Translate

Monday, September 30, 2013

“ፕሬዚዳንት እንድሆን ብጠየቅ በቅድሚያ ምን ያህል ላገለግል እችላለሁ እላለሁ – ወ/ሮ ሰሎሜ ታደሰ

የቀድሞዋ የመንግስት ቃል አቀባይ ወ/ሮ ሰሎሜ ታደሰ ሃገር ቤት ከሚታተመው ሎሚ መጽሔት ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች። የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ግንዛቤ ይረዳቸው ዘንድ ቃለ ምልልሱን እንደወረደ አስተናገድነው…

ሁሉ ነገር ራዕይ ሆኖ ይቀጥላል እንዲባል አልፈልግም
በሥልጣን የሚመጣ ክብር ደግሞ ከሥልጣን ጋር አብሮ ይቀራል

ሎሚ፡- አምባሣደር ዮዲት እምሩ በሕይወትሽ ከፍተኛ መነቃቃት እንደፈጠሩብሽ ይሰማል፤ እንዴትና ለምን?
ወ/ሮ ሰሎሜ፡- እሳቸው ከፈጠሩብኝ መነሣሣትና መነሳሳት ይልቅ አባቴ እሳቸውን ምሣሌ በማድረግ ውስጤ የፈጠረው መነሣሣት ነው የሚበልጠው፡፡ ልጅ እያለሁ እሣቸው አምባሣደር ነበሩና በቴሌቪዥን በተደጋጋሚ ይታዩ ነበር፡፡ የዛን ጊዜ እኔ አራተኛ ክፍል ነበርኩ፡፡ ሁልጊዜም በቴሌቪዥን ሲመጡ አባቴ ይጠራኝና “…በቃ አንቺ ስታድጊ እሣቸው ስራ የላቸውም” ይለኝ ነበር፡፡ የእሱ አባባል ስታድጊ ስራቸውን ትወስጅባቺዋለሽ ዓይነት ነበር፡፡

አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ (ተመስገን ደሳለኝ)

Temesgen Desalegn
ኢህአዴግ ከቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ በተከሰተበት ውስጣዊ ልዩነት በተለዋዋጭ የኃይል ሚዛን ሥር ለማደር በመገደዱ የስልጣኑን መዘውር የሚያሽከረክረውን አካል ለመለየት አዳጋች ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህ ሽኩቻ መፍትሄ ማግኘቱን የሚያመላክቱ ሁናቴዎች መፈጠራቸውን የውስጥ አወቅ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
እንደ መግቢያ
ድንገቴው የመለስ ህልፈት ህወሓትን ቢከፍለውም፣ ብአዴን ራሱን እንዲያጠናክር መደላድል ፈጥሮለታል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት መለስ ዘመኑን ሙሉ በብአዴን ታማኝነት ላይ ጥርጣሬ ስላልነበረው ቀድሞውንም እንዲዳከም ባለማድረጉ ይመስለኛል፡፡ እርሱ በአይነ ቁራኛ ይጠብቀው የነበረው ህወሓትን ነበር፤ በተለይም በሠራዊቱ እና በደህንነቱ ውስጥ ‹‹ተፅእኖ መፍጠር ይችላሉ›› የሚባሉት አቦይ ስብሃት ነጋ እና የትግራይን መዋቅር በእጁ ያደረገው የቀድሞ የክልሉ አስተዳዳሪ ፀጋዬ በርሄ በጥርጣሬ ዓይን የሚታዩ ሆነው ቆይተዋል፡፡ በምርጫ 2002ቱ ማግስትም ድርጅቱ አቦይን ‹‹በክብር›› እንዲሸኝ ሲደረግ፣ ፀጋዬ በርሄን ደግሞ ‹‹አማካሪ››  በሚል ሽፋን ከመቀሌ ወደ ቤተ-መንግስት (ጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ) አዛውሮ በቅርብ እይታ ስር በማዋሉ ሁለቱንም ከጨዋታ ውጪ አድርጓቸዋል፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ይህንን የማፊያ ቡድን በማፍረስ ታሪክ ይስሩ! በግርማ ሠይፉ ማሩ


ግርማ ሠይፉ ማሩ
በ2005 ዓ.ም የምክር ቤት ዘመን መጨረሻ ላይ የደህንነት መስሪያ ቤቱን በሚኒስትር ደረጃ ለማዋቀር የሚረዳ አንድ አዋጅ ለምክር ቤት ቀርቦ ፀድቆዋል፡፡ ይህ አዋጅ ሲፀድቅ ከነቅሬታዬ ያለኝ ድጋፍ መስጠቴ ይታወቃል፣ ለዚህ አዋጅ ድጋፍ መስጠት የፈለኩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከበረሃ ይዘውት የመጡት ልዩ ልዩ አፋኝ ቡድን ስለማይኖራቸው እንዲሁም ቀደም ሲል የነበሩትን አፋኝ ቡድንች ወደ አንድ መዋቅር በማጠቃለል ተጠሪነቱ ከተለያዩ መዋቅሮችና ግለሰቦች ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ (ወደ ተገቢው ማለት ነው) ቁጥጥር በማስገባት ለዜጎች ስጋት ሳይሆን ለዜጎች እና ለሀገር ደህንነት የሚስራ ተቋም ይሆናል በሚል ተስፋ ነው፡፡ ይህ ተስፋዬም ዝም ብሎ ሳይሆን በአዋጁ አንቀፅ 3 “ይህ አዋጅ በመላው ሀገሪቱ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ በፌዴራልም ሆነ በክልል መንግስታት ደረጃ ሌላ የመረጃና ደህንነት ተቋም  ማቋቋም አይቻልም” የሚል ድንጋጌ በመያዙ ነው፡፡ በመስከረም 19 እሁድ ዕለት አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ “በሰላም” ከተጠናቀቀ በኋላ እጅግ አሰገራሚ የሆነ ተግባር አጋጥሞናል፡፡ ተስፋዬንም ስለአጨለመብኝ ይህን ጉዳይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲያውቁትና የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎቱ ኃላፊውን ጠርተው ማብራሪያ እንዲጠይቁ መነሻ ለመስጠት ነው፡፡

Sunday, September 29, 2013

ሰላማዊ ሰልፉ ቢታገትም ፣ የተሳካ ሕዝባዊ ንቅናቄ ነበር! – ከአንድነት ፓርቲና ከ 33ቱ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ

603944_622133674503606_213601633_n አንድነት ፓርቲ ከ33ቱ ፓርቲዎች ስብስብ ጋር በመሆን ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ለማድረግ ያቀዱት ሰላማዊ ሰልፍ በገዢው ፓርቲ (መንግስት) ክልከላ ሠልፉ ሊደረግበት ወደነበረው መስቀል አደባባይም ሆነ በአማራጭ ነት ያቀረቡት 9 አደባባዮች እንዳይንቀሳቀስ ተደርጎ ከአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት እስከ ቀበና አደባባይ ባለው አስፋልት ላይ ቁጥሩ ከ80 ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተገኙበት ደማቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ ተደርጓል፡፡ 
1374061_10201496850957121_1380175466_n603944_622133674503606_213601633_n994913_10201496979000322_682846221_n1374061_10201496850957121_1380175466_nለዚህ ደማቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች አመራሮች አባላትና ደጋፊዎች ያደረጉት ያላሰለሰ ጥረትና ሕዝቡ የመንግሥትን ፀጥታና የፖሊስ ኃይሎች ማስፈራራት አልፎ የላቀ አዎንታዊ ምላሽ ከፍተኛ ድርሻ አበርክተዋል፡፡

Thursday, September 26, 2013

“አጐቶቼ ሙስሊሞች ናቸው” – ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም

lllll
“ኢትዮጵያዊ አሸባሪ አለ ብዬ አላምንም”
“የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የምሆነው ፓርቲዎች ከተዋሐዱ ብቻ ነው”
“አጐቶቼ ሙስሊሞች ናቸው”
ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም
ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም ለሁለት ወራት በአሜሪካ ቆይታ አድርገው ተመልሰዋል፡፡ ስለቆይታቸው እንዲሁም በሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮች “በተለይ” ከሎሚ መጽሔት ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች በሃገር ቤት የሚታተመውን የሎሚ መጽሄት ለማንበብ እድሉ ካልገጠማቸው በሚል የዶ/ር ያ ዕቆብን ቃለ ምልልስ እንደወረደ አስተናግደነዋል።
ሎሚ፡- እንኳን በሰላም ተመለሱ!
ዶ/ር ያዕቆብ፡- እንኳን ደህና ቆያችሁኝ፡፡
ሎሚ፡- የአሜሪካ ቆይታዎ ምን ይመስል ነበር;

የመንግስት የደህንነት መስሪያ ቤት ከወልድያ ሙስሊም ተማሪዎች አመጽ ጀርባ ሼክ ሙሀመድ አላሙዲን አሉበት አለ

original_al_amoudi_wearing_eprdf_tshirt_may_2005
መንግስት ፣ “ኢህአዴግን የፈተነ ወሳኝ ክስተት” በማለት የገለጸውን የሙስሊሞች እንቅስቃሴ አልሻባብ፣ አልቃይዳ ፣ ግንቦት ሰባት ፣ እና የኤርትራ መንግስት እንደሚደግፉት በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙሀን ቢገልጽም፣ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ደግሞ የደህንነት ሀይሎች ቱጃሩን ሼክ ሙሀመድ ሁሴን አላሙዲንን ከእንቅስቃሴው ጀርባ እንዳሉበት የሚጠቁም መረጃ ለመንግስት ባለስልጣናት ማቅረቡ ታውቋል።

እነ ወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱ ፕሬስ ካውንሰል መመስረት አልቻሉም

qwe

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ምክርቤት ወይንም ፕሬስ ካውንሰል ለማቋቋም ኃላፊነቱን የተረከበው ጊዜያዊ ኮምቴ የካውንስሉን መስራች ጉባዔ መጥራት እንዳልቻለ ተጠቆመ፡፡
በኢህአዴግ ደጋፊነት በሚታወቁት ወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱ የሚመራው ጊዜያዊ መስራች ኮምቴ ፕሬስ ካውንስሉን እንዲመሰረት ኃላፊነት ቢሰጠውም አመራሩ እርስበርስ ባለመግባባቱና ከብዙሃኑ ጋዜጠኞች አዎንታዊ ምላሽ ባለማግኘቱ የምስረታውን ጉዳይ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ጥሎታል፡፡
ይህ ኮምቴ በወ/ሮ ሚሚ ሊቀመንበርነት፣ በአቶ አማረ አረጋዊ ምክትል ሊቀመንበርነት መመራት ከጀመረ ሶስት ዓመታት የቆጠረ ሲሆን በተለይ በሁለቱ ሰዎች መካከል ባለ
ግልጽ የስልጣን ሽኩቻና መናናቅ ምክንያት ምስረታውን ማካሄድ እንዳልተቻለ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

የሀይማኖት አቋም የእድገት መመዘኛ መስፈርት እንዲሆን ተወሰነ የሀይማኖት አቋም የእድገት መመዘኛ መስፈርት እንዲሆን ተወሰነ

Bereket_simon

መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ በረከት ስምኦን በተመራው የኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ውይይት ላይ ፣ የሀይማኖት አክራሪነት ከምርጫ 97 ቀጥሎ ከፍተኛ ፈታኝ አደጋ እንደሆነ ከተገለጸና ውይይት ከተካሄደ በሁዋላ የአገሪቱ ሲቪል ሰርቪስ የሀይማኖት ጉዳይን እንደ አንድ የእድገት መመዘኛ መስፈረት እንዲተገብር ስምምነት ላይ ተደርሷል።

Wednesday, September 25, 2013

ሰማያዊ ፓርቲ ሕገ-መንግስት አረቀቀ

በረቂቅ ሕገ-መንግስቱ ላይ የውይይት መድረክ ለማዘጋጀት አቅዷል

semayawi 12


በቅርቡ የተመሰረተው የሰማያዊ ፓርቲ ‘‘የዜጎች የቃል ኪዳን ሰነድ ለዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ’’ በሚል መርህ ወደፊት የፖለቲካ ሥልጣን ሲይዝ የሚመራበትን አዲስ ህገመንግስት ማርቀቁን አስታወቀ። ረቂቅ ሰነዱ ላይ ምሁራንና ባለሙያዎች ውይይት ካደረጉ በኋላ ለሕዝብ እንደሚቀርብ ፓርቲው አስታውቋል።

ፖሊስ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን አሰረ

ww
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ፕሬዘዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የታሰሩ የፓርቲውን የቅስቀሳ ቡድን አባላት ለማስፈታት ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ የሽሮ ሜዳ ፖሊስ ማዘዣ ጣብያ በማምራት ለፖሊሶቹ ‹‹ልጆቹ የፈጸሙት ህገ ወጥ ድርጊት የለም፣ሲቀሰቅሱ የነበሩትም እውቅና የተሰጠውን ሰላማዊ ሰልፍ ነው፡፡ቅስቀሳው ህገ ወጥ ነው የምትሉም ከሆነ እነርሱን የላኳቸው እኔ በመሆኔ እኔን ልታስሩኝ ትችላላችሁ ››ብለዋል፡፡
ፖሊስ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን በማሰር ወጣቶቹን ለቅቋቸዋል፡፡

Tuesday, September 24, 2013

ከለውጡ በኋላስ? (ተመስገን ደሳለኝ)

My moments behind the walls of Kaliti prison – Part Four (Temesgen Desalegn)ኢህአዴግ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ (በውስጥም በውጪም ተግዳሮቶች) መገፋቱን በሚያመላክቱ የፖለቲካ አጀንዳዎች ላይ የሚያጠነጥን አንድ ፅሁፍ (‹የአብዮቱ የምፅዓት ቀን ምልክቶች›› በሚል ርዕስ) አቅርቤ እንደነበር ይታወሳል፤ ይዘቱም በመጪዎቹ ወራት ወይም ዓመት ስርዓቱ ‹ምርጫ› አሊያም ‹ህዝባዊ›  እምቢተኝነት ከሚያመጣው ‹ማዕበል› (እንደበረከት ስምዖን አገላለፅ ‹ናዳን በሚገታ ሩጫ›) የማምለጥ ዕድሉ የጠበበ መሆኑን የሚያመላክት ነው፤ ይሁንና አንድ አብዮት ታላቅ (ውጤታማ) ሊባል የሚችለው አምባገነን ስርዓትን በመቀየሩ ብቻ ስላልሆነ (ሥር-ነቀል ለውጥ የሚፈጥር አብዮት ዋጋ የሚኖረው የዲሞክራሲ ተቋማትን መሰረት መጣል ሲችል ነውና) በቀጣይ መፃኢ ዕድሉ ላይ መነጋገሩ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
በዚህ ፅሁፍህ ተጠየቅም ‹ከስርዓቱ ለውጥ በኋላ፣ ማን ነው አማራጩ?› የሚለው ጥያቄ ትኩረት ይደረግበት ዘንድ አመላክታለሁ፡፡ ምክንያቱም በጠለፉ መንገድ ከቀሩ አብዮቶች ታሪክ ተምረን፣ ‹መጥነን ካልደቆስን› የሚከፈለውን ዋጋ በብላሽ የሚያስቀር አሳዛኝ ሁናቴ ሊፈጠር ይችላልና (ቭላድሚር ኤሊች ሌኒን ‹‹አብዮት፣ ለአብዮት ብቻ ሲባል መካሄድ የለበትም›› እንዲል፣ ከኢህአዴግ መገላገሉ መልካም ቢሆንም፣ የአገላጋዩን ማቀፊያ ከወዲሁ መምረጡ ወይም የምንጠይቀውን ማወቁ ብልህነት ነው)

ዜና ከአዲስ አበባ – 15 የሚሆኑ የአንድነት ፓርቲ አባለት ዛሬ ህገወጥ እስር ተፈፀመባቸው፤ የአራት ኪሎን ህዝብ እናመሰግናለን – ፍኖተ ነጻነት

553582_717269128289551_1267195516_nአንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ መስከረም 19 ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ የመኪና ላይ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ 15 አባላቱ ህገወጥ እስር ተፈፀመባቸው፡፡ አባላቱ ከስድስት ኪሎ ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው ጎዳና በመኪና ላይ እየቀሰቀሱ ባለበት ወቅት ሚኒሊክ ት/ቤት ፊትለፊት የፖሊስና የደህንነት ኃይሎች የሚተላለፈውን መኪና መንገድ በመዝጋት ቅስቀሳውን አደናቅፈዋል፡፡
በስፍራው የነበሩ በርካታ ሰዎች “ቀስቃሾቹ ህጋዊ ወረቀት ይዘዋል፤ልቀቋቸው” በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል ከአንድነት ፓርቲ ጎን እንደሚቆሙም ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ 15 የሚሆኑትን የቅስቀሳ ቡድን አባላት ወደ ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋቸዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች አባላቱ ወደ ታሰሩበት 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ረ/ኢ መንግስቱ ለማ የተባሉትን የፖሊስ ጣቢያው ኃላፊ የታሰሩት አባላት እንዲለቀቁ ጠይቀዋል፡፡

Monday, September 23, 2013

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት የበይነ መረብ ዘመቻ መግለጫ – አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ

553582_717269128289551_1267195516_nላለፉት ሶስት ወራት ስኬታማ ህዝባዊ ንቅናቄ ሲያደርግ የቆየው አንድነት ፓርቲ የመጀመሪያውን ዙር ለሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ከሰላሳ ሶስቱ ፓርቲዎች ጋር በሚያደርገው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ያጠናቅቃል፡፡ የህዝባዊ ንቅናቄው አካል የሆነው የበይነ መረብ ዘመቻ(online social media campaign) ከመስከረም 14-18 ቀን 2006 ዓ.ም ይደረጋል፡፡ ዘመቻው ትኩረት የሚያደርገው የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ቀዳሚ አጀንዳ በሆነውና የፀረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ በሚጠይቀው የትኩረት ነጥብ ላይ ነው፡፡
ለአምስት ቀናት የሚቆየው የበይነ መረብ ዘመቻ አንድነት ፓርቲ የጸረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ የጠየቀባቸውን ጉልህ ህገ መንግስታዊ መሰረታዊያን በማብራራት ህዝባዊ ንቅናቄውን በበይነ መረብ (online social media campaign) የሚያቀጣጥል ነው፡፡

መውጫ አብጅቶ መግቢያ የከለከለን አሳዳጁ ማን ነው? – ከግርማ ሠይፉ ማሩ


ከግርማ ሠይፉ ማሩ
Girma Siefuሀገራቸን ኢትዮጵያን ለቀው ለስደት የተዘጋጁት ዜጎችን ቁጥር መገመት አስቸጋሪ ቢሆንም በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት መውጣት የቻሉት ግን ላለመመለስ ብዙ ምክንያቶች አሉዋቸው፡፡ ይህን የዜጎች (በተለይ የተማሩና ወጣቶች) ስደት ሀገራችንን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት እንደሆነ እና ወደፊትም ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትል ለማወቅ ሊቅ መሆን የሚያስፈልግ አይመሰለኝም፡፡ አሜሪካኖች በዲቪ እንኳን ሊወስዱት የሚፈልጉት ፊደል ቆጥሮ አንድ ነገር ሊያደርግላቸው የሚችለውን እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ለዜጎች ስደት ምክንያቱ መንግሰት እንደሚለው ህገወጥ ደላሎች አይደሉም ይልቁንም የመንግሰት የተለያየ ፖሊሲ ውጤቶች ናቸው ብዬ ማሳየት ፈለኩኝ እና ይህን ፅሁፍ ጀመርኩ፡፡
የስራ ዋስትና በሀገራችን የተረጋገጠ አይደለም፡፡ ቀደም ሲል የመንግሰት ስራ ያልተመቸው ኢትዮጵያዊ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ገብቶ በሞያው ማገልገል አንድ የሚታይ ጠባብ አማራጭ ነበር፡፡ ይህ ጠባብ አማራጭ እንደሚታወቀው ከ1997 ምርጫ በኋላ ይህ “የኪራይ ሰብሳቢዎች ምሽግ እንዲፈርስ” በሚል በወጣ አዋጅ ጠባብ አማራጭነቱ ቀርቶዋል፡፡ የዚህ አማራጭ የተዘጋው ህጋዊ በሚመስል እና ለድሆች በማሰብ በሚል ነው፡፡ አዋጅ ቁጥር 621/2001 የበጎ አድራጎትና ማህበራት ምዝገባ አዋጅ እና ተከትለው የወጡትን መመሪያዎች ማየት በቂ ነው፡፡ ውጤቱ ግን ኢህአዴግ እንደሚያስበው የመንግሰት ተቀጣሪነት የሰለቻቸው ሰዎች ፀጥ ለጥ ብለው እንዲገዙ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋሞች ውስጥም አንፃራዊ ነፃነት አግኝተው ይሰሩበት ከነበረበት ወደ መንገስት ተቋም በመምጣት የመንግሰትን ተቋምን አላሳደጉም፡፡

አባይ ወልዱና ደብረጽዮን ሽጉጥ ተማዘው ነበር (አብርሃም ደስታ – ከመቀሌ)

አባይ ወልዱና ደብረጽዮን ሽጉጥ ተማዘው ነበር – የአባይ ቡድን በሁለት ተከፈለ (አብርሃም ደስታ – ከመቀሌ) ህወሓት በአባይ ወልዱና ደብረፅዮን ቡድኖች በሁለት መከፈሉ ይታወቃል። ባለፈው የህወሓት የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የአባይና የደብረፅዮን ጠብ በጣም በመክረሩ የተነሳ ሽጉጥ መማዘዛቸው ተሰምቷል። ሃይለማርያም ደሳለኝና በረከት ስምዖን ለማስታረቅ የሞከሩ ሲሆን ዉጤቱ አልታወቅም። ይህ በንዲህ እንዳለ የአባይ ቡድንም ሰሞኑ በሁለት ተከፍሏል፤ የአባይ ወልዱና የበየነ መክሩ። ከህወሓት ስብሰባ በኋላ የስልጣን ሽግሽግ ለማድረግ የተሞከረ ቢሆንም በየነ መክሩና ኪሮስ ቢተው ከስልጣናቸው ለመውረድ (ሓላፊነት ለመቀየር) ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ከአባይ ወልዱ ጋር ከፍተኛ አምባጓሮ ተፈጥሯል።
 ኪሮስ ቢተው የግብርና ቢሮ ሓላፊና የኢንተርፕራይዞች የቦርድ ሰብሳቢ ነበር። አባይ ወደ ሌላ ቢሮ ሊቀይሮው አስቦ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።

Sunday, September 22, 2013

የዛሬው የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ፎቶና የሚያሰሟቸው መፈክሮች በጥቂቱ !!

በአሁኑ ሰዓት ሰማያዊ ፓርቲ ከሶሰት ወር በፊት የጠራውን ሰልፍ እያካሄደ ይገኛል:: ሰልፉ በደማቅ ሁኔታ ተጀምሮ ነበር የሰልፉ መድረሻ መሰቀል አደባባይ ቢሆንም ሕዝቡ አራት ኪሎ አካባቢ ሲደርስ የአዲስ አበባ ፓሊሶች ሰልፈኛውን ወደ መሰቀል አደባባይ እንዳይሄድ ሲያግዱ የፌድራል ፓሊስ ደግሞ በርቀት እየተመለከተ ነው::ሰልፈኞቹ ወደ ስማያዊ ፓርቲ ቢሮ እንዲመለስ ተደርጓል ሕዝቡ ግን ድምጹን ከማሰማት ወደኋላ አላለም

Blue party

ሌ/ጀነራል ገዛኢ አበራ ቤተሰቦቻቸውን ሰብሰበው ስዊድን ገቡ!!


(ዘ-ሐበሻ) የጦር ሃይሎች የሎጂስቲክስ ዋና ሐላፊ የነበሩት ሌ/ጀነራል ገዛኢ አበራ ቤተሰቦቻቸውን ሰብስበው ስዊድን መግባታቸውን አብርሃ ደስታ ከመቀሌ ባስተላለፈው መረጃ አመለከተ። አብርሃም ገዛኢ ከሃገር የወጡት በጡረታ ለተገለሉ በኋላ ነው  በማላት  ”የህወሓት ሃላፊዎችማ የያዙትን ይዘው ከሀገር እየወጡ ነው። የተቸገሩ ታችኞቹ ካድሬዎች ናቸው። እንደ አለቆቻቸው ወደ ዉጭ በመኮብለል የግል ደህንነታቸው መጠበቅ አይችሉም።” ሲል ትችቱን አስፍሯል።
ጄነራል ገዛኢ አበራ በሱዳን አቢ ግዛት ሰፍሮ የነበረውን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል የመሩ ናቸው።
ከአንድ ዓመት በፊት የግንቦት 7 የኢትዮጵያ የጥናት ቡድን ባሰራጨው ምስጢራዊ መረጃ ወያኔ የአገዛዝ እድሜውን ለማራዘም የትግራይ ተወላጆች የሆኑትን የጦር አለቆች ከፍተኛ የሆነ ሃብት እንዲያካብቱና ዘረፋ እንዲፈጽሙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ለተለያዩት የጦር መኮንኖች ሟቹ ጠ/ሚ/ር በ1989 ለአ/አበባ አስተዳደርና ለመከላከያ ሚ/ር መ/ቤት ለ25 የወያኔ የጦር መኮንኖች፣ ለእያንዳንዳቸው በሽልማት በአዲስ አበባ ውስጥ 500 ካሬ ሜትር 1ኛ ደረጃ መሬት እንዲሰጣቸው ትእዛዝ በሰጡት መሰረት ይህን መሬት የተቀበሉት ሌ/ጄነራል ገዛኢ አበራ በወር 170 ሺህ ብር የሚከራይ ቤት ቦሌ አካባቢ ሠርተው እንደሚያከራዩ ተጋልጦ ነበር።

በኢህአዴግ ቀይ መስመር ላይ የተደረገ ታሪካዊና ውጤታማ ሰለፍ


የሰልፊ አጀማመር ልክ እንደባለፈው ነበር ልዩነቱ የሰአቱ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ የዛሬው 3፡45 ሲሆንየጀመረው የባለፈው ከሶስት ሰአት በፊት ለጉዞ ተነስቶ ነበር፡፡የባለፈው ሰልፍ ላይ መጀመሪያ ላይ የአካባቢው ህብረተሰብ የለሁበትም አይነት የሞላበት የፍርሀት ስሜት የተንጸባረቀበት የነበረ ሲሆን የዛሬው ግን የዛ ፍጹም ተቃራኒ ነበር፡፡በአካባቢው የነበሩ ጥቂት የማይባሉ ፖሊሶች ላይ ሳይቀር ይነበብ የነበረው ስሜት ደግ አደረጋችሁ ፈጣሪ ከእናንተ ጋር ይሁን አይነት ነበር፡፡

አየር ሃይል አደጋ ላይ ነው ተባለ “ተዋጊ አውሮፕላኖች የኮንትሮባንድ ማመላለሻ ሆነዋል”

የኢትዮጵያ አየር ሃይል እንደገና ካልተዋቀረ አገርን መከላከል የሚችልበት ደረጃ እንደማይገኝ ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ለኢሳት አስታወቁ። ተዋጊ አውሮፕላኖች የኮንትሮባንድ ማመላለሻ ሆነው እንደሚአገለግሉ፣ አብራሪ የሚባሉት በሚሊሻ ደረጃ መገኘታቸው፣ የዘር መድልዎ እንደሚደረግ፣ የህወሃት ድጋፍ ያላቸው ብቻ የሚስተናገዱበት መሆኑ፣ ከችግሮቹ በግንባር የሚገለጹ ናቸው።
ላለፉት 15 ዓመታት ያህል በታማኝነት የተጣለባቸውን አደራ መወጣታቸውን የገለጹት ሻለቃ አክሊሉ ” የአውር ደንብር” እንዲሉ በአየር ሃይል ውስጥ የሚሰራው የቡድን፣ የዘርና አጠቃላኢ አለው አሰራር ብልሹነት አሳሳቢ በመሆኑ አገር ጥለው በመውጣት ከሶስት ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ግንቦት7 ንቅናቄን መቀላቀላቸውን አመልክተዋል።

Saturday, September 21, 2013

ወጣቱ የግብርና ኤክስፐርት በአሰቃቂ ሁኔታ በፖሊስ መገደሉ ተገለጸ

ወጣቱ የግብርና ኤክስፐርት በአሰቃቂ ሁኔታ በፖሊስ መገደሉ ተገለጸ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ጎጃም ዞን በጐንጅ ቆለላ ወረዳ በሸበሌ ቀበሌ ዘመናዊ የግብርና አሠራር ለአካባቢው ነዋሪዎች በማሠልጠንና አብሮ በመሥራት ላይ የነበረ ወጣት የግብርና ኤክስፐርት፣ ፖሊስ በጥይት ደብድቦ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደገደለው ዘመዶቹና የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
በአካባቢው ለፖሊሲ ኮሙዩኒቲንግ ሥራ ከወረዳው በተላከ ፖሊስ በጥይት ተደብድቦ ሕይወቱ አልፏል የተባለው የግብርና ኤክስፐርት ዘለዓለም ፀሐይ የሚባል የ29 ዓመት ወጣት መሆኑን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ በ2002 ዓ.ም. ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በግብርና የትምህርት ዘርፍ ከተመረቀ በኋላ፣ ላለፉት ሦስት ዓመታት ‹‹ያሳደገኝን አርሶ አደር መርዳት አለብኝ›› በማለት ከከተማ ሥራ ይልቅ ገጠሩን መርጦ ሲያገለግልና ሲያሠለጥን እንደነበር አስረድተዋል፡፡

የአንድነት ፓርቲ ቀጣይ እጩ ሊቃነመናብርት ተለይተው ታወቁ – አንድነት የአንድነት ፓርቲ ቀጣይ እጩ ሊቃነመናብርት ተለይተው ታወቁ አንድነት

1238242_721208644562266_1225807894_n
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ፓርቲውን ለቀጣዮቹ 3አመታት በሊቀመንበርነት ለመምራትከተወዳደሩት 5 ከፍተኛ አመራሮች ውስጥ 3ቱን ለመጨረሻው ዙር ውድድር እንዲያልፉ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መርጧል፡፡ ፓርቲውን በሊቀመንበርነት ለመምራት የተወዳደሩት አቶ ትግስቱ አወሉ፣ ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ አቶ ሽመልስ ሀብቴ እና አቶ ተክሌ በቀለ ናቸው፡፡
ዛሬ የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት በሚስጥር ድምፅ አሰጣጥ ስርአት ባደረጉት ምርጫ 1ኛ.ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው 2ኛ.አቶ ተክሌ በቀለ 3ኛ.አቶ ግርማ ሰይፉ ለመጨረሻው ዙር ውድድር አልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዋነኛ ጠላት ወያኔ ብቻ ነው!!

የግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በቅርቡ ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ዋነኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊና ዘላቂ ጥቅም ጠላት ወያኔ መሆኑን አስረግጦ ተናግሮ ነበር። ይህንን አባባል አንድ ተቃዋሚ ለተቃውሞ ያህል ወይም ስርዓቱን የሚጠላ አንድ ግለሰብ ስርአቱን ስለሚጠላዉ ብቻ እንደተናገረው አድርጎ አቃልሎ ማየት ትልቅ ስህተት ነው። ወያኔ ከፍጥረቱ ጀምሮ እስከአሁኑ ቅጽበት ድረስ በሀገራችን ላይ የፈጸመውን ደባ በቅጡ ያላዩ ሰዎች ይህ አባባል የተጋነነ ይመስላቸው ይሆናል። ኢትዮጵያ ዛሬም አንደ አገር የቆመችዉ በህዝቦቿ ታላቅነትና እንዲሁም ለታሪካቸው ባሳዩት ክብርና ብርታት ነዉ እንጂ እንደወያኔማ ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ ህልውና አደጋ ላይ ከወደቀ ሰንብቷል።
ኢትዮጵያ የሚለውን ውብና ታሪካዊ የስም ለመጥራት እየተጸየፈ “የሀገራችን ህዝቦች” እያለ ሲጠራን የነበረው የወያኔዉ ሹም የንቀት አጣራር ወያኔዎች ከሀገሪቱ ስም ጋር ሳይቀር የገቡበትን ጠብ ያሳያል። ወያኔ አባቶቻችን ባቆዩልን ዳር ድንደር የሚደራር ብቻ ሳይሆን የአገራችንን መሬት ላብዕዳን እንካችሁ ያለ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ነዉ። በወያኔ እንደባሪያ ፈንግሎ የሚገዛት አገራችን ኢትዮጵያን የታሪክ አጋጣሚ እጁ ላይ ጥሎለት ነዉ እንጂ እሱ እንደሚነግረን ወያኔ ከራሱና ከጉጅሌዎቹ ጥቅም አስበልጦ ኢትዮጵያን አስቧት አያውቅም።

መስከረም 10, 2006 ዓ/ም በእሰር ላይ በምትገኘው ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ላይ «የስነ-ስርዓት ማስከበሪያ» ያለውን እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።

መስከረም 10, 2006 ዓ/ም በእሰር ላይ በምትገኘው ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ 

ላይ «የስነ-ስርዓት ማስከበሪያ» ያለውን እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ 

መንግሥት አስታወቀ።

ከሰማይ ወረደ ለተባለው መስቀል የሳይንስ ምርመራ አይፈቀድም ተባለ

ከሰማይ ወረደ ለተባለው መስቀል የሳይንስ ምርመራ አይፈቀድም ተባለ
ለህዝብ የሚታየው ፓትሪያርኩ በተገኙበት ነው በየእለቱ ከ3ሺህ ሰው በላይ ቦታውን እየጎበኘ ነው
በአቃቂ ቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ከሰማይ ወረደ የተባለው መስቀል ፓትርያርኩ በተገኙበት ለህዝብ እንዲታይ መግቢያ መንገድ እስኪሰራ ድረስ የተራዘመ ሲሆን፣ በመስቀሉ ላይ የሳይንስ ምርመራ እንደማይፈቀድ ተገለፀ፡፡

ኦሮማይ፣ ትግሉ በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ!

ከቴዎድሮስ ሓይሌ (tadyha@gmail.com)
47252279622a2c371378326050ሠሞኑን የግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስለ ኤርትራ ቆይታቸውና ስለድርጅታቸው ቀጣይ የትግል እንቅስቃሴ ሠፊ ገለጻና ማብራሪያ በኢሣት ቴሌቪዠን ከሠጡ ወዲህ የዘረኛው የትግሬ ነጻ አውጪ ግንባር ደጋፊ የሆኑት መርገማዊ ልሳኖች( አይጋ ፎረም ፤ ትግራይ ኦላይንና አውራንባ ታይምስ) እና አንዳንድ ተንበርካኪ የመንደር ሬድዮኖች ሰፊ የውግዘትና የህዝብን መንፈስ ያሸብርልናል በተቃዋሚዎችም ላይ ጥርጣሬ ይዘራልናል በሚል ደካማ ግንዛቤ እያካሄዱ ካለው አሰልቺና ኋላቀር ፕሮፓጋንዳ እጅግ ተጋኖ እየቀረበ ያለው ከሻብያ ጋር አብሮ መስራት ታላቅ የሃገር ክህደት ስለመሆኑ እፍረት የለሽ ኡኡታ በማሰማት ላይ ይገኛሉ።Ato Andargachew Tsige, Ginbot 7
ይህንን ጽሑፍ እንድጽፍም ያነሳሳኝ ይህ የወያኔ በቀቀኖች ልቅ ያጣ የፀረ ሻብያ ውትወታ ወያኔ የምትባለው የጠባብ ዘረኞች ቡድን ለዚህ ዛሬ ለደረሰችበት የዘረፋና የልዕልና ደረጃ የበቃችው ከቶ በማን ትከሻ ሆነና ነው ።

Friday, September 20, 2013

በኢትዮጵያ የመብት ጥሰት በከፍተኛ ሁናቴ ተባብሷል፤

በኢትዮጵያ የመብት ጥሰት በከፍተኛ ሁናቴ ተባብሷል፤ በሃገራችን በሚገኙ ‹ማረሚያ› ቤቶች እየደረሱ ያሉ ሰብኣዊ መብት ጥሰቶች በተለይም በፖለቲካ እና የህሊና ‹ታራሚዎች› ላይ እየደረሰ ያለው ጥሰትን የመጨረሻ ደረጃ ማሳያ አይደለም፡፡ ምናልባትም ይህ ግፍ በህውሃት ዝቅተኛው ሊሆን ይችላል፡፡
በህውሃት እስር ቤት የሚደርስባቸው በደል፣ግፍ፣ስቃይ እና የመብት ጥሰት ሊሰማላቸው ያልቻለ ብዙዎች እንዳሉ ለመረዳት ነብይ መሆን አይጠይቅም ነገሩ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡
እንደ አጋጣሚ ሆኖ ታዋቂ ወይም ስራው/ዋ ከሚዲያ ጋር የተያያዘ ከሆነ፤ የሱ/ሷ ጉዳይ ለሚዲያ የመቅረቡ እድልም ሰፊ ነው፡፡ታዋቂና ለሚዲያ ቅርብ የሆነ ሰው የሚደርስባት ማንኛውም ኢ-ሰብኣዊ ድርጊት ለሚዲያ እንደሚደርስ እየታወቀ መብቶቿ በአደባባይ የተጣሱ፤ የሌሎች የፖለቲካ እና የህሊና ‹ታራሚዎች› አያያዝ ሁኔታ ከነሱ የባሰ እንደሚሆን ማስብ ተገቢ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በሞተሩ ላይ ባጋጠመው እክል ማልታ ላይ ለማረፍ ተገደደ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 10 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 757-200 አውሮፕላን ባጋጠመው ችግር ማልታ ላይ አረፈ።

ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ ይባል ነበር ዱሮ ወግ ነው ምርጫ ማሸነፍ ሆነ ዘንድሮ! አስተሳሰብና ጉልበት (ሕገ አራዊት)

ሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም
በረከትን በደንብ የሚያውቀው ያሬድ ጥበቡ ሙልጭ አድርጎ ነግሮታል፤ ያሬድ ከዚህ በፊትም ስለበረከት ጽፎ ነበር፤ አሁን ከጻፈው ጋር ሳስተያየው አንድ ግጥም ትዝ ይለኛል፤ አንዲት የቸገራት ሴትዮ ያንጎራጎረችው ይመስለኛል፡-
mnnnወደድኩህ ወደድከኝ፤ ጠላሁህ፤ ጠላኸኝ፤
እንደሚጣራ ጠጅ እየጣልክ አታንሣኝ!
ያሬድ ስለበረከት በሚጽፈው ሁሉ እያነሣ የመጣልና እየጣለ የማንሣት ዝንባሌን ያሳያል፤ እስከዛሬ በናፍቆት የሚጠብቀውን ወዳጁን ሸፍጥንና የአእምሮ ሕመምን ሲያለብሰው ማንኛቸው መቼ እንደተለወጡ ለመረዳት ያስቸግራል፤ ለማናቸውም የዲክንስን መጽሐፍ ያሬድ እንደሚለው በረከት ከመጀመሪያው ገጽ በላይ አነበበም አላነበበ እንግሊዝኛው ትርጉም መሆኑን የተረዳሁት ከያሬድ ነው፤ ለምን ወደ እንግሊዝኛ እንደተሄደም አልገባኝም፡፡

አሳዛኙ የወገናችን ኅልፈት!

"ህይወት እንደዋዛ"

the pic


ዲፕሎማቱ እጅ ላይ ያረፈችው ኢትዮጵያዊት ወጣት ሬሳ ትላንት ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወሰደ ።

ወያኔም በስደት (ጌዲዮን ከኖርዎይ)

ጌዲዮን (ከኖርዎይ)

መቼም እንደወያኔ አገዛዝ ስደት የሰፈነበት የኢትዮጵያ ታሪክ የለም፥፥ ምሁራን፥ ተማሪ፥ ሰራተኛ፥ የሃይማኖት አባቶች፥ ገበሬው፥ ወጣት ወንድሞችና እህቶች፥ ብቻ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተሰዷል፥ አሁንም በመሰደድላይ ነው፥፥ ብዛት ያላቸው ወንድሞችና እህቶቻችንም ከተሰደዱ በኋላም ወይ መንገድ ላይ ወይ ሰው ሃገር ከገቡ በኌላ ህይወታቸውን ያጣሉ ይሰቃያሉ፥፥
በመላው አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከገዛ ሃገራቸው በወያኔ/ህወሃት አፋኝ ስርአት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት ረገጣ፥የዲሞክራሲና የነፃነት እጦት፥ የዘረኝነት መስፋፋት፥ የህግ የበላይነት አለመከበር፥ የኑሮው ከአቅም በላይ መሆንና በሌሎችም በበርካታ ምክንያቶች በግፍ ከገዛ ሃገራቸው ተሰደው ከወጡ በኋላ በሚኖሩበትን ሃገር የመናገር የመፃፍና ሃሳባቸውንበነፃ የመግለፅ መብታቸውን በመጠቀም፥ የወያኔ መንግስትንእኩይ ተግባር ለማጋለጥ ይሞከራል፥፥ ይሁንና ይህ እንቅስቃሴ የወያኔ ማህበርን እንቅልፍ እንደሚነሳ ደሞ አያጠያይቅም፥፥

Thursday, September 19, 2013

አና ጎመሽ – ርዕዮትና እስክንድር “የኅሊና እሥረኞች ናቸው” አሉ

ለያዝነው የአውሮፓ 2013 ዓ.ም የአውሮፓ ፓርላማ የሳኻሮቭ ሽልማት ሁለት ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ሰባት ዕጩዎች ቀርበዋል፡፡ ለያዝነው የአውሮፓ 2013 ዓ.ም የአውሮፓ ፓርላማ የሳኻሮቭ ሽልማት ሁለት ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ሰባት ዕጩዎች ቀርበዋል፡፡ ሽልማቱ ለሃሣብ ነፃነት ለሚታገሉና ለታገሉ የሚሰጥ የአውሮፓ ፓርላማ ዓመታዊ ክንዋኔ ነው፡፡
ኢትዮጵያዊያኑን ዕጩዎች ርዕዮት ዓለሙንና እስክንድር ነጋን ለሽልማት ካቀረቡት አርባ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት አንዷ የፓርላማው አባል፣ እንዲሁም የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴው እና የሰብዓዊ መብቶች ንዑስ ኮሚቴ አባል የሆኑት አና ጎመሽ ይገኙበታል፡፡

Tuesday, September 17, 2013

“የበሰበሱት” ህወሃት እና ሻዕቢያ አንዱ ሌላውን የማጥፋት እሽቅድድም!

tplf-vs-eplf
አምባገነነኖች ከሚታወቁበት አንዱና ዋንኛ መለያቸው መካከል ሁለተኛ ሰው አለማዘጋጀታቸው ነው። አቶ መለስ በድንገት ሲስፈነጠሩ በውል የታየው አስከሬን ደብቆ ድብብቆሽም የዚሁ ውጤት ነው። ኢሳያስ ከስልጣን ቢወገዱ ማን ይተካቸዋል? የሚለው ችግርም ጎልቶ የሚታየው ከዚሁ የአምባገነኖች በሽታ አንጻር ነው።

ርዕዮትና እስክንድር የአውሮፓ ህብረት በሚያዘጋጀው “ሻካሮቭ የነጻነት ሽልማት” የ2013 ተሸላሚ ለመሆን ከሰባቱ እጩዎች ውስጥ ገቡ፡፡

ርዕዮትና እስክንድር የአውሮፓ ህብረት በሚጋጀው  “ሻካሮቭ የነጻነት ሽልማት” የ2013 ተሸላሚ ለመሆን ከሰባቱ እጩዎች ውስጥ ገቡ፡፡ ከ15 ቀን በኋላ መስከረም 20 ለመጨረሻ ውድድር ሚቀሩት 3 እጩዎች የሚታወቁ ሲሆን መስከረም 30 በሚደረገው የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ስብሰባ የአመቱ ተሸላሚ እንደሚለይ ከህብረቱ መግለጫ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ህዳር 11 ቀን በምስራቅ ፈረንሳይ በምትገኘው ስትራስበርግ ከተማ የሽልማት ስነስርዓቱ ይከናወናል፡፡
መልካም ዕድል ለርዕዮትና ለእስክንድር!
ሙሉ መግለጫው የሚከተለው ነው

Monday, September 16, 2013

734 ሚሊዮን 600 ሺ ብር የመዘብሩ የስራ ሃፊዎች አለመቀጣታቸውን መረጃዎች አመለከቱ

መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን የተገኝው መረጃ እንደሚያመለክተው ከተለያዩ የፌደራል መስሪያ ቤቶች 734 ሚሊዮን 6 መቶ ሺ ብር የመዘብሩ የስራ ሃፊዎች በተጣራ መረጃ ክስ ቢመሰረትባቸውም የውሳኔ ቅጣት እንዳልተላለፈባቸው ታውቋል።
ለረጅም ጊዜ በተደረገ ምርመራ ተጣርቶና መስረጃ ተገኝቶባቸው ከ2004 ዓም ጀምሮ ክስ የተመሰረተባቸው የተለያዩ የሙስና ወንጀሎች የውሳኔ ሀሳብ እንዳልተላለፈባቸው ከመሰሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ላይ  94 ሚሊዮን 300 ሺ ብር  ከትምህርት ተቋማት ግንባታ ጋር በተያያዘ የተፈጸመ የሙስና ወንጀል ምርመራ ተጠናቆ ክስ ቢመሰረትም በቂ ውሳኔ ሳያገኝ ቀርቷል።
ከአራዳ ክ/ከተማ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ  ህገወጥ የካሳ ክፍያ በመፈጸሙ ሦስት የምርመራ መዝገቦች ተጠናቀው በ2004 ዓ.ም ክስ ቢመሰረትም የቅጣት ውሳኔ አላገኝም።

Monday, September 9, 2013

በተጭበረበረ አፋኝ ፖለቲካ የተገነባው ኢኮኖሚ ተንኮታኩቷል:: ለስርኣቱ ቅርበት አላቸው ያሉ ምንጮች ወያኔ ወገቡ እንደተሰበረ እየተናገሩ ነው::

ምንሊክ ሳልሳዊ ገበናን ገበና ይገፈዋል እንደሚባለው የወያኔ ጁንታ በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የገነባው ኢኮኖሚያዊ ገበና በገበና ተጋልጧል:: የማይሰማ ነገር የለም እና እኛም ሰማን አነበብን አየንም እነሆ ታዝበን ዝም አላልንም ገበናዎቹ ገበናውን ሲገልቡት አብረን አልሳቅንም ሀገር ነውና ገበናዎቹን ተመርኩዘን የምንለውን ልንል ይኸው ተከሰትን::
ወያኔ እየመራው የሚገኘው ኢኮኖሚ ተሽመድምዶ ሃገርን ረመጥ ላይ እየከተታት ሲሆን የወያኔ ሳቦታጅ ጥቂት ሰዎች በሃገር ሀብት በህዝብ ላይ እንዲፈነጩ አድርጓቸዋል::በሃገሪቱ ማንኛውም አይነት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ከበፊቱ በተለየ እና በባሰ ሁኔታ ተንኮታኩተው አፈር መልበሳቸው በይፋ ታውቋል::ለስርኣቱ ቅርበት አላቸው ያሉ ምንጮች ወያኔ ወገቡ እንደተሰበረ እየተናገሩ ነው::በፖለቲካው ረገድ የስርኣቱ ገዢ ፓርቲዎች እርስ በርስ አለመተማመን ደረጃ ላይ ከመድረሳቸውም በላይ አመራሮቹ አድፍጠው አንዱን አንዱን እየጠበቀ በፍራቻ አለም ውስጥ እየዋተቱ ይገኛሉ::አቤት የሚባልበት እየጠፋ ነው፡፡ የውሳኔ ሰጪ ያለህ ቢባል መልስ አይገኝም፡፡ ፋይሎች የሚያያቸውና የሚያነባቸው አጥተዋል፡፡ መልካም አስተዳደር ገደል ገብቷል::በአላማ ሳይሆን በጊዜያዊ የመኖር ሂደት ላይ የተመሰረተው የካድሬዎቹ ሩጫ ድካምን በመፍጠሩ ሁሉም በያለበት ቆም ብሎ እያሰበ ሲሆን አሳቡም የገፈፍኩትን ገፍፌ ሃገርን ድባቅ መትቼ ልሽሽ ሆኗል::

የሕግ ባለሙያ፣ ባለሀብትና አርቲስት የሆነው አበበ ባልቻ ተከስሶ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሔዷል፡፡

የሰው ለሰዉ አስናቀ – 18ሺ ብር ከፈለ!
የሕግ ባለሙያ፣ ባለሀብትና አርቲስት የሆነው አበበ ባልቻ ተከስሶ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሔዷል፡፡ አበበ ባልቻ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሊሔድ የቻለው ባለፈው ሐሙስ ሌሊት ከሙያ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን ሸገር ሕንፃ ስር በሚገኘው ዩጎቪያ ክለብ በመዝናናት ላይ ነበር፡፡ በቦታው ለእረፍት ከኖርዌይ የመጣውና በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ኖርዌያዊ የሆነው ሐሰን መሐመድና የወንድሙ እጮኛ እየተዝናኑ ነበር፡፡ ከሐሰን ጋር የነበረችው ሴትም አበበ አስናቀን ሆኖ በሚጫወትበት የሰው ለሰው ድራማ ታደንቀው ስለነበር ወደ እሱ በመሄድ አብራው ፎቶ ለመነሳት ትጠይቃለች፡፡ አበበም ፈቃደኛ በመሆን አብሯቸው ይነሳል፡፡ ትንሽ ቆይቶ ግን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ መበሳጨት ይጀምራል፡፡ ከዚያም ወደ ሰዎቹ በመሄድ ከሐሰን ላይ ፎቶ ያነሳበትን አይፎን 5 ይቀበለውና መሬት ላይ በመጣል በእግሩ ይሰባብረዋል፡፡

“በስልጣን ምክንያት ህወሓት ለሁለት የተከፈለ ይመስለኛል” – አቶ ገብሩ አስራት (ቃለ ምልልስ)

ሐገር ቤት የሚታተመው ሎሚ መጽሔት አቶ ገብሩ አስራትን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አነጋግሯቸዋል። ዘ-ሐበሻ ለአንባቢዎቿ ይጠቅማል በሚል እንደወረደ አቅርባዋለች።
246522dcb1a158f71378732826ሎሚ፡- ባለፈው መቀሌ ላይ “አረና” ሕዝባዊ ስብሰባ አከናውኖ ነበር፡፡ የነበረው ሁኔታ በአጠቃላይ ምን ይመስል ነበር;
አቶ ገብሩ፡- እንግዲህ የመቀሌውን ስብሰባ ከሁለት ጉዳዮች አንፃር ልንመለከተው እንችላለን፡፡ አንዱ ሕዝቡ እንዴት እንደተቀበለው ስብሰባውን … ሁለተኛው መንግስት ወይም በክልሉ ያለው ፓርቲ ስብሰባው እንዳይካሄድ ያደረጉትን ጫና በተመለከተ መመልከት ይቻላል፡፡ እንግዲህ አስቀድሜም መንግስት ስብሰባው እንዳይካሄድ የፈጠረውን ጫና ነው የማየው፡፡ እንግዲህ ትግራይ ውስጥ ገዢው ፓርቲ ህወሓት ነው፡፡ ህወሓት ከእሱ ውጭ ሌላ ፓርቲ እዛ ቦታ ላይ እንዲንቀሳቀስ ፍላጐት የለውም፡፡

Friday, September 6, 2013

የጋራ ንቅናቄው ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን ይቆማል!

የወጣት አመራሮቹን ሰላማዊ የትግል መስመር ይደግፋል!

smne-and-semayawi


ያለፈው እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጠርቶ በነበረው የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ላይ በህወሃት/ኢህአዴግ የተወሰደውን ጽንፈኛ፣ አክራሪና አጸያፊ የውንብድና ተግባር የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ይኮንናል፤ ያወግዛል፡፡ ፓርቲው ሰልፉን ለማካሄድ ከሁለት ወራት በፊት ፈቃድ ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ቅዳሜ ነሐሴ 25፤2013 የፌዴራል ፖሊስና የደኅንነት አባላት የፓርቲውን ጽ/ቤት ጥሰው በመግባት የፈጸሙት ተራ የውብንድና ተግባር ብቻ ሳይሆን የህወሃት/ኢህዴግን ማንነት በግልጽ ያሳየ ለመሆኑ ከማንም በላይ ተግባሩ ራሱ ምስክር ነው፡፡

Thursday, September 5, 2013

ዜና በጨዋታ፤ አየር መንገዴ ሆነ እንዴ… መደዴ…!? (አቤ ቶኪቻው)

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ ተደጋጋሚ ጉዳቶችን ሰምተንበት ደንግጠናል፡፡ ባለፈው ጊዜ በመላው ድሪም ላይነሮች ላይ የደረሰው የባትሪ መጋል የእኛንም አንድ ለእናቱ ድሪም ላይነር ስጋት ላይ የጣለ ነበር፡፡ ቀጠለ በለንደን ከተማ አንዱ አውሮፕላናችን ሲጨስ ታየ ተብሎ ትልቅ ወሬ ሆኖ እኛም ኤድያ…. አሁንስ አየር መንገዴ ቁጣ መጣበት እንዴ… ብለን አድነነ ከመዓቱ ብለን ፀሎት አደረግን፡፡ አሁን ደግሞ ከወደ ደቡብ አፍሪካ አንድ ወሬ ሰማን እቃ ጫኙ ካርጎ አየር መንገዳችን ሸክሙ ከብዶት እንደ ሮኬት ከአፍንጫው ወደላይ ተቀስሮ አየነው… አሁን ማንጎራጎር ጀመርን…

Abe Tokichaw (Abebe Tolla) the Popular Ethiopian Political Satirist
ጥሩም አላወራም ሰው ሁሉ ባገሩ
ውድ አየር መንገዴ ምንድነው ነገሩ
መንሸራተት በዛ ቀረ እና መብረሩ
ካዋዋሉ ይሆን ወይ ካስተዳደሩ…
ብለን ሳናበቃ ከወደ አስተዳደሩ አንድ ዜና ሰማን፤ ይሄማ ካለ አዲስ መስመር አይሞከርም ይከተሉኝማ…

እነ ማን ነበሩ? አሁንስ ማን ናቸው?

0040

ገብረመድህን አርአያ , ፐርዝ፤ አውስትራሊያ
ይህ ጽሑፍ ትኩረት የሚሰጠው በትግል በረሃ በነበርንበት ወቅት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ(ህ.ወ.ሓ.ት.) በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖቶች ላይ ሲከተል የነበረውን አቋሙን ተቀብሮ ከነበረበት ጉድጓድ አውጥቼ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እነማን ናቸው የሚለውን ታሪካቸውን እና የተፈጸመውን ጸረ-እምነት ግፍ በአጭሩ ለማሳወቅ ነው። ህ.ወ.ሓ.ት. ገና ሲፈጠርና ተ.ሓ.ህ.ት. ተብሎ እንደተመሰረተ ሙልጭ ያለ ጸረ-ዲሞክራሲ ድርጅት ነው። በጸረ-ኢትዮጵያነትና በጸረ-ሕዝብነት የተሰማራ ቅጥረኛ ድርጅት መሆኑን ብዙ ጊዜ በጽሑፍና በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ለኢትዮጵያ ህዝብ ተናግሬአለሁ። የአሁኑ
ጽሑፌ ህ.ወ.ሓ.ት. በሃይማኖት ላይ ሲከተለው የነበረውን ፖሊሲ ገና ከመጀመሪያ ትግሉ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ የነበረውን ጸረ- ሃይማኖት ተግባራቱን የኢትዮጵያ ሕዝብ በግልጽ አውቆታል። እኔ ደግሞ የራሴን ልበል።

Wednesday, September 4, 2013

የኢትቪ ሽርፍራፊዎች – በሃብታሙ አያሌው (የአንድነት ፓርቲ ምክትል የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ)

እንደ መግቢያ

የፀረ ሽብረ አዋጅና የፓርቲዎች አቋም ሲል ወይም ኢ.ቲ.ቪ በላከው ደብዳቤ መስረት የሶስት ሰዓታት በእጅጉ የተጋጋለ ውይይት
 ከተካሔደ በኋላ ውይይቱ በዜና እንኳን ሳይዘገብ ከሳምንት በላይ ለሆነ ግዜ በመራዘሙ ተወያይ ፓርቲዎች በተለያየ መንገድ ቅሬታቸውን ሲገልጹ የግል ኘሬስና ማህበራዊ ገፆችም የፓርቲዎቹን ክርክር ኢቲቪ የውሀ ሽታ ሊያደርገው ይችላል ከሚለው መላምት ባሻገር በተለያየ መንገድ አገኘን ያሉትን መረጃም ሲለቅቁ ሰንብተዋል፡፡ አንዳንዶች ተቃዋሚዎች ውኃ የሚቋጥር ኃሣብ ማንሳት እንዳልቻሉ የውስጥ መረጃ አገኘን ሲሉ ሌሎችም በተከራካሪዎች ላይ አለ የሚሉትን የአቅም ማነስ ሳይቀር በመዘርዘር ኢህአዴግ ከውይይቱ ትርማማ ይሆናል ሲሉ ተነበዩ ከዚህ አስተሳሰብ በመጠኑ እንለያለን የሚሉም ውይይቱ ፋይዳ የለውም ኢቲቪ ቆራርጦ መቅኖ ያሳጣዋል ሲሉ ስጋታቸውን ሲገልፁ ስንብተዋል፡፡

ወያኔ የሚገነፍል ድስት ነዉ

ኤፍሬም ማዴቦ

Ephremስፖርት በጣም እወዳለሁ፤ ወቅታዊ ዜናና ጥናታዊ ፊልምም አዘወትራለሁ። ከሁለቱ ዉጭ ግን ኢትዮጵያ እያለሁም ሆነ ዛሬ በስደት ኑሮዬ ከቴሌቪዥን ጋር ብዙም አልዋደድም . . .  ግን አንዳንዴ እበድ ሲለኝ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ቴሌቪዥን ሆኖ ከመተኛቴ በፊት ኢቲቪ እየከፈትኩ አብዳለሁ።  አዎ . . . አብዳለሁ። ሆዴ ያመቀዉ ቁጣና ልቤ የተሸከመዉ የ22 አመት በደል ቀለል የሚለኝ ሳብድ ነዉና ኢቲቪ እየከፈትኩ አብዳለሁ። ምን ላድርግ ተሰድጄ ልበድ እንጂ በወያኔዋ ኢትዮጵያማ እነ በረከት ካልፈቀዱ ማበድም አይቻልምኮ!   አደራ እንግዲህ እንደኔ ጠንካራ ቆዳ የሌላችሁና በትንሹም በትልቁም እየተበሳጫችሁ ዕቃ የምትወረዉሩ ሰዎች ኢቲቪን ከመክፈታችሁ በፊት ባንካችሁ ዉስጥ ቴሌቪዥን መግዢያ ትርፍ ገንዘብ መኖሩን አረጋግጡ፤ አለዚያ እዉነትም ማበዳችሁ ነዉ።

Tuesday, September 3, 2013

ከሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ (ለውጥ ፈላጊዎች በሙሉ ሊሰሙት የሚገባ)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጂነር ይልቃል፤ ከአትላንታው ማህደረ አንድነት ሬዲዮ ጋር ከ30 ደቂቃ በላይ የፈጀ ቃለ ምልልስ አድርገዋል። በዚህ ቃለ ምልልስ በኢህአዴግ አንጋቾች እና ደህንነቶች የደረሰባቸውን ወከባ በዝርዝር ይገልጻሉ። ከዚህ ሁሉ ወከባ እና እንግልት በኋላም ቢሆን፤ ሰላማዊ ትግሉን ለመቀጠል ጽኑ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። በለውጥ የሚያምኑ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ሊሰሙት የሚገባ ቃለ ምልልስ ነው። እርስዎ ይስሙት፤ ላልሰሙትም ያሰሙ።

አዜብ መስፍን ይታሰራሉ?

"አዜብን ማሰር፣ መለስን ከሞት ቀስቅሶ ለፍርድ ማቆም ነው"

azeb-mesfin-e