታ ከአሰሪወችዋ ልታመልጥ ከሶስተኛ ፎቅ የወደቀችበትን አሳዝኝ ታሪክ ጀምሮ ከብላቴና ልጀ ጋር ውለው ሲያድሩ የነበረውን ሁሉ ስደት እና ድህነት በልጅነት እድሜዋ ላይ የጣለውን ህመም አስታወስኩ። እግረ መንገዴን ይህን ሁሉ አውጥቸ አውርጀ ያ ሁሉ አልፎ ለዛሬ ወግ ማዕረግና ለመንታ ልጆች በረከት ያደላትን ፈጣሪ ስራ አስታውሸ” ለፈጣሪ ምን ይሳነዋል!” ስል አምላኬን አመሰገንኩት!

Wednesday, May 21, 2014

“ጅብ ቲበላህ በልተኸው ተቀደስ” (ከጸጋዬ ገብረ መድኅን አርአያ)

ከጸጋዬ ገብረ መድኅን አርአያ

ወያኔዎች አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላ የነበሩትን ዕለታት ክንውኖች በሥርዓት የመመዝገብ ልምድ ያለው ሰው የሚያሰፍራቸው ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ይኖሩታል። ከመጀመሪያው ዕለት አንስቶ። የእኔን የመጀመሪያ ዕለት አጭር ማስታወሻ ልንገራችሁ። በማለዳ ተነስቼ ጋቢዬን አጣፍቼ ከበሬ ላይ ቆሜ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው አህዮች ወደ መሐል ከተማው (አዲስ አበባ) ሲጓዙ አያለሁ። ያንኑ ያህል ባራባሶ ጫማ የተጫሙ፣ የአካል ዝለት የሚታይባቸውና ከእህል ጋር ከተለያዩ አያል ቀን የሆናቸው የሚመስሉ “ሰብአዊ ፍጥረቶች” አብረዋቸው ይሮጣሉ። ሲያሳዝኑ! ቆይ ቆይ…ከፓስተር ኢንስቲቱት በር ላይ አንድ ጥይት ተተኰሰ። ሌላ ጥይት- ሌላ ጥይት! ሰዎቹ ካለፉ በኋላ ወጣ ብለን ያየነው ሟች በሰፈሩ እንደ ሕሊና ሕመምተኛ የሚታወቅ ነበር።
Ethiopian columnist Tsegaye Gebremedhin Arayaእንግዶቹ አልመው የሚተኩሱ፣ አስበው የሚገድሉ አልመሰሉኝ አሉ። የሚያስቡበትና የሚያልሙበት ሕሊና የሌላቸው ፍጥረታት አድርጌ ላያቸው አልደፈርሁም። ባይሆን ሁሉም ጠላታችሁ ነውና አንዲት ጥይት ጮኸች ወይም አንድ ሰው ትንሽ ድምፅ አሰማ “በለው” በሚል መዘውር የተዘወሩ “መዘውራን” በመሆን በሳሩም በቅጠሉም ኤኬ47ቱን ማንጣጣት ያዙ። ያን ጊዜ በአእምሮዬ ጥግ በምትገኘው የማስታወሻ ሰሌዳዬ ላይ “ይኽ ቀን ገሐነም ባዶውን ያደረበት ዕለት ነው” ብዬ መዘገብሁ። እነዚህ ሰዎች እንደ መሪዎቻቸው በጥላቻ የተጠመቁ ከሆኑ መመለሻው ይቸግረናል። ከቶ ከየት ተነሥተን የት እንደርስ ይሆን? የማልረሳው ማስታወሻዬ ነው።

Tuesday, May 20, 2014

Detained Journalists and Bloggers in Ethiopia Must be Charged or Released, says IFJ

(reliefweb) The International Federation of Journalists (IFJ) has today severely criticised authorities in Ethiopia following the decision by a court to grant police nearly one more month to conduct investigations against the journalists and bloggers detained in the country last month.

Free Detained Journalists and Bloggers in Ethiopia
Three journalists and six bloggers were arrested on 25 and 26 April by police using an arrest warrant from a public prosecutor in Addis Ababa, the country’s capital city. The police on May 17 said that while the investigations continue the three journalists and six bloggers will remain in prison.
“This is a clear human right violation,” said Gabriel Baglo, IFJ Africa Director. “These journalists and bloggers have not been charged yet and must be released immediately. The court is clearly hesitating because there are no strong charges against our colleagues”.

Monday, May 19, 2014

ዘር ማጥራት ወይስ ኢህአዴግን ማፍረስ ? (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ )

ኢህአዴግ ያነበረውን ቋንቋንና ዘውግን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም አደገኛነት በተመለከተ በርካታ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች… ሳያሰልሱ ለመምከርና ለማስጠንቅቅ መዋተታቸውን አልዘነጋሁም፡፡ እኔም ከ“ፍትህ” ጋዜጣ እስከ “ፋክት” መጽሔት ድረስ ችክ ያልኩበትም ሆነ ዛሬ በዚህ ተጠየቅ የተመለስኩበት ምክንያት ችግሩ እያደር እየተባባሰ በመምጣቱና ከምንጊዜውም በላይ አዘናግቶ ወደተፈራው የእርስ በእርስ እልቂት ሊዘፍቀን እየተንደረደረ በመሆኑ፣ ቅድሚያ ሰጥተን በሕብረ-ድምፅ ‘የሀገር ያለህ!’ ብለን መጮህ እንዳለብን ስለማምን ነው፡፡

Temesgen Desalegn "Fact" Ethiopian Amharic newspaper editor
አርባ አራት ዓመት ወደኋላ…
በኢትዮጵያ የዘውግ ጥያቄ ለአደባባይ የበቃው በ60ዎቹ መጀመሪያ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ከዘመነኞቹ የተማሪ እንቅስቃሴ መሪዎች ይህንን ጥያቄ አለቅጥ ለጥጦና አጋንኖ በማቅረብ ግንባር ቀደሙ ዋለልኝ መኮንን ነው፡፡ በ1962 ዓ.ም በአራት ገፅ ቀንብቦ ባዘጋጀው ታሪካዊ ጽሑፉ አማካኝነት “የብሔሮች ጥያቄ” ይፋ ሆኖ ለውይይት ከመቅረቡ በፊት፣ የተማሪው ዋነኛ የመታገያ አጀንዳ የመሬት ጉዳይ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ (በደብዛዛውም ቢሆን ይንፀባረቅ የነበረውን መደብ ተኮር መንፈስ ሳንረሳ)፡፡ ዋለልኝ የሀገሪቱን መንግስታዊ አወቃቀርም ሆነ ባሕልን በአማራና በትግሬ ተፅእኖ ስር ስለመውደቁ በተቸበት በዚያ “ዝነኛ” ጽሑፉ ላይ እንዲህ ይላል፡-

Sunday, May 18, 2014

ዝክር ለግንቦት 7 1997 እና ለግንቦት 7 ቀን 2000 ዓ.ም

ዘንድሮ፣ የታሪካዊው ግንቦት 7 ቀን 1997 አገር ዓቀፍ ምርጫ ዘጠነኛ ዓመት እና ንቅናቄዓችን የተመሠረተበት ስድስተኛ ዓመት የምንዘክረው ከመችውም በላይ አገራችን አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ሁና ነው። ወያኔ የማይገዛትን አገር እንዳትኖር ለማድረግ እማትወጣው አረንቋ ውስጥ ከመክተት የማይመለስ ኃይል መሆኑን ዛሬ በአምቦ፣ በጉደር፣ በጊምቢ እና መሰል ቦታዎች በተግባር እያስመሰከረ ነው።

Ginbot 7 logo
የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ እውነተኛ ፍላጎቱን የመግለጽ አንፃራዊ ነፃነት አግኝቶ የነበረበት የግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም. ምርጫን ስናስብ ዛሬ ያለንበት ሁኔታ መመዘናችን አይቀርም። ያኔ ለአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ እጁ መዳፍ ቀርባ ትታየው የነበረችው ድል እስከዛሬ አልጨበጣትም። ትግሉ ግን ቀጥሏል። የዛሬው ትግላችን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከያኔው በበለጠ ከታሪክና ከራስዋ ጋር የታረቀች አገር የመመሥረትን ርዕይ አስፈላጊነት ላይ ትኩረት መስጠትን የሚጠይቅ ሆኗል።
ወያኔ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ለአለፉት አርባ ዓመታት ሲያብላላው የቆየው፤ በመንግሥት ሥልጣን በቆየባቸው ሃያ ሶስት ዓመታት ውስጥ ደግሞ በፓሊሲ ደረጃ ሲያስፈጽመው የቆየውን የዘር ፓለቲካ አስከፊ ውጤት አሁን እየታየ ነው። ይህ የዘር ፓለቲካ ራሱ ወያኔን ያጠፋዋል። ችግሩ ግን የዘር ፓለቲካ ወያኔን ነጥሎ አያጠፋም፤ ከወያኔ ጋር አገራችንንም ሊያጠፋ ይችላል። ከሁሉም በላይ አሳሳቢው ጉዳይ ደግሞ የዘር ፓለቲካ የበርካታ ኢትዮጵያዊያንን ሕይወት አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል። በጎረቤት አገራት ውስጥ ያየነውን ዓይነት የእርስ በርስ እልቂት ወደ አገራችን ለማምጣት ህወሓትና ኦህዴድ ተግተው እየሠሩ ነው። ሌሎች የወያኔ ተቀጥላ ድርጅቶችም የዚህ ትልቅ የጥፋት ፕሮጀክት አካል ናቸው።

ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ላለፉት ሶስት ወራት ያሰለጠናቸውን የአራተኛ ዙር ታጋዮችን አስመረቀ

የኢትዮጵያዊያንን ስቃይና መከራ ሊያቅብና እንባቸውን ሊየብስ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጎጠኛው ሕወሃት የደረሰባትንና እየደረሰባት ያለውን ውርደት ወደ ክብር ለመለወጥና የናቋትና ያዋረዷት በፍትህ ሚዛን ላይ እንዲቀመጡና ፍርዳቸውን እንዲያገኙ ለማድረግ ዓላማየ ብሎ ምሎ ዱሩ ቤቴ ካለ ገና ሁለት ዓመት እንኳ ያልሞላው ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በቃሉ መሰረት አራተኛውን ዙር የታጋዮች የምረቃ በአል ሚያዚያ 26 2006 ዓ/ም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ማክበሩን አስታወቀ። ይህ የአራተኛው ዙር ስልጠና በሰልጣኞች ቁጥርም ሆነ በስልጠናው ጥንካሬ ካለፉት ሶስት ዙሮች በእጅጉ የተለየ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ያለውን የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና ወቅቱ የሚፈልገውን ቴክኖሎጅ በመጠቀም መረጃን መቀበልና ማስተላለፍን የጨመረም እንደነበር ተያይዞ ተጠቅሷል።

Ginbot 7 Popular Force - GPF formed
በሀገር ውስጥ ፋሽስት ወያኔ እያደረሰው ባለው መረን የወጣ ግፍ የተበሳጩና ሁሉም ልክ እንዳለው ለማሳየት ቆርጠው የተሰለፉት እነዚህ ምሩቅ ታጋዮች ከወታደራዊው ስልጠና በተጨማሪ የፖለቲካ፣ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ሌሎችንም ተያያዥ ክህሎቶችን በበቂ ሁኔታ እንደቀሰሙም ተጠቁሟል። ስልጠናው ታጋዮቹ ወደፊት ከሚያጋጥማቸው ጠንካራ ፈተናና ከሚሰለፉበት ጥብቅ ግዳጅ አንጻር በቀላሉ ተስፋ እንዳይቆርጡ ለማድረግ በአካልም ሆነ በመንፈስ ዝግጁ እንደሚያደርጋቸው የተገለጸ ሲሆን የተጀመረው ሕዝባዊ ትግል በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በጋራና በተቀነባበረ ሃይል ለድል እንደሚበቃና ይህን የጋራ ሃይል በጠነካራ እጆች ላይ ላመስቀመጥም የተሰጠው ስልጠና ከበቂ በላይ ነበር ተብሏል።

Friday, May 16, 2014

የ አንበጣ ምድር (ሄኖክ የሺጥላ)

Henok Yeshitlaእግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው ” ወደ ፈርዖዎን ግባ ፣ እኔ የ ፈርዖዎንን ና የሹሞቹን ልብ አጽንቼአለሁና፣ ተአምራቴ በነሱ ላይ በትክክል ይመጣ ዘንድ፣ በግብጻውያንም ላይ የተዘባበትሁትን ሁሉ፣ ያደረጉሁባቸውንም ተአምራቴን በልጆቻችሁና እና በልጅ ልጆቻችሁ ጆሮዎች ትነግሩ ዘንድ፣ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ። ሙሴና አሮንም ወደ ፈርኦን ገቡ ፣ አሉትም ፣ ” የእብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ እኔን ማፈርን እስከ መቼ እምቢ ትላለህ? ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ፣ ህዝቤን ለመልቀቅ እምቢ ብትል ግን፣ እንሆ ነገ በዚህ ጊዜ በተራራዎችህ ላይ አምበጣ አመጣለሁ ፣ የምድሩንም ፊት ይሸፍናል፣ ምድሩንም ለማየት አይቻልም፣ ከበረዶውም ተርፎ በምድሩ ላይ የቀረላችሁን ትርፍ ሁሉ ይበላል; ያደገላቹን የእርሻ ዛፍ ሁሉ ይበላል; ቤቶችም፣ የሹሞችህም ሁሉ ቤቶች፣ የግብጻውያን ሁሉ ቤቶች በእርሱ ይሞላሉ፣ አባቶችህ ፣ የዓባቶችህም አባቶች በምድር ላይ ከተቀመጡበት ቀን ጀምሮ እስቀዝ ቀን ድረስ እንደ ርሱ ያለ ያላዩት ነው። ሙሴም ተመልሶ ከፈርዖን ዘንድ መጣ። እናም እግዚአብሔር አምላክ ቃሉን ጠብቆ መጣ። እኔም ይሄንን አየሁ ያየሁትንም እናገራለሁ። አንደበቴ ያንተን ትልቅነት ያወራል፣ በቃልህ ትገኛለህ፣ ከቀጠሮህ አትዛንፍም፣ ሃጣን ከጥፋት ውሃው አይተርፍም የተረፉ ምስክሮች ያንተን ትልቅነት ተናጋሪዎች ይሆናሉ።

ኖህ መርከቡን ሳያንጽ ሃጣን ንስሐ ሳይገባ ያፈሰሱትን ደም ሳይደርቅ ያንተ ፍርድ ደረሰ እንሆ ይሄ የመጨረሻ ሰዓት ነው። ውንድማምቾች ተለያይተዋልና፣ የአባቶች ደም በከንቱ ፈሶዋልና፣ ብላቴናው ያለ እናት፣ አውድማው ያለ ዘር ቀርቶዋል ፣ አንተም ይህንን ባደረጉት ላይ ለመፍረድ መጣህ ።

Thursday, May 15, 2014

እምዬ ምኒልክ ሲመጥቅ፣ ወያኔ ሲወድቅ

ከሮበሌ አባቢያ፤ 14/5/2014

ቅጥረኛው አምባገነን መለስ ዜናዊ
ወያኔ በ1983 አዲስ አበባ ሲገባ እግረ መንገዱን የገበሬውን ልጆች፣ ጋዳፊና የአረብ ሀገር ከበርቴዎች ባስታጠቁት ዘመናዊ ታንክና መሣሪያዎች፣ እያጨደ በሬሳቸውና በደማቸው ላይ እየተረማመደ እንደነበር መሪር የቅርብ ትዝታ ነው። በቅጥረኛው አምባገነን መለስ ዜናዊ ይመራ የነበረው ጎጠኛው የወያኔ መንግሥት፣ የኢጣልያ ፋሺስት ያወጣውን በተለይ በአማራና በኦሮሞ ላይ ያነጣጠረውን የከፋፈለህ ግዛው ፖሊሲ ኮርጆ በመከተል፣ የአፄ ምኒልክ ሐውልት እንዲፈርስ ለማደረግ ሕዘቡን አነሳስቶ እንደነበር ይታወቃል።ሆኖም ሙከራው ወያኔ አስቦት በነበረበት ወቅት ባይሳካም፣ ሐውልቱን የማንሳት ሃሳብ አሁንም አለ። ስለዚህ ሕወሐት የሚመራው በውስጡ በሚስጥር በተሰገሰጉ ባንዳዎች እንደሆነ እያደር ሊታወቅ ስለቻለ የእምዬ ምኒልክ ወደጆች መዘናጋት የለባቸውም።Ethiopian king Atse Menelik
ሐውልቱና ከኢጣልያን ጋር የተደረጉት ሁለት ከባድ ጦርነቶች
እምዬ ምኒልክ፣ እስከ አፍንጫው ድረስ ዘመናዊ የጦር መሣሪያ በገፍ ታጥቆ ኢትዮጵያን ሊወር የመጣውን ጦር፣ አድዋ ላይ ገጥመው ወራሪውን ድባቅ መትተው አንፀባራቂ ድል ሲጎናፀፉ፣ ከሰሜን ሸዋ አብሮአቸው የዘመተው ስምንት ሺህ (8000) ፈረሰኛ የኦሮሞ ሚሊሽያ ሠራዊት በጦርነቱ ለተገኘው ድል ወሳኝ አስተዋፅዖ አድርጎ እንደነበረ በታሪክ የተመዘገበ የጀግንነት ሐቅ ነው። የአድዋው ድል የአውሮፓን ሀያላን መንግሥታትን አስደንግጦ ኢትዮጵያን እንደ አንድ ሉአላዊ ነፃ ሀገር እንዲያውቋት አስገድዷቸዋል። ይህ ታላቅ የጥቁር ሕዝብ ድል በዓለማችን ላይ ለሚገኙት ጭቁን ጥቁሮች ሁሉ ሕያው ተስፋ ሰጥቷል።

Wednesday, May 14, 2014

እናስራችኋለን? ለካንስ የነአጅሬ ጋጠወጥነት ከድንበርም ተሻግሯልና!

ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)

President Salva Kir of Sudanበሀገራችን ባደመነው አጠቃላይ የሀዘን ድባብ ሳቢያ ፈገግታ እያማረኝ ፈገግ ለማለት ምንም ዕድል ሳላገኝ ብዙ ሰሞኖችን ባጀሁ፡፡ ዕድሜ ለዚህ ነገረኛ ኢሳት የሚባል ቴሌቪዥን ዛሬ ማታ ግና በሣቅ የሚያፈርስ ዜና ሰማሁና ምሽቱን ብቻ ሳይሆን ትዝ ባለኝ ቁጥር ሌቱን ሁሉ በሣቅ ስፈርስ አደርኩ – የግራ ጎን አጥንቶቼ ክፋይ ጉድ እስክትለኝ፡፡ ሣቅ ጥሩ ነው፡፡ አንዳንዴ በሣቅ የሚገድል ነገር ማግኘት የመታደል ያህል ነው፡፡ እውነተኛው ሣቅ ሞቶ ቢቀበርም ወያኔን መሰል ጅላንፎ ጉጅሌ የሚሠራቸው አንዳንድ ነገሮችን በመታዘብ ለጊዜውም ቢሆን ፈገግ መሰኘት ሲያስፈልግም ሆድን ያዝ አድርጎ በሣቅ መንፈርፈር ሰውነትን ያፍታታል፤ ወቅታዊ እፎይታንም ይሰጣል፡፡ እኔ – እውነቴን ነው – ለብዙ ጊዜ ያጣሁትን ሣቅ ዛሬ አገኘሁትና ከልቤ ተዝናናሁ፡፡ ወያኔ እኮ አልታወቀለትም እንጂ ደምበኛ የኮሜዲ መፍለቂያ ውድብ ነው፡፡ ልዩ የኢትዮጵያ ቻርሊ ቻፕሊን ሆነው የለም እንዴ!

“አማራንና አማርኛን ማጥፋት የህወሃት ፕሮግራም ነው”

“አማራንና አማርኛን ማጥፋት የህወሃት ፕሮግራም ነው”

evicted

አማርኛ ተናጋሪዎችን የማመናመን፣ የማደህየት፣ የማራቆትና ክልላቸውን እያሳነሱ የማጥፋት እቅድ በህወሃት መርሃግብር ውስጥ የተካተተ ዋና ተግባር እንደሆነ ተገለጸ። አማርኛ ቋንቋንም ማሽመድመድ የዚሁ እቅድ አካል መሆኑ ተዘግቧል።

ኢትዮጵያዊነት ክፍል ሁለት ትግሬ ሆነህ አታንብበው (ሄኖክ የሺጥላ)

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት ፣ ” መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” የሚለው መጽሐፋቸው ላይ በሚደር ውይይት ካንድ ተሳታፊ ለቀረበላቸው ትያቄ ሲመልሱ፣

Henok Yeshitla“አንዳን የሚያሳዝኑ ነገሮች ተነስተዋል እዚህ አካባቢ ነው መሰል ትግሬ ነኝ ያለ ልጅ አለ፣ ትግሬ ነኝ ብለሃል፣ እኔም ትግሬ ነኝ፣ ነገር ግን ልዩነታችን ትግሬ ሆነህ በማንበብህና ኢትዮጵያዊ ሆነህ በማንበብህ ላይ ነው። እውነት ነው፣ ትግሬነትን እያሰቡ እንደ ኢትዮጵያዊ መኖር አይቻልም፣ ኦሮሞነት ኢትዮጵያዊ ለመሆን ባሰበ ቁጥር የተበዳይነት እና የተገፊነት ስሜት የሚጭር ከሆነ በምንም መልኩ ኢትዮጵያዊ መሆን አይቻልም። ፋሲለደስን ስንመለከት አማራ አደረሰብን የምንለው በደል ከሆነ ትዝ የሚለን ኢትዮጵያዊ መሆን አይቻልም ፣ አክሱምን ስንመለከት የትግሬዎች ክፋት ከሆነ ትዝ የሚለን ኢትዮጵያዊ መሆን አይቻልም፣ ሰንደቅ አላማችንን ስንመለከት አሁንም ሰንደቁ ከተሸከመው ምልክታዊ ትርጉም ውጪ የአማራነት መለኪያአንድን ጎሳ የጥፋት ብብሃር ታሪክ ካደረግነው አሁንም ኢትዮጵያዊ መሆን አይቻልም። ስለ ብራና እና መሰንቆ ስናወራ ወደ አእምሮዋችን ቀድሞ የሚመጣው ቁሶቹ የኢትዮጵያውያኖች እሴት ስለ-መሆናቸው ካልሆነ ኢትዮጵያዊ መሆን ይከብዳል።

Tuesday, May 13, 2014

ተቃውሞ እና ጭፍጨፋ በኦሮሚያ (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ )


ዕለተ-ሐሙስ፤ ሚያዚያ 23 ቀን 2006 ዓ.ም የታሪካዊቷ አምቦ ከተማ ጀንበር አዘቅዝቃ ሰማዩ መቅላት ሲጀምር፣ ከወትሮው ለየት ያለ ጉዳይ በሰደድ እሳት ፍጥነት ጠቅላላ የዩንቨርስቲ ግቢውን አዳርሶ ተማሪውን ከባድ ሃሳብ ላይ ጣለው፡፡ ሌሊቱ ዕኩሌታ ላይ የግቢው ኦሮምኛ ተናጋሪ ተማሪ በሙሉ ስለጉዳዩ መረጃው እንደደረሰው ያረጋገጡ ጥቂት አስተባባሪዎች በተረፈችዋ ሰዓት ቢያንስ ጎናቸውን ለማሳረፍ ወደየመኝታቸው ሲያዘግሙ ተስተዋሉ፡፡ …ነገስ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን? አንዳቸውም ይህን አስቀድመው የማወቅ መለኮታዊ ፀጋ አልነበራቸውም፤ የሚያውቁት በግቢው ስታዲዮም ለመሰብሰብ ቀጠሮ መያዛቸውን ብቻ ነው፡፡ ከዚያስ? አንድ ስሙን መናገር ያልፈለገ የዩኒቨርስቲው ሁለተኛ ዓመት ተማሪ እና የተቃውሞው አስተባባሪ ክስተቱን በእኔ ብዕር እንዲህ ይተርክልናል፡-
አርብ
የንጋት ፀሐይ ዓይኗን ከመግለጧ በፊት ተማሪው አንድ፣ ሁለት… እያለ በቀጠሮው ቦታ መሰባሰብ ጀመረ፡፡ ረፋዱ ላይም ምልአተ ጉባኤው የተሟላ መሰለ፤ ኦሮሞ ያልሆኑ ተማሪዎችም አብረውን ነበሩ፡፡

ደቡብ ሱዳን – የሰላም ድርድር ወይስ ቁማር?

“ካልፈረማችሁ ለICC አሳልፈን እንሰጣችኋለን” ሃይለማርያም

Ethiopia South Sudan

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ስምምነቱን የማይፈርሙ ከሆነ ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ለዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድቤት (ICC) አሳልፈው እንደሚሰጧቸው መግለጻቸውን በጁባ የጎልጉል ምንጭ አስታወቁ፡፡ ሱዳን ትሪቢዩን በበኩሉ ስምምነቱ የማይፈረም ከሆነ እስር እንደሚጠብቃቸው ሃይለማርያም ለሳልቫ ኪር መናገራቸውን ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ አርብ የተፈጸመው የስምምነት ፊርማ ገና ሳይደርቅ ሁለቱም ኃይላት ወደ እርስበርስ ውጊያው ተመልሰው በመግባት እየተካሰሱ ነው፡፡

Sunday, May 11, 2014

ብአዴን ማን ነው?

[ጭንጋፍ ወይስ ልጅ? ምስክርነት!]

andm12

የአበበ ገላው “ጩኸት” አንደምታ

ዳጉ ኢትዮጵያ (dagu4ethiopia@gmail.com)

አንድ የማህበራዊ ድረ-ገጽ ወዳጄ “በአበበ ገላው የሰሞኑ ድርጊት ምን አስደሰተህ?” ሲል ግራ በመጋባት ጠየቀኝ፡፡ የወዳጄ ጥያቄ የአበበ ገላው በፕሬዚደንት ኦባማ ፊት የኢትዮጵያውያንን የነፃነት ጩኸት ማስተጋባት በኔ በኢትዮጵያ ምድር የምኖር ዜጋ ላይ ስለሚኖረው አንደምታ በጥልቅ እንዳስብ አደረገኝ፡፡Abebe Gellaw interrupted President Obama's speech
ዜጎች ሐሳባቸውን በነጻነት መግለጽ በማይችሉባት ሐገር፤ ይልቁንም “ለዚህ ሥርዓት ጥሩ አመለካከት የለህም፣ የወጣት ሊግ፣ የሴቶች ፎረም፣ የነዋሪዎች ፎረም ወዘተ በተሰኙ የስርዓቱ አደረጃጀቶች አልተሳተፍክም” በሚል – መገለል፤ ባስ ሲልም መዋከብና ከስራ መፈናቀል በሚደርስበት ሐገር የማስበውን የሚተነፍስልኝ፣ አንደበት የሚሆንልኝ ሳገኝ ብደሰት፣ ባሞግሰው – ጀግና ብለው ምን ይገርማል? የህዝቡን ይሁንታ አግኝቼ ተመርጫለሁ፣ ኮንትራት ተሰጥቶኛል ወዘተ የሚል ማመካኛ እየደረደረ በምከፍለው ግብር የሚተዳደሩ የህዝብ ንብረት የሆኑ ሚዲያዎችን ወደራሱ የግል ንብረትነት አዛውሮ ጠዋት ማታ ሳልጠግብ – ጠግበሃል፣ በሥራ አጥነት እየተንከራተትኩ – ሥራ በሽ በሽ አድርጌልሃለሁ፣ የኑሮ ውድነቱ አጉብጦኝ – ኑሮህ ተሻሽሏል እያለ የራሱን ሹማምንት ምቾት የኔ እንደሆነ አድርጎ ለኔው የሚለፍፍ ስርዓት ባለበት ሐገር የነጻነት ጥማቴን የሚናገርልኝን አበበን ባወድሰው የሚያስገርመው ምኑ ነው?

Saturday, May 10, 2014

Breaking News: Abebe Gellaw interrupted Obama and Obama agrees with Ethiopia’s call for freedom

San Jose, California–U.S. President Barack Obama has agreed with journalist Abebe Gellaw’s demand to support freedom in Ethiopia and help free bloggers, journalists and political prisoners jailed by the tyrannical regime.

While Obama was wrapping up his speech last night at a glitzy Democratic National Committee reception in San Jose’s Fairmont Hotel, journalist and activist Abebe Gellaw interrupted the president and called support for freedom in Ethiopia. The event jointly hosted by Yahoo CEO Marissa Mayer and and Y Combinator CEO Sam Altman was mainly attended by Silicon Valley business and political leaders.

የወያኔን ውድቀትና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማፋጠን ኅብረታችን ይጠንክር! (ግንቦት7)

የወያኔን ውድቀትና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማፋጠን ኅብረታችን ይጠንክር! (ግንቦት7)

Ginbot 7 weekly editorialግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ በግፍ ሕይወታቸውን ባጡ ዜጎች መርዶ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እና ቁጭት ይገልፃል፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ይመኛል። ህወሓት እና አጋፋሪው ኦህዴድ በነዙት ሽብር ሳቢያ የአካል ጉዳት የደረሰባችሁ፣ የተደበደባችሁ እና ለእስር የተዳረጋችሁ ወገኖቻችንም ህመማችሁም እስራችሁም የሁላችንም ነው። መላው ኢትዮጵያዊ ወገናችሁ ከእናንተ ጋር ተገድሏል፣ ቆስሏል፣ ተደብድቧል፣ ተግዟል፣ ታስሯል። ህወሓት፣ ኦህዴድ እና በዚህ ጭፍጨፋ እጃቸው ያለበት ሁሉ ከተጠያቂነት የማያመልጡ መሆኑን ግንቦት 7 ደጋግሞ ያስገነዝባል።
በህወሓት ዘረኛና ፋሽስታዊ አገዛዝ ያልተበደለ የኢትዮጵያ ክፍል የለም። የወያኔ አጋፋሪ የሆነው አህዴድ የኦሮሞ ወጣቶችን፣ ሕፃናትንና አዛውንትን ሲጨፈጭፍና ሲያስጨፈጭፍ፣ ሌላው አጋፋሪ ብአዴን ደግሞ በጎንደርና አካባቢው ተመሳሳይ ጭፍጨፋዎችን አካሂዷል። ወያኔ ከፋሺስት ኢጣልያ ወርሶ ለሃያ ዓመታት በትጋት ያራመደው “የከፋፍለህ ግዛ” ፓሊሲ ምርት እነሆ ዛሬ በዓይኖቻችን እያየን ነው። ፋሽስት ጣልያን ጀምሮት የነበረውን ኢትዮጵያን የማጥፋት ስትራቴጄ ለማጠናቀቅ ህወሓት በጥድፊያ ላይ ነው። ይህን እኩይ ዓላማ ማስቆም የሁላችን ኃላፊነት ነው።

Thursday, May 8, 2014

በሬየን አልሸጥም – አጭር ወግ (በሄኖክ የሺጥላ)

በሄኖክ የሺጥላ*

አዲሱን (የነበረውን ግን ሰሞኑን የሾረውን) የ “ኦሮሞ ወጣቶች ” ግድያ። በነገራችን ላይ ለምንድን ነው “የኢትዮጵያ ወጣቶች ” የማንለው? ማለት ስለማንፈልግ? ወይስ ብንል ባንል ምን ይጠቅማል ( ምንስ ይጎዳል በሚል ሃሳብ?) ሁለቱንም ያዙልንና እንቀጥል።Ethiopian poet Henok Yeshitla
ሰሞኑን አምቦ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ወዳጆች ” ልጅ ሄኖክ በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ነገር በል እንጂ “ጠላቶች ደሞ ” አንተ ምንትስ አማራ አሁን አማራ ቢሆን ኖሮ ይሄ ሁሉ መከራ የደረሰበት አምሳ ገጽ ጽፈህ ፣ ነገሩን ለውጠሕና ለጥጠህ ባቀረብከው ነበር ” የሚሉ መልዕክቶችን አስቀምጠውልኛል። እኔም እንደ ለገዳዲ ሬዲዮ ” ጦማሪዎችች ሆይ ምልእክታችሁ ደርሶኛል ለሁሉም እንደነገሩ ለመመለስ እንሆ–”
በነገራችን ላይ አማራ ስለመሆኔ እኔ በበኩሌ እርግጠኛ አይደለሁም ፣ ቢያንስ እርግጠኛ እስክሆን ብትታገሱኝ ምን ነበረበት (ስለ-ኔ ከኔ በተሻለ መልኩ የምታውቀው እናቴ እንኩዋ እንዲህ በሙሉ አፍዋ “አንተ አማራ!” ብላኝ አታውቅም። ታዲያ የምታውቀው ነገር ቢኖራትም አይደል? አለበለዚያ ማኛና ሰርገኛ በሚል ማህበረስብ ውስጥ አድጋ እኔን በደም ስሜ መጥራት ባልዳገታት “እስኪ ለናቴ ጊዜ እንደሰጠሁዋት እናንተም ለኔ ጊዜ ስጡኝ” ደሞ ለዘር፣ እድሜ ለወያኔ እንኩዋን የሰው የንብ ሰፈር እንኩዋ በታወቀበት ዘመን የምን መንገብገብ ነው!) ። አቦ እናት ለዘላለም ትኑር! ቀጣዩን ሃሳብ በሚቀጥለው መስመር ላይ ያንብቡት።

“የዞን ዘጠኝ ጀግኖች ብረሳችሁ ታሪክ ይርሳኝ” በውቀቱ ስዩም

በውቀቱ ስዩም (በፌስቡክ ገጹ እንዳሰፈረው)

Bewketu Seyoum is an Ethiopian writer
Bewketu Seyoum
ነጻነትና ፍትህ በሌሉበት አገር ውስጥ የልማት አውታሮችን መገንባት የት ለመድረስ ነው?የባቡር ሀዲድ ግንባታ ሳይ፣ የሚመጣብኝ እንደ አይሁድ በባቡር ታጭቀው ወደ መግደያ ጣቢያ የሚጓጓዙ ዜጎችን ነው። የኤሌክትሪክ ግንባታ ሳይ የሚመጣብኝ የኤሌክትሪክ መግደያ ወንበር ነው። የሚቆፈር ነገር ሳይ ድቅን የሚልብኝ የጅምላ መቃብር ነው።
የዞን ዘጠኝ ጀግኖች ብረሳችሁ ታሪክ ይርሳኝ። ባንድ በኩል የዘመናችሁ ተካፋይ በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል። በሌላ በኩል፣ የመከራችሁ ተካፋይ ባለመሆኔ ሐፍረቱን አልችለውም። ያም ሆኖ ‹‹በሉ እናንተም ሂዱ እኛም ወደዛው ነው። ወትሮም መንገደኛ ፊትና ኋላ ነው›› የሚለው የዓለሙ አጋ የበገና እንጉርጉሮ ባጸደ-ነፍስ ላሉት ብቻ ሳይሆን ባጸደ-ወህኒ ላሉትም ይሆናል። ስሜቴን እንዴት መግለጽ እንዳለብኝ አላቅም። የገላውድዮስ ዜና- መዋእል ጸሐፊ በዚህ ሰዓት የሚሰማኝ ስሜት ከምእተ አመታት በፊት ተሰምቶት ነበር።
መዓልትኒ ኮነ ሌሊተ፣ዘኢነአምሮ ወጽልመት ዘኢልማድ መጽአ
ወደፈነ እንስሳ ወሰብአ
(ቀኑ ሌሊት ሆነና፣ ወጋገኑ ተሰደደ
እንግዳ ጨለማ መጣ፣ጠባዩ ያልተለመደ
ሰውን፣ እንስሳን ጋረደ)