Translate

Wednesday, June 19, 2013

ይድረስ ለአለምነህ ዋሴ፣ የአሜሪካ « ሰይጣን» በአገራችን?

ከኢየሩሳሌም አርአያ

ዛሬ ጠዋት ከመኖሪያዬ ወጥቼ ጥቂት እንደተጓዝኩ ሁለት አሜሪካዊያን ወጣቶች ከፊት ለፊቴ ሲመጡ ተመለከትኩ። እጅ ለእጅ ተያይዘዋል…በጥንቃቄ ምስላቸውን ለማስቀረት ሞከርኩ።… ( ወንድ ከወንድ- ሴት ከሴት፣ እጅ – ለእጅ መያያዝና መተቃቀፍ ግብረ-ሰዶማዊነትን ያመለክታል በአሜሪካ)… ታዲያ ምንድነው?.. ትለኝ ይሆናል፤… ይህ «ሰይጣናዊ» የነአሜሪካ «ቁሻሻ» በአገራችን መስፋፋቱ አሳስቦኝ ነው። የ11 እና 10 አመት ታዳጊ ሕፃናት ቦሌ አካባቢ በሚገኝ ት/ቤት ዳይሬክተሩን ጨምሮ 6 አስተማሪዎች እየተፈራረቁ «ሰይጣናዊ» ድርጊት ሲፈፅሙ እንደከረሙ መስማት አያስጨንቅም?… ለትምህርት የላከው ልጅህ ያውም በአስተማሪዎች እንዲህ አይነቱ ርካሽ ተግባር ሲፈፀምበት ምን ይሰማኻል?… «14ሺህ ግብረሰዶማዊያን በኢትዮጲያ አሉ» ተብሎ በአንድ ወቅት የተነገረውን ስትሰማ ምን አልክ?…ምነው ቤቲ ላይ በረታህ?… እርግጥ ነው ቤቲ የሰራችው ከአገራችን ባህል ጋር የሚጣረስ ነው!! ይህ አያከራክርም።

የሙስና ምርመራ እየተወሳሰበ ነው!

"መበላላት እንዳይጀመር ስጋት አለ"

sheraton
በጉምሩክና ገቢዎች ባለስልጣን የተጀመረው የጸረ ሙስና ዘመቻ ተከትሎ እየተካሄደ ያለው ምርመራ እየተወሳሰበ መሔዱ ተሰማ። በከፍተኛ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ተከሳሾች የሚሰጡት መረጃ መበላላት ያስነሳል የሚል ፍርሃቻ እያስነሳ ነው። “ሰፈር የለየው” የጸረ ሙስና ዘመቻ የፈጠረው ስጋት የሃይል ሚዛን የያዙትንም ስጋት ውስጥ ከትቷል።

ከአረብ ሃገራት ሰማይ እስከ ሚሊንየም አዳራሽ!

front


እኔን ያሰፈራኝ ጎርበጥባጣው መንገድ . . .  
ኢትዮጵያውያን በግብጽ . . .
ሰሞነኛ የማለዳ ወጌን ወደ እናንተ ላደርስ አንዱን አንስቼ አንዱን ስጥል አንድ ወዳጀ ስልክ ደውሎ በግብጵ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአባይን ግድብ ውዝግብ ተከትሎ አደጋ ላይ መሆናቸውን መረጃ ቢጤ አቀበለኝ ። በማስከተልም ከጥቆማ መረጃው ጋር በቀጣዩ ቀን ነዋሪዎች በነቂስ ሰላማዊ ስልፍ ለማደረግ እንዳቀዱ በመግለጽ እንዳነጋግራቸው መከረኝ ። መረጃ ለመሰብሰብ የሚረዱኝን ወንድሞች አድራሻ የሰጠኝን ወንድም አመስግኜ ወደ ሃገረ ግብጽ ካይሮ ደጋግሜ ደወልኩ። ከብዙ ጥረት በኋላ ግን የፈለግኩትን መረጃ ሙሉ በሙሉ ባላገኝም ያገኘሁትን ሰባስቤ ለተጨማሪ መረጃ የሚረዱኝን ተጨማሪ ስልክ ቁጥሮች ሰባሰብኩ። ያሰባሰብኳቸው መረጃዎች ግን ለኢትዮጵያ መጻኤ ህይወት እንድሰጋ እንድፈራ አድርገውኛልና ፈራሁ! ልቤ እንቢ እያለኝ ጥረቴን ገፋሁበት  . . . “ (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል)

Monday, June 17, 2013

የቢሮ ኃላፊው በሙስና ላይ ምስክር ሳይሆኑ ተገደሉ

“ብዙ ሳይታወቅ የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ”
food


በነበራቸው የስራ ሃላፊነት በድብቅ መረጃ ሲያሰባስቡ ቆይተው ለመንግስት ካጋለጡ በኋላ ራሳቸውን ደብቀው የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኢሬሣ ምሳ እየተመገቡ ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ። አቶ ተስፋዬ ሰኞ ለጸረ ሙስና ኮሚሽን የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት ከኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ቀጠሮ ይዘው ነበር።

የኢትዮጵያን ደስታ የፊፋ ዜና አቀዘቀዘው( Fisseha Tegegn)

_68206993_ethiአዲስ አበባ ላይ የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድንን ያስተናገደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጌታሁን ከበደ እና የደቡብ አፍሪካው የፊታ አጥቂ በርናርድ ፓርከር በራሱ ጎል ላይ ባስቆጠሯቸው ጎሎች 2 ለ 1 አሸንፏል።
የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን በተላይ በመጀመሪያዎቹ 20 እና 25 ደቂቃዎች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመሀል ክፍል ኳሱን እንዳይቆጣጠር ለማድረግ በሚል ተጭኖ የተጫወተ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ሰባት እና ስምንት የደቡብ አፍሪካ ተጨዋቾችን የኢትዮጵያ ቡድን ግማሽ ሜዳ ላይ ማየት የተለመደ ነበር።
ሆኖም የጨዋታውን የመጀመሪያ የጎል ማግባት እድል የፈጠረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሲሆን ሳልሀዲን ሰኢድ በግንባሩ የገጨውን ኳስ የደቡብ አፍሪካው ግብ ጠባቂ ኩኔ አድኖበታል።

Sunday, June 16, 2013

ከፍተኛ የደህንነት ሹም ከስልጣን ተነሱ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

ከኢየሩሳሌም አርአያ

የሕወሐት አባልና የአገር ውስጥ ደህንነት ዋና ሃላፊ አቶ ወልደስላሴ ከስልጣናቸው እንዲነሱ መደረጉን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። ወ/ስላሴ ከስልጣን እንዲነሱ ያደረጉት የደህንነት ዋና ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ መሆናቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል። የሁለቱ ሹማምንት ፀብ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ ቆይቶ መጨረሻ መፈንዳቱ ታውቋል። በመቀሌ በተካሄደው የፓርቲው ጉባኤ አቶ ጌታቸው የፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባል ሆነው እንዳይመረጡ ሰፊ ቅስቀሳ ሲካሂድ የቆየው ወ/ስላሴ በመጨረሻም የአባላት ምርጫ ሲካሄድ ባቀረበው ተቃውሞ ላይ «..ጌታቸው የተሰጠውን የፓርቲና መንግስታዊ ሃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ አይደለም፤ የአልሙዲ ተላላኪና አሽከር ሆኗል… የአላሙዲ አገልጋይ ሆኖዋል… ስለዚህም በማ/ኮሚቴ አባልነት መካተት የለበትም..» ሲል መናገሩን ያወሱት ምንጮቹ፣ የወ/ስላሴ ተቃውሞ ተቀባይነት ባለማግኘቱ አቶ ጌታቸው በማ/ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲቀጥሉ መደረጉን አያይዘው ገልፀዋል።…

Saturday, June 15, 2013

አገር በቤተሰብ ስትዘረፍ ኢህአዴግ የት ነበር?

“አዲስ አበባ የተገተሩት ህንጻዎችስ?”

የሁለት አገር ነዋሪዎች


በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለስልጣናት፣ ባለሃብት፣ ደላሎችና ባለድርጅቶች በልጆቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም “ዘርፈው አስቀመጡት” የተባለው ንብረታቸውና የባንክ ሂሳባቸው መታገዱ ታወቀ። የዜናውን ይፋ መሆን ተከትሎ አዲስ አበባን ያጥለቀለቋት ህንጻዎችና የንግድ ድርጅቶች ጉዳይ ለምን ዝም ተባሉ የሚል ጥያቄ እየተሰነዘረ ነው።

በረከት ስምኦን ማነው??? እውነተኛው በረከት ስምኦን አሁንም በህይወት ፓሪስ ይገኛል።

የበረከት የልጅነት ስም ከእነአባቱ፣ “መብራህቱ ገብረህይወት” ይባላል። ወደ ትግል ከወጣ በሁዋላ ስሙን “በረከት ስምኦን” ሲል ቀየረው። ስሙን ከእነ አባቱ ለምን እንደቀየረው ብዙ ሰዎች አያውቁም። በትግሉ ጊዜ ስምህን እንጂ የአባትህን መቀየር የተለመደ አልነበረም። ለምሳሌ መለስ፣ ስብሃት፣ ስዬ፣ ሳሞራ፣ ሃየሎም፣ ህላዌ፣ የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል። ስማቸውን እንጂ የአባታቸውን ስም አልቀየሩም። ምክንያቱም ስም መለወጥ ያስፈለገው ለቤተሰባቸው ደህንነት ሲባል ብቻ ነበር። የአባት ስም ለመለወጥ ምክንያት አልነበረውም። እንዲያውም ብዙዎቹ ደርግ ከወደቀ በሁዋላ ወደ ልጅነት ስማቸው ተመልሰዋል። በረከት ከእነዚህ ሁሉ ተለይቶ ስሙን ብቻ ሳይሆን የአባቱንም ስም ቀየረ። በዚያውም ፀና።
 የአባትህን ስም ለመቀየር የግድ አንድ ምክንያት መኖር አለበት። ምናልባት አባትህን የምትጠላ ከሆነ፣ ዲቃላ ሆነህ በእንጀራ አባትህ የምትጠራ ከሆነ፣ የመሳሰሉ ምክንያቶች የአባትህን ስም ሊያስቀይሩ ይችላሉ።

የበረከት መፅሃፍ

ከተስፋዬ ገብረአብ
- 1 -

የበረከትን መፅሃፍ አነበብኩት… 

በእውነቱ ህትመቱ ቆንጆ ነበር። ሽፋኑ እንደ ሃብታም ጉንጭ ይለሰልሳል። ከቻርልስ ዲክንስ ታዋቂ መፅሃፍ የተኮረጀ ቢሆንም ርእሱም ቢሆን አሪፍ ነው - የሁለት ምርጫዎች ወግ። የበረከትን መፅሃፍ ያሳተመው መሃመድ አላሙዲ የተባለው ነጋዴ መሆኑን ፍትህ ጋዜጣ ላይ አንብቤ ነበር። መፅሃፉ 314 ገፆች እና 10 ምእራፎች ይዞአል። ዋጋው 90 ብር ነው። 

ሪፖርተር በዜና ዘገባው፣ ሼክ መሃመድ አላሙዲ የበረከት ስምኦንን አዲስ መፅሃፍ ሳያነቡ፣ “መፅሃፉ ለወደፊቱ ትውልድ ጠቃሚ ነው” ሲሉ መናገራቸው እንዳስገረመው ፅፎአል። ምን ችግር አለው? ገንዘብ ወይም ስልጣን ካለህ የሚያዳምጥና የሚስቅልህ አታጣም። “ሃብት ያለው! ልብ አለው!” እንዲሉ። በረከት የመፅሃፉን ርእስ፣ “የሁለት ምርጫዎች ሞት” ቢለው ይሻል እንደነበር አስተያየት የሰጡም አሉ። ይልቁን ይቺን አስተያየት ወድጄያታለሁ።

Friday, June 14, 2013

እነሱ ከአባቶቻቸው አይበልጡም እኛም ከአባቶቻችን አናንስም!!!

292643_197873413697583_587677658_nእነሱ ከአባቶቻቸው አይበልጡም እኛም ከአባቶቻችን አናንስም!
ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ ወረራና ደባ መፈፀም የጀመረችው ኢትዮጵያ ዛሬ በአባይ ላይ ግድብ ለመስራት ከመነሳቷ እጅግ በርካታ አመታት በፊት ጀምሮ ነው፡፡ ሀገራችን ከግብፅም ሆነ ከሌሎች የተቃጣባትን ተደጋጋሚ ወረራዎች በመመከትና ጠላቶቿንም ድባቅ በመምታት ነፃነቷን ጠብቃ መኖሯ ለጠላቶቿ መራር የሆነ እውነት ነው፡፡ በተለይም ከጥንት ጀምሮ የአባይን ምንጭ ለመቆጣጠር ጥልቅ ምኞት የነበራት ግብፅ በሃገራችን ላይ የፈፀመችውን ግልፅና ድብቅ ወረራ በመመከት ተደጋጋሚ ሽንፈትን አከናንበን መልሰናታል፡፡
ሀገራችንን በጦር አውድማዎች ማሸነፍ እንደማትችል በቂ ትምህርት የወሰደችው ግብፅ ከቅርብና ሩቅ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በማበር ዛሬ በኤርትራና በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ የተቀመጡ አማፅያንን በማስታጠቅና ሁለንተናዊ ድጋፍ በመስጠት ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንድትገነጠልና ኢትዮጵያም እንድትዳከም ከፍተኛ ደባ ፈፅማለች ፡፡ ግብፅ ይህን ሁሉ ግልፅ እና ስውር ደባ የምትፈፅመው ኢትዮጵያ በወንዞቿ መጠቀም የማትችል ደካማ ሐገር እንድትሆን ለማድረግ ነው፡፡ ይህ ጥረቷ ግን ደካማ ኢትዮጵያን ለመፍጠር ከመሞከሯ ውጭ የምኞቷን ያህል አልተሳካላትም፡፡

Thursday, June 13, 2013

ኢትዮጲያ የማን ናት?

June 13, 2013

Aden Mesfin, from Norway
ከኤደን መስፍን(ኖረዌይ)
እንደሚታወቀው በአንድ ሃገር የኤኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማህበራዊ ክንውኖች የቀን ተቀን ለውጥ ውስጥ የህብረተሰብ ተሳትፎ(አስተዋጾ) ጉልህ ሚና አለው፡፡ እንዲሁም በሂደትቱ ውስጥ የሚያጋጥሙ አገራዊ ጠቀሜታ ያላቸው ጉዳዮችም ይሁኑ ወይም በተቃራኒው የሚከሰት ተፈጥሯዊም ሆነ በመልካም አስተዳድር ችግር ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮች ከህብረተሰብ  ጫንቃ ላይ አይወርድም፡፡ ይህ ስለሚታወቅ ሃላፊነት  የሚሰማቸው፣ ለሃገርና ለሕዝብ ታማኝ  የሆኑ፣ በሕዝብ  ይሁንታ ስልጣን የያዙ  መንግስታት ያላቸው ሃገሮች በየትኛውም ሃገራዊ እንቅስቃሴ ላይ ሕዝባቸውን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳታፊ በማድረግ በቤሔራዊ ስሜት የታነፀ በሃገሩ ጉዳይ የማያመነታ ህብረተሰብ ይገነባሉ፡፡ የእንደኛ አይነቶቹ የሃገርና የሕዝብ ፍቅር የሌላቸው አምባገነን መሪዎች ግን እንኳን የሃገርህ ጉዳይ ያገባሀል ብለው ሊያሳትፉት ቀርቶ የሕዝብን የመናገርና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ተፈጥሮዊ መብቱን ገፈው ሃገሪቱን የቁም እስር ቤት አርገዋታል፡፡

ይድረስ ለአባይ ባለበት… (ከአቤ ቶኪቻው)

አቤ ቶኪቻው

ጉዳዩ፤ በጣም አበዛኸው…!
Abe Tokichaw's letter to Abbay (Nile) River.
ይቺ ለአባይ የተፃፈች ደብዳቤ ናት፡፡ አፃፃፏ “ስዲ ወ ግጥሚ” አይነት ናት፡፡ ትንፋሽ ያለው ሰው እንደ ግጥም ቢወርዳት ግጥም ግጥም ትመስላለች፡፡ ትንፋሽ የሌለው ሰው ደግሞ እንዲሁ ቢዘልቃት ስድ ንባብ ትሆናለች፡፡ እስቲ እንደዚህ አዳዲስ ፈጣራዎችን እናስተዋውቅ… ብዬ አካብጄ በአዲስ መስመር እጀምራታለሁ ትድላችሁ…!!

Wednesday, June 12, 2013

ጉድ በል ሰላሌ 2

Abe Tokchaw
ልክ እሁድ ነግቶ ሰኞ ሲመጣ አንዲት ማስታወሻ ለዘመዶቼ ከትቤ ነበር፡፡ ማስታወሻዋ ብዙ ምላሾችን አምጥታለች፡፡ በሌላ አባባል ገበያዋ ደርቷል ማለት ነው፡፡ በመጀመሪያ ገበያዋን ያደሯትን ሁሉ ምስጋና ላቀርብ ይገባኛል፡፡ የመከራችሁኝ፣ የተቆጣችሁኝ፣ ያመሰገናችሁኝ፣ እንኳንስ ሌላው ቀርቶ ሙልጭ አድርጋችሁ የሰደባችሁኝ ሁሉ ለኔው ብላችሁ እንደሆነ እረዳለሁ፡፡ እንዲሁም የቤተዘመድ ስድብ ከምርቃት እኩል ነው ባዬ “ገለቶማ” እላለሁ፡፡
በመጀመሪያ ወዳጆቻችን ተቃውሞውን ያሰሙት ለካስ በግብፅ UNHCR ቢሮ ፊት ለፊት ነው፡፡ (በቅንፍም ራሴን እወቅሳለሁ፤ እንዴት ያለሁት ከንቱ ነኝ ባካችሁ… በኢትዮጵ ኤምባሲ ፊት ለፊት ብዬ ያሳሳትኳችሁን በሙሉ ይቅርታ ጠይቃለሁ፡፡) የሰልፉ አላማ ኢትዮጵያውን በአባይ ግድብ ጦስ በግብጻዊያኑ ጥቃት እየደረሰባቸው በመሆኑ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ጥበቃ ሊያደርግልን ይገባል በሚል ነው፡፡ ይሄ በጣም ትክክለኛ ነገር ነው፡፡ እኛም እዚህ ሆነን የምንሰለፍለት ካልሆንልም ግብጽ ድረስ ሄደን የምንሰየፍለት የወገኖቻችን ጉዳይ ነው፡፡

ተጠርጣሪዎች ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የቀረጥ ነፃ ዕቃዎች ተጠቅመዋል ተባሉ

ተጠርጣሪዎች ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የቀረጥ ነፃ ዕቃዎች ተጠቅመዋል ተባሉ

-እነ አቶ መላኩ ፈንታ ወደ ማረሚያ ቤት እንዛወር አሉ
-ከአንድ ተጠርጣሪ 1.3 ሚሊዮን ብር መያዙ ተገለጸ
-ሦስት ተጠርጣሪዎች ሲፈቱ ሁለት አዲስ ተጠርጣሪዎች ታሰሩ 

አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው!!

(ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ)

building


ወያኔን ማስወገድ አይደለም የሚያስቸግረው፤

አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው !!

“We are just leaving barbarism and are still entirely at the beginning. The French, however have already gone a piece of the way and have a century`s lead in every respect.” Friedrich the Great II to Wilhelm of Prussia

Tuesday, June 11, 2013

ዛሬም እዚያው ነሽ ወይ (ሸንቁጤ፤ ከአዲስ አበባ)

Abe Tokchaw
ወዳጃችን ሸንቁጤ ከአዲስ አበባ ይቺን ጨዋታ ከላከልን ሶስት ቀን አለፈው በራሴ ጣጣ አዘገየሁት መዘግየት አልነበረባትም በሉ አሁንም በርዶ ሳይበርድ ፉት አድርጉልኝማ…!
ዛሬም እዚያው ነሽ ወይ
ሸንቁጤየዱሮ ግጥሞች መሰረታቸው የማይነቃነቅ፤ ትርጉማቸው ረቂቅ በመሆናቸው እወዳቸዋለሁ፡፡ለምሣሌ
እዚያው ነሽ ወይ ዛሬም እዚያው ነሽ ወይ
አስሮ የሚቀጣ ዘመድም የለሽ ወይ
ዛሬም እዚያው ነሽ ወይ?
ይህ የተባለላት መግባባት ተስኗቸው ከተለያዩ በኋላ እንቅፋት በመታ፤ አስደንጋጭ ነገር በተሰማ ቁጥር፤ ያንን የተፈታውን ባል ስም በመጥራት ለምትፎክር የተገጠመ ነው ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡እንዲያው በግርድፉ እንተርጉመውም ቢባል የቀረን ነገር ለሚያስታውሱና ባለፈው ላይ ለሚንጠላጠሉ፤ አለያም ተበልቶ ያለቀን እቁብ የሚመኙትን በተመለከተ የተገጠመ ነው ማለት ይቻላል፡፡

አዲስ አበባ ረክሳለች! ለጋ ህጻናትን ለባለስልጣናትና ባለሃብቶች ማቅረብ “ትርፋማ” ሆኗል

ትውልድ አምካኝ ቤቶችን፣ ትውልድ አምካኝ ደላሎችን፣ በህጻናት የወሲብ ንግድ ገንዘብ የሚሰበስቡትን፣ ማጥፋት ቀላል ነው። ግን ተጠቃሚዎቹ ህግ አስከባሪዎቹ፣ ህግ አወጪዎቹና ዋናዎቹ “የአገሪቱ ህዳሴ ባለቤቶች” የሚባሉት በመሆናቸው አይታሰብም። አንዳንድ ዝግ ቤቶች በሲቪል ጠባቂዎች የሚጠበቁ ናቸው። አንዳንዴ ቤተመንግስቱንና ሟቹን የቤተመንግስት ነዋሪ ይጠብቁ የነበሩት በፈረቃ ይታደሙባቸዋል።
ሃኪሞች፣ የህግ ባለሙያዎች፣ አገር የሚመሩት፣ ህግ የሚያስከብሩት፣ የመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች፣ አውራ ባለስልጣናት፣ ህዝብ ፊት ቀርበው በልማት ስም የሚምሉት ሃብታም ተብዬዎች፣ የፖሊስ የበላይ አመራሮች፣ የስለላ አውራ ሰዎች፣ አጫፋሪዎች፣ የአቻ ፓርቲ አመራሮችና መካከል ጥቂት የማይባሉ ከዳር እስከዳር መመሸጊያቸው ዝግ ቤቶች ናቸው። አንዳንዴም ከዝግ ቤቶች ፍራሽ ላይ ሆነው የፖለቲካ መመሪያ የሚሰጥበት አጋጣሚ አለ። ይህን አስደንጋጭ እውነት “መርከስ” ነው። አዲስ አበባ ይፋ አደረገችው እንጂ በየክልሉ ከተሞች የሚደረገው ተመሳሳይ ነው።

የሰማያዊው ፓርቲ ሰልፍ ሰሞኑን አነጋጋሪ ሆኖዋል፤ ገናም አነጋጋሪነቱም ይቀጥላል )ሰላማዊ ሰልፍን አስመልክቶ ዶ/ር መራራ ጉዲና ቆይ ለእኛ እንቢ የተባለው ሰልፍ እንዴት ለእነርሱተፈቀደ?

merera_gudinaየሰማያዊው ፓርቲ ሰልፍ ሰሞኑን አነጋጋሪ ሆኖዋል፤ ገናም አነጋጋሪነቱም ይቀጥላል። መድረክን በተለይም ደግሞ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ እና ዶ/ር መራራ ጉዲና የሰጡትን አስተያየት በተመለከተ የምጽፈውን ነገር አሰበኩኝ እና ብዕሬ ልተፋብኝ የምትችውን የቃላት ውርጅብኝ በመፍራት ላልፋቸው ወደድኩኝ…. ቢያንስ እነዚህ ሰዎች ስለእኔ እና ስለራሳቸው ሲሉ ደክመዋል እና እግዚአብሔር ድካማችሁን ይቁጠርላችሁ፣ በቁማችሁ ኢትዮጵያ ነጻ ወጥታ ለማየት ያድላችሁ በማለት ለመመረቅ እወዳለሁኝ። ደግሞ በተለያዮ ጊዜአት የሚያነሱዋቸውን አተያየት በተመለከተ ሰምቶ እንዳልሰማ ቅር ተሰኝቶ ቅር እንዳልተሰኘ በመሆን ዝም ብሎ ማለፉንም አልወደድኩትምና የማደርገውን አሰብኩኝ ለጥቂት ጊዜም….ምን ላድርግ ይሆን? በማለት እያሰብኩ…እያወረድኩኝ… እያጠነጠንኩኝ ሳለ በአንድ ወቅት በአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ተማሪ እያለሁኝ ዶ/ር መራራ ጉዲና ስለ ግል ሕይወታቸው ፣ ስለ ቤተሰባቸው እና ስለ አጠቃላይ ስለ መላው እምነታቸው ከተወሰንን የዮኒቨርስቲው ተማሪዎች ጋር በመሆን አዘውትረው መኪናቸውን ከሚያቆሙበት ስፍራ ሄደን የተለያዮ ጥያቄዎችን ጠይቀናቸው…. ዶ/ር መራራ ግልጽ እና ተግባቢ ሰውን አቅራቢ የሆኑ ሰው ናቸው እናም በወቅቱ ለጥያቄዎቻችን ሁሉ ያገኘነውን ምላሽ አልረሳውም….. አንዳንዱ ምላሻቸው በተለይ ቤተሰብን፣ ትዳር እና ልጆችን በተመለከተ የዶ/ር መራራ መስዋዕትነት ትልቅ መሆኑን አስገንዝቦኝ ነበረና ነው። ምንም እንኳን አሁን ሰማያዊዎቹን በተመለከተ የሰጣችሁት አተያየት ባልስማማም እናንትን ከልቤ ማክበሬን በመግለጽ ወደ ፍሬ ነገሬ ወይ ወደ ፍሬ ከርስኪዮ ልግባ ( በቅንፍ ለእኔ ፍሬ ነገር የሆነው ለሌላው ፍሬ ከርስኪ ቢሆንስ ብዮ ነው)።

Monday, June 10, 2013

አንድ ብስጭት፤ ጉድ በል ሰላሌ ኢትዮጵያ አይደለህም ተባልክ…

946655_4270475898383_1063122582_n
ABE  TOKCHAW

አበበ ቶላ ፈይሳ እባላለሁ፡፡ አባቴ አቶ ቶላ ፈይሳ ልጅነቱን በኦሮምኛ ቋንቋ ተረት እየሰማ፤ ወጣትነቱን በኦሮምኛ ቋንቋ እያዜመ፤ ጉልምስናውን በኦሮምኛ እየፎከረ፤ እርጅናውን በኦሮምኛ እየመከረ የኖረ ኢትዮጵያዊ ነበር፡፡ አባቴ የአባት እና እናቱ ቋንቋ ኦሮምኛን አጥብቆ እንደሚወደው ያህል እኔ ልጁን እና እናት ሀገሩ ኢትዮጵያንም ከመውደድ በላይ ይወደናል፡፡
ጣሊያን ሀገራችንን ሊወር የመጣ ጊዜ እርሱ የአስራ ሶስት አመት ልጅ ነበር፡፡ በዛን ጊዜ አባቱ እና በርካታ ጓደኞቻቸው በሰላሌ ጫካ መሽገው ነበር፡፡ አባቴ እና በርካታ ጓደኞቹ ደግሞ ልጅነታቸውን ተጠቅመው ቀን ከብቶች ሲጠብቁ እግረ መንገዳቸውን ጣሊያንን እየሰለሉ ሌሊት ለአባቶቻቸው ጣሊያን በዚህ ገባ በዚህ ወጣ የሚል ወሬ ያቀብሉ ነበር፡፡
ይህ በአንድ አንቀጽ ሲነገር ቀላል ይምሰል እንጂ በውስጡ ብዙ ፈተናዎች ብዙ መከራዎች ነበሩት፡፡ ግን ለሀገር የተከፈለ ነበርና እረኛው አባቴም አርበኛው አያቴም መላው ቤተሰቡም በእልህ እና በወኔ ነበር የሚያደርጉት፡፡ በወቅቱ ይህ ከዳር ዳር ሁሉም ኢትዮጵያውያን ያደርጉት የነበረ የተባበረ ተጋድሎ እንደሆነ አባቴም ነግሮኛል መፅሀፍ ላይም ተፅፏል፡፡

Sunday, June 9, 2013

አርዐያ ተስፋማርያም፣ ሰሜናዊው ኮከብ

ቴድሮስ ሃይሌ (tadyha@gmail.com)

Ethiopian Journalist Araya Tesfamariam
ጋዜጠኛ አርአያ ተስፋማርያም
አርዐያን የማውቀው በሃገራችን ይታተሙ ከነበሩት ነጻ ጋዜጦች በሲሳይ አጌና ባለቤትነት ይተዳደር በነበረው ስመ ጥሩው ኢትዮጽ ጋዜጣ ላይ በተመስጦ እከታተለው ከነበረው የጋዜጣው አምዶች ውስጥ ከህወሐት መንደር በሚል አብይ ርዕስ ስር በተከታታይ ይቀርብ የነበረው የወያኔን ገበና ገላጭ ጽሑፍ እየሩሳሌም አርዐያ በሚል የብዕር ስም ይጽፍ የነበረው ብርቱው ጋዜጠኛ አርዐያ ተስፋማርያም ምንም ቅርርብ ኖሮን ባያውቅም የጽሁፉ እድምተኛ በመሆን ብዙ ቁም ነገር የቀሰምኩበት በመሆኑ በቅርብ የማውቀው ያህል የሚሰማኝ ከመሆኑም በላይ የደረሰበት ግፍና በደል ከእርሱ አልፎ ቤተሰቡን ጭምር ችግር ላይ መጣሉን ስከታተለው የነበረ ሲሆን እንዲህ አይነቱን በዚህ በኔ ትውልድ ውስጥ በብርሃን ተፈልጎ የማይገኙ ጥቂቶች ብቻ ጥቅምና ምቾትን ንቀው መስሎ በማደርና ሕሊናን በመሸጥ ከሚገኝ የተደላደለ ህይወት ትቶ ላመነበትና አላማ ጸንቶ ለተሰለፈበት ሙያ ተግቶ በቆራጥነት የሚቆም ዜጋ ተምሳሌትነቱ ለትውልድ ጠቃሚ በመሆኑ አንድ ነገር ለማለት ሳመነታ ሰሞኑን በአጋጣሚ ይህን ጎበዝ ጋዜጠኛ የተመለከተ ስብሰባ መኖሩን ስመለከት ሳስበው የቆየሁትን ለመተንፈስ አጋጣሚው መልካም ከመሆኑም በላይ የዝግጅቱ ማስታወቂያ ላይም ያለኝን ቅሬታ ለወገን ለማካፈል ፈለግሁ።

ኢህአዴግ ጣና በለስን ለምን አፈራረሰው?

"በሩ ይከፈት፣ በአባይ ጉዳይ አገራዊ አቋም እንያዝ"

BELES inlet


በግብጽ ረዳትነት፣ በሱዳን መሪነት መንግስት ለመሆን የበቃው ህወሃት/ኢህአዴግ ግዙፉን የጣና በለስ ፕሮጀክትና ንብረቱ እንዲዘረፍ ያደረገበትን ምክንያት በማንሳት መከራከር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ። የግብጽ ፕሬዚዳንት ሙርሲ እንዳደረጉት በአገር ጉዳይ ሁሉንም ያሳተፈ ግልጽ አቋም እንዲያዝና አጋጣሚውን በመጠቀም ብሔራዊ ህብረት እንዲፈጠር ኢህአዴግ በሩን ሊከፍት እንደሚገባ ተገለጸ።

Thursday, June 6, 2013

ወያኔ የፈጠረዉ የፍርሀት ድባብ ሲሰበር . . .


በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚደርሰዉ በደልና መከራ ወለደን ብለዉ ለትግል ጫካ የገቡት ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች አዲስ አበባ ገብተዉ ከተደላደሉ በኋላ በህዝብ መብትና ነጻነት፤ በአገር አንድነትና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ብሄራዊ ጥቆሞች ላይ ይህ ነዉ ተብሎ ሊነገር የማይችልና ከእነሱ በፊት ከነበሩት መንግስታት ጋር ሲተያይ እጅግ በጣም የከፋ በደል ፈጽመዋል እየፈጸሙም ይገኛሉ። ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች አዲስ አበባ ገብተዉ የኢትዮጵያን መንበረ ስልጣን ከመቆጣጠራቸዉ በፊት ዕቅድ አዉጥተዉና ተዘጋጅተዉ የመጡት የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር፤ በሐይማኖትና በክልል በመከፋፈል በጠመንጃ ኃይል የያዙት ስልጣን በግዜና በህገመንግስት ያልተገደበ መሆኑን ለማረጋገጥና የእኛ ነዉ ለሚሉት የህብረሰተብ ክፍልና ለሚተባበሯቸዉ ሆዳሞች ተቆጥሮ የማያልቅ ሀብት ማጋበስ የሚችሉበትን መንገድ ለመፍጠር ነዉ። የወያኔ መሪዎች ይህንን አገራዊ በደል ያለምንም ተቃዉሞ መፈጸም እንዲችሉ ከአገሩ ይልቅ የተወለደበትን ክልል ብቻ፤ ከብሔራዊ አንድነቱና አጋራዊ ጥቅሙ ይልቅ የራሱን ጥቅም ብቻ የሚመለከትና የእነሱን ኃይለኝነትና የተለየ ጀግንነት እየሰበከ የሚኖር በፍርሀት የተሸበበ ፈሪ ትዉልድ ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።
የወያኔ ክፋት፤ ዘረኝነትና “ልማት” በሚል ሽፋን የተደበቀ አገር የማፍረስ ሴራ ከወዲሁ የገባቸዉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ልጆች ከ1997ቱ ምርጫ በፊትም ሆነ በኋላ የወያኔን ገመና ለማጋለጥና የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱ፤ ለነጻነቱና ለእኩልነቱ እንዲታገል ለማድረግ እንደሻማ እየቀለጡ ብርሀን ሆነዉ አልፈዋል።

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም በአባይ ጉዳይ ላይ

ዛሬ ደግሞ…

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም
Prof. Mesfin Woldemariam
ጦርነት እንኳን ገና በልቶ ላልጠገበ ሕዝብና ለጥጋበኞቹም አይመችም፤ የተራበ ሕዝብ በጠገቡ መሪዎች ሲነዳ ግን ጦርነት ለአጉል ጀብደኛነት ዝና የሚጠቅም መስሎ ይታያቸዋል፤ ከኤርትራ ጋር ጦርነት ለመግጠም በሚያሰፈስፉበት ጊዜ በርቱ እያሉ የሚያቅራሩ ሞልተው ነበር፤ ዛሬ አቀራሪዎቹም ሆኑ ጀብደኖቹ በኤርትራ ጦርነት ያለቀባሪ ስለቀሩት ሰዎች፣ ጠዋሪ ስላጡ እናቶችና አባቶች፣ አሳዳጊ ስለሌላቸው ልጆችና አካለ-ጎደሎ ለሆኑት የሚያስብላቸው አለ ወይ? የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት መነሣትና በኢጣልያ የግራዚያኒ ሐውልት እንዳይሠራ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ከልክሎ ለሰልፍ የወጡትን አስሮ ያሳደረ አገዛዝ ለአገራቸው ለሞቱት ኢትዮጵያውያን የሚሰጠውን ዋጋ በመጠኑም ቢሆን ያሳያል፤ ስለዚህም ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ሲወዱ ራሳቸው በልጽገው ለልጆቻቸው ብልጽግናን እንዲያወርሱ ሕይወታቸውን ቢጠብቁ ለአገራቸውም ክብር ይሆናሉ፡፡

“ይህ መንግሥት አይመጥነንም” የ“ምርቃና” መግለጫ ለኢህአዴግ ድንጋጤ

shemelis2-

ሰሞኑን ኢትዮጵያ የዓለም መገናኛ አጀንዳ ሆናለች። ለዘመናት እጇን ኢትዮጵያ ላይ ተክላ የኖረችው ግብጽ የምትዝተው ዛቻና፣ በቅርቡ ተቋቁሞ ታላቅ ታሪክ በማስመዝገቡ የተረጋገጠለት ሰማያዊ ፓርቲ ያዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ አጀንዳዎቹ ናቸው።

በሰላማዊ ሠልፉ ሰማያዊ ፓርቲና መንግሥት እየተወዛገቡ ነው

selfegnoch


ሰማያዊ ፓርቲ ከአንድ ወር በፊት በጠራውና ባለፈው እሑድ የተደረገውን ሰላማዊ ሠልፍ መንግሥት ሲያወግዝ፣ ሰላማዊ ፓርቲ ደግሞ የመንግሥት ውግዘት በተቃውሞ የተነሳውን ሕዝብ ከማሸማቀቅ ባለፈ የሕግ ድጋፍ እንደሌለው እየገለጸ ነው፡፡

በወይዘሮ አዜብ መስፍን ላይ ምርመራ እንዲደርግ ግፊቱ ጨምራል

ግፊቱ ጨምሯል!!አዜብ መስፍን የሙስና ንግስት ጉድ ፈላባት ዘንድሮ
እነመላኩ ፋንታን ተከትሎ በአዜብ መስፍን ላይ የሚቀርቡ የሙስና አቤቱታዎች ጨምረዋል::
የሙስና ኮሚሽን በአቶ ገብረዋህድ ቤት ባደረገው ፍተሻ እንዲሁም ከኣሁን ቀደም በመርማሪ ደህንነቶች ክትትል በተደረገ የስልክ ጠለፋ የቀድሞ ሟች ጠ/ሚ ባለቤት እና በአለም ትልቁ የሙስና አባት ኤፈርት ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ አዜብ መስፍን ከአቶ ገብረዋህድ ባለቤት እና እህት ጋር በከፍተኛ ደረጃ የቢዝነስ ስራ ይሰሩ እንደነበር እና ከታሰሩት ባለስልጣናት እና ባለሃብቶች ጋር የንግድ አጋርነት እንዳላት አረጋግጧል::ይህንን የሚጠቁሙ ሰነዶች እና ከተለያዩ ወገኖች የሚቀርቡ ጥቆማዎች እና አቤቱታዎች ምርመራው ወደ አዜብ መስፍን አምርቶ ለጥያቄ እንደምትፈለግ ፍንጭ እየሰጠ ነው ሲሉ የሙስና ኮሚጽሽን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::

Wednesday, June 5, 2013

. ህወሓቶች ሙስና ላለማጋለጥ ወሰኑ …(Abraha Desta)

ባለፈው ከግብር ከፋዮች የተሰበሰበ ገንዘብ ዘርፈው ለማምለጥ ሲሞክሩ የተያዙ የገቢዎች ባለስልጣናት ምክንያት አድርገን ስለ ህወሓት/ኢህኣዴግና የሙስና መሰረቱ ተወያይተን ነበር።
ህወሓት/ኢህኣዴግ በሙስና የተገነባ ድርጅት መሆኑ፣ አሁን አሁን ሙስና ለድርጅቱ አደጋ መደቀኑ፣ ሙስና ካላስወገደ ዕድሜው አጭር እንደሚሆን፣ ኢህኣዴግ ዕድሜው ለማራዘም ሙስና መዋጋት እንዳለበት፣ ሙስና ከተዋጋ ደግሞ ከራሱ ድርጅት ጋር ግብግብ እንደሚገጥም፣ በመጨረሻም ሙስና ለማስወገድ የሙስና ምንጭ መድረቅ እንዳለበት፣ የሙስናው ምንጭ ደግሞ ህወሓት/ኢህኣዴግ መሆኑና፣ ሙስና ለማጥፋት ኢህኣዴግ ማጥፋት እንደሚያስፈልግ፣ ኢህኣዴግ ራሱ ሙስናን ለመታገል ቆርጦ ከተነሳ ግን ራስ በራስ ማጥፋት እንደሚሆን፣ ይህን ራስ የማጥፋት ስራ ደግሞ ከባድ መሆኑ ጠቅሰን ነበር።

በጦርነቱ ሰበብ በተዘረፈ ሐብት የሕወሃት ጄነራሎች ሚሊየነር ሆነዋል፡፡

“ማን ያውራ የነበረ…….ማን ያርዳ የቀበረ……”
“….የጦር መኮንን ሆነህ እንደባለሙያ ስታየው ውጊያው በጥቅሉ የሙያ ብቃት ያልታየበት አሳፋሪ ጦርነት ነበር ማለት ይቻላል፡፡በጃንሆይ እና በደርግ ዘመን ኤርትራ ላይ ውጊያ ተደርጎ የተሰዋው ዜጋችን ቁጥር ከ250 ሺ እስከ 300 ሺ ይደርሳል፡ከዚህ አንፃር ወያኔ በአንድ ዓመት ውስጥ ኤርትራ ላይ ያስፈጀው የወታደር ቁጥር በጣም አሳፋሪ ነው፡፡ከመከላከያ የሰው ኃይል አስተዳደርና ልማት መምሪያ ሰነዶች ያገኘሁት መረጃ እንደሚያሳየው በጠቅላላ በኢትዮ ኤርትራ ውጊያ 98,700 ወታደር ሲሞትብን 194¸300 ቁስለኛ ተረክበናል፡፡ ከኦርዲናንስ እዝ ያገኘሁት መረጃ ደግሞ መጀመሪያ ለውጊያ ከተዘጋጀው ከባድ መሳሪያ 2ሐ3ኛው መውደሙን ነግረውኛል፡፡ ይህንን ትርጉም አልባጦርነት የመሩት መሪዎች ሰዓረ መኮንን፣ ሳሞራ የኑስ፣ዮሀንስ ገብረመስቀል፣ታደሰ ወረደ፣ኳርተር /አብርሃ ወልደማርያም/፣ ብርሃነ ነጋሽ የተባሉት ጄነራሎች ናቸው፡፡

አገዛዙ ለሰላማዊ ሰልፉ ዕውቅና የሰጠው ፈጽሞ አማራጭ ስላልነበረው ነው – በእኔ አመለካከት!

ክብሩ ደመቀ

ECADF Statment regarding Addis Ababa's demonstration
ሕወሓት/ኢህአዴግ በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት የተካሄደውን ሰላማዊ ዕውቅና የሰጠው ወድዶና ፈቅዶ ወይም ሕገ-መንግሥቱ አጣብቂኝ ውስጥ ከትቶት አልነበረም። ይልቅስ አጣብቂኝ ውስጥ የከተቱት ሁለት ነገሮች ናቸው ፡-
1ኛ – ወቅታዊነት! በወቅቱ የሚካሄደውን ርዕሰ-ሃገራትና ከፍተኛ የዓለም ባለሥልጣናት (እንደ ጆን ኬሪ እና ባንኪ ሙን) በተገኙበት እንዲሁም በዓለም መገናኛ ብዙሃን እየተዘገበ በሚካሄደው የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት ጉባዔ ላይ ሰማያዊ ፓርቲ ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ዕውቅና መጠየቁ፣

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም በአባይ ጉዳይ ላይ

ዛሬ ደግሞ…

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም
Prof. Mesfin Woldemariamጦርነት እንኳን ገና በልቶ ላልጠገበ ሕዝብና ለጥጋበኞቹም አይመችም፤ የተራበ ሕዝብ በጠገቡ መሪዎች ሲነዳ ግን ጦርነት ለአጉል ጀብደኛነት ዝና የሚጠቅም መስሎ ይታያቸዋል፤ ከኤርትራ ጋር ጦርነት ለመግጠም በሚያሰፈስፉበት ጊዜ በርቱ እያሉ የሚያቅራሩ ሞልተው ነበር፤ ዛሬ አቀራሪዎቹም ሆኑ ጀብደኖቹ በኤርትራ ጦርነት ያለቀባሪ ስለቀሩት ሰዎች፣ ጠዋሪ ስላጡ እናቶችና አባቶች፣ አሳዳጊ ስለሌላቸው ልጆችና አካለ-ጎደሎ ለሆኑት የሚያስብላቸው አለ ወይ? የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት መነሣትና በኢጣልያ የግራዚያኒ ሐውልት እንዳይሠራ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ከልክሎ ለሰልፍ የወጡትን አስሮ ያሳደረ አገዛዝ ለአገራቸው ለሞቱት ኢትዮጵያውያን የሚሰጠውን ዋጋ በመጠኑም ቢሆን ያሳያል፤ ስለዚህም ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ሲወዱ ራሳቸው በልጽገው ለልጆቻቸው ብልጽግናን እንዲያወርሱ ሕይወታቸውን ቢጠብቁ ለአገራቸውም ክብር ይሆናሉ፡፡

የፍርሃቱ ኢያሪኮ ተደረመሰ

ይኸነው አንተሁነኝ

ሰኔ 5 2013
Protest rally against Ethiopian government in Addis Ababa
የሚሆን የማይመስለው ሆነ፤ ልቦች በአንድነት ዘመሩ፤ የደስታ እንባ ፈሰሰ፤ አእዋፍ በደስታ አብረው እስኪቀዝፉ ድረስ የነጻነት ድምጽ የነጻነት ጩኸት አየሩን ሞላው፤ የሕዝብ አሸናፊነት በግልጽ ገኖ ታየ፤ የታፈነው የድምጽ ማእበል ግድቡን ትሶ ወጣ፤ የምን እንደረግ ይሆን ጭንቀት እትትም ተደረመሰ፤ ምድር የጠበበች እስኪመስል ሽዎች በነጻነት ፈሰሱባት፤ በእውነት 1997ን በ2005 አየነው።

የግንቦት 25ቱን አገራዊ ሰልፍ ተከትሎ መንግስት ያንጸባረቀውን ሴራ ተኮር አቋም አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ!

ግንቦት 27/2005
ድምፃችን ይሰማ
ባሳለፍነው እሁድ አገሪቱ ውስጥ እየተካሄዱ ያሉ ከፍተኛ የመብት ጥሰት ወንጀሎችን ለመቃወም በሰማያዊ ፓርቲ የተጠራ የተቃውሞ ሰልፍ ስነስርአት መካሄዱ977861_10200726226811999_641498735_o ይታወሳል። የተቃውሞ ሰልፉ አጀንዳ አድርጎ ካቀረባቸው ጥያቄዎች መካከል መንግስት በሀይማኖት ላይ በጣልቃ ገብነት እየፈጸመ ያለውን ኢ-ህገ መንግስታዊ በደል እንዲያቆም የሚጠይቅና የታሰሩ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትም እንዲፈቱ የሚተይቅም እንደነበር ይታወሳል። በሰልፉ ላይም ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ልክ እንደሌላ ሀይማኖት ተከታይ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ሁሉ ተሳትፎ ያደረጉና የጋራ ድምጻቸውን ያሰሙ መሆኑን ከሰልፉ ስነስርዓት መረዳት ተችሏል፡፡ ምንም እንኳን የዚህ መግለጫ አላማ ሰልፉን አስመልክቶ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ መስጠት ባይሆንም ሰልፉን ተከትሎ ከመንግስታዊ አካላት የተሰጡ ፈር የለቀቁና በሴራ የተሞሉ ግብረ መልሶችን አስመልክቶ ግን መሰረታዊ የመነሻ ነጥቦችን ማስቀመጥ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።

Tuesday, June 4, 2013

ኢትዮጵያ ተነስታለች ! (ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም)

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
The long youth march to freedom and dignity has begun in Ethiopia. It is beautiful.
እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ግንቦት 20 1983 መለስ ዜናዊና ሽምቅ ተዋጊዎቹ ከላሽኒኮቭ ደግነው የጅ ቦንቦች ታጥቀው አዲስ አበባን ወረው ገቡባት፡፡

የሰሞኑ የአባይ ግርግር

እስከ ነጻነት

ሰሞኑን በማህበራዊ መገናኛዎችና የውጭ ዜና አውታሮች ጭምር ስለ አባይ ግድብ ብዙ ሲሉ ይሰማል፡  ለምን? ለምን አሁን? ምን የተለየ ነገር ተገኘ?
በመሰረቱ አባይ መገደብና ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ የመጠቀም መብትም ግዴታም አለባት፡ እዚህ ላይ ማንም ጥያቄ ያለው አይመስለኝም፡ ጥያቄ የሚነሳው ግን በርግጥ የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር የሚመራው ብድን አባይን አገድባለሁ የሚለው ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም ነው ወይ? ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መክሮና ተስማምቶ ነው ወይ? ግድቡስ ለግርጌ ተፋሰስ አገሮች ጉዳት ያመጣል ወይ የሚሉት ጥያቆዎች መመለስ አለባቸው።
ስለ አባይ ጉዳይ ዝርዝር ከመግባቴ በፊት ወያኔ ለምን በተለያየ ዘዴ ስለ አባይ እንዲነሳ ፈለገ? ግብጽስ አሁን ሰለጉዳዩ ለምን አጀንዳ አረገችው? ወዴትስ ሊያመራ ይችላል? የሚሉትን ከወያኔ ምግባርና ጸባይ ተነስቼ ያለኝን አስተያየት አጠር አርጌ ላቅርብ፡

Thousands march for rights in rare Ethiopia protest

Thousands march for rights in Ethiopia
(Reuters) – About 10,000 Ethiopians staged an anti-government procession on Sunday in the first large-scale protest since a disputed 2005 election ended in street violence that killed 200 people.

Monday, June 3, 2013

የኢትዮጵያውያን የ15ኛው ክፍለ ዘመን ገዳማት በሊባኖስ ተገኙ

• በዋሻው የተገኙት የግእዝ ጽሑፍና ሥዕሎች ማረጋገጫ ሆነዋልየኢትዮጵያውያን የ15ኛው ክፍለ ዘመን ገዳማት በሊባኖስ ተገኙ
ኢትዮጵያውያን መነኮሳት በ15ኛው ክፍለ ዘመን በሊባኖስ ቀዲሻ ሸለቆ (Holy Valley) ይገለገሉባቸው የነበሩ አራት ገዳማት ከግእዝ ጽሑፍና ሥዕሎች ጋር ተገኙ፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሰሜን ጎንደር ሉግዲ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ።

4444444
የወያኔው አምባገነናንዊ ስርዓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የጫነውን የግፍና የመከራ እንዲሁም የችግርና የሰቆቃ ዘመን ለማሳጠር ስርዓቱን በግንባር እየተፋለመ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በግንቦት 24-2005 ዓ.ም ሉግዲ በተባለው አካባቢ ከወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ጋር ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት በተካሄደው ውጊያ 44 የጠላት ወታደሮችን በመግደልና 66 በማቁሰል እንዲሁም ብዛት ያላቸው ተተኳሽ መሳሪያዎችን ከነሙሉ ትጥቃቸው በመማረክ አኩሪ የአርበኝነት ጀብድ ፈፅሟል።

ምርመራው ወደ አቃብያነህጉ ተዛወረ!

የሙስናው “ሻርኮች” በዒላማ ውስጥ?

berhane


* “አዲስ ነገር የለም” ጸረ ሙስና ኮሚሽን
በተለያዩ ከፍተኛ ወንጀሎች በተጠረጠሩ ሰዎች ላይ የተከፈቱ ክሶችን በማፈንና በመመሪያ ፍትህ በማዛባትና በማቋረጥ ወንጀል የተጠረጠሩ አቃቤያነህግ ላይ ምርመራ መጀመሩ ከፍተኛ ድንጋጤ መፍጠሩ ተሰማ። በተለይም ከወንጀል ጋር ቁርኝት እንዳላቸው በህዝብ የሚታወቁ ክፍሎች ክፉኛ መደናገጣቸው ተሰምቷል።

ከእሁድ እስከ እሁድ

(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)

skypeከእስረኞች ጠበቆች ጋር የተደረገው ውይይት ታፈነ
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ከአሜሪካ የህግ ባለሙያዎች ማህበር ጋር በመሆን  በኢትዮጵያ እስር ቤት ለሚገኙ የህሊናና የፖለቲካ አስረኞች ጥብቅና ከቆሙ የህግ ባለሙያዎች ጋር ለመነጋገር ያደረገው ሙከራ ታፈነ። የጋራ ንቅናቄው ለጎልጉል እንዳስታወቀው ዓርብ ሰባት ከሚሆኑ ጠበቆች ጋር ለመያየትና መረጃ ለመለዋወጥ መስመር ተዘርግቶ ነበር።

በህዝብ አቆጣጠር አሁን ጨዋታው ተጀመረ!

ወደ "ሻርኮቹ" ይቀጥል!! (ርዕሰአንቀጽ)

shark


ሙስናው ላይ የተጀመረው ዘመቻ ሙስናን በስንጥር የሚያሰኝ ቢሆንም አቶ መለስ ያልደፈሩትን ሰፈር አቶ ሃይለማርያም ነክተውታልና በኢህአዴግ ታሪክ የሙስናን ሰፈር በማንኳኳት ግንባር ቀደሙ ሰው ያደርጋቸዋል። እኛም ጅምሩ መልካም ነው እንላለን። ግን ጥያቄም ማሳሰቢያም አለን። ለማንኛውም በህዝብ አቆጣጠር አሁን ጨዋታው የተጀመረ ይመስለናል።

እኛ ያልነው ለፉገራ…

እኛ ያልነው ለፉገራ…

(ክንፉ አሰፋ)
abay Dam


በሰሞኑ ቀልድ ልጀምር። የአፈሪካ ህብረት ድርጅት 50ኛ አመቱን በያዝነው ሳምንት በአዲስ አበባ ሲያከብር በነበረው የሻምፓኝ ስነ-ስርዓት ላይ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ብቻ ከመሪዎቹ ተነጥለው ያለ ብርጭቆ  ቆመዋል። ለፕሮቶኮል እንዲመሳሰሉ ቢጠየቁ አሻፈረኝ አሉ። የህብረቱ የወቅቱ ሊቀመንበር ስለነበሩ ለይሰሙላ እንኳን ብርጭቆዋን ጨብጡ ቢባሉ አይሆንም፣ ሃይማኖቴ አይፈቅድም አሉ።  በመጨረሻ ግን በረከት ስምዖን በጆሯቸው አንዳች ነገር ነገራቸውና የያዘውን ብርጭቆ ሲሰጣቸው ተቀብለው በደስታ ጨለጡት።

Saturday, June 1, 2013

ዓባይና የመለስ ዜናዊ (ወያኔ) ታላቁ ሴራ

በከፋለ

ሰሞኑን የአለምንና የኢትጵያውያንን ሀሳብና አስተየት ለመለዎጥ ወይም ለማሳሳት ወያኔ በወኪሎቹ አማካይነት የተለመደዉን ፕሮፓጋንዳ ሲነዛ ከርሞአል። ዓባይ እንደሚጠቅመን ሆኖ ቢገደብልን እጂግ ደስ ይለን ነበር። የወያኔ ትግሬዎች ሰለአባይ ከባለቤቱ ከኢትጵይያ ህዝብ በላይ የሚያቀነቅኑበት የሚጮሁበትና ሚያስመስሉበት ምክንያቱ ሌላ ነው። እነሱ ሃገር ወዳድ ሌሎች ኢትዮጵዉያን ሀገራቸዉ ብታድግና ብትጠቀም የሚጠሉ ሆነው አይደለም።
የኢትዮጵያም ህዝብ ይህንን በደንብ ያዉቀዋል። ከእባብ እንቁላል እርግብ ኣልጠብቅም ብሎአቸዋ። ታዲያ ይኸ ሁሉ የአዞ እንባ ማፍሰስና የኢትዮጵያን ሀዝብ ጩኸት ለመቀማት የመሞከር ሚስጥሩ ምንድነው??? ወያኔ ኢትዮጵያን ለመጉዳትና ለረጂም ጊዜ እችግር ዉስጥ ለማስገባት ካስጠናቸዉ ትልልቅ ጉዳዮች (ፕሮጀችቶች) ኣንደኛዉና ዋናው የአባይ ግድብ ነው። ለዚህም ማስረጃ የሚከተሉትን ነጥቦች ተመልከቱ:

ሰበር ዜና፣ በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት አካባቢ ዝግጅቱ ተጧጡፏል

ዘሬ ጠዋት ላይ ሁኔታውን ለመከታተል ወደ ሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያመራው በቅጽል ስሙ “ማጀስቲ” የተባለው ወጣት በተመለከተው እንቅስቃሴ እጅግ ተደስቷል።

በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ከ5 በላይ መኪናዎች ቆመዋል፣ ድንኳን ቢጤም ተጥሏል፣ በራሪ ወረቀቶችን እና ሌሎችም ለሰላማዊ ሰልፉ ግብአት የሚሆኑ ቁሳቁሶች የያዙ ወጣቶች ገባ ወጣ ይላሉ። የወጣቶች ተሳትፎ የሚያስደንቅ ነው። የጸሀዬ ዮሀንስ ቀስቃሽ ዘፈን ጎላ ብሎ ይሰማል።
ሰዎች ወደ ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት እየጎረፉ ነው፣ ምን እናግዝ ምን እንስራ ይላሉ።
ይህ በዚህ እንዳለ ወጣቱ ቅሬታውንም አልሸሸገም፣
ቀደም ሲል የመኢህአድና አንድነት ፓርቲ ሰልፉን እንደሚደግፉና በቅስቀሳውም እንደሚተባበሩ አሳውቀው የነበረ ሲሆን እያደረጉ ያሉት ተሳትፎ ግን እምብዛም አልታየም ብሏል።

የውሃ-ፖለቲካ እና የአባይ ጉዳዮች፡ ወፍ በረር ቅኝት

እንደ መነሻ
ባለቅኔ እና ጸሐፌ-ተውኔት ጸጋዮ ገብረመድህን ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ ባሳተመው የግጥም ካሴት አዋሽ ለሚለው ግጥሙ መግቢያ ማብራሪያ ሲሰጥ… “በማናቸውም የዓለም ህዝብ ባህል ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ የየአገሩ ወንዝ ጉዞ በተለይ የታላላቅ ወንዞች ጉዞ፤ የየአገሩ የሰፊው ህዝብ ጉዞ፤ የየትውልዱ ጉዞ ተምሳሌት ሆኖ ይቀረፃል፡፡” ይለናል፡፡ በርግጥየእያንዳንዱ ሀገር ወንዝ የእያንዳንዱን ህዝብ ጉዞ ታሪክ ይናገራል፡፡ እውነት ነው ከዶን በራይን እና በቴምስ እስከ ዳኑብ በአውሮጳ፣ ከዮርዳስ እስከ ኤፍራጠስ እና ጢግሮስ በመካከለኛው ምስራቅ፣ ከኮሎራዶ እስከ ሚሲሲፒ በሰሜን አሜሪካ፣ አማዞን በደቡብ አሜሪካ፣ ኢንደስ-ጋንጅስ በህንድ፣ ፓኪስታንና ባንግላዴሽ፣ ያንገቲዝ በቻይና፣ እንዲሁም ጉዳያችን የሆነው አባይ በአፍሪካ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ እነዚህ ወንዞች የሚያልፉባቸውን የሚያገናኟቸውን ህዝቦች እና ሀገሮች ስናይ ከወንዙ ጋር የሚያቆራኛቸው እጅግ በጣም አያሌ ምክንያቶች አሉ፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ወንዞች ህይወትን፣ ስልጣኔን እና ማንነትን ገንብተዋልና፡፡ እርግጥ ነው ኤፍራጠስ የሚባል ከገነት የሚፈስ ወንዝ ባይኖር የአሲሪያም ሆነ ሞሶፖታሚያ ወይም የባቢሎን ስልጣኔ ባልኖረ፤ እርግጥ ነው አባይ የሚባል ህይውትን ያዘለ ከኤደን የሚመነጭ ወንዝ ባይኖር ግብጽ የሚባል ሀገርም ሆነ ህዝብ ባልኖረ፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ባቀረበዉ ሪፖርት ላይ ከዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተሰጠው መግለጫ የሚከተለው ነዉ፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ባቀረበዉ ሪፖርት ላይ ከዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተሰጠው መግለጫ የሚከተለው ነዉ፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ  መንግስት የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ መጀመሩን መጋቢት 24 ቀን 2003 አመተ ምህረት በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትራችን በክቡር አቶ መለስ ዜናዊ በተጣለው የመሰረት ድንጋይ ለአለም ማህበረሰብ መበሰሩ ይታወሳል፡፡ግድቡ በመላ አገራችን ህዝቦችና  በልማታዊ መንግስታችን ጥረት የሚገነባ ቢሆንም ኢትዮጵያን ጨምሮ ሶስቱንም የአባይ ተፋሰስ አገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይታመናል፡፡የኢፌድሪ መንግስት በአባይ ወንዝ ላይ የዚህ ታላቅ ግድብ መገንባት የተፋሰሱ የታችኛው ተጋሪ አገሮች ማለትም በግብፅና በሱዳን  በግድቡ ግንባታ ዙሪያ ግልፅነት፣በቂ ግንዛቤ መተማመንና መረዳዳት የሚዳብርበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ጠቃሚ መሆኑን በማመን በወሰደው ተነሳሽነት በሶስቱም አገሮች ትብብር አንድ አለም አቀፍ የባለሞዎች ቡድን እንዲቋቋም አድርጓል፡፡